cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪

♥አላማው ☞መንፈሳዊ ወንድምነት እህትነት ማጠናከር ☞መንፈሳዊ ምግብን ተመግበን ንስሀ ገብተን በቅዱስ ቁርባኑ የበቃን መሆን ☞ተሞክሮዎችን በማካፈል መልካም ፍሬዎችን ማግኘት 👉ወደ ግሩፕ ለመቀላቀል @egzabehertalakenew

Show more
Advertising posts
1 808
Subscribers
-224 hours
-77 days
-2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድ አማኝ ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለበት ጊዜ በኋላ ኃጢአት ቢያስተው ይቀሠፋል የሚባለው ሙሉ ለሙሉ ሐሰት ነው፡፡ እንዲህ ቢሆንማ፥ እኔን ጨምሮ ስንት ሰው እስካሁን ተቀሥፎ አልቆ ነበረ፡፡ "እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን" ከምንልበት የቅዳሴያችን የኅብረት ተማጽኖ በተቃራኒ የተሰለፈ፥ ዲያቢሎስ የሚያራግበው የወሬ ነፋስ ነው ይሄ፡፡ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ሊቀ ካህኑ ኢየሱስ ራሱ ባርኮ ባቀበለው ሥጋና ደሙ ስለመቀደሱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የመከራዋ ለሊት ስትደርስ፥ ማታቸው ስትመጣ፥ የጨለማ ሥልጣናቸውን አግኝተው ክርስቶስን ያሰሩ ጉልበተኞች "አንተም ከእርሱ ጋር ነህ" ቢሉት ከአንድም ሦስቴ "ኸረ አላውቀውም" ሲል ካደ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 18፥25 ፤ የሉቃስ ወንጌል 22፥58) ሥጋውን በልቶ፥ ደሙን ጠጥቶ አላውቀውም? እንዴት ነው ነገሩ? ከተቆረበ በኋላ ስሕተት ሊኖር እንደሚችልና ጴጥሮስና ሐዋሪያቱ እነሆ በታሪካቸው አስተማሩ፡፡ አስቀድመው ሲከተሉት፣ ድንቅ ሥራውን ሲያዩ፣ ቃሉን ሲሰሙ የቆዩት ሥጋና ደሙን ከተቀበሉ በኋላ እንደማያውቁት ሆነው ጥለውት ሸሹ፡፡ ወደነበሩበት ሊመለሱ አፈገፈጉ፡፡ ሕብረተሰባችን መካከል ዛሬ እንደሚመላለሰው ወሬ ቢሆን፥ ሐዋሪያቱ መቀሠፍ ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ ሥጋና ደሙን ወስዶ ስለፈጸመው ጥፋት ንስሐ ገባ እንጂ አልተቀሠፈም፡፡ (የሉቃስ ወንጌል 22፥62) እንደውም ሦስት ጊዜ ደጋግሞ ከድቶ የነበረውን ስምዖን፥ በደልን ፈጽሞ የሚረሳው ጌታ ከትንሣኤው በኋላ ሲያገኘው "ትወደኛለህን?" አለው፡፡ ከዚህ በፊት በአስቸጋሪው ወቅት "አላውቀውም" ሲል የነበረው አገልጋይ፥ እዚህ ከንስሐ በኋላ ቋንቋው ተቀይሮ ሦስቴ "እንድወድህስ አንተ ታውቃለህ" ይለው ጀመረ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 21፥15-17) ፍቅሩንም ሕይወቱንም አሳልፎ ሰጠው፡፡ ወንጌል የሚያውቀው እውነት እንግዲህ ይሄ ነው፡፡ ዛሬ አንዳንድ የንስሐ አባቶች፣ አገልጋይ ነን የሚሉ ሰዎችና ማኅበረሰብ ወጣቱን ከማስተማር ይልቅ ያርቁታል፡፡ "ወዮውልሽ" አይነት ማስፈራሪያዎች ከዛም ከዚህም ይወረወራሉ፡፡ ጫት ሲበላ ተው ትቀሠፋለህ የሚል እምብዛም የለም፡፡ መጠጥ ሲጠጣ ተው ትጠፋለህ የሚል ትንሽ ነው፡፡ ሥጋና ደሙን ልውሰድ ሲል ግን ብዙዎች ያንጎራጉራሉ፡፡ ለምን? ለምን ከሥጋና ደሙን ወጣቶችን እናርቃለን? ወጣቶች እወቁ! ቅዱስ ቁርባንን ለመውሰድ የተቀመጠ የዕድሜ ገደብ የለም፡፡ "ወጣት ከሆንክ ስለምታጠፋ አትቁረብ" የሚሉት፤ ስለ አምልኮት ሕይወትና የክፉ መናፍስት ጥልቅ ሥራ በተግባር ያልተገነዘቡ፥ በልምድ አካሄድ የሃይማኖትን ጎዳና የጀመሩ ሰዎች እንጂ ቤተክርስቲያን አይደለችም፡፡ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቀድሳ ሥጋና ደሙን አዘጋጅታ ጠቦቶቿን ከእረኛቸው ሥጋ የማካፈል አደራዋን ዘወትር ትወጣለች እንጂ ዕድሜውን ቆጥራ "አንተ አትቁረብ" የምትለው አንድም ወጣት የለም፡፡ ሲሆንማ፥ ይልቁኑ ሥጋና ደም ለማን በጣም ያስፈልጋል ካላችሁኝ ለወጣቱና ለጎልማሳው ነው ያስፈልጋል የምለው፡፡ ምክንያቱም ስሜታዊነት የሚወጣበት፣ ጉልበት የሚጠነክርበት፣ ብዙ ሥራ የሚሠራበት፣ ትዳር የሚመሠረትበትና እንደ አገርም አምራች ዜጋ የሚኮንበት የዕድሜ ክልል ስለሆነ፥ በዚህ የጉብዝና ጊዜ ነው እግዚአብሔር አብሮ መገኘት ያለበት፡፡ ስሜታዊነትን ወደ መንፈሳዊ ኃይል እንዲቀይረው፣ ጉልበታችን በመናፍስት እንዳይደክም አሊያ ለክፋት እንዳይውል፣ ሥራችን እንዲባረክ፣ ትዳራችን እንዲሰምር፣ የአገር ፍቅር ከታሪክ ቁጭት ጋር ያለው የተቀደሰ ዜጋ እንዲኖር ሥጋና ደሙ መቅረብ የነበረበት ለወጣቶች ነበረ፡፡ አልሆነም! ተገላበጠና ወጣቶች ከቅዱስ ቁርባን ሲርቁ ይኸው ነገራችንም ከብዙ እውነቶች ተገላብጦ ቁጭ አለ፡፡ #ጸባዖት_ይከተላችሁ @bemaledanek
Show all...
እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ እንኪያስ ለምንድነው ምእመናን ከቅዱስ ቁርባን የተለዩት? ከክርስቶስ ማዕድ መካፈል ያቃተቸው ክርስቲያኖች ስለምን በርካታ ሆኑ? አዲስ ኪዳንን የምሕረት ዘመን ያሰኘው የመዳን ዋስትናችን የመስቀሉ መሥዋዕት ሆኖ እያለ ብዙዎች ከእርሱ ለምን ራቁ? የተዋሕዶ ሃይማኖት አንዱ ዓምድ (ዶግማ) የበጉ ሥጋና ደም ነው መባሉ በአማኞች ሕይወት ላይ ለምን በተጨባጭ አልተተረጎመም?.. ? የነዚህና መሰል ጥያቄዎች ቀጥተኛ መልስ በመነሻ አንቀጻችን ላይ የተጻፈው ይሆናል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ያለማቋረጥ የሚጥረው ዲያቢሎስ፥ አትንኩት ብሎ በዐዋጅ እንዲከለከሉ ካደረጋቸው ገደቦች መካከል መቀደስ (ቀ ጠብቆ ይነበብ) በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል፡፡ ስናስታውስ፥ በመጀመሪያ በእኛ በእግዚአብሔር መካከል "አትብሉ"ን አሰበልቶ ከፈቃዱ ነጥሎን ነበር፡፡ አሁንም ይሄው አካሄዱ ይዘቱን ሳይለውጥ ቀጠለና "ብሉ" የተባለውን አትብሉ አስደርጎ ፈቃዱን እንዳንኖር እየተዋጋን ይገኛል፡፡ የተከለከልነውን አስፈቅዶ፥ የተፈቀደልንን