9 997
Subscribers
No data24 hours
-517 days
-26930 days
Posts Archive
9 997
🔥 ጎል! ማይኬል ኦሊሴ ሶስተኛውን ጎል ለባዮርን ሙኒክ አስመዘገበ! 🔥
⚽ ባዮርን ሙኒክ 3-0 አክላንድ ሲቲ
🕘 19ኛ ደቂቃ፤ ኦሊሴ ፣ ባዮርን እየተዝናኑ ነው።
9 997
🔥 ጎል! ኪንግስሊ ኮማን ባዮርን ሙኒክን ቀዳሚ አድርጎዋል ! 🔥
⚽ ባዮርን ሙኒክ 1-0 አክላንድ ሲቲ
🕔 5ኛ ደቂቃ፤ ኮማን ጎል ውብ አጨራረስ !
9 997
🚨
ቪክቶር ዮከሬሽ (ስፖርቲንግ ሊዝበን) በዚህ ክረምት ማን ዩናይትድን ጥሎ አርሰናልን መቀላቀል ይመርጣል! ምክንያቱ የአርሰናል የአጨዋወት ዘይቤ መሆኑ ተነግሯል።
አርሰናል ዮከሬሽን የሚመለከተው የሴስኮ ዝውውር ካልተሳካ ብቻ ነው!
9 997
⚽️ ማትያስ ቴል ወደ ቶተንሃም በቋሚ ዝውውር?
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ፈረንሳዊውን አጥቂ ማትያስ ቴልን በቋሚነት ለማስፈረም ተቃርቧል! በውሰት በነበረው ጊዜ 19 ጨዋታዎችን አድርጎ 3 ጎሎችን አስቆጥሯል። የዝውውር ዋጋው 35 ሚ.ዩሮ + 10 ሚ.ዩሮ ተጨማሪ ሊሆን ይችላል።
በሌላ ዜና ፊፋ ባዶ መቀመጫዎችን በመደበቅ ላይ?
ለአለም ክለቦች ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ትኬቶች አልተሸጡም! ፊፋ ባዶ ወንበሮችን ከካሜራ ለመደበቅ ርካሽ ትኬት የገዙትን ወደ ተሻለ ቦታ እያዛወረ ነው ተብሏል። የትኬት ዋጋውም ከ 300 ዩሮ ወደ 20 ዩሮ ወርዷል። ዛሬ ምሽት ኢንተር ሚያሚ ከ አል አህሊ ይጫወታሉ።
9 997
🔥 የሸገር ደርቢ በቡናማዎቹ አሸናፊነት ተጠናቀቀ! 🔥
በተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 2-0 ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል! 🏆
አማኑኤል አድማሱ እና ዲቫይን ዋቹኩዋ ለአሸናፊነቱ ግቦችን አስቆጥረዋል! ⚽️⚽️ ይህ ድል ቡናማዎቹን በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል።
የሊግ ደረጃ ፦
2️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 59 ነጥብ
7️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 45 ነጥብ
9 997
🚨ቶተንሃም አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ከዚህ ቀደም ሲሰለጥኑት የነበረውን የብሬንትፎርድን ምቤሞን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሆኖም ምቤሞ ማንችስተር ዩናይትድን ይመርጣል መባሉ ዝውውሩን ፈታኝ ያደርገዋል።
9 997
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2017 - 35ኛ ሳምንት መርሃ ግብር
🏟️: አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም
📆: ቅዳሜ ሰኔ 07/2017
⏰ 09:00: ኢትዮጵያ ቡና ☕ - ቅዱስ ጊዮርጊስ 🐎
⏰ 12:00: ኢትዮጵያ መድን 🛡️ - ሀድያ ሆሳዕና
9 997
🔥ብራዚላዊው አጥቂ ማቲውስ ኩንያ ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ያላቸውን ልዩ አመለካከት ገለጸ!
🇧🇷 "ለኔ ከማንችስተር ዩናይትድ የሚወዳደር ክለብ የለም!"
