cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በክርስቶስ

፠ ጸጋ ብቻ ፠ እምነት ብቻ ፠ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ፠ ክርስቶስ ብቻ ፠ ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ " በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:3) For comments https://t.me/Wend7 @BenHel

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
147
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስለአገራችን እንጸልይ ስለአገራችን እንጸልይ ስለአገራችን እንጸልይ.................
Show all...
#የእግዚአብሔር_ሉአላዊ_ምርጫ ==================== እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን!! መጽሐፍ ቅዱስ ከአዕምሮ ስለሚያልፈው ስለ እግዚአብሔር ሉአላዊ ምርጫ እና አስቀድሞ ሰዎችን በክርስቶስ ስለ መምረጡ ወይም ስለመወሰኑ ምን ያስተምረናል? መመረጥ ወይም መወሰን ማለት ሉአላዊ የሆነው አምላክ ለአንዳች አላማ በክርስቶስ ሰወችን ከብዙዎች መካከል ሲመርጥ, ሲለይ እና ነጥሎ (ለቅሞ ) ሲወስድ እና ለፈለገው አላማ ሲያውል የሚል ትርጉም ይሰጠናል ምርጫ (አስቀድሞ መወሰን ) እግዚአብሔር በሰወች ከሚታየው መልካምነት በመነሳት እና ሰዎች እንደሚያምኑት ስላወቀ ሳይሆን እግዚአብሄር በሉአላዊነቱ እና በማይመረመር እውቀቱ ሰዎች እንዲድኑ እና ልጆች እንዲሆኑ በክርስቶስ ከዘላለም አስቀድሞ መምረጡን እና መወሰኑን የሚያሳይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነው። ብዙ ስዎች እና ሀይማኖቶች እንደሚሉት እግዚአብሔር የመረጠን እንደምናምነው አስቀድሞ ስለሚያውቅ ነው ይላሉ ይህ አስተሳሰብ ለሰውኛ አዕምሮ የሚመች ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ስለሌለው የእግዚአብሔር ሉአላዊነት ላይ ጥያቄ የሚፈጥር ነው። እንዲሁም እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ለእግዚአብሔር ምርጫ እና ለሰው እምነት እኩል መጨብጨብ አለበት ማለት ነዋ?? ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ሉአላዊ ምርጫ እና አሰራር ብቻ ያውጃል። ስለ ምርጫ ( አስቀድሞ መወሰን) ፈፅሞ ለተማረ ክርስቲያን፦ 1) ትክክለኛ መፅናኛ ነው:: ሮሜ 8:29 2) እግዚአብሔርን የማመስገኛ በስራው የመደነቂያ ምክንያት ነው። ኤፌ 1:5-6,ኤፌ 1:12, 1ተሰ 1:2, 2ተሰ 2:13 3) ወንጌል ሥርጭትን የሚያበረታታ ነው። 2ጢሞ2:10 ምርጫ በብሉይ ኪዳን፦ ================ 1) እግዚአብሄር የእስራኤል ሕዝብ አባት እንዲሆን አብርሀምን ከሀገሩ ሰዎች እና ከቤተሰቡ ለይቶ መጥራቱ ። ዘፍ 12:1- የእስራኤል ህዝብ አባት የሆነው አብርሃም በእግዚአብሔር ለመመረጥም ሆነ ለመጠራት የሚያበቃ አንዳች ነገር ሳይኖረው ጣዖት ከሚያመልኩት ቤተሰቦቹ መካከል ተለይቶ እንዲወጣ እና እግዚአብሔር እንዲከተል ያደረገው የእግዚአብሔር በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ምርጫ ብቻ እና ብቻ እንደሆነ እንመለከታለን። ይደንቃል። 2) ከአብርሀም ዘር እስማኤልን ሳይሆን ይስሀቅን ቀጥሎም ኤሳውን ሳይሆን ያዕቆብን መምረጡ ። ዘፍ 21:12,ሚልክ 1:2-3 ከአብርሃም ዘሮች መካከልም ከእስማኤል ይልቅ ይስሀቅን መምረጡ ከኤሳው ይልቅ ያዕቆብን ሲመርጥ እንመለከታለን። ይህ ምርጫ በተመረጡት በጎ ጸባይ እና መልካምነት ላይ የተመሠረተ ነው እንዳንል ኤሳው እና ያዕቆብ ገና ሳይወለዱ የተወሰነ ምርጫ ነው። በስራቸው ነው እንዳንል ምህረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም ተባለ። ታድያ መልሱ ምን ይሆን መጽሐፍ ቅዱስ በምርጫ የሚሆነው የእግዚአብሔር ሉአላዊ ሀሳብ ይፈጸም ዘንድ ነው ይላል። ይደንቃል። 3) ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ሲናገር " እግዚአብሄርም የወደዳችሁ እና የመረጣችሁ ከአህዛብ ሁሉ በቁጥር ስለበዛችሁ አይደለም ......"ብሎ በመናገር የእግዚአብሄር ምርጫ በህዝቡ ታላቅነት ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ብቻ የሚፈፀም መሆኑን አሳየ። ዘዳ 7:7-8 4) እግዚአብሄር ንጉስ ዳዊትን "አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድኩህ " በማለት ቀድሞ የነበረውን ህይወት ያሳስበዋል። 2ሳሙ 7:8 5) በመጨረሻ እግዚአብሄር ራሱ ለእስራኤል እና ለአሕዛብ አዳኝ መረጠ "...ነፍሴ ደስ የተሰኝችበት ምርጤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ ......" ኢሳ 42:1- ይቀጥላል........... ሮሜ 11 (Romans) 33፤ የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።...... 36፤ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። የወንጌል እውነት አገልገሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 👇👇👇👇👇👇👇👇 ''ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን'' @Inchrist_Inchrist
Show all...
