cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Witnes, black man የማርያም ልጅ

የመዳናችን ምክንያት የንፅህነታችን መሠረት የሆንሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የሃጢያት ስርዬትን ይሰጠን ዘንድ ለምኝልን።

Show more
Advertising posts
196
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​​ታህሳስ 3 በአታ ለማርያም እመቤታችን በሶስት አመቷ ቤተመቅደስ የገባችበት ቀን ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም።" በሚል ይናቁ ነበር። ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት - ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነርሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም። የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን፣ እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች። ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ። እርሱ፦ ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ በማኅጸኗ ስትደርስ አየ። እርሷ ደግሞ፦ የኢያቄም በትር አብቦ፣ አፍርቶ፣ ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን።" አሉ። ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ።  በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ ፯) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ። "ዓለም የሚድንባት የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ።" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች። "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ..... ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም።" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም) "ለጽንሰትኪ በከርሥ እንበለ አበሳ ወርኩስ ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ..... ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው። የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።....." (መጽሐፈ ሰዓታት ፣ ኢሳ. ፩፥፱) "ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ። ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን። ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን፤ (ወለደች - አስገኘችልን።)" የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል፤ ተመስግነዋል። ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኳ መሆን የማይችል የሰማይና የምድር ንግሥት የእግዚአብሔርን እናት እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን። ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ። ቅዱሳኑ እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ጸልየዋል። ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል። እመቤታችን ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን ተወልዳለች። ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች።  (ኢሳ. ፩፥፱) የእመቤታችን የዘር ሐረግ፦ አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ በእናቷ፦ ሌዊ- ቀዓት- እንበረም- አሮን- ቴክታና በጥሪቃ- ሔኤሜን- ዴርዴን- ቶና- ሲካር- ሔርሜላና ማጣት- ሐና። በአባቷ በኩል፦ ይሁዳ- ፋሬስ- ሰልሞን- ቦኤዝ- እሴይ- ዳዊት- ሰሎሞን- ሕዝቅያስ- ዘሩባቤል- አልዓዛር- ቅስራ- ኢያቄም ይሆናል። ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች።  ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ድንግል እመ ብርሃንን ከወለዱ በኋላ ለሦስት ዓመታት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ፣ ነዳያንንም ሲጠግኑ ኖሩ። በእነዚህ ዓመታትም ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከእቅፏ አውርዳት አታውቅም። ቅዱሳን መላእክትም ዘወትር እየመጡ ያጫውቷት ይንከባከቧትም ነበር።  ሦስት ዓመት በሞላት ጊዜም በቅድስት ሐና አሳሳቢነት ብጽዓታቸውን (ስዕለታቸውን) ይፈጽሙ ዘንድ ተዘጋጁ። እንደ ሥርዓቱ የሚዘጋጀውን (መባውን) ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሲደርሱ አበው ካህናትና የመቅደሱ አገልጋዮች ሁሉ ሊቀበሏቸው ወጡ። ሕዝቡ፣ ሊቃነ ካህናት ቅዱሳን ዘካርያስና ስምዖን፣ ኢያቄም ወሐና ከድንግል ማርያም ጋር ቆመው ሳሉም ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ከሰማይ ወርዶ ረቦ ታየ።  ከቅዱስ ዘካርያስ ጀምሮ ሁሉም ሰው ሕብስትና ጽዋዑን ለመቀበል ቀረበ፤ ግን መልአኩ ራቀ። ድንግል ማርያም በቀረበች ጊዜ ግን ከመሬት አፈፍ አድርጐ አንስቶ ክንፉን ጋርዶ ሰማያዊውን ማዕድ መገባት። በዚህ ደስ የተሰኙ ካህናትና ሕዝቡ እየዘመሩ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል። አማናዊት መቅደሰ መለኮት ድንግል ማርያም ወደ ኦሪቱ ቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ጸሎታችን እንድትሰማን እንደ ሊቃውንቱ፦ "ማርያም አንቲ ሰዋስው ዘምድረ ሎዛ ዲቤኪ ትዕርግ ጸሎትየ ከመ ጼና ሠናይ መዓዛ ኀበ ለነፍስየ ታሰስል ትካዛ።" እንላለን።  ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...

#አቡነ_ሃብተ_ማርያም_ጻድቅ እኒህ ጻድቅ ደግሞ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል:: ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ: እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ: ምጽዋትን ወዳጅ: ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር:: ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች:: ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር:: የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል:: ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም:: ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ:: በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው) በ40 ቀናት: ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ:: ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው:: በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና) ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ: ክቡር ደሙን ይጠጣሉ:: በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን: መከፋትን አላሳደሩም:: በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው:: "ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው:: ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: #የናግራን_ሰማዕታት በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ናግራን (የአሁኗ የመን) የክርስቲያኖች ሃገር ነበረች:: የሳባ ግዛትን የእኛ ነገሥታት ሲተዋት የተተካው ፊንሐስ ደግሞ ጨካኝ አይሁዳዊ ነበርና ናግራንን ሊያጠፋት ተመኘ:: ቀጥሎም "ሃገራችሁን ልጐብኝ" ብሎ በማታለል ገባ:: ወዲያውም ሕዝቡንና ካህናትን ሰብስቦ "ክርስቶስን ካዱ" አላቸው:: ጽኑ ክርስቲያኖች ግን "አይደረግም" አሉት:: እርሱም ሊያስፈራራቸው አስቦ 4,000 ያህል ካህናት: ዲያቆናትና ምሑራንን ጨፈጨፋቸው:: ይሕንን አድርጐ "አሁንሳ?" አላቸው:: ሕዝቡ ግን አሁንም "ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን የለም" አሉት:: (ሮሜ. 8:5) ጨካኙ ፊንሐስም እንደ ገና ከሕዝቡ መካከል ከ4,100 በላይ የሚሆኑትን ጨፈጨፈ:: ታላቁን ቅዱስ ሒሩትንም (የሕዝቡ መሪ ነው) ብዙ አሰቃይቶ ሰየፈው:: ሚስቱን ቅድስት ድማሕንም 2 ሴት ልጆቿን ሰይፈው የልጆቿን ደም አጠጧት:: ከዚያም ሰየፏት:: ይሕንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ:: ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ40 ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል:: አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን:: #ኅዳር 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 2.አቡነ ሃብተ ማርያም ንጹሕ 3.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 4.ቅዱስ ሒሩት አረጋዊ 5.ቅዱሳን ቢላርያኖስ: ኪልቅያና ታቱስብያ (ሰማዕታት) 6.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘደሴተ ሰንሲላ 7.ቅድስት ዮስቴና ቡርክት #ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን " እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" (መዝ. 36:28-31) ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞ ✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞ ✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞ ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
​​እንኳን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ "ጽዮን ማርያም" "ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል:: እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች:: ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን:: ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም:: ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው:: "ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19) #በመጨረሻም_ኅዳር_21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:- 1. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19) 2. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1) 3. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል:: "ሰላም ለኪ ማርያም እምነ:: ዘሰመይናኪ ጸወነ:: ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ:: ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ:: ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21) 4. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1) 5. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል:: 6. በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል:: 7. በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል:: 8. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው:: " አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን " "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና:: ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና:: #እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው:: 1. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት:: "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም) 2. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: ¤ "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ¤ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) 3. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና:: 4. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና:: #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...