ኩንያ አክሎም "ውሳኔዬ ክለቡ ለእኔ ምን ማለት እንደሆነ ያሳያል። ማንችስተር ዩናይትድን ከምንም በላይ አስቀድማለሁ!"
9 997
🚨 ኒኮ ዊሊያምስ ወደ ባርሴሎና? 🤔
ስፔናዊው ኮከብ ኒኮ ዊሊያምስ በአውሮፓ ክለቦች ተፈላጊ ነው! 💎
ባየር ሙኒክን በዚህ ሳምንት ሁለት ጊዜ አግኝቶ ተነጋግሯል። 🇩🇪 ከባርሴሎናው ዴኮ ጋርም ዛሬ ንግግር አድርጓል። 🗣️ ለተጫዋቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ባርሴሎናን ለመቀላቀል ደሞዙን ለመቀነስ ፍቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል።
አርሰናልም ተጫዋቹን ይፈልጋል። ⚽️ ዝውውሩ ወደ የትኛው ክለብ ይሆን?
9 997
🚨 ፖል ፖግባ ወደ ሜዳ ይመለሳል? ⚽️
ፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወደ ሞናኮ ሊያቀና ነው! ሞናኮ የሁለት አመት ኮንትራት አቅርበዋል። ንግግሮች በመካሄድ ላይ ናቸው።
አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅሟል በሚል ታግዶ የነበረው ፖግባ እገዳው ወደ 18 ወራት ተቀንሷል። ከጁቬንቱስ ጋርም ተለያይቷል።
በተጨማሪም ሞናኮ የባርሴሎናውን አንሱ ፋቲ ለማስፈረም እየሰሩ ነው ተብሏል። 🔥
9 997
ባርሴሎና እና ሞናኮ የአንሱፋቲ ዝውውር ላይ የመጨረሻ ዝርዝር ጉዳዮችን በመጨረስ ላይ ናቸው!
ዝውውሩ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ፋብሪዚዮ ሮማኖ በገፁ አብታውቋል!
አንሱፋቲ በባርሴሎና እጅግ ተስፋ ከተጣለባቸው ተጫዎቾች መካከል ነበር
ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ በጉዳት እና በተለያዩ ምክንያቶች አቋሙ ወርዶ ወደ ነበረበት መመለስ አቃተው!
አሁን ባርሴሎናን በቋሚነት ሊለቅ ነው😢
9 997
🚨ሪያል ማድሪድ የአጥቂ አማካዩን ፍንኮ ማስታንቱኖን አስፈረመ! 🇦🇷💎
ሪያል ማድሪድ የ17 ዓመቱን አጥቂ አማካይ ፍንኮ ማስታንቱኖን ከሪቨር ፕሌት ጋር ለ6 ዓመታት ተፈራርሟል። ዝውውሩ በነሐሴ ወር ይፈጸማል። የዝውውር መጠኑ 45 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን ይህም ሪቨር ፕሌት በክለብ ሪከርድ የሸጠው ተጫዋች ያደርገዋል።
9 997
🚨 ገብርኤል ማጋሀልስ ሮድሪጎን በአርሰናል እንዲጫወት ይፈልጋል! 🇧🇷
"ወደ አርሰናል እንዲመጣ እፈልጋለሁ፣ አስደናቂ ተጫዋች ነው!" - ገብርኤል ስለ ብራዚላዊው የቡድን አጋሩ። 🔥
ለስፖርቲንግ ዳይሬክተሩም "እሱ ምርጥ ተጫዋች ነው!" ብሏል። 👀
9 997
ፍሎሪያን ቪርዝ ሊቨርፑልን የፕሪምዬር ሊግን የዝውውር ረከርድ ጭምር በመስበር መቀላቀሉ እርግጥ ይመስላል!
ሊቨርፑል ለተጫዋቹ ያወጣው ወጪ ይገባዋል ብለው ያስባሉ?
