cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

akotetzemarian(የጴጥሮስ ዶሮ)

ይህ አኮቴት የዘማሪያን ማህበር ነው ። ልዩ የዝማሬ ና የትምህርት እንዲሁም ዝክረ ቅዱሳንን የሚለቀቅበት ቻናል ነው ምህረቱ ለዘላለም ነውና መዝ:136 "ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ"

Show more
Advertising posts
198
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#እንኳን_ለጾመ_ፍልሰታ_በሰላም_አደረሳችሁ ፍልሰታ ማለት ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ከአንድ ቦታወደ ሌላ ቦታ ማዛወር የነበሩበትን ሀገር ለቆ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ መፍለስማለት ነው፡፡ 💐💒 ጾመ ፍልሰታ ሲባልም የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኒ ወደገነት መፍለስን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱንለማመልከት የሚነገር ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚህ ዓለም ኖራበሞት ከተለየች በኋላ እንደ አንድ ልጅዋ ሞታ መነሣቷንና ዕርገቷን ያዩዘንድ ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 16 የጾሙት ጾም ነው፡፡ 💐💒ጾመ ፍልሰታከሰባቱ ዐበይት አጽዋማት አንዱ ሆኖ በቀኖና እንዲጾም ከተወሰነበት ጊዜጀምሮ ምእመናን ይጾሙታል፡፡ 💐💒እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና “እምሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረውመሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ 💐💒ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባልወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረእግዚአብሔር ሆናለች፡፡ 💐💒እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ12 ዓመት፣ መድኃኔዓለምን በማህጸንዋ ጸንሳ ዘተኝ ወር ፤ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ 33 ዓመት ከሦስት ወር፣ ከዮሐንስ ወልደነጐድጓድ ዘንድ 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር ጠቅላላ ድምር 64 ዓመት ሲሆናትጥር 21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ 💐💒ነቢያት አስቀድመው ስለ እመቤታችን እረፍትና ትንሳኤ በምሥጢርተናግረዋል፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር /መዝ 136¸8/ “አቤቱ ወደ ዕረፍትህተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” ብሎአል፡፡ ፈጣሪዬ ሆይ ምእመናንን ወደምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ ሲል ነው፡፡ ይህም እመቤታችን እንደ ልጅዋትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው፡፡ ታቦት ያላትም ማደሪያውስለሆነች ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምትአለፈ 💐💒ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፡፡ የዜማም ጊዜደረሰ የቀረ… ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ ወይኖችም አበቡመዓዛቸውንም ሰጡ፡፡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ” ሲል ስለእመቤታችን በምሳሌ ተናግሮአል፡፡ /መኃ 2¸1ዐ-13/ 💐💒ወዳጁን ውበቱን ተነሺ ነይ እያለ የተጣራው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ተጠሪዋም እመቤታችን ናት፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ማለት በስደትበአይሁድ የዘወትር ጠላትነት በልጅዋ መከራና ስቅላት ስምዖን በቤተመቅደስ እንደተናገረ ልቧ በሀዘን ሠይፍ የተከፈለበት በሀዘን ፍላጻየተወጋበት የመከራ ክረምት /ወቅት/ አልፎ የክርስቶስ ሕማሙ ፣ ሞቱ፣ቤዛነቱ ተፈጽሟል፡፡ 💐💒ትንሣኤው በምድር ላይ ተገልጧል፣ ተሰብኳል ማለትነው፡፡ በምድራችን አበባ ታይቷል ማለት የሐዋርያት ድምፅ በምድር ሁሉደርሷል ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውምእስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ ብሎ ስለ ሐዋርያት የተናገረው በዓለም ያለውንመከራ ስድት ሲገልጽ ነው፡፡ /መዝ 18¸4/ 💐💒የዜማም ጊዜ ደረሰ ያለው የመከራን ጊዜ ነው፡፡ ሸለቆችም በእህልተሸፈኑ በደስታ ይጮሃሉ፣ ይዘምራሉም ተብሏል፡፡ /መዝ 14¸13/ የመከርጊዜ ደረሰ የተባለው መከር የፍሬ ጊዜ በመሆኑ ክርስትና አፍርቷል ማለትነው፡፡ በለሱ ጐመራ ማለት ደግሞ በጐ ምግባረ ፍሬ ሳያፈሩ የነበሩ ሰዎችበጐ ምግባር መሥራት መጀመራቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ 💐💒 