✞________«ሰው እናታችን ጽዮን ይላል»________✞ «እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ፥ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ፤ ወውእቱ ልዑል ሣረራ። ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጧም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።» ይላል። መዝ ፹፮፥፭። ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን እናት ብሏታል። እናት፦ ወላጅ፥ መገኛ፥የአባት ሁለተኛ ናት። እግዚአብሔር በአሠርቱ ትእዛዛት፦ «አክብር አባከ ወእመከ፤ ከመ ይኩንከ ጽድቀ፥ ወይኑኅ መዋዕሊከ በውስተ ምድር ዘይሁበከ እግዚአብሔር አምላክከ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ (ቸርነቱ ረድኤቱ ይደረግልህ ዘንድ) ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚስጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም፤ » እንዳለ፦ እናት ከአባት እኲል ክብር ይገባታል። ዘጸ ፳ ፥፲፪። ጽዮን ማለት ደግሞ አምባ መጠጊያ ማለት ነው። ጽዮን ማርያም ፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም «ጽዮን» ተብላ ትጠራለች። ምክንያቱም ጽዮን ማለት አምባ መጠጊያ ማለት እንደ ሆነ ሁሉ እመቤታችንም፦ ለነፍስና ለሥጋ ፥ለኃጥአንና ለጻድቃን፥ አምባ መጠጊያ ናትና። ቅዱስ ዳዊት፦ «እስመ ኀረያ እግዚ አብሔር ለጽዮን ፥ ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ ፥ ዛቲ ይእቲ ምእራፍየ ለዓለም፤ ዝየ አኅደር እስመ ኅረይክዋ። እግዚአብሔር ጽዮን መርጧታልና ፥ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና ፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።» ያለው እመቤታችንን ነው። መዝ ፩፻፴፮ ፥ ፲፫። ምክንያቱም ፦ ለእናትነት መርጦ ያደረው በእርሷ ማኅፀን ነውና። «ለ ዘላለም መረፊያዬ ናት፤» ማለቱም፦ እርሱ የዘለዓለም አምላክ እንደሆነ ፥ እርሷም ለዘለዓለም ወላዲተ አምላክ ተብላ እንደምትኖር የሚያመለክት ነው። በሌላ ምዕራፍም፦ « ደብረ ጽዮን ዘአፍቀረ ፥ ሐነፀ መቅደሶ በአርያም ፥ወሳረረ ውስተ ምድር ዘለዓለም። የወደ ደውን የጽዮንን ተራራ ፥ መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ። ለዘለዓለምም በምድር ውስጥ መሠረታት።» ብሏል። መዝ ፸፯፥፷፰። ጽርሐ አርያም ከሰባቱ ሰማያት አንዱ ነው። በዚያ፦ ኪሩቤል የሚሸክሙት ፥ ሱራፌል የሚያጥኑት የእግዚአብሔር የእሳት ዙፋን አለ። ዙፋኑም በሰባት የእሳት መጋረጃዎች የተጋረደ ነው። ኢሳ ፮፥፩ ፣፪ኛ ሳሙ ፬፥፬ ፣ ሕዝ ፩፥፭-፲፰ ፣ ራእ ፬፥፮-፱። ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ድርሰቱ፦ እመቤታችንን፦ «በሰማይ ባለ ጽርሐ አርያም ፈንታ በምድር ላይ አርያምን ሆንሽ፤» ብሏታል። ከ ዚህም፦ ቅዱስ ዳዊት «የወደደውን የጽዮንን ተራራ፥ መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ፤» ያለው ለእመቤታችን እንደሆነ እንረዳለን። ድንግልናዋን በተመለከተም፦ «ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ፥ ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጸዮን ፥ እስመ አጽንዐ መናግሥተ ኆኃትኪ ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ ፥ ጽዮንም ሆይ አምላክሽን አመስግኚ ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፤» ብሏል። መዝ ፩፻፵፯፥፩። ይህም ፦ ለጊዜው ለከተማይቱ ሲሆን ለፍጸሜው ለእመቤታችን ነው። ይኸውም ይታወቅ ዘንድ ኢየሩሳሌም ፥ ጽዮን ፥ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፦ በመንፈስ ቅዱስ ግብር አምላክን በድንግልና በፀነ ሰች ጊዜ፦ «ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች። ልቡናዬም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች።» በማለት አመስግናለች። ሉቃ ፩፥፵፮። የእርሷ ሰውነት፦ የሥጋን ንጽሕና ፥ የልብን ንጽሕና ፥ የነፍስን ንጽሕና ፥ አስተባብራ አንድ አድርጋ ይዛ የተገኘች ናት። «የዶጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤» የተባለውም ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን ነው። እመቤታችን፦ ቅድመ ወሊድ ፥ ጊዜ ወሊድ ፥ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና። ይኽንንም ነቢዩ ኢሳይያስ፦ «እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ፤ ወንድ ልጅም (ወልድን) ትወልዳለች ፤ ስሙ ንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።» በማለት ተናግሯል። ኢሳ ፯፥፲፬። ነቢዩ ሕዝቅኤልም፦ «ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስ ተውጭ ወዳለው በር መለሰኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ አትከፈትም፤ (ድንግል ማር ያም ለዘለዓለም በድንግልና ጸንታ ትኖራለች)። ሰውም አይገባባትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶባታልና ተዘ ግታ ትኖራለች። (አምላክ በማኅፀኗ ተፀንሶ፥ ከእርሷ ተወልዷልና በድንግልና ጸንታ ትኖራለች)።» ብሏል። ሕዝ ፵፬፥፩-፪። ደብረ ጽዮንና ታቦተ ጽዮን ምሳሌዋ የሆኑላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረላት፦ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል። ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፥ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ ፥ ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስን፦ «እነኋት እናትህ፤» ብሎታል። ዮሐ ፲፱፥፳፭። ✞✞✞✞✞ሰናይ ሚዲያ✞✞✞✞✞ Share https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
Show all...