ከልክሎናል፡፡ አንባቢ የምለውን ተመልከት፥ በነገሩ ላይ ጌታ ማስተዋልን ይስጥህ! ክፉው መንፈስ እንደ ፍላጎቱ በሰውነታችን ላይ ፈላጭ ቆራጭ እንዲሆን እኛነታችንን ከመንፈስ ቅዱስ መለያየት ያስፈልገዋል፡፡ በቃ ቅዱስ ቁርባን ላይ ከተለያየ አቅጣጫ የተከፈተው አጠቃላይ ዘመቻ ከዚህ የጠላት ፍላጎት ይመነጫል፡፡ ከእግዚአብሔር በራቅን ልክ እርሱ ወደኛ የሚጠጋበት ርቀት ያጥርለታልና፥ ከአምላክ ጋር የሚያስተባብረንን የኪዳኑን ጸጋ እንዳናገኘው ባገኘውና በሆነለት መንገድ ሁሉ እየተጠቀመ ያሸሸናል፡፡ እንዴት?                           3.3.1.  በኃጢአት በኩል ኃጢአት በሰውና በአምላክ መካከል ያለ የዓመፅ ግድግዳ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር እንዳንሆን የሚፈልገው መንፈስ፥ ኃጢአትን በማስተዋወቅ፣ በማስፈጸምና በመምራት ከመለኮት ንጽሕና ይለያየናል፡፡ ብቻ ሳይሆን፥ ኃጢአት ከሕይወታችን ሳይወጣ እንዲቆይ በማጽናት ቅድሰና እንዳያገኘን ነቅቶ ይጠብቃል፡፡ የመድኃኒታችን ሥጋና ደም ስለ ኃጢአት ሥርየት የተሠዋ ዘላለማዊ መሥዋዕት እንደሆነ በክፍል ፫ አይተናል፡፡ እነሆም ዲያቢሎስ በኃጢአት ረግረግ ተውጠን እንድንያዝ ሲወድ፥ ኃጢአትን ከሥር መሠረቱ ነቅሎ የሚጥለውን ቅዱስ ቁርባን በእጅጉ ይጠላዋል፤ ይፈራዋል፡፡ ይሄንን ፍራቻውንም ባላጋራ ሆኖ ላደረበት አስተሳሰባችን ለማጋባት የሚከተሉትን ሁለት ዋና ዋና ስልቶች አቀናጅቶ ይተገብራል፡፡ እንመልከታቸው፡፡                       1•  ከኃጢአት የመላቀቅ ፍራቻ "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ለሥጋና ደሙ የበቃሁ አይደለሁም፤.. " የሚሉ ዓይነት ምላሾች፥ ቅዱስ ቁርባን ለምን እንደማይወስዱ ከተጠየቁ ብዙ ምእመናን ዘንድ ይነገራሉ፡፡ እነዚህ ንግግሮች በአብዛኛው ሰማያዊውን አምኃ ከማክበርና ከመፍራት የተነሱ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ በእርግጥስ፥ ከኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ አካል የሚያካፍለን ክቡር ሥጋና ክቡር ደም እንደምን ያለ የክብር ጥግ፣ እንዴት ያለ የፍርሃት መጨረሻ ቢቸረው (ቸ ጠብቆ ይነበብ) ይመጥነው ይሁን? ነገር ግን መላእክት፣ ቅዱሳን እና ቀደም ሲል እምነታቸውን በየዋህነትና በፍቅር ሲኖሯት የነበሩት ሁሉ ለቅዱሱ መሥዋዕት የሰጡት የክብር ፍራቻ፥ ለዛሬዎቹ እኛ፥ ከኃጢአት ሳይርቁ የመኖር ፍራቻን የምናለባብስበት መጋረጃ ሆኖ ነው እያገለገለ ያለው፡፡ የአብዛኞቻችን "ለክርስቶስ ሥጋና ደም አልገባም" (ገ ጠብቆ ይነበብ) ከምትለዋ የትሕትና ንግግር ጀርባ፥ ኃጢአትን የለመደ ሽሽግ ማንነት አለ፡፡ በሥጋዊቷ ዓለም ስንኖር ክፋቶች ክፉነታቸው እንዳይገለጥልን፥ ቢገለጥልንም ከክፋቶች እንዳንመለስ ማድረግ የክፉ መናፍስት ቀንደኛ ሥራ ነው፡፡ ይኸውም ከእግዚአብሔር የሆነ ቅዱስ ዕውቀት በማሳጣትና ኃጢአትን ተላምደን እንድንኖር ሁለንተናችንን በማጠር የሚከውኑት