cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Jesus for all nation 🧍‍♂🧍‍♀🧍🧍‍♀🧍🧍‍♂🧍‍♀

JESUS FOR ALL MANKIND'S ራእይ 1፥5-6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ #ለወደደን #ከኃጢአታችንም #በደሙ #ላጠበን፥ #መንግሥትም #ለአምላኩና #ለአባቱም #ካህናት እንድንሆን #ላደረገ፥ #ለእርሱ #ከዘላለም እስከ #ዘላለም ድረስ #ክብርና #ኃይል ይሁን፤ አሜን Owner: Samuel Teshome Phone no: +251945862135

Show more
Advertising posts
247
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ማቴዎስ 13 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ እንግዲህ እናንተ #የዘሪውን #ምሳሌ #ስሙ። ¹⁹ #የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው። ²⁰ #በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው፤ ²¹ ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፥ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል። ²² #በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል። ²³ #በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።
Show all...
ማቴዎስ 13 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም። ¹² ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። ¹³ ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ። ¹⁴ መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም። ¹⁵ በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል። ¹⁶ #የእናንተ ግን #ዓይኖቻችሁ #ስለሚያዩ #ጆሮቻችሁም #ስለሚሰሙ #ብፁዓን ናቸው። ¹⁷ እውነት እላችኋለሁ፥ #ብዙዎች #ነቢያትና #ጻድቃን #የምታዩትን #ሊያዩ #ተመኝተው #አላዩም፥ #የምትሰሙትንም #ሊሰሙ #ተመኝተው #አልሰሙም።
Show all...
👍 1
ዕብራውያን 4 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ ወደ #ዕረፍቱ #ገና #የሚገቡ አንዳንዶች አሉ፤ ቀድሞ የምሥራቹ ቃል የተሰበከላቸው #ባለመታዘዛቸው ምክንያት ወደ #ዕረፍት #አልገቡም። ⁷ ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “ዛሬ” ብሎ እንደ ገና አንድን ቀን ወሰነ፤ ይህም ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት በኩል፣ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ ልባችሁን አታደንድኑ” ተብሎ ቀደም ሲል እንደ ተነገረው ነው። ⁸ #ኢያሱ #ዕረፍትን ሰጥቶአቸው ቢሆን ኖሮ፣ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን ባል ተናገረ ነበር። ⁹ ስለዚህ #የሰንበት #ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ገና ቀርቶለታል፤ ¹⁰ ምክንያቱም ወደ #እግዚአብሔር #ዕረፍት #የሚገባ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፣ እርሱም ደግሞ ከሥራው #ያርፋል። ¹¹ እንግዲህ ማንም የእነዚያን #አለመታዘዝ ምሳሌ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደዚያ #ዕረፍት #ለመግባት #እንትጋ።
Show all...
ኤርምያስ 32 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁹ ለእነርሱና ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም እንዲሆንላቸው ዘወትር ይፈሩኝ ዘንድ፣ አንድ ልብ አንድም ሐሳብ እሰጣቸዋለሁ። ⁴⁰ መልካምን ነገር ለእነርሱ ከማድረግ እንዳልቈ ጠብና ከእኔም ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በውስጣቸው ላኖር ከእነርሱ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን እገባለሁ። ⁴¹ ለእነርሱ መልካም በማድረግ ደስ ይለኛል፤ በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በእውነት በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።’ ”
Show all...