ትሕትና ✍️Bini Girmachew  ኃጢአትህ እየበዛ ሲመጣ የሌሎች ስህተት እየታየህ ይመጣል ፡፡ ጽድቅ በውስጥህ እየተስፋፋ ሲመጣ የራስህ ደካማነት ይታይሃል ፡፡ ትሕትና በአደባባይ እንደ ለበስከው ነጭ ሸማ ነው ፡፡ ታጌጥበታለህ ፡፡ ትዕቢት ግን ያዋርድሃል ፣ የማያውቅህ ሳይቀር አይቶ ይጸየፍሃል ፡፡ ቁመተ ረጅሞች ሲኮሩ ሰማይን የምታይ ይመስልሃል ፡፡ አጭሮች ሲልመጠመጡ መቃብር የገቡ ይመስላል፡፡ የረጅምነት ውበቱ ዝቅ ማለት ነው ፡፡ ትዕቢተኛ ስትሆን ሰዎች እንከን እንዲፈልጉብህ መንገድ ትከፍታለህ ፡፡ ትሕትና ራስን የማወቅ ውጤት ነው ፡፡ ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሊታበይና በሌሎች ሊፈርድ በፍጹም አይችሉም ፡፡ ትሕትና የሌሎችን ክብር ማወቅ ነው ፡፡ ማክበር መከበር ነውና ሌሎችን ስናከብር ትሕትና ታስከብረናለች ፡፡ ትሕትና ሁልጊዜ እንደሚማሩ ሁኖ መኖር ነው ፡፡ ትሕትና በጠፋበት ዘመን ሁሉም ሰው አስተማሪ ይሆናል ፡፡ ሁሉም ሰው ቅዱስ ነኝ በማለት ሌሎችን ያጣጥላል ፡፡ ጆሮ ጠፍቶ አፍ ብቻ የበዛበት ዘመን ዘመነ ትዕቢት ነው ፡፡ እገሌ ክፉ ነው ማለት በተዘዋዋሪ እኔ መልካም ነኝ ማለት ነውና ትዕቢት ነው ፡፡ ትሕትና የሰዎችን ትልቅ ድካም አሳንሶ ፣ ትንሽ ብርታታቸውን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ ትሕትና እንዳልኖሩ ሁኖ ከሌሎች ልምድን መቅሰም ነው ፡፡ ከፍ ላሉት ዝቅ ማለት ትሕትና አይደለም ፡፡ ከፍ ያሉትማ ግርማቸው በግድ ያሰግዳል ፡፡ ትሕትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው ፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ ስትሰጥ አንድ ነገር አስብ ፡- “መኪና ለሰው እንጂ ሰው ለመኪና አልተፈጠረም፡፡” እውነተኛ ትሕትና ለሚያንሱን መታዘዝ ነው ፡፡ ሰው እንደዚህ ሁኖ እንደማይቀር ብናስብ ስንት ሕጻናትን ስንት ድሆችን ባከበርን ነበር ፡፡ ትሕትና የልብ መሰበር ያመጣልና ለዝማሬና ለንስሐ ያበቃል ፡፡ አበባ ካልታሸ አይሸትም ፣ ፍራፍሬ ካልተጨመቀ አይጠጣም ፡፡ ሰውም ትሑት ካልሆነ መልኩ አይወጣም ፡፡ ትሕትና ያወቁትን ያለ ትችት ማስተማር እንጂ አላውቅም ማለት አይደለም ፡፡ እያወቁ አላውቅም ማለት ልግመት ፣ ሳያውቁ አውቃለሁ ማለት ራስን አለማወቅ ነው ፡፡ ያወቁትን በትጋት ማስተላለፍ ትሕትና ነው ፡፡ የተማርከው ሌሎችን ደንቆሮ ብሎ ለመሳደብ ሳይሆን በጨለማ ላሉት ብርሃን ለማወጅ ነው ፡፡ የጋን ውስጥ መብራት ከመሆን የሚያድነው ትሕትና ነውና ስታውቅ ትሑት ሁን ፡፡ ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ፡፡ ቀና የሚሉት ዛፎች ግን ፍሬ የሌላቸው ናቸው ፡፡ በእውነት ካወቅህ ያላወቅከው ስለሚበዛብህ ትሑት ትሆናለህ ፡፡ በአንድ ጥቅስ ጫካ የሚገቡ የአቡጊዳ ሽፍቶች ግን ትዕቢተኞች ናቸው ፡፡ “ድምፅና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” ይባላል ፡፡ ቁንጫም እንደ ልቡ ይዘላል ፣ ባዶ አዳራሽም ድምፅን ያስተጋባል ፡፡ ጩኸት ማብዛት የባዶ ቤት ምልክት ነው ፡፡ ባዶ ሰው ከቀድሞ የከፉ የሰባት ኣጋንንት ማደሪያ ይሆናልና እባክህ ባዶ አትሁን ፡፡ ትሕትና የልብ ነው ፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር ፣ የጉልበት መሸብረክ ብቻ ነው ፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትሕትና ማጣት ነው ፡፡    የወደቀውን ለማንሣት ዝቅ ትላለህ ፣ ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደ ደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ ፡፡ የስድብ አምሮትህን ለመወጣት “ውሾች” ይላል ቃሉ ፣ የነቀፋ ጥማትህን “ተኩላ” ይላል ወንጌሉ እያልህ ከተወጣኸው ኃጢአትና በቅዱሱ ነገር መበደልህ ነው ፡፡ ውሻ ፣ ተኩላ ያለው ጠባያቸውን ለመግለጥ እንጂ ላንተ ስድብ ለማበደር አይደለም ፡፡ ትሕትና ተፈትኜ አልጨረስኩም ብሎ በራሱ በጣም አይመካም ፡፡ ገና በፈተና ዓለም ያሉ ሰዎችንም በጣም አያመሰግንም ፡፡ እባክህ ወዳጄ ትሑት ሁን ፡፡ የበላይ የበታች ሁሉም ልቡ ጎረምሳ ሁኗልና የሚያስተነፍስ መዓት ሳይመጣ ትሕትናን ገንዘብ እናድርግ ፡፡ ትሕትናን በማጣት ያሳዘንከውን ፈጣሪን በብዙ ትሩፋት አታስደስተውም ፡፡ ትሕትና የእምነት መጀመሪያ ነውና ፡፡ በስተመጨረሻ 1-  ከሰው ጋር ንግግር ከመጀመርህ በፊት በማለዳ ጸልይ ። 2-  አእምሮህን ሰፊ ለማድረግ ቀኑን በንባብ ጀምር ። 3-  ከእንቅልፍ እንደ ተነሣህ የዓለምን ወሬ አትስማ ። 4-  ያላለቀው ጉዳይህ የዛሬው ሥራህ ነውና ተደሰትበት ። 5-  ንጽሕናህን ጠብቅ ፣ ለራስህ ያለህ ክብር ማሳያ ነውና ። 6-  ሁሉም ነገር ከተሳካ የምትሠራው አይኖርህምና ሁሉም ነገር ይሳካ ከማለት ተቆጠብ ። 7-  ለትምህርት የዕድሜ ገደብ የለውምና እስክትሞት ተማር ። 8-  ለሚወዱህና ለሚያከብሩህ ቅድሚያ ስጥ ። 9-  ጉዳይን ከባለቤቱ እንጂ ከሦስተኛ ሰው አትስማ ። 10-   በትሕትና ለሚያገለግልህ ክብር ይኑርህ ፣ ምቹ ነገርንም አዘጋጅለት ። 11-   ባዶ እጅህን ተወልደሃልና ፣ ባዶ እጅህንም ትሄዳለህና ስለ ንብረት ሕይወትህን በብስጭት አትጉዳ ። 12-   መታዘብህ ውስጥህን እንዳይጎዳው ከብልጦች ጋር ጊዜ አታጥፋ ። @Bini_Girmachewbot @BiniGirmachew Bini Girmachew ( ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን)  ትዩብን ሰብስክራይብ ለማድረግ ይሄን ሊንክ ይጠቀሙ!! 🔔 👉   https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
Show all...
​​​​👆 #የቀጠለ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35) እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡ እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡ #ምንጭ፦ የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መልአከ ሠላም ሰንበት ትምህርት ቤት ገጽ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...

​​#ሕዳር_ሚካኤል ! #እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን ! በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12) (አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE_SHARE_SHARE ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡ በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ #ይቀጥላል ....... 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...

​​#ህዳር 6 +በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው። ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹ ወደ #ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው ""ያቺ የተባረከች ሀገር ናት"" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!!ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰቷታል በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ታምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል። እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት አለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ! የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን !! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !! ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1 ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ! «ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ...ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩ የተዋህዶ ልጆች እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ! 👉 @ortodoxmezmur
Show all...

​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞ ✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞ ✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል:: ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: 7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: +በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው:: ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም:: በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል:: © ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...

፪.ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ(አቤል ተስፋዬ).mp37.60 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.