en
Feedback
Motivational Speech & Truth

Motivational Speech & Truth

Open in Telegram

💎እኳን ወደቻናላችን በደህና መጡ 🌐ይህ ቻናል አናቃቄ ንግግሮችን ፣ ምስሎችን፣ቪዲዬወችን እና ጥቅሶችን በአማርኛ እና በእግሊዘኛ ያቀርባል፡፡ 🌐በተጨማሪም፦የተመረጡ ወቅታዊ እና አገብጋቢ የሆኑ እዉነታወችን በመምረጥ ያቀርባል 🔵 እረሶ ተጠቅመው ለወዳጅዎም Invite ማድረግዎን እንዳይረሱ! 👥 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ያሳዉቁን 👇👇 @Motiv2team @motivational6

Show more
4 422
Subscribers
-424 hours
-227 days
-5330 days
Posts Archive
አንተ ሁሌም ከችግሩ በላይ ነህ በሕይወትህ ውስጥ ችግሩን ከማሸነፍህ በፊት ችግሩ የማይታለፍ እና ከባድ ነበር የሚመስልህ ችግሩን ካለፍከው በኋላ ግን ሁሉም ችግር አላፊ እና የሚረሳ መሆኑን ትረዳለህ፤
አንተ ሁሌም ከችግሩ በላይ ነህ በሕይወትህ ውስጥ ችግሩን ከማሸነፍህ በፊት ችግሩ የማይታለፍ እና ከባድ ነበር የሚመስልህ ችግሩን ካለፍከው በኋላ ግን ሁሉም ችግር አላፊ እና የሚረሳ መሆኑን ትረዳለህ፤ ምን ጊዜም ችግሩን ማሸነፍ የሚችል ሰው ሆነህ መገኘት አለብህ። የሰው ልጅ ደግሞ የማሰብ ነፃነት አለው፤ ማሰብ የአዕምሮ መሳሪያህን በመጠቀም ቀዩን የማትፈልገውን የህይወትህን ገፅ አቃጥለህ ከአዕምሮህ አውጣው፤ ስታቃጥለው ድጋሜ በህይወትህ ስላቃጠልከው ነገር አዕምሮህ እንዲያስታውስ እድል አትስጠው። ውብ ቀን @motivational6

ሁሉም ለበጎ ነው! ፈጣሪ በነገሮች በሁኔታዎች ነው የሚናገርህ፤ በጆሮህ መጥቶ እንዲህ አድርግ አይልህም፤ በህይወት እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ለምክንያት ነው። ንቁ ሆነህ በህይወትህ የሚሆነውን ሁሉ ማ
ሁሉም ለበጎ ነው! ፈጣሪ በነገሮች በሁኔታዎች ነው የሚናገርህ፤ በጆሮህ መጥቶ እንዲህ አድርግ አይልህም፤ በህይወት እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ለምክንያት ነው። ንቁ ሆነህ በህይወትህ የሚሆነውን ሁሉ ማስተዋል አለብህ! ደግሞ አትርሳ ተማሪ ካለ አስተማሪ የትም ቦታ አለ። 🙏🙏🏻🙏🏻🙏🏻🙏🏻🙏🏻 @motivational6

👆🏽👆🏻👆 ‹‹የተወሰኑ ነገሮች አይንህን ይይዙሃል፤ ነገር ግን ልብን የሚይዙትን ነገሮች ብቻ ፈልግ። ምክንያቱም አንተ የምትለወጠው በልብህ ውስጥ ያለው ስሜት ሲለወጥ ብቻ ነው። 🙏የተባረከ ውሎን ተመኘንልዎ @motivational6

የምትፈልገውን ሕይወት ለመኖር ምን ገታህ? ምን ገታሽ? ፍርሃት፣ ገንዘብ፣ ስንፍና፣ ወቅታዊ ሁኔታዎች ወይስ አላወቁትም @motivational6
የምትፈልገውን ሕይወት ለመኖር ምን ገታህ? ምን ገታሽ? ፍርሃት፣ ገንዘብ፣ ስንፍና፣ ወቅታዊ ሁኔታዎች ወይስ አላወቁትም @motivational6

🗣ራሳችንን ማክበር አለብን ወደ ሀሳባችን የምንከተው ማንኛውም ነገር እኛን ይቆጣጠረናል። ምንም አይነት ዜና ፣ ፊልም ከማየታችን በፊት እውነት ይሄን ነገር ካየሁ በኋላ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል ፣ ደስተ
🗣ራሳችንን ማክበር አለብን ወደ ሀሳባችን የምንከተው ማንኛውም ነገር እኛን ይቆጣጠረናል። ምንም አይነት ዜና ፣ ፊልም ከማየታችን በፊት እውነት ይሄን ነገር ካየሁ በኋላ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል ፣ ደስተኛ እሆናለው ፣ እማርበታለው ? ብለን እንጠይቅ። ገራሚ ከሰዓት ተመኘን🙏 @motivational6

