cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ህብረ ቀለማት ግጥሞች

ህብረ ቀለማት ግጥሞች የተሰኘው ቻናላችን የተለያዩ በመድብል ደረጃ ለንባብ ያልበቁ ፝ የፍቅር ፝ የሀገር ፝ የነገር ፝ እና ሌሎች ሀገርኛ ጣዕመ ዜማ ያላቸውን ግጥሞች እምንለቅበት ሲሆን እናንተ ከየትኛው ጎራ እንደሆናቹ እራሳቹን እምፈትኑበት አንዳንድ ውድድሮች ይኖሩናል። @lanchi_new11 @ethiopiagna @ethiopiagna11 For daily poems @EthPoetrybot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
1 939
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

። የኔ ብዬ ስዬሽ ሙሉ እድሜን ልኖር ካንቺ ጋር ስዳራ ላይሰሙኝ ጆሮዎችሽ ስምሽን ደጋግሜ በልቤ ስጣራ መስማት አትችል ይሆን እያልኩኝ ቀን ተሌት ስፋጠጥ ስፈራ ንግግሬ ታክቶሽ ሰማው ስታወሪ ያላንዳች ምስክር ያላንዳች አባሪ ። አንቺ ስታወሪ ስውር ነው ድምጸትሽ ረቂቅ ነው ቃልሽ አንቺ ስታወሪ አይኖቼ ይሰማሉ የልቤ ምቶቿ አንቺን አምጣ ይላሉ ። ግና ምን ዋጋ አለው ታድያ አንቺን ለማናገር ብሞክር በመላ ሆነሽ ከተገኘሽ ሳናግርሽ የኔ ስታወሪ የሌላ.. ምን ዋጋ አለው እናት? ምን ትርፍ አለው ማየት ጣትሽ ተሽቆጥቁጦ የማውቀው ቀለበት ከጣትሽ አምልጦ ምንስ ትርጉም አለው ልብሽ ላያስበኝ ስሜን ሺ ቢጣራ አይንሽ ቢፈልገኝ ቀን ሌት በጠራራ ምኑ ሊገባኝ ነው ቅኔ ሆኖ ተግባርሽ ስትፈልጊ ብቻ ሁል ጊዜ እማገኝሽ ባል ልሁን ወንድምሽ?? አኒታ
Show all...
4
Show all...
1
Show all...
0
Show all...
2
Show all...
"ከብረው ይቆዩን ከብረው በአመት ወንድ ልጅ ወልደው ሰላሳ ጥጆች አስረው ከብረው ይቆዩን ከብረው" ከሚል ምርቃት ላይ ፣ ጥያቄ ነጎደ መክበር አይችልም ወይ ፣ ሴትን የወለደ ? "የመበልፀግ ዘመን" ... የሚል ጥቅሷን ይዛ ፣ በተነሳች ሀገር አይቻላትም ወይ ከሰላሳ በላይ ፣ እልፍ ጥጃ ማሰር? ።፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ ሁልጊዜ ወንድ ልጅ ፣ እየተከበረ ሁል ጊዜ ሰላሳ ፣ ጥጃ ከታሰረ ድግግሞሽ እንጂ ፣ ይህን ምን ይሉታል አዲስ ዓመት መጣ፣ አዲስ ነገር የታል? መልካም አዲስ ዓመት
Show all...
Hagerigna Tattoo #share 0923880303
Show all...
https://vm.tiktok.com/ZMdbFstN5/ ስለ ሀገራችን በወጣቶች ብቻ የተሰራ የ2ደቂቃ ቪድዮ ነው:: ስለ ስደተኛ ወገኖቼ ይመለከተኛል እምንል ከሆነ ከላይ ያለውን ሊንክ በመጫን ቪድዮውን ላይክ እና ኮሜንት እንስጠው:: ደት ይብቃን!
Show all...
