cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ግጥም እና ወግ ( ረሂማ ሁሴን)

ጥበብ የሙስሊም ሀብት ናት! ካገኘባት ቦታ ይውሰዳት ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጥበበኛው ጌታ የሰጠኝን ሂክማ ተጠቅሜ እይታወቼን እና ሀሳቦቼን በግጥም እና በወግ አዚህ ቻናል ላይ አጋራችኋለሁ። . .ተቀላቀሉን ለአስተያየትዎ @rehimahubot

Show more
Ethiopia6 874Amharic5 978The category is not specified
Advertising posts
722
Subscribers
+124 hours
+27 days
+530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

 ለሦስት ጊዜያት አባቷን "አሚን" እንዲል የጠየቀችው ሴት አያድ ውስጥ ከሚገኙ ዑለሞች አንዱ የሚከተለውን ተርከዋል፡- ከሆስፒታሉ ከፍሎች ወደ አንዱ ጎራ ስንል በታመመች ልጅ አጠገብ የሚገኝን አባት አስተዋልን። የልጅቷ ዕድሜ አርባዎቹን ደፍኗል። ቢሆንም ግን እስካሁን ድረስ አላገባችም። ወደርሷ የሚመጡ ባሎችን ሁሉ አባቷ ኢያከላከለ እስከዚህ ዕድሜዋ አድርሷታል። ይህ ሰው ለገንዘብ እጅግ ከሚስገበገቡ ሰዎች አንዱ ነው። ያጠራቀመው ገንዘብ ግን ለምንም ነገር አልጠቀመውም። በርካታ የሚከራዩ ሕንፃዎች፣ ሪል ስቴት፣ መኪኖችና ከሊኒክ ያለው ቢሆንም ልጁን የሚያገባ ሰው መቶ ሺህ ሪያሎችን ለጥሎሽ ካልሰጠ እንደማይድር በመናገሩ እርሷን ፈልገው የመጡ ባሎቿ ሁሉ ይህን ያክል የገንዘብ መጠን ስለማያገኙ እየፈሩ ሸሹ። ከዚህም በተጨማሪ ልጅቷን ለጋብቻ የጠየቀ ሁሉ ስለደመወዙ፣ ስለመኪናውና ይህን ስለመሣሠሉ ቀሳዊ ጉዳዮች ጥያቄ ይቀርብለታል። በመጨረሻም ልጅቷ ሳታገባ አርባ ዓመት ሞላት። እነሆ አሁን በክፉ ደዌ ተይዛ ወደ ሆስፒታል ከመጣች በኋላ መሞቻዋ ተቃርቧል። እንግዲህ በዶይና ተበዳይን ያለ አድሎ የሚዳኘው ጌታ ሁለቱንም በመጪው ዓለም ያፋርዳቸዋል። አሁን ግን ልጅ አባቷን “አባዬ ወደኔ ጠጋ በል!" አለችው። ወደርሷ ሲጠጋም “አሚን” በል አለችው። አሚን” አለ። እሚን በል” አሚን” እሚን በል" “ኣሚን “የጋብቻን ሕይወት እርም እንዳደረግኽብኝ ሁሉ አላህ ጀነትን እርም ያድርግብህ።” ለአርባ ዓመታት በአባቷ ቤት ያለ ትዳር መቀመጧ ለምን ይሆን? እነሆ አባት የመጨረሻውን ምርቃቷን አግኝቷል። @rehimahu @rehimahu
Show all...
😢 2👏 1
ይህች ዓለም እናንተው ፈቃድ እስካልሰጣችኋት ድረስ አትሰብራችሁም፡ የልቦናችሁን ቁልፍ እስካላቀበላችኋት ድረስ ልትገዛችሁና የራስዋ ልታደርጋችሁ አትችልም። ለጊዜው እንኳን ቁልፎቹን የሠጣችኋት ቢሆን እንኳን መልሳችሁ ተቀበሉ። ይህ መጨረሻችሁ አይደለም። እዚህ ጋም መሞት የለባችሁም፡፡ ልባችሁን አስመልሱና ለትክክለኛው ባለቤቱ አስረከቡ። እሱ አላህ ነው:: rehimahu rehimahu
Show all...