🗣ራሳችንን ማክበር አለብን ወደ ሀሳባችን የምንከተው ማንኛውም ነገር እኛን ይቆጣጠረናል። ምንም አይነት ዜና ፣ ፊልም ከማየታችን በፊት እውነት ይሄን ነገር ካየሁ በኋላ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል ፣ ደስተ
🗣ራሳችንን ማክበር አለብን ወደ ሀሳባችን የምንከተው ማንኛውም ነገር እኛን ይቆጣጠረናል። ምንም አይነት ዜና ፣ ፊልም ከማየታችን በፊት እውነት ይሄን ነገር ካየሁ በኋላ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል ፣ ደስተኛ እሆናለው ፣ እማርበታለው ? ብለን እንጠይቅ። ገራሚ ከሰዓት ተመኘhu 🙏 @motivational6

🦚የዱባና የቲማቲም ተክሎች በሳምንት እና ቀናት ውስጥ ያድጋሉ፤ ለረጅም ቀናትና ሳምንታት ፍሬያማ ሆነው ብዙ ያመርታሉ የበረዶው ጊዜ ሲያልፍ ግን ፍሬያቸው ረግፎ ይሞታሉ። በተቃራኒው ዛፎች ለማደግ ብ
🦚የዱባና የቲማቲም ተክሎች በሳምንት እና ቀናት ውስጥ ያድጋሉ፤ ለረጅም ቀናትና ሳምንታት ፍሬያማ ሆነው ብዙ ያመርታሉ የበረዶው ጊዜ ሲያልፍ ግን ፍሬያቸው ረግፎ ይሞታሉ። በተቃራኒው ዛፎች ለማደግ ብዙ ወራትን አመታትን ይወስዳሉ፤ ካደጉ በኋላ ግን የበረዶውንና ከባዱን ጊዜ በኩራት ያልፉታል። አየህ በፍጥነት ወደላይ ሽቅብ ከወጣህ በፍጥነት ቁልቁል ትወርዳለህ! ዛፎቹን እንዲቆዩ ያደረጋቸው በአመታት መሬት ለመሬት የዘረጉት ስር ነው፤ አንተም ለገንዘብና ስኬት ሳትጓጓ ራስህ ላይ በደምብ ስራ! አለበለዚያ ስኬት የመሰለህ ነገር ጊዜያዊ ስለሆነ እንደ ንፋስ ሽው ብሎ ያመልጥሀል። የተባረከ ሰንበት ተመኘንላችሁ🙏 @motivational6

ስኬትን ፍለጋ “ስኬትን ከፈለክ ስኬትን ዓላማህ አድርገህ አትያዝ፡፡ የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል” - David Frost ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ “ቢሳካልኝ ኖሮ ይህንና ያንን አደርግ ነበር” በማለት በገንዘብና በተለያዩ አቅጣጫዎች “ቢሳካላቸው” ሊያደርጉ ስለሚፈልጉት የወደፊት አላማ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንድ ማስታወስ ያለባቸው እውነታ ግን አንድን አላማ ይዘው መስራታቸው ወደ ስኬት እንደሚወስዳቸው ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰዎች ሳይሆኑ ለአንድ አላማ በጽንአት የኖሩ ናቸው፤ ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው፡፡ @motivational6

በሕይወት አለህ የሚባለው ዛሬን አመስጋኝና ደስተኛ ሆነህ መኖር ስትጀምር ነው። መናደድና ማማረር ምርጫህ ከሆነ መብትህ ነው፤ ነገር ግን በሕይወትህ ባማረርክ ቁጥር የሚያማርር ነገር ነው የሚጨመርልህ።
በሕይወት አለህ የሚባለው ዛሬን አመስጋኝና ደስተኛ ሆነህ መኖር ስትጀምር ነው። መናደድና ማማረር ምርጫህ ከሆነ መብትህ ነው፤ ነገር ግን በሕይወትህ ባማረርክ ቁጥር የሚያማርር ነገር ነው የሚጨመርልህ። በማንኛውም የሕይወትህ ዘርፍ የበደሉህ፤ ያስቀየሙህ፤ ያሳዘኑህ፤ የከዱህ፤ ሰዎች ይኖራሉ፤ በተቃራኒው አንተም ይህን ፈፅመህ ሊሆን ይችላል፤ አትሸከመው፤ ሁሉንም በይቅርታ ዝጋውና ሸክምህን አራግፍ። ባለችን አጭሯ ጊዜያችን ግን ትርጉም ያለው ሥራ ሰርተን ደስታ የሚሰጠንን ነገር በማድረግ እንለፍ" 🤍❤️🤍

ምንድነው በአዕምሮህ የሳልከው ፍርሀት ምንድንነው ከልጅነትህ ጀምሮ በአዕምሮ የተሳለለህ ፍርሀት? ለምንድነው የምትፈራው? ውስጥህ ይከብደኛል፤ አልችልም፤ አይሳካም በሚሉ ሀሳቦች ስለተሞላ ነው ትልቁ አቅምህን ሸብሽቦ ሕልምን እንዳታሳካ የሚጎትትህ፤ አሁን በሕይወት ብትኖርም አንድ ቀን ግን መሞትህ አይቀርም፤ የምትፈልገውን አርአያነት ያለው ስራ ሠርተህ ስምህን በመልካም ተግባር አስጠርተህ ትሄዳለህ ወይስ በውሸት ስዕል ፍርሃት ተሸብሽበህ ሕልምህን ሳታሳካ ተራ ሞት ትሞታለህ? ምርጫው የአንተ ነው! ስለዚህ እራስህን መርምርና የፍርሀትን ጥግ ፍፃሜ አበጅለት።                                       መልካም ቀን👍

የሰዎችን መልካም የሆነን ነገር ተመልከት አድናቆትና አስተያየትን በመጨመር (impression of increase) ከሰዎች ላይ መልካም ነገሮች ፈልግ፤ እንደዚህ አይነት ሰው ከሆንክ በውስጣዊ ሃሳብህ
የሰዎችን መልካም የሆነን ነገር ተመልከት አድናቆትና አስተያየትን በመጨመር (impression of increase) ከሰዎች ላይ መልካም ነገሮች ፈልግ፤ እንደዚህ አይነት ሰው ከሆንክ በውስጣዊ ሃሳብህ ብቻ አትገደብም፤ አይንህም፤ ልብህም መልካም ነገር ብቻ የሚያዩ ይሆናሉ። ይህን ደግሞ ሆን ብለህ መለማመድ አለብህ፤ በሰው ላይ መልካም ነገር መፈለግን፤ በሰው ላይ ጤናማ ጠባያት መመልከትን፤ የሰውን መልካም ጎኖች ማድነቅን፤ የሰዎችን ድንቅ ተግባራት ማበረታታትን፤ ሆነ ብለህ ተለማመድ ከዚህ በተቃራኒ የሰውን ጉድለት ብቻ እየፈለፈልክ የምታይ ከሆነ ለአንተም የሚመለስልህ ይህን ይሆናል። የበጎ እሳቤ ባለቤት ከሆንክ ደግሞ በመልሱ የምታገኘውም በጎነትበረከትን ነው። @motivational6 መልካም ተመኘን

መጀመሪያ አሁን ባለህ ደስተኛ ሁን እኔ የምፈልገውን መኪና፤ ቤት ስገዛ ወይም ሕልሜን ሳሳካ እደሰታለሁ ብለህ እራስህን አትሸውድ፤ መኪና የገዛ ሕልሙን ያሳካ ሁሉ ደስተኛ አይደለም፤ ዋናው ነገር ደስተኝነት ሕልም ሲሳካ ወይም የምትፈልገውን ስታገኝ ሳይሆን፤ መጀመሪያ ምንም ሳይኖርህ ባለህ ነገር ለመደሰት ስትወስን ነው። በራሥህ የውስጥ ሠላም የምትደሰት ከሆነ፤ የውጭው ረብሻና ጫጫታ ምንም አይመስልህም አሁን ባለህ ስትደሰት ሌላው ቀስስስስስ እያለ ይመጣል የደስታ ቀንን ተመኘን

የታየህ ስለሚቻል ነው ሕልምህን ለማሳካትና ሕይወትህን ለመቀየር ሳልደርስበት እንዴት እወስናለሁ አትበል መጀመሪያ ወስንና ትደርስበታለህ ከአቅምህ በላይ የሆነ ነገር አይታይህም፤ የታየህ ስለምትችልና ስለምታደርገው ነው። እኔ ይህንን እገዛለሁ ይሄን አደርጋለው ብለህ ስትል ታይቶሃል ማለት ነው፤ ከአቅምህ በላይ አይታይህም፤ እኔ ይሄንን ካላደረኩ እኔ አይደለሁም ብለህ እርግጠኛ ሆነህ ለራስህ ስትነግረው ግን የስኬትህ ትልቁ ውሳኔ እሱ ነው። 😁 ውብ ቀን ተመኘን!