ኤርምያስ 32 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁷ “አቤት፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰማያትንና ምድርን በታላቅ ኀይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፤ የሚሳንህም አንዳች ነገር የለም። ¹⁸ ፍቅርና ቸርነትን ለእልፍ አእላፍ ታሳያለህ፤ ይሁን እንጂ የአባቶችን በደል ከእነርሱ በኋላ በሚነሡ ልጆቻቸው ጒያ ትመልሳለህ፤ ስምህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ፣ ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ፤ ¹⁹ ዕቅድህ ታላቅ፣ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ዐይኖችህ የሰው ልጆችን መንገዶች ሁሉ ያያሉ፤ ለእያንዳንዱም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ። ²⁰ በግብፅ ታምራትንና ድንቆችን አደረግህ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤልና በሰው ልጆች ሁሉ መካከል እንደዚያው እያደረግህ ዛሬም ስምህ ገናና ነው። ²¹ በታምራትና በድንቅ፣ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ እጅግ በሚያስፈራም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብፅ አወጣህ። ²² ለአባቶቻችን ልትሰጣቸው የማልህላቸውን፣ ማርና ወተት የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠሃቸው፤ ²³ ወደዚያም ገብተው ወረሷት፤ ነገር ግን አልታዘዙህም፤ ሕግህንም አልጠበቁም፤ እንዲያደርጉት ያዘዝሃቸውን ከቶ አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ሁሉ ጥፋት በላያቸው አመጣህ።
Show all...
#ወደ ጌታ ከመምጣታችን በፊት እኛም እንዲሁ እንደ #አናሲሞስ ለጌታም ለሰውም #የማንጠቅም ነበርን አሁን ግን የክርስቶስን ልብ ተቀብለናል ለሁሉም #እንጠቅማለን። “አስቀድሞ #ስላልጠቀመህ፥ አሁን ግን ለእኔም ለአንተም #ስለሚጠቅም በእስራቴ ስለ #ወለድሁት ስለ ልጄ ስለ #አናሲሞስ እለምንሃለሁ።” — ፊልሞና 1፥10-11
Show all...
❤ 2🥰 1
Repost from Henok Tarekegn /Enoch/
ዛሬ ኦክቶበር (October) 31 ነው። ቀኑ ለፕሮቴስታንት በተለይም ለሉተራን አስተምህሮ ተከታዮች የተለየ ትውስታ አለው። ልክ የዛሬ 506 ዓመት ኦክቶበር 31 ቀን 1517 ነበር ሉተር የካቶሊክ ቤ/ክ በክርስትና እምነት ምክንያት የምታራምደውን የተሳሳተ አመለካከት በመቃወም 95 አንቀጽ የያዘውን ጽሁፍ በዊተንበርግ ካቴዴራል ላይ የቸነከረው ። ጉዳዩ መላ አውሮፓን አናወጠ በእርግጥ ሉተር ይህንን ሲያደርግ የራሱን አመለካከት ከማጋራት እና ምሁራዊ ውይይት እንዲደረግ ከመሻት ባለፈ ያን ያህል ታላቅ ተጽእኖ በዓለማችን ላይ ያመጣል ብሎ ገምቶ አልነበረም ሆኖም ግን የአውሮፓን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ፓለቲካ፣ እምነት፣ ኢኮነሚ፣ ስልጣኔ የቀየረና ልዩ ቅርጽ የሰጠ ነበር ። ወደ ኋላ መመለስ ad fonts! – #_back_to_the_sources ሉተር ምን ተቃወመ ?! የመካከለኛው ዘመን አብያተ ክርስቲያናት ለግዙፍ ዘመናዊ ካቴደራል ግንባታ ልዩ ስፍራ የሚሰጡበት ጊዜ ነበር። እነዚህ ታላላቅ ግዙፍ ህንጻዎች አሁን ድረስ ይጎበኛሉ፡ የሮም ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ #_ሊዮ በሮም የቅዱስ ጴጥሮስን ባሲሊካ እና ሌሎች ካቴደራሎች በማስገንባት ላይ ነበር የሚያጠናቅቅበት በጅት አጠረው ፤ተራው ህዝብ ድሀ ስለነበር በቀጥታ መዋጮ ቢጠየቅ ሊያዋጣ ስለማይችል በሕዝቡ ስስ ጎን በእምነቱ በኩል ብልሀት ሰሩበት ፤የዚህም ዋናው መሀዲስ ዮሀንስ ተስል የተባለ አፈ ጮሌ ነበር። ተስል የስርየት ትኬት #_indulgency_card አዘጋጀ፤ ይህ ትኬት አንድ ሰው በህይወት እያለ ለሰራው ኃጥያት የይቅርታ ዋስትና ወይንም ወደ መንግስተ ሰማያት የሚያቀናበት የይለፍ ፈቃድ እንደማለት ነው። የሚገርመው በህይወት ለሌለ ሰው ይሰራል መባሉ ነው። ልክ ፍራንኩ ሳንዱቅ ውስጥ ጥልቅ ሲል የሟች ነፍስ በሰማይና በምድር መሀላ አለ ተብሎ ከሚነገረው ፑርጋቶሪ ከተባለው የነብስ ማቆያ ጣቢያ ውልቅ ትላለች የሚል ነበር። ይህ የጥልቅ ውልቅ ስነ-መለኮት ለመነኩሴው ሉተር አልተዋጠለትም የበራለት ቃል ጻድቅ በእምነት ይኖራል ሮሜ 1፡17 የሚለው እረፍት ነሳው። የጳጳሱ ፊርማ ኃጢያትን ያስተሰርይ ዘንድ ማን ስልጣን ሰጠው !? ይህ እውነት ከሆነ ለምን በነጻ አይሆንም !? ከሆነስ ፍራንካ አንጣን ምን አመጣው !? የሚል ነበር አጣቃላይ ተሀድሶ ያነገበው መርህ 5 ናቸው፤ #_Sola_Gratia 👉 ጸጋው ብቻ #_Sola_fide 👉 እምነት ብቻ #_Sola_scriptural 👉 ቃሉ ብቻ #_Soluis_Christus 👉 ክርስቶስ ብቻ #_Sola_die_gloria 👉 ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ የሚሉ ነበር። የሉተር ተሀድሶ በርካታ ሊህቃን የሃይማኖት አባቶች አጼዎችን ያሳተፈ ትልልቅ ሸንጎዎች የተካሄደበት ነበር ። በተደጋጋሚም ሉተር ላነሳው ሀሳብ ተጸጽቶ ንስሀ እንዲገባ ቢጎተጎትም የሉተር አቋም ወይ ፍንክች የሚል ነው። በተለይ በዋርምስ ሸንጎ ላይ በ1521 ንስሀ ግባ ሲባል የሰጠው ምላሽ አንዲህ የሚል ነበር “በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት እና ግልጽ በሆነ አመክንዮ እስካልተረጋገጠ ድረስ በጳጳሱ ወይም በሸንጎዎች ብቻ አላምንም ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሲሳሳቱ እና እራሳቸውን እንደሚቃረኑ ይታወቃል። እኔ ለጠቀስኳቸው ቅዱሳት መጻሕፍት እስረኛ ነኝ። ሕሊናዬ በእግዚአብሔር ቃል የተማረከ ነው። ከሕሊና ጋር መቃቃር አስተማማኝም ትክክልም ስላልሆነ ምንም ማድረግ አልችልም፣ አላፈገፍግምም። እዚሁ እቆማለሁ እግዚአብሔር ይርዳኝ። አሜን።” ይህ ንግግር ወሽመጣቸውን የበጠሰ ታሪካዊ ንግግር ነበር። ያለንበት ዘመን ከማርቲ ሉተር ዘመን ጋር የሚመሳሰልበት ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ይህም ሀይ ባይ ያጣው አወናባጅ የሆኑ የሀሰተኛ መምህራን እና አባይ ነብያት ጉዳይ ነው ። ዓለም አጓጊ ሆናለች የኑሮ መበላለጡም እንደዛው በሽታው ድህነቱ ተበራክቶአል በተለይ በሀገራችን አብዛኛው ሰው ከድህነት ወለል በታች እየማቀቀ ይሆራል፥ ከዚህ አስከፊ ኑሮ ለመላቀቅ ሐሰተኞቹ ፍትሁን አስተምሮና ፣ትንቢት ፣የሚቸበቸቡ ውሀ፣ ዘይት፣ ቅባት አሏቸው ። አስቀድመው ችግሩን ይነግሩታል የምትጨነቅ ፣እንቅልፍ ያጣህ ፣መቼ ነው ? የእኔ ጉዳይ የምትል፣ወዘተ እያሉ በስሜት ቀስቃሽ ንግግራቸው ይነካኩትና ያስለቅሱታል ፡መለስ ብለው ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ ቀንበርህ ተሰብሮአል ይሉትና በሀሰት ተስፋ አጥግበው ያስጨበጭቡታል አብዛኛ ሰው ነብዩ ችግሬን አወቀልኝ ሚስጥሬን ነገረኝ በሚል የበላውን ሲያኩለት ሲፈነጥዝ ይውላል። ውሎ ሲያድር ጠብ የሚል ነገር ያጠል ምክንቱም የአንድን ሰው ጓዳጎድጓዳ የሚዘረዝሩት፤ 1.