👍 2
ዝም አትበሉ! ሰወች ጥፋት ውስጥ ሁነው ስናይ ከመጥፎ ካልከለከልን እና በመልካም ማዘዝ ካቆምን ትልቅ ውድቀት ውስጥ ነን! አንድ አማኝ ከጌታው ፍቅር በሚያርቀው ተግባር ላይ ሲዘወትር እና ወደ ጀሀነም በሚወስድ መንገድ ላይ ሲጓዝ የማያመን ከሆነ ነፍሳችንን እንፈትሽ! 🌑 ደዩስ አንሁን! كُنتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ። Rehima hussen @rehimahu @rehimahu
Show all...
3👍 2
ፊርአውን ለኔ ክብር ተከፈለ ያለው ውቅያኖስ ሲያጥለቀልቀው ነፍሱን ለማትረፍ "አድነኝ አምኛለሁ" እያለ ሙሳን 70 ጊዜ ተጣርቶ ነበር። አላህም "እኔን አንድ ጊዜ ተጣርቶ እንዳድነው ቢለምነኝ ባተረፍኩት ነበር" አለ። ፊርአውን መጠየቅ ያለበትን ጌታ ትቶ ከፍጡር እርዳታ ፈለገ እና ጠፋ ብዙ ጭንቀት ፣ብዙ ሀጃ፣ ብዙ ፍላጎት አለን እና ጉዳያችንን ሰው እንዲፈፅምልን ከመለመን ይልቅ ጌታችንን ችክ ብለን እንጠይቀው። ዛሬ ቀኑ የኛ ነው በዱአ አንበርታ መልካም ቀን ❤️
Show all...
🥰 4
ታውቂያለሽ ነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) እውነትን ከፍ ለማድረግ እና ህዝቦቻቸውን ከውሸታሙ እና ከአምባገነኑ ፊርአውን ለማዳን የሄዱትን አይነት ተመሳሳይ መንገድ እያለፍኩ ነው አለኝ። ስለ አሹራ እና ተያይዞ ስለሚነሳው ስለ ሙሳ ታሪክ ስናወራ ከቆየን በኋላ።እንዴት? አልኩ የሙሳን አይነት ታሪክ እንዴት ሊያሳልፍ እንደሚችል እያሰብኩ። ልዩነታችን እሳቸው አላህን በህዝባቸው ልብ ውስጥ ለማንገስ እና የአላህን ውዴታ ለማግኘት ሲሆን እኔ ደግሞ የምወዳትኔ ሴት ለማግኘት እና ልቦ ውስጥ ለመንገስ ነው የሳቸውን መንገድ እያለፍኩ ያለሁት አለኝ እጁን እያወናጨፈ። አልገባኝም?... ቆይ እሺ የፃፍኩትን ግጥም ላንብብለሽ አለኝ ግጥሞቹን ስለምወዳቸው ቶሎ ብዬ እሺ አልኩ ለመስማት እየተዘጋጀሁ....... መች ነው የኔ አሹራ? ልክ እንደ ሙሳ እናት፣ አንቺን ያጣሁ ለታ ልቤ ባዶ ይሆናል እሶን የሚነጥቅህ ወንድ አለ ያሉኝ ቀን፣ ልክ እንደ ፊርአውን ልቤ ይጨነቃል። አንቺን ለማግኘት ስል ጣፋጩን ወይን ትቼ እሳት እጎርሳለሁ፣ ጀግንነቴን አይተሽ እንድትደመሚ፣ አንቺ ያቃተሽን ክብደት አነሳለሁ። አይኑን ሰባሪ ጨዋ እንድትይኝ ከፊቴ አትሁኚ፣ ከኋላ ሁነሽ ምሪኝ እላለሁ ግን ውዴ... ይሄን ሁሉ አድርጌ ባንቺ ለመመረጥ ከኔ ፍቅር ይልቅ የሌላ ከመረጥሽ፣ እንደ ፈርኦን ሁኜ፣ እምቢ ካልሽኝ ኋላ አላሳድድሽም። እንደ ሙሳ ሰወች እውነቴን ተረድተሽ ከተከተልሽኝ ግን.... አትጠራጠሪ ባህሩን ታልፊያለሽ ፍቅር እና እውነት ፈፅሞ አያሰምጥም። ፐ ምኑን ከምኑ ነው ያገናኘኸው ባክህ? ጣፋጩን ወይን ትቼ እሳት እጎርሳለሁ...... ገጣሚወች እንዲህ እያላችሁ ነዋ ሴቱን የምታፈዙት አልኩት አገላለፁ ገርሞኝ። ምን ዋጋ አለው የተፃፈላት አይገባት አለኝ ትካሻውን እየሰበቀ። አካሄዱ ስላላማረኝ ምን የዘንድሮ ሴት ቅኔ አይገባው ብዬ ባህሩን የሚከፍለውን ሙሴዬን ተሰናበብቼ ወደ ቤቴ አቀናሁ። ✍rehima hussen @rehimahu @rehimahu @rehimahubot
Show all...
