en
Feedback
On Call & Off Pages

On Call & Off Pages

Open in Telegram

Here to share thoughts on the books I read, the shows I binge and all the curious little things I stumble upon in this beautiful mess called life.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
405
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-430 days
Posts Archive
photo content

" Communicating