በፈጠሩት የመረጃ መረብ አማካኝነት የተለቃቀሙ መረጃዎ ናቸው፤ 2. ሥነ ለቦናዊ ታክቲክ ይጠቀማሉ ለምሳሌ ፦የማህበርሰቡን የወል ችግሮች ማንሳት ነው ፤ ይህ በትንቢት መልክ ሲነገር ገብያው የደራ ይሆናል፤ 3. የአየሩ ሁኔታ በማየት ሲደምን ይዘንባል በማለት የሚነገሩ ናቸው፤ 4.አጋንት የሚያናግራቸው አሉ። ተነቀለ የተባለው ሲያቆጠቁጥ ፤ ተቀበረ ያሉት ሲነሳ ሰው ግራ ይጋባል ፤ ደፍሮ ባያወጣም እምነቱ ይሸረሸራል። በሀገራችን ጦርነት ፣ድርቅ፣ረሀብ ፣ድህነት፣ በሽታ የሚፈራረቅባት ምድር ሆናለች ለዚህች ሀገር ምክሩም መልእክቱም መሆን ያለበት ጠንክራችሁ ስሩ የሚል ነው ። የማይሞላ ተስፋ ማሽጎድጎድ ሰቃይዋን ያረዝመው ካልሆነ በቀር መፍትሄ አላመጣም ሆኖም ግን ይህ ንግድ ለበርካታ ነብያት እና ሀሰተኛ መምህራን ቀን የወጣላቸው እና የሌሎችን ቀን ያጨለሙት በነዚህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ንግድ ላይ ተሰማርተው ነው ። ሌላው በከፍተኛ ሁኔታ የተጦጣፈው የዘይትና የውሀ ችብቸባ ነው ። ዛሬ የለም እንመለስ የሚሉ እንደማርቲን ያሉ ደፋሮች ያስፈልጉናል። በ15 ኛው እና በ16 ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የሰብአዊነት ፍልስፍና ወደ ጥንታዊ ምንጮች ማለትም የሮማውያን እና የግሪክ ፍስፍና እንመለስ ad fonts back to the sources የሚል ሁሉን አቀፍ የህይወት ፍልስፍና ሲቀነቀን ነበር ። እነ ማርቲንም ሉተርም ወደምንጩ እንመለሰ የሚለውን ሀሳብ በተመሳሳይ ተጋርተው አንጸባርቀውት ነበር። እነ ማርቲን ወደ ምንጩ እንመለስ ያሉት ወደ ጥንት የሐዋርያት አስተምህሮ ወደ እግዚአብሔር ቃል ነው። በመንፈሳዊ ዓለም ለውጥ የሚጀምረው ወደፊት በመሮጥ እና አዳዲስ ልምምዶችን በማምጣት ሳይሆን ወደ ተውነው ወደ ዘነጋነው #_የእግዚአብሔር_ቃል እና #_ወደ_አባቶች_እውነተኛ_የፍቅር #_የአንድነት #_የንጽህና_አስተምህሮ በመመለስ ነው ad fonts back to the sources ዛሬ እኛ ባለንበት ቦታ የለውጥ ሐዋርያ መሆን እንችላለን ዋጋ ለመክፈል ከፈቀድን እግዚአብሔር ይረዳናል ወደ ተውነው የቀድሞ የሐዋርያት እምነት እንመለስ ጌታ ይርዳን።
Show all...
ራእይ 22 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ እነሆም፥ #በቶሎ #እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ። … ¹² እነሆ፥ #በቶሎ #እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። … ¹⁷ መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ #ና #ይላሉ። የሚሰማም፦ #ና #ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ። … ²⁰ ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ #በቶሎ #እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።
Show all...