🥰 3👍 1 1
عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه ، قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم: ✨صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ ✨رواهُ مسلم ከአቢ-ቀታዳ (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)  እንዲህ  አሉ:- ✨ የዐሹራን ቀን መጾም ከርሱ በፊት (ያለፈውን) አመት   ወንጀል ያስሰርዛል  ብዬ  ከአሏህ  እከጅላለሁ። አሹራ ነብዩላህ ሙሳ (አለይሂ ሰላም) ከአምባገነኑ ፊርአውን እና ከወታደሮቹ በአላህ ፈቃድ ነፃ የወጡበት ቀን ነው። ከኋላቸው የመጣውን ወታደር የሚሸሹበት ቦታ አጥተው ከሰፊ ባህር ጋር በተጋፈጡ ጊዜ ሲመኩበት የማ'ያሳፍረው አል -ወኪል ባህሩን 12 ቦታ ከፍሎ ለ12ቱ ጎሳወች ከፊርአውን ማምለጫ፣ ለፊርአውን እና ለወታደሮቹ ደግሞ መጥፊያ አደረገው። በዚህ አመት ደግሞ ይህ ቀን( አሹራ) ከቀኖች በላጭ በሆነው በጁመአ ቀን መሆኑን ሰምተናል እና የኛ ነብይ የከጀሉትን ያለፈውን አመት ወንጀላችንን ለማስማር የምንከጅል እና ሱናቸውን መከተል የምንወድን ሁሉ አላህ ይወፍቀን! ✨እንደ ሙሳ እና ህዝቦቹ ከፊርአውን አይነት ሙጅሪሞች ነፃ የምንወጣበት፣ እንደ ሀገርም እንደ ኡማም ማምለጫ የለለ በመሰለን ጭንቅ ውስጥ ነን እና አላህ ማምለጫን እንዲያመጣልን በዱአ አሸብርቀን የምንውልበት ቀን ያድርግልን በሌላ ሀዲስ ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል:- ﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾ “የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።” 10ኛውን ቀን አይሁዶችም ስለሚፆሙት ከእነሱ ጋር ላለመመሳሰል የኔ ነብይ ቀጣይ አመት ከደረስኩ ዘጠነኛውን ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ነገር ግን ቀጣዩ አመት ላይ ሳይደርሱ ወደናፈቁት ጌታቸው ለመሄድ ሩሀቸው ቸኮለች። ምን አልባት እኛም የአሁኑ አሹራ የመጨረሻችን ይሆናል እና ዘጠነኛውን እና አስረኛውን ቀን( ነገ እና ጁመአን) ለመፆም አላህ ይወፍቀን ✨✨በኢባዳ አሸብርቁ✨✨ Rehima hussen @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot    
Show all...