ዛሬ ነገ ነው? "አባዬ ዛሬ ነገ ነው?" አለ አቡሽ አባቱን ከተኛበት እየቀሰቀሰ። አባት እየተበሳጨ "ምንድን ነው የምትለኝ?" አለ። ልጅም "ዛሬ ነገ ነው ወይ?" አባት እንቅልፉ ስላለቀቀው "ሂድና እናትህን ጠየቃት በቃ ልተኛበት" አለና እየተበሳጨ ፊቱን ቨፈነ። ልጅ ወደ እናቱ ሄዶ ያንኑ ጥያቄ ደገመላት " እማዬ ዛሬ ነገ ነው?" እናት ፈገግ አለች "ምን ማለት ነው ደግሞ ዛሬ ነገ ነው? ማለት?" አለች የልጇን የተጋለጠ ደረት እየሸፈነች "ትናንት አስተማሪያችን 'ነገ ትምህርት የለም' ብላን ነበር፣ ዛሬ ነገ ነው?" አላት። እናት "እ እ አዎ ልክ ነህ ዛሬ ነገ ነው" አለች እየሳቀች። ይህ ለሕፃኑ የተሰጠ መልስ ለእኛም ሳያስፈልገን አይቀርም። ብዙዎቻችን የምንኖረው ለነገ ነው። ለነገ እንማራለን፣ ለነገ እንሰራለን፣ ለነገ እንገነባለን። የተፈጠርነው ለዘላለማዊነት ነውና እንደምንኖር አስበን ማቀዳችን ባልከፋ። ነገር ግን ላላየነው ነገ ስናስብ ያየናትን ዛሬ እንዘነጋታለን። ለነገ ደመና የዛሬን ፀሐይ እንገፋታለን። እንዳቀድን እንዳለምን ለመኖር ስንዘጋጅ እንሞታለን። መጽሐፍ" ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ ተመልከቱ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና" "ነገ ለራሱ ያስባልና ለነገ አትጨነቁ!" ይላል። ያዕ 4:15 / ማቴ 6:34 ሰይጣን ከሚጠቀምበት ሰውን ማጥቂያ መሳሪያም አንዱ "ነገ" በሚል ቃል ማዘናጋት ነው። ነገ እማራለሁ፣ ነገ እሔዳለሁ፣ ነገ የታመመ እጠይቃለሁ፣ ነገ ንስሐ እገባለሁ፣ ነገ ወደ እግዚአብሔር እመለሳለሁ፣ ነገ ይሄንን መልካም ነገር እሰራለሁ ነገ ነገ ነገ። ፈርኦን የሚባለው ጨካኝ ንጉስ በመቅሰፍት ጓጉንቸር ተወርሮ ነበር። በመጨረሻም እስራኤልን እለቃለሁ ሲል ሙሴ:- ጓጉንቸሮቹ ከቤትህ እንዲጠፉ መቼ ልጸልይልህ? አለው። ፈርኦንም :- ነገ አለ። እንግዲህ ዛሬን ከጓጉንቸሮች ጋር ማደር ፈልጓል ማለት ነው። ወዳጄ በሕይወትህ ውስጥ ጓጉንቸሮች ምንድን ናቸው? ምን አይነት ክፉ አመል አለብህ፣ ምን ዕረፍት ያሳጣህ፣ ሰላም የነሳህ ነገር አለ? አልላቀቅ ያለህ ሱስ፣ አልተስተካከል ያለህ ድክመት፣ አልድን ያለህ ቁስል ምንድን ነው? እርሱን መቼ ትላቀቀዋለህ? መቼ መዳን ትሻለህ? ነገ ካልከኝ ፈርኦን መሆንህ ነው? "አቤቱ አሁን አድን" ካልክ ደግሞ እንደ ዳዊት ትሰማለህ። ነገ ይህንን ሱስ እተዋለሁ፣ ነገ ይህን ልማድ እላቀቃለሁ፣ ነገ ይህን መልካም ነገር አደርጋለሁ የሚል ቀጠሮ ሠርቶ አያውቅም። ነገ እንላለን እንጂ የሚገርመው በማግስቱም መልሳችን ነገ ነው። "ዱቤ ዛሬ የለም ነገ ነው" እንደሚለው የብልጥ ባለሱቅ ማስታወቂያ ነገ ስንሔድ ነገ እየተባለ የምንፈልገውን ሳንሰራ የማንፈልገውን እየሰራን እንኖራለን። ወዳጄ ነገ የአንተ አይደለችም "የተወደደ ሰዓት አሁን ነው" መኖርህን ሳታውቅ ቀጠሮ አትስጥ። ኃይልህ በአሁን ላይ ብቻ ነው። ማንም ሊሰራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ አሁንን ተጠቀምባት። አሁኑኑ ተነስ ያሰብከውን መልካም ነገር ለመስራት፣ ክፉውን ነገር ለመተው ነገ አደርገዋለሁ አትበል ትናንት ኅሊናህ ሲጠይቅ "ነገ አደርገዋለሁ" ብለህ ነበር፣ ዛሬም "ነገ" አትበል ምክንያቱም ሕፃኑ እንዳለው "ዛሬ ነገ ነው!" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ቪክቶሪያ አውስትራሊ
Show all...
የተበላሹ ንቅሳቶችን እንዲ ለማሳምር 0923880303 ይደውሉ
Show all...