ይሆናል፡፡ ስለ ኃጢአትና የኃጢአት ራስ ዲያቢሎስ ደገኛ ትምህርት ካለማግኘታችን ጋር ተያይዞ፥ ዓለም በዘመናት ሂደት ሰብስባ ባጠራቀመቺው የአስተሳሰብ ሥርዓት እንድንቀረጽ እየሆነ ከልጅነታችን እናድጋለን፡፡ ይሄ አስተዳደጋችን ደግሞ፤ ጠባይን፣ ፍላጎትን፣ ውሳኔንና ዓላማን ሁሉ በተጽዕኖ የሚነካ፥ ከሕይወታችን ጋር ተጋብቶ ያለ የማንነት መገለጫችን ይሆናል፡፡ ክፉው ለዚህ አስተዳደጋችን ነው እንግዲህ ኃጢአትን በተለያየ ዕውቀት በኩል ለአመለካከታችን በመመገብ፥ ዓመፃዎችን ከለጋነት የሚያለማምደን፡፡ [ወጣቶች፥] ኋላችሁን አስቡት እስኪ፡፡ እስከ አሁናችሁ ድረስ ያወቃችኋቸውና የለመዳችኋቸው ነገራት ምንድን ናቸው? ለጽድቅ ያላቸው ቅርበት ለኃጢአት ያላቸው ርቅትስ ምን ይመስላል?.. ምእመናን ከኃጢአት ጋር ተዛምደው የኖሩባቸው የዕድሜ ቆይታዎች ወደ ተቀደሰው መብል እንዳይመጡ የሚጠልፉ ዕንቅፋቶች ናቸው፡፡ ትናንትናችን ተሳስሮት የቆየው የልምድ ኑሮ ለውጥን አፍኖ የሚይዝ የክፉ መንፈስ ጥምጣም ነው፡፡ ለረጅም ጊዜያት ከውስጣችን ሲገነባ የቆየን ካብ ማፍረስ ራሱን የቻለ ጣር አለበት፡፡ ለምሳሌ ሐሜት ዕለት ተዕለታችን የሆነብን ሰዎች ከቅዱስ ቁርባን በኋላ ያሉት ቀኖቻችንን ምን እንደሚያወሩ ከወዲሁ ስለምናውቅ "የበቃሁ አይደለሁም" በሚል ቋንቋ ሸፍነን "ልምዴን የምተው አይደለሁም" የምትል የውስጠታችንን መልእክት እንተነፍሳለን፡፡ ዝሙት፣ ስካር፣ ዳንኪራ፣ ጉቦ፣ ውሸት፣ ስርቆት፣ ትዕቢት፣ ምቀኝነት፣.. ምሳሌ እንደጠቀስነው እንደ ሐሜቱ ናቸው፡፡ እነዚህና ሌሎችም "ለቁርባን አልገባም" እያልን እሽሩሩ የምንላቸው፣ የዲያብሎስ መንፈስ በምሽግነት የተደበቀባቸው፣ እንድላቀቃቸው በጽድቅ ቀናዒነት ያልጨከንባቸው፣ ከዘወትር ደቂቃዎቻችን መካከል ቦታ ያገኙ ኃጢአቶቻችን፥ የአዲስ ኪዳኑ ታላቅ መሥዋዕት ከሕይወታችን እንዲቋረጥ ለአጥፊው መንፈስ በብዙ አግዘዋል፡፡                      2•   ከኃጢአት ያለመላቀቅ  ፍራቻ ቅዱስ ቁርባንን የተመለከቱ እንደ ማኅበረሰብ ደንቦች ሲዛመቱ ከምንሰማቸው ወጎች መካከል "ቁርባን ዓለም በቃኝ ላለ ሰው ነው፣ ከተቆረበ በኋላ ኃጢአትን መሥራት ያልተላቀቀ ይቀሠፋል" የሚሉት ዝነኛ ሆነው ከጫፍ ጫፍ ተዳርሰዋል፡፡ ያሳዝናል! ወገኖቼ፥ ክርስቶስ የሚያፈቅር እንጂ የሚቀሥፍ፣ የሚያከብር እንጂ የሚያዋርድ፣ የሚያነሳ እንጂ የሚጥል፣ የሚያቅፍ እንጂ የሚገፋ በጭራሽ አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም፤ ወደፊትም አይሆንም፡፡ እንኳን ሰዎችን "ሥጋና ደሜን ከወሰዳችሁ በኋላ ኃጢአት ሠራችሁ" ብሎ ሊያጠፋ ይቅርና፥ የጠፉ ሰዎችን ሲያይ የሚያለቅስ የዋህ አባታችን እንደሆነ የሰቀለቺውን ኢየሩሳሌም ባየ ጊዜ እንባውን አፍስሶ ገርነቱን ገልጧል፡፡ "በቅዱስ ቁርባን ምክንያት" መቅሠፍት ይመጣል የሚሉ መነሻቸው ያልታወቁ ድምፆች፥ ዲያቢሎስ የነዛቸው ተንኮሎች እንደሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ አዎ፤ የጌታን ሥጋና ደም ሳይገባን (ገ ላልቶም