በመጨረሻም ወይኖች አብበዋል፣ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል እንደተባለ በመላው ዓለምአብያተ ክርስቲያናት በሃይማኖት ማበብ መዓዛ ምግባራቸውን ማቅረብ ከጀመሩ በኋላ እመቤታችን ዐረፈች፡፡ 💐💒እመቤታችን ጥር 21 ቀን ዕረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያትየእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሣሥተው “ቀድሞልጅዋን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ፡፡ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል፡፡ እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለንብንተዋት እርሷንም እንደ ልጅዋ ተነሣች ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን; 💐💒 ኑ ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት ብለውተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋኒያ የተባለው ጐበዝ አይሁዳዊ ተመርጦ ሄዶ የእመቤታችንን ሥጋ የተሸከሙትን አልጋ ሽንኮር ያዘ፡፡የአልጋውን ሽንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጁን ስለ ቆረጣቸው ከአልጋው ሽንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ ታውፋንያ በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በኅቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደ ቀድሞ አድርጋ ፈውሳዋለች ፡፡ 💐💒የእግዚአብሔር መልአክ የእመቤታችን ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ተድላ ደስታ ወደ አለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቁ፡፡ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ትወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከዕፅ ሕይወት በታች ካለ መቃብርየእመቤታችን የማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ ጌታችንም ዘላለማዊ ወደሆነ መንግሥተ ሰማያት መላእክት እና ሰማዕታት እየሰገዱላት አሳረጓት፡፡ 💐💒ንጉሥ ዳዊት “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህትቆማለች” እንዳለ፡፡ /መዝ 44¸9/ ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ተመልሶ ከሰማይወረደ፡፡ ሐዋርያት ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋም በታላቅ ክብርማረጉን ነገራቸው፡፡ 💐💒 ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ፡፡ የነሐሴም ወር በባተ/በገባ/ ቀን ዮሐንስ እንዲህ አላቸው፡፡ የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት ኑ፤ሁለት ሱባኤ በመጾም እንለምን አለ፡፡ በጾም በጸሎት ሱባኤ ያዙ፤ 💐💒ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ፣ በውዳሴና በጽኑምሕላ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀው መካነ እረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ መዝሙረ ዳዊት: የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌምሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ ተነሥታ ስታርግ ያገኛታል፡፡ 💐💒ትንሣኤዋን ሌሎቹ ሐዋርያት አይተውለ እርሱ የቀረበት መስሎት ተበሳጭቶ “በመጀመሪያ የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ” ብሎ ከማዘኑ የተነሣ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ በቀር ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤዋን እንዳላዩ ነግራው አጽናንታው ሄዶም ለሐዋርያትየሆነውን ሁሉ እንዲነግራቸው አዝዛው ምልክት ይሆነው ዘንድ ሰበኗን/መግነዟን/ ሰጥታው ዐረገች፡፡ 💐💒ሐዋርያው ቶማስም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮቀበርናት ብለው ነገሩት እርሱም “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴትይሆናል?” አላቸው፡፡ 💐💒“አንተ እንጂ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም አታምንምን;” 💐💒 ብለው በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ወደ እመቤታችን መካነመቃብር ይዘውት ሄደው መቃብሩን ቢከፍቱ ሥጋዋን አጡት፡፡ደነገጡም፡፡ ቶማስም “አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችን ተነሥታዐርጋለች” ብሎ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፡፡
Show all...
ሜልኮሎች ዝም በሉ
Show all...
