Gonder muslims couples
Open in Telegram
1 418
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ኩልሱም ቢንት አቢበክር እንዲህ አለች፦
"በኔ ላይ ፍቅርን ማፍሰስን የሚያፈስብኝ የሆነንና ለሱም ምርጥ ባሪያ የሆነን ባል እንዲወፍቀኝ አላህን ለመንኩት"
አላህም ጀነት ከተመሰከረላቸው አስርቱ ሰሀቦች ውስጥ "ጠልሃ ቢን ኡበይዱላህ"ን ወፈቃት።
ሰለፎች ከሷ ወስደው እንዲህ ማለቷን ዘግበዋል፦
"እኔን ባየ ቁጥር ፊቱ እንደ ጨረቃ ያበራል፣ ድምፄን ሲሰማ ይደሰታል(ፈገግ ይላል)፣...ባለቀስኩ ጊዜ ያለቅሳል...በደረቴ ላይ እስካልተረጋጋ ድረስ እንቅልፍ አይወስደውም ነበር...ከሱ በፊት ለኔ ዱአ ሳያደርግ በፊት ከሰላት ተነስቶ አያውቅም...በታመምኩ ጊዜ ህመሜን ይካፈለኝ ነበር....የህመሙ ምልክት እሱ ላይ እስኪታይበት ድረስ...ጎኑ እስካላስቀመጠኝ ድረስ አይረጋጋም ነበር...ለምግብ ስንቀርብ ቀድሞ ለማጉረስ ይሽቀዳደመኝ ነበር...ቀድሞም ያጎረሰኝ ነበር..
#ቤት_ውስጥም_ከቤት_ውጭም_እኔ_ለሱ_ኩራቱና_ክብሩ_ነበርኩ።"g
ምንም አልረባም ብለህ በተደጋጋሚ በራስህ ተስፋ የቆረጥክበት ጊዜ አለ፡፡ አላስፈልግም ከንቱ ነኝ ብለህ ራስህን የረገምክበት ጊዜም ብዙ ነው፡፡ ከባድ ችግር አግኝቶህ ሞትን በራስህ ላይ የጠራህበት ጊዜም አንድ ሁለት አይባልም፡፡
እናት መርየም፣ ያች ቅድስቲቷ እመቤት ... ምጥ ላይ በሆነች ጊዜ ጭንቅ ተደራረበባትና “ ዋ ምነዋ ከዚህ ፊት ሞቼ ተረስቼ በሆነ ኖሮ!” አለች፡፡ በሆዷ ምን እንደያዘች ሳትገነዘብ።
ከባዱ ምጥ የያዘው ከባዱን ሰው ነበር፡፡ ነቢዩ ዒሳን (ዐለይሂ ሰላም)፡፡
ዱንያ መላ አካለዋ ምጥ ነው ወዳጆቼ፡፡ ከተፈጠርንበት ጊዜ ጀምሮ ምጧ አልተፋታንም ይሆናል፡፡ ግና ቀናት ምን እንዳረገዙም አናውቅም። ፈተናና ችግሮቻችን ነገ መልካም ነገር ይወልዱ ይሆናል ማን ያውቃል።
መልካም ሚስት የባሏ ንግስት የልጆቿ መምህር የቤቷ ድምቀት ነች"
መልካም ሚስት ከትላልቅ የአላህ ፀጋዎች ናት
من رزقه الله امرأة صالحة عاقلة فقد زاده دينا وعقلا
【فهنيئا له】
አላህ አስተዋይ የሆነች መልካም ሚስት የሰጠው ሰው በእርግጥም አላህ ዲንና አቅሉ ጨመረለት።
【ይህ ሰው ምንኛ ታደለ】
https://t.me/gondermuslimcouples
የዐረፋ ፈገግታ ☺️
ቃዲ-አህዋዝ ..( አህዋዝ በአሁን ሰዓት ኢራን ውስጥ የምትገኝ ከተማ ናት ።) የዚች ከተማ ቃዲ የሸሪዐ ዳኛ በጣም ድሀ ነበሩ.. የዐረፋ በዓል መጥቶባቸው የሚያርዱት ነገር አላገኙም። ይሄን ጭንቀታቸውን ለባለቤታቸው ሲያካፍሏት ..