ጠብቆም ይነበብ) መውሰድ አይፈቅድም (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፥27)፡፡ ይሄ የሕግ ድንበር የተሰመረው ግን በመሢሑ በሥጋ መምጣት ያላመኑ፣ አምነውም በስሙ ያልተጠመቁ፣ የመስቀሉን ፍቅር ያልተቀበሉ፣ የቅዱስ ቁርባንን ሚሥጢር ያልተማሩ፣ መንፈሳዊ ኃይልን ለመፈታተን የሚቀበሉ፣ ለሌላ ድብቅ ተልዕኮና አጀንዳ የቀረቡ፣ ከመቁረብ በፊት ንስሐ ያልወሰዱ ሲኖሩ ለማረም ተፈልጎ እንጂ ክርስቲያኖችን ለማስፈራራት ታስቦ አይደለም፡፡ እንደውም ክርስቲያን ከክርስቶስ እንጀራና ጽዋ የማይካፈል ከሆነ ነው ዕዳ ያለበት፡፡
Show all...
3•  ቅዱስ ቁርባን   ክፍል - ፯        3.3•  የመናፍስት ውጊያ በቅዱስ ቁርባን ላይ ውድቀትን በባሕሪዩ የተጣባት ክፉ መንፈስ "አምላክ እኔ ነኝ" ሲል ዋሽቷል፡፡ እንደ ፈጣሪ መሆን ተስፋ አልቆርጥ ያለ ምኞቱ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ወዳስገኛቸው እያመለከተ "የእኔ ናቸው" ማለትን ከጥንት ጀምሯታል፡፡ የሰውን ልጅ ጭምር! ሰውነት ቤተመቅደስነት እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡ ዲያቢሎስ በዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ ነው መመለክ የሚፈልገው፡፡ የሰውን ልጅ መግዛት፣ መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ልክ እንደ አምላክ "ይሄን ይሄን አትንኩ" የሚላቸውን ትእዛዛት ያሰቀምጣል፡፡ እርሱ እንደፈቀደው እንዴት መኖር እንዲገባን ደንብና ሥርዓት የሚያሳዩ ሕግጋት ያረቃል፡፡ ከእግዚአብሔር በተቃራኒ የሚሠራ መንፈስ እንደሆነ ሲታወቅ፥ ሕግ አድርጎ የሚያስቀምጣቸው ትእዛዛቱ የእግዚአብሔርን እንደሚጻረሩ እንዲሁ ለመገመት አይከብድም፡፡ ጽድቅን የሚጠሩና በጽድቅ የሚያኖሩ ማንኛቸውንም ነገራት አትንኩ ይላል፡፡ ይሄ የክፋት ኃይል አዳምን ካሳተ በኋላ ዓለምን በመላ በራሱ መስመርና ዓላማ ለመምራት ያለመታከት ሲደክም ዘመናትን አሳልፏል፡፡ ተሳክቶለትም የምድር ማዕዘናት ጽድቅን በሚቃወሙ፣ በሥጋ ድክመት ላይ በሚመኩ ሥርዓቶች እንዲተዳደሩ አስገድዷል፡፡ ከዚህም የተነሳ በምድራችን የአስተሳሰብና የኑሮ ሚዛን ቅዱስ የሆኑት ከብደው፥ ርኩሳኑ በእጅጉ ቀልለውና በዝተው ይገኛሉ፡፡ ለዚህ በቂ ማሳያ አድርገን የምንናነሳው ርእሳችንን፥ የአዲስ ኪዳኑን አማናዊ ቃልኪዳን፥ የመድኃኒታችንን ሥጋና ደም ነው፡፡ [በተለይ] ባለንበት በዚህ ዘመን፥ ቅዱስ ቁርባን ሲባል የሚጠራው የኪዳኑ ስጦታ ከሰዎች ሕይወት በእጅጉ የራቀ ጉዳይ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ከታዳጊነት እስከ መካከለኛው የዕድሜ እርከን ያሉ ብዙ አማንያን፥ ከሰማያዊው ማዕድ መካፈል ካቆሙ ሰነባብተዋል፡፡ ቅዱስ ቁርባን በእርጅና ጊዜ የሚወሰድ ልምዳዊ ድርጊት ወደ መሆን ከመጣ ቆየት ብሏል፡፡ ሕፃናት እስከ ዐሥራ መጀመሪያዎቹ ይቆርባሉ፤ ከዛ ሥጋና ደሙ የጠፋ እስኪመሰል