ሰዎችን በመክሰስ ጊዜህን አታጥፋ በሕይወትህ በሚያጋጥምህ ችግር የምትቃጠለው ጣትህን ወደ ራስህ ከማመልከት ይልቅ ወደ ሌላ ስለምትጠቁም ነው፤ የውስጥ ሰላም ከሌለህ እራስህን መፈተሽ አለብህ፤ የውጭው
ሰዎችን በመክሰስ ጊዜህን አታጥፋ በሕይወትህ በሚያጋጥምህ ችግር የምትቃጠለው ጣትህን ወደ ራስህ ከማመልከት ይልቅ ወደ ሌላ ስለምትጠቁም ነው፤ የውስጥ ሰላም ከሌለህ እራስህን መፈተሽ አለብህ፤ የውጭው አለም ሲቆጣጠርህ እንትና እንዲህ ቢያደርግ ኖሮ እያልክ ሰዎችን ታማክራለህ ፤ እሱ ቢሰራ ኖሮ ትላለህ እንዲህ ቢሆን ትላለህ፤ ለሌላ ሰው ምክር ለመስጠት ትነሳለህ፤ እጅህን ወደ ሌላው በመጠቆም በማያገባህ ገብተህ ስትከሥ ትውላለህ፤ አብዛኛው የሚረብሽህ ነገር በሙሉ የራስህ የውስጥ ሠላም መጠበቅ ባለመቻልህ ስለ ሰዎች በማሰብ የውጭው አለም እንዲቆጣጠርህ ስለምትፈቅድ ነው። አሁን ዋናው ቁም ነገር የራስህን የውስጥ ሰላም በመፈትሽ ከራስህ ጋር ታርቀሀል ወይ? @motivational6

መልካም አዲስ አመት!🌼💛 አዲስ ባልነው አመት በተግባር አዲስነትን ፣ በስራ ስኬታማነትን ፣ በኑሮ ደስታን ደስታን ..፣ በህይወት ሰላምን እንላበሳለን።
መልካም አዲስ አመት!🌼💛 አዲስ ባልነው አመት በተግባር አዲስነትን ፣ በስራ ስኬታማነትን ፣ በኑሮ ደስታን ደስታን ..፣ በህይወት ሰላምን እንላበሳለን።

መልካም አዲስ አመት!🌼💛 አዲስ ባልነው አመት በተግባር አዲስነትን ፣ በስራ ስኬታማነትን ፣ በኑሮ ደስታን ደስታን ..፣ በህይወት ሰላምን እንላበሳለን።

😁🥰😁🥰😁🥰😁🤣 ደስተኛ ሁን "ሆን ብለህ ፈልገህ እንጂ ደስታ በአጋጣሚ አይመጣም፤ ደስታ በቁስ አይለካም፤ ምንም ነገር ባይኖርህ እንኳን፤ በጠዋት በሕይወት በመነሳትህ ፈጣሪህን አመስግንና ደስተኛ ሁን" መልካም ቀን ተመኘን!

ተረጋግተህ ማሰብ ስትጀምር ተአምር መመልከት ትጀምራለህ "ማሰብ ታላቅ የአዕምሮ መሳርያ ነው፤ ማሰብ ስትጀምር ማንም አያሽከረክርህም፤ ማሰብ ስትጀምር ማንም አያቃጥልህም፤ ማሰብ ስትጀምር ተአምር መመልከት ትጀምራለህ፤ የራስህን አቅም ለማውጣት ተረጋግተህ በጥልቀት ማሰብ አለብህ፤ ለዚህም አዎንታዊ የማሰብ ሂደት ያለው ሰው፤ በጧት ቀኑን በፀሎት እና በምስጋና ይጀምራል፤ የገጠመውን ችግር ሳይሆን በእጁ ያለውን በረከት እየቆጠረ ያመሰግናል፤ የውጭው አለም የውስጡን ሰላም እንዲረብሸው በጭራሽ አይፈቅድም፤ ወደ ፈጣሪው ሲፀልይ እርዳኝ ሳይሆን በትህትና ምራኝ ይላል"

ከአንተ ውጪ ለአንተ ማንም የለም " የውሳኔ ሰው ስላልሆንክ ነው ህልምህ ያልተመለሰው ፤ አንተ እንኳን ከውጪው አለም ከውስጥህ ጋር ያለው ክርክር ገና አልተፈታም ፤ ስትወስን እና እንደሚቻል ስታምን ሁሉም ይሳካል። ተርሚኔተር ፊልምን ለመስራት ከሺዋዚንገር የቀረበና ተመራጭ ሆኖ ያሚያሳካው ሰው የለም ፤ ያንተንም ህልም ከራስህ ውጪ የሚያሳካው የለም " @motivational6