እሷም : « አትጨነቅ ፣ ያደለብኩት አንድ ትልቅ ዶሮ አለ ..ዒዱ ሲመጣ እሱን እናርድና በሱ እንብቃቃለን ».. ትለዋቸዋለች..
የዐረፋ ዒዱም ደረሰና ሊያርዱት ሲዘጋጁ እንደ ድንገት ዶሮው በሮ የጎረቤት አጥር ላይ መሮጥ ሲጀምር ማሯሯጥ ጀመሩ ወሬውም ተሰራጨና ሰዎች ዘንድ ደረሰ ።
የሰፈሩ ሰው ባለሀብቶች ነበሩና ለቃዲያቸው አዝነው እያንዳንዱ አንድ አንድ በግ ወደ ሼኹ ቤት ይልካሉ።
እሳቸው ለሰላት በሄዱበት ቤታቸው ውስጥ ብዙ በግ ተሰብስቧል .. የሚያውቁት ነገር የለም። ከሰላት ቡኃላ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ይሀን ሁሉ በግ ያዩና ምንድነው ብለው ባለቤታቸውን ይጠይቃሉ.. እሷም እንትና እንትና እንትና እያለች ስም እየቆጠረች በግ የሰጧቸውን ሰዎች ጠቀሰችላቸው።
እሳቸውም : « በይ እንግዲህ ይሄን ዶሮዋችንን በደንብ አድርገሽ ጠብቂው ተንከባከቢው ፤ የኢብራሂም ልጅ እኮ አንድ በግ ነው ፊዳ የሆነለት.. ይሄ የእኛ ዶሮ ይሄ ሁሉ በግ ነው ፊዳ የሆነለት ...!!» 😅 አሏት ..
ይሄን ቂሷ
📗 ኢብኑ ዐብዱል በር በህጀቱል መጃሊስ ኪታባቸው
📗 ኢብኑል ሙፍሊሕ አል ኣዳብ አሽ-ሸርዒያ ኪታባቸው ላይ አስፍረውታል ..
Social media
ከፓኪስታን - መካ በእግር . . .
የፓኪስታኑ ተማሪ ኡስማን አርሻድ ለሃጅ ሃይማኖታዊ ጉዞ ጃንጥላ እና በጀርባ ላይ የሚታዘል ሻንጣ ይዞ 4,000 ኪሎ ሜትር በእግሩ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ደርሷል።
አቅሙ ያለው ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለማሳካት የሚመኘውን የሃጅ ጉዞ ኡስማን አርሻድ በእግሩ በመጓዝ አውን አድርጎታል።
ጉዞውን የጀመረው፤ከትውልድ ከተማው የፓኪስታኗ ኦካራ ሲሆን፣ስድስት ወራትን ተጉዞ ነው መካ የደረሰው።
ቅዱሱን የሃይማኖታዊ ጉዞ በእግሩ የፈጸመው ኡስማን በሺዎ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በእግር በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ለመድረስ የተለያዩ አገራትን ማለትም ኢራን፣የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን አቆራርጧል።
ኡስማን አርሻድ ስለ ጉዞው ምን አለ?