👍 4
እሱ እንዳይደብረው ብዬ ጌታዬ ያስቀመጠልኝን ድንበር አለፍኩ። "እንዴት ለሰው ፍቅር ብለሽ የጌታሽን ፍቅር ትገፊያለሽ? " እያለ ለሚወቅሰኝ ልቤ "የልቤን የሚያውቀው ጌታ ይ'ረዳኛል! "በሚል የሞኝ ሰው ንግግር ሸነገልኩት። የሰው ፍቅር ለማግኘት ስለፋ የጌታዬን ፍቅር ላጣ እንደምችል ግን ፈፅሞ ረስቼ ነበር። ከጥቂት አመታት በኋላ የጌታዬን ፍቅር የሰዋሁለት የፍጡር ፍቅር አለቀ። ያኔ አንካሳ እና ያደፈ ልቤን ይዤ በእዝነቱ አሳብቤ ሳምፀው ወደነበርኩት ጌታዬ ተመለስኩ። ያኔ ግን ከጌታዬ ፍቅር ስርቅ እንደነበርኩት ወጣት፣ ቆንጆ፣በሁሉም ሰው ተፈላጊ እና ተሰሚ አልነበርኩም። እንዲያውም ተመጦ እንደተጣለ ሸንኮራ አገዳ በሰወች ዘንድ ማንም ሊያየኝ የማይፈልግ እርባና ቢስ ነበርኩ። ወደ ጌታዬ ፍቅር ለመመለስ ለቀናት በሰላት ፣በቁርአን እና በዚክር በፍጡር ፍቅር የቆሸሸ ልቤን መፈግፈግ ጀመርኩ። ከቀን ወደቀን ልቤ ላይ የተከማቸው የወንጀል ክምር እየቀለለ እንደሆነ ሲሰማኝ ምህረቱን ለመጠየቅ እና ወደ እውነተኛ አፍቃሪዬ ወደ ወዱድ ለመመለስ እሪሪታዬን ገፋሁበት። ምሬሻለሁ ፣ ይቅርታዬን እና ፍቅሬን አጊንተሻል እንዳለኝ እስኪሰማኝ ድረስ ለአመታት አነባሁ። በነዛ በተውበት እና በኢባዳ በሸበረቁ አመታት ውስጥ ብዙ የአላህ ባሮችን እና መልካም ሰወችን አወቅኩ። ሰወች እኔን መውደድ ሲጀምሩ አላህ እንደተታረቀኝ ተሰማኝ። በኢስላም መንገድ ላይ ያወቅኳቸው ሰወች ፍቅር ጌታዬን ካስከዳኝ ፍቅር ፍፁም የተለየ ሁኖ አገኘሁት። ጀሀነም ከሚወረውረኝ የፍጡር ፍቅር ፣ ጀነት ወደ ሚ'ያስገባኝ የአላህ እና የሙስሊሞች ፍቅር ተመለስኩ። ዛሬ ላይ አንድ ነገር ብቻ ይፀፅተኛል፤ አላህን ያመፅኩባቸው እና ይህን የሂወት ጥፍጥና ገፍቼ መራራ ፍቅርን ፍለጋ የባከንኩባቸው አመታት። "አደራ የጌታሽን ፍቅር ገፍተሽ የሰው ፍቅር የምታሳድጂ ብኩን እንዳትሆኜ " ብላኝ ከተቀመጠችበት ተነሳች። Rehima hussen @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot
Show all...
5👍 2
እሱ እንዳይደብረው ብዬ ጌታዬ ያስቀመጠልኝን ድንበር አለፍኩ። "እንዴት ለሰው ፍቅር ብለሽ የጌታሽን ፍቅር ትገፊያለሽ? " እያለ ለሚወቅሰኝ ልቤ "የልቤን የሚያውቀው ጌታ ይ'ረዳኛል! "በሚል የሞኝ ሰው ንግግር ሸነገልኩት። የሰው ፍቅር ለማግኘት ስለፋ የጌታዬን ፍቅር ላጣ እንደምችል ግን ፈፅሞ ረስቼ ነበር። ከጥቂት አመታት በኋላ የጌታዬን ፍቅር የሰዋሁለት የፍጡር ፍቅር አለቀ። ያኔ አንካሳ እና ያደፈ ልቤን ይዤ በእዝነቱ አሳብቤ ሳምፀው ወደነበርኩት ጌታዬ ተመለስኩ። ያኔ ግን ከጌታዬ ፍቅር ስርቅ እንደነበርኩት ወጣት፣ ቆንጆ፣በሁሉም ሰው ተፈላጊ እና ተሰሚ አልነበርኩም። እንዲያውም ተመጦ እንደተጣለ ሸንኮራ አገዳ በሰወች ዘንድ ማንም ሊያየኝ የማይፈልግ እርባና ቢስ ነበርኩ። ወደ ጌታዬ ፍቅር ለመመለስ ለቀናት በሰላት ፣በቁርአን እና በዚክር በፍጡር ፍቅር የቆሸሸ ልቤን መፈግፈግ ጀመርኩ። ከቀን ወደቀን ልቤ ላይ የተከማቸው የወንጀል ክምር እየቀለለ እንደሆነ ሲሰማኝ ምህረቱን ለመጠየቅ እና ወደ እውነተኛ አፍቃሪዬ ወደ ወዱድ ለመመለስ እሪሪታዬን ገፋሁበት። ምሬሻለሁ ፣ ይቅርታዬን እና ፍቅሬን አጊንተሻል እንዳለኝ እስኪሰማኝ ድረስ ለአመታት አነባሁ። በነዛ በተውበት እና በኢባዳ በሸበረቁ አመታት ውስጥ ብዙ የአላህ ባሮችን እና መልካም ሰወችን አወቅኩ። ሰወች እኔን መውደድ ሲጀምሩ አላህ እንደተታረቀኝ ተሰማኝ። በኢስላም መንገድ ላይ ያወቅኳቸው ሰወች ፍቅር ጌታዬን ካስከዳኝ ፍቅር ፍፁም የተለየ ሁኖ አገኘሁት። ጀሀነም ከሚወረውረኝ የፍጡር ፍቅር ፣ ጀነት ወደ ሚ'ያስገባኝ የአላህ እና የሙስሊሞች ፍቅር ተመለስኩ። ዛሬ ላይ አንድ ነገር ብቻ ይፀፅተኛል፤ አላህን ያመፅኩባቸው እና ይህን የሂወት ጥፍጥና ገፍቼ መራራ ፍቅርን ፍለጋ የባከንኩባቸው አመታት። "አደራ የጌታሽን ፍቅር ገፍተሽ የሰው ፍቅር የምታሳድጂ ብኩን እንዳትሆኜ " ብላኝ ከተቀመጠችበት ተነሳች። Rehima hussen @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot
Show all...
አንዳንድ ውድ ነፍሶች አሉ! ሰማዩ ጠቆቁሮ፣ ጉርምርምታ እንደጉድ እያጓራ ፣አስፈሪ መብረቅ እየመጣ እያዩ እንኳን አብረውህ መበስበስ የማይፈሩ። ከቻሉ የጠቋቆረው ሰማይ በውብ ፀሀይ ተሸንፎ ቀኑ እስኪበራ፣ አስፈሪው ጉርምርምታ በወፎች ዝማሬ እስኪቀየር፣ መብረቁ በተወርዋሪ ኮከቦች እስኪለወጥ ሶብር እንድታደርግ እና አላህ ሁሉንም በጊዜው እስኪፈ'ታ እንድትጠብቅ ያደርጉሀል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ አስፈሪውን ዝናብ እና መብረቅ መጋፈጥ ካለብህ ግን በጭራሽ ለብቻህ ሊተውህ አይፈቅዱም።ዶፍ ዝናቡንም ሆነ መብረቁን አብረውህ ይጋፈጣሉ። ጊዚያቸውን እና ጉልበታቸውን ሲሰጡህ ለሰከንድ እንኳን አይሰስቱም። ከሁሉም የሚገርመው ጨለማው ተገፎ እና ጉርምርምታው አልቆ ወደሰላማዊ ኑሮህ እና ስኬትህ ስትደርስ እዚህ ከደረስክልኝማ ብለው ካንተ ምንም ሳይፈልጉ አንተጋር ሲበሰብሱ ያዘመመ ሂወታቸውን ለማቅናት ወደ ሂወታቸው ሲመለሱ ማየትህ ነው። አንዳንዴ ከመለአክ ጋር ይመሳሰሉብኛል Rehima hussen @rehimahu @rehimahu
Show all...
🥰 6👍 3 2
#በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም። መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል። ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። አጋጣሚ ነው ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል። ብዙ ጊዜ ሰዋች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለአላህ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል። 👉 ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር። Aniley Legese
Show all...
🥰 5👍 4💯 2