ከቁርባን ጠፍተው ያድጋሉ፡፡   በመሆኑ ብዙው ሰው፥ "አንቱ በመቁረቢያ ዕድሜዎት እንዲህ ያደርጋሉ እንዴ?" እስከሚባልበት የጊዜ ማምሻ ድረስ ሕይወት እንደመራው፥ ኑሮ እየጣለው፥ እርሱም ሌላውን እየጣለ፥ የነፍስ እውነትን ረስቶ ይቆይና፤ የዕድሜ በረከት አግኝቶ ለሽበት ሲደርስ ቅዱስ ቁርባን ይቀበላል፡፡ ለዚህ ካልታደለም በዛው ጥቁር ጸጉር ሳለ፥ ጥቁር ኃጢአትና ጨለማ ዘመን ወርሶት፥ "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ እኔ በእርሱ እኖራለሁ እርሱም በእኔ ይኖራል" ያለውን፥ የክርስቶስን ወዳጅነት በወጣትነቱ ሳያገኘው ወደ መቃብር ይሸኛል፡፡ ለመሆኑ ይሄ የሆነው ለምንድነው? ስለ ቅዱስ ቁርባን ስንማር የቆየነው ቃል ምንድን ነው? በውስጣችን ተቀርጾ ያለው መንፈሳዊ ትምህርት ምን አይነት ነው? እንዴት ነው ክርስትናን የተረዳነው? የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት እንዴት ነው የምንመለከታቸው? ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ ሞትን ድል ነሥቶ የዘላለም ሕይወት ሰጠን የሚለውን የድኅነት አገላለጽ እንዴት ነው የተገነዘብነው? ክርስቲያኖች ነን ስንል መቼም በክርስቶስ አምነን ነው፡፡ በክርስቶስ ስናምን፥ የተናገራቸውን የታመኑ ቃላት እናምናለን ማለት ይሆናል፡፡ እንግዲያው "እንካችሁ፥ ብሉ ይሄ ሥጋዬ ነው፤ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ኃጢአት የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይሄ ነው" ያለውን ቃል እንዴት ነው ያመንነው? "ሰው ዓለሙን ሁሉ አትርፎ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?" የሚለው ንግግር የቅዱስ ቁርባን ልክ ይዞ ቢነገር "ክርስቲያን ነገርን ሁሉ አድርጎ የክርስቶስን ሥጋና ደም ካልተቀበለ ምን ይበጀዋል?" ሊባል ይችላል፡፡ ይህም ማለት እንኳን ዓለማዊ፥ መንፈሳዊ ጉዳዮችን ሁሉ ምእመናን አድርገው፥ ከሥጋና ደሙ ጋር ባወቀ ካልተገናኙ ትልቁን ዋጋ አጥተውታል ማለት ነው፡፡ አስተምህሮቱ "የሚሥጢራት ሁሉ ፍጻሜ ቅዱስ ቁርባን ነው" እያለ የሚያውጀው ለዚህ ነው፡፡ ታዲያ ምንድነው የምናስበው? ምንድነው ከውስጣችን ቆይቶ ለዘመናት የገዛን አመለካከት? ስለ ዘላለም ሕይወት ያለን መንፈሳዊ እይታ ርቀቱ እስከየት ይጠልቃል? ስለ መቁረብ ስናስብ ምንድነው ወደ ጭንቅላታችን አስቀድሞ የሚመጣው?    ብዙ ክርስቲያኖች ለቅዳሴ ይቆማሉ፡፡ የሚቆርቡት ግን ከሕፃናትና ከአዛውንት ውጪ ከእጅ ጣቶች የማይበልጡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ይሄም ነገር የተለመደ ከመሆን አልፎ አሁን ያልተለመደው የወጣቶች ከሕይወት እንጀራ መቁረስ ሆኗል፡፡ ለምንድነው ነው እንደዚህ የሆነው? ለምንድነው ወጣቶች ከክርስቶስ ሥጋና ደም የማይቀበሉት? ለምንድነው መምህራን ስለዚህ ነገር አበክረው የማያሳስቡት? የሚያሳስቡትንስ፥ አማኙ ሕብረተሰብ የማይሰማቸው ለምንድነው? ሥርዓተ ቅዳሴ ያለ ቅዱስ ቁርባን መሥዋዕት ቅዳሴ ይባል ዘንድ አይችልም፡፡ ዝርዝር ትንታኔ ውስጥም ሳንገባ ከስያሜው ብንጀምር "ቅዳሴ" የሚለው ቃል የሚጠቁመው አንድን ነገር የመቀደስ ሂደት ነው፡፡ ያ በምስጋና፣ በአምልኮትና በኅብረት ጸሎት የሚቀደሰው ነገር ሕብሥተ ስንዴው እና ሕብሥተ ወይኑ ነው፡፡ የተቀደሰው ማዕድ ከዛ በእምነት የሚወስዱትን ሁሉ ይቀድሳቸዋል፡፡ ከቤተልሔም እስከ ቀራኒዮ የሚገሰግሰው ቅዳሴ፥ ዋነኛ አንድምታው ይሄ ነው፡፡ ቅዳሴ የአዲስ ኪዳን ቃልኪዳን የሚፈጽምበት ሰማያዊ ሥርዓት ነው መባሉ በክርስቶስ ሥጋና ደም ምክንያት ነው፡፡ ያለ ቅዱስ ቁርባን ቅዳሴ የለም፡፡ በዚህ መሠረት ቅዳሴ አስቀድሰን ከተቀደሰው ምግብና መጠጥ የማንሳተፍ ሰዎች፥ ምን ቀድሰንና በምን ተቀድሰን እንደተመለስን ያልታወቀበት ቆይታ አድርገን ነው የመጣነው ማለት ነው፡፡ ሱታፌ ቅዳሴ ኖሮ ከቅዱስ ቁርባን አለመቀበል አግባብ እንዳልሆነ የቤተክርስቲያን አያሌ ሥርዓተ መጽሐፍት በግልጽ ይደነግጋሉ፡፡ ሌላውን እንተወውና ራሱ ቅዳሴ ከቅዱስ ቁርባን [በፍትሐ ነገሥት ከተዘረዘሩ በቂ ምክንያቶች ውጪ] ሥጋና ደሙን አለመቀበል የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ስለመሆኑ ገና በመግቢያው ክፍል ላይ ያስጠነቅቃል፦         "በቅዳሴ ጊዜ የሚገኙ ምእመናን፥ መጽሐፍተ ቅዱሳትን ባይሰሙ፣ ቅዳሴ እስኪፈጸም ድረስ ባይታገሡና ከቁርባንም ባይቀበሉ ከቤተክርስቲያን ይሰደዱ፤ ሕገ እግዚአብሔርን አፍርሰዋልና"                                                         መጽሐፈ ቅዳሴ የቅዳሴ ብቻ ሳይሆን የንስሐም አድራሻ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ "በአዲሱ አቁማዳ አዲሱ ወይን ሊሞላ ይገባል" የሚለውን የጌታ ትእዛዝ ይዛ፥ ቤተክርስቲያን ማንኛውም ግለሰብ ሥጋና ደሙን ከመቀበሉ በፊት ንስሐ እንዲገባ ታዝዛለች፡፡ በመሆኑ ቅዳሴ ያስቀደሰ ሰው መቁረብ እንዲገባው ሁሉ፥ ንስሐውን የጨረሰ አማኝም ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ምርጫው አይደለም፡፡ የውዴታ ግዴታው ነው፡፡ ጸድቶ የተቀመጠ ብርጭቆ ለታጠበለት አገልግሎት ካልዋለ፥ ቆሽሾ ከተቀመጠው ብርጭቆ ከመታጠቡ ባሻገር አልተለየም፡፡ ንስሐ የገባም አንድ ሰው፥ ከእግዚአብሔር መንግሥተ ማዕድ ተካፍሎ የዘላለም ሕይወትን የቃልኪዳን ማኅተም በሰውነቱ እስካልያዘ ድረስ የንስሐውን አገልግሎት ከግብ አላደረሰም፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 6፥51)
Show all...
✝ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ / በኦድዮ ለማግኘት ከስር ( ክፈት ) ሚለውን ይጫኑ።
Show all...
ክፈት
ለመ🀄️ላ🀄️ል
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
Show all...