" ሁሉም ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ መካ መጥቶ የፈጣሪን ቤት ማየት ይነኛል።
የእኔ ምኞች ደግሞ በእግር ተጉዤ የፈጣሪንና የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መስጂድ ማየት ነበር።
ጉዞው ከባድ ነበር የኢራቅ ቪዛን ማግኘት ስላልቻልኩ ከኢራቅ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ለመግባት ጀልባ ነበር የተጠቀምኩት
አንዳንድ ችግሮች ነበሩ መጥፎ የሆነ የአየር ሁኔታ እና በጉዞው ምክንያት እግር መቁሰል አጋጥሞኛል
አብዛኛው መንገድ ሰው የማይታይበት እና መንደርም ሆነ ከተማ ያልነበረው ነው
ጉዞዬን እንድቀጥል ያደረጉኝ መንገድ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎች ናቸው
ረጋ ብዬ ጉዞዬን መጨረስ እንዳለብኝ አበረታተውኛል
ባገኘሁበት ቦታ ነበር የማድረው፣ በመስጂድ፣በፍተሻ ጣቢያ በሆቴል፣ ወይም እንዳርፍ ከፈቀዱልኝ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል
አማራጭ ሳጣ ድንኳን ጥሬ በረሃ ላይ ብዙ ጊዜ አድሬያለሁ
በመጨረሻም ከ6 ወር በኃላ ያሰብኩበት ደርሻለሁምንም ነገር ማድረግ ብትፈልጉ በራሳችሁ ተማመኑ
ማንኛውንም ጉዞ እንድትፈፅሙ ፈጣሪ ይረዳችኋል
BBC - Al Jazeera

الله اكبر الله اكبر الله اكبر لا اله الا الله
الله اكبر الله اكبر ولله الحمد
لبيك اللهم لبيك لبيكلاشركلك لبيك
عيد موبارك
ኮሎራዶ ውስጥ በሚገኘው በዚህ የስጦታ መሸጫ መደብር ውስጥ አንዲት ያልታሰበች እንግዳ ድንገት መጣች ። ይህች እንግዳ ፡ በአካባቢው ከሚገኘው ጫካ እግር ጥሏት የመጣች አጋዘን ናት ። እና ልክ እንደቤቷ ሰተት ብላ ወደመደብሩ ስትገባ ያየቻት የመደብሩ ባለቤት ፡ አላባረረቻትም ። ይልቁንም ፡ እንኳን ደህና መጣሽ በሚል ስሜት ተቀብላት ፡ ከወንበሯ ተነስታ ዳበሰቻት ፡ ኩኪስ ትበላ እንደሁ በማለት አውጥታ ሰጠቻት ፡፡ አጋዘኗ የተሰጣትን ኩኪስ በላች ፡ እና ከመደብሩ ወጥታ ሄደች ።
ከግማሽ ሰአት በኋላ ፡ የቅድሟ አጋዘን ተመልሳ ኩኪስ ወደተሰጣት መደብር ተመልሳ መጣች ። አሁን ግን ፡ ብቻዋን አልነበረችም ። እኔ የቀመስኩትን ይቅመሱ ብላ ልጆቿንም አስከትላ ነበር የመጣችው ።
" አዳኝ ብሆን ፡ ትሸሸኝ ፡ ነበር ፡ ባባርራት ተመልሳ አትመጣም ነበር. .. ነገር ግን ለአጋዘኗ ጣፋጭ ኩኪስ ሰጠኋት ፡ ይህን እሷ የቀመሰችውን ነገር ለልጆቿም እንድሰጥላት ፡ ልጆቿን አስከትላ መጣች ። በየትኛውም አጋጣሚ ፡ ለማንኛውም ፍጡር ፡ ፍቅርን ከመስጠት ወደኋላ አንበል ስትል ምስሉን በድረገፅ አጋርታለች ፡፡
ከ ፌስቡክ መንደር
#የአሏህ_ስጦታ
የትዳር አጋርህን በማንኛውም ሁኔታ ላይ የሚትችላት (የሚትታገሳት) መሆን አለብህ።
የትዳር አጋርህን አስደስታት ያንተን ደስታህን ከሷ ደስታ ታገኘዋለህ
ፍቅርህን ሁሌም ግለፅላት
ፍቅርን በደንብ ልትሰጣት እንዲሁም ልትንከባከባት ይገባሀል።
ሁሌም ስጦታ ማበርከትህን አትርሳ
ስትታመም ወደ ጎን መተው የለብህም!
ወይም በመካከላቹህ የሆነ ነገር ሲከሰት አንተ ወንድ ስለሆንክ ብቻ እሷ ይቅርታ ለመጠየቅ የምትቸገር መሆን የለባትም!
በመካከላቹህ የነበረውን ፍቅር ረስተኸው ነው!?
ልጆች እንዳላቹህ ረስተህ ነው!?
ትክከለኛ ወንድ ማለት ኒያውን ለአሏህ አጥርቶ በሁሉም ሁኔታ ማስተካከል የሚጀምር ነው።
ጥሩ የትዳር አጋር ማለት ሚስቱን የተንከባከበ ስትደክም አበርትቶ በድካሟም ጊዜ ሊረዳትና ሊንከባከባት የሚችል ነው
ምክኒያቱም
ሚስት የ አሏህ ስጦታ ነች
Hubi
https://t.me/gondermuslimcouples
ከሁሉም የሰላት ጥሪዎች (አዛን) እንደ ፈጅር አዛን ጥርት ብሎ የሚሰማ የለም። ለጥሪውን ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው ምላሽ የሚሰጡት።