እንደ ሶስቱ ህፃናት ቂርቆስ በረታ በእቶን እሳት ውስጥ ገባ እናቱንም መራት ወደ ገነት የሶስት ዓመት ሕፃን ቂርቆስ ሰማዕት እኛ ልጆቹ ምልጃውን አምነን ጌታን አክብሮ ለሰበሰበን በማሕቶት በጸዳል ያየው በሠረገላ ስጋው ያረገው ቂርቆስ(3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) አንጌቤናዊው በሮም ከተማ በሕፃን አንደበት ድምፅህ ተሰማ መልክና ውበትህ ቂርቆስ ደም ግባትህ በንጉሱ ፊት አንተን ሊያስወድድህ ልጅ እንድትሆነው ንግስናን ሰጥቶ ለጣዖት ስገድ ብሎ ማለደ ቂርቆስ ከፈጣሪዬ ቂርቆስ ከአምላኬ በቀር ቂርቆስ አትስገድ ተብሎ ቂርቆስ ተጽፎ ነበር ቂርቆስ ብለህ ነገርከው ቂርቆስ ለእስክንድርዮስ ቂርቆስ በሕፃን አንደበት ቂርቆስ ወንጌልን ሰበክ ቂርቆስ ቂርቆስ (3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) አትፍሪ አልካት እናትህን ነጎድጓድ ድምጹ ሲያርድ ልቧን ጸለይክ ወደ አምላክ በቅን ልቦና ያበረታት ዘንድ ቀና አልክና ፍሬው ያለ ግንድ እንዴት ይሆናል አንተም አበርታት ልቧም ይጸናል ቂርቆስ የእናትህን ቂርቆስ ጣቶቿን ይዘህ ቂርቆስ እየመራሃት ቂርቆስ ገባህ ወደ እሳት ቂርቆስ ለእናትህም ቂርቆስ አባት ሆነሃት ቂርቆስ እሳቱ ሳይሆን ቂርቆስ ገነትም ታያት ቂርቆስ ቂርቆስ (3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) የራማው መልዓክ ገብርኤል መጣ ከእቶን እሳት አንተን ሊያወጣ ከጸጉርህ ጫፎች ሳይቃጠሉ ገብርኤል ገባ ከነበልባሉ ነጎድጓድ ዲኑ ስለ በረደ ንጉስ አፈረ ልብሱን ቀደደ ቂርቆስ በእምነት ጽናት ቂርቆስ ያንተ ብርታት ቂርቆስ ዛሬም ያበራል ቂርቆስ በእኛ ሕይወት ቂርቆስ በቃልኪዳንህ ቂርቆስ በፍቅርህ ቂርቆስ እንኖራለን ቂርቆስ በአንተ ቤተ መቅደስ ቂርቆስ ቂርቆስ (3) ሕፃን አማልደን እኛን ልጆችህን(2) ብላቴናው የሶስት ዓመቱ ሆነ ሰማዕት ቂርቆስ ከእነ እናቱ በሮም ከተማ ደምህ ሲፈስ አንገትህን ሰጥተህ እንደ ጳውሎስ ደም እና ውሃ ፈሰሰ ወጣ ቃሉን በእምነት ፈጽመህ ጸናህ ቂርቆስ በጥር 15 ቂርቆስ በማለዳው ቂርቆስ ስጋህ አረፈ ቂርቆስ በሰረገላው ቂርቆስ ረሀብ ጥማቱ ቂርቆስ ክፉ ቁራኛ ቂርቆስ እንዳይደርስብን ቂርቆስ ለመንክ ለእኛ ቂርቆስ 👇👇👇👇👇👇 👉@Mezmurahen👈 👉@Mezmurahen👈 👉@Mezmurahen👈 👆👆👆👆👆👆
Show all...
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ✅ ታላቅ የንግስ ጥሪ ለመላው ህዝበ ክርስቲያን 🌹🌹🌹💚💛❤️ እነሆ በደብራችን ጬሚሲ ደብረ ሳህል የአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ አመታዊ ክብረ በአል ደረሰ። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ሐምሌ 7 አመታዊው የንግስ ጥሪ የሰማህ አሰማ ላልሰማ 📣🔔📢🔉🔊 💚💛❤️ ✅ አድራሻ:- ለገጣፎ ከጋሪ ተራ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው ጩሚሲ ቅዱስ ሚካኤል ቅጥር ግቢ ውስጥ በአንድነት ይገኛል ✅ ይህን መልዕክት ለሁሉም አዝምቱ አዛምቱ ሼር ሼር forward አድርጉ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን @akotetzemarian
Show all...
ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ በቀሲስ ሰለሞን @akotetzemarian
Show all...