💒 ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን 💒
⛪️ የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ⛪️
✝ መንፈሳዊ ትምህርት ✝
✝ ኪነ ጥበብ ብቻ ✝
✝ በማለዳ ንቁ !፪ ✝
✝ ታሪክ ዘ ኢትዮጵያ ✝
💠 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 💠
✝ ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ ✝
✝ ዘ ተዋሕዶ ✝
🌷Harmee Tewaahidoo🌷
✝ ቤተ_ልሔም ~ Betelehem
✝ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ✝
💒 ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር 💒
💒 መዝሙረ ማህሌት 💒
🇨🇬  ደጉ ሳምራዊ  ✝
💒 ኑ በብርሀኑ እንመላለስ 💒
🔔 የተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
💠 በዓላት 💠
🖱መንፈሳዊ ፊልም 🖱
🖱መንፈሳዊ ግጥም 🖱
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
🔔 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆 የተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ቻናሎች መገኛ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
Photo unavailableShow in Telegram
Show all...
💒 ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን 💒
⛪️ የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ⛪️
✝ መንፈሳዊ ትምህርት ✝
✝ ኪነ ጥበብ ብቻ ✝
✝ በማለዳ ንቁ !፪ ✝
✝ ታሪክ ዘ ኢትዮጵያ ✝
💠 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 💠
✝ ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ ✝
✝ ዘ ተዋሕዶ ✝
🌷Harmee Tewaahidoo🌷
✝ ቤተ_ልሔም ~ Betelehem
✝ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ✝
💒 ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር 💒
💒 መዝሙረ ማህሌት 💒
🇨🇬  ደጉ ሳምራዊ  ✝
💒 ኑ በብርሀኑ እንመላለስ 💒
🔔 የተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
💠 በዓላት 💠
🖱መንፈሳዊ ፊልም 🖱
🖱መንፈሳዊ ግጥም 🖱
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
🔔 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆 የተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ቻናሎች መገኛ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
✝ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ / በኦድዮ ለማግኘት ከስር ( ክፈት ) ሚለውን ይጫኑ።
Show all...
ክፈት
ለመ🀄️ላ🀄️ል
Free FaceSwap🤖
garment removal🙈
Show all...
💒 ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን 💒
⛪️ የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ⛪️
✝ መንፈሳዊ ትምህርት ✝
✝ ኪነ ጥበብ ብቻ ✝
✝ በማለዳ ንቁ !፪ ✝
✝ ታሪክ ዘ ኢትዮጵያ ✝
💠 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 💠
✝ ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ ✝
✝ ዘ ተዋሕዶ ✝
🌷Harmee Tewaahidoo🌷
✝ ቤተ_ልሔም ~ Betelehem
✝ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ✝
💒 ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር 💒
💒 መዝሙረ ማህሌት 💒
🇨🇬  ደጉ ሳምራዊ  ✝
💒 ኑ በብርሀኑ እንመላለስ 💒
🔔 የተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
💠 በዓላት 💠
🖱መንፈሳዊ ፊልም 🖱
🖱መንፈሳዊ ግጥም 🖱
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
🔔 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆 የተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ቻናሎች መገኛ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
Free FaceSwap🤖
garment removal🙈
✝ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ / በኦድዮ ለማግኘት ከስር ( ክፈት ) ሚለውን ይጫኑ።
Show all...
ክፈት
ለመ🀄️ላ🀄️ል
Free FaceSwap🤖
garment removal🙈
Show all...
💒 ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን 💒
⛪️ የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ⛪️
✝ መንፈሳዊ ትምህርት ✝
✝ ኪነ ጥበብ ብቻ ✝
✝ በማለዳ ንቁ !፪ ✝
✝ ታሪክ ዘ ኢትዮጵያ ✝
💠 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 💠
✝ ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ ✝
✝ ዘ ተዋሕዶ ✝
🌷Harmee Tewaahidoo🌷
✝ ቤተ_ልሔም ~ Betelehem
✝ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ✝
💒 ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር 💒
💒 መዝሙረ ማህሌት 💒
🇨🇬  ደጉ ሳምራዊ  ✝
💒 ኑ በብርሀኑ እንመላለስ 💒
🔔 የተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
💠 በዓላት 💠
🖱መንፈሳዊ ፊልም 🖱
🖱መንፈሳዊ ግጥም 🖱
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
🔔 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆 የተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ቻናሎች መገኛ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
Free FaceSwap🤖
garment removal🙈