ትምህርተ_መለኮት_፩_ሔኖክ_ኢሳይያስ.pdf1.35 MB
* ልሳንና ዘመናችን! * > በዘመናችን ብዙ ሰዎች ልሳን እንናገራለን ሲሉ እንሰማለን፣ ልሳን ነው የሚሉትንም ሲናገሩ እንመለከታለን። > እያንዷንዷን ነገር በቃሉ መመርመር ስለሚገባን ስለ ልሳን ጠቅለል ባለ መልኩ በጥያቄና መልስ መልክ የተወሰኑ አሳቦችን እናንሳ 1ኛ፡ ልሳን ምንድነው? > ልሳን ሰዎች የሚያውቁትና በዓለም ላይ መግባቢያ የሆነ ቋ*ን*ቋ ነው(ኢሳ፡28÷11፣ ማር፡ 16÷17፣ የሐዋ፡2÷8-11፣ 1ቆሮ፡14÷10-11፣ 21)። 2ኛ፡ ልሳን በመጀመሪያ የተሰጠበት ዓላማ ምን ነበረ? > ሰው በሚያውቀውና በሚገባው ቋንቋ ሲነገረው አልሰማ ካለ በሌላ ቋንቋ ይነገረዋል። እስራኤላውያን በገዛ ቋንቋቸው አልሰማ ስላሉ በሚጠሏቸው አህዛብ ቋንቋ እንዲሰሙ ሆነዋል(ኢሳ፡28÷11፣ የሐዋ፡2÷8-11፣ 1ቆሮ፡14÷22)። > ስለዚህ ልሳን በዚህ ገፅታው ለማያምን ምልክት ሆኖ ሲያገለግል ነበር። 3ኛ፡ ልሳን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዴት ይታያል? ..........ይቀጥላል........... 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 👇👇👇👇👇👇👇👇 ''ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን'' @Inchrist_Inchrist
Show all...
" ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ #ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ #ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።" (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:27)
Show all...
የነገረ መለኮት ሙሑሩ ቻርል ሆጅ በ “መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ” መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ምንድነው? እንዴት ተጻፈ? ልናምነው እንችላለን? ስህተት የለበትም? ቀጥተኛ ነው? ግልጽ ነው? እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መግቢያ ሀተታ ያስቀምጣል። አንብቡት። Join and share for more book updates 👉 @amanbooks 👉 @amanbooks
Show all...
Charles Hodge on Scripture .pdf2.54 KB
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 119) ---------- 103 ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ። 104 ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ። - ኖን - 105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው። @Inchrist_Inchrist
Show all...
(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 3) ---------- 1፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ያገኘኸውን ብላ፤ ይህን መጽሐፍ ብላ፥ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር አለኝ። 2፤ አፌንም ከፈትሁ መጽሐፉንም አጐረሰኝ። 3፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ። 👇👇👇👇👇👇👇👇 ''ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን'' @Inchrist_Inchrist
Show all...
ጌታ ሆይ፥ በእኔ ውስጥ ያለው መልካም ነገር ሁሉ ያንተ ነው፤ የቀረው ሁሉ ደግሞ የእኔ ስሕተት ነው። ቅዱስ አውግስጢኖስ
Show all...
“Christ in us the hope of glory. Christ for us our full redemption. Christ with us our guide, and our solace; and Christ above us pleading and preparing our place in heaven. Jesus Christ Himself is our Captain, our armor, our strength and our victory! We inscribe His name upon our banner, for it is hell’s terror, heaven’s delight, and earth’s hope. We bear this upon our hearts in the heat of the conflict, for this is our breastplate and coat of mail” (Charles Spurgeon, Sermon #1388, preached December 9, 1877). 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 👇👇👇👇👇👇👇👇 ''ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን'' @Inchrist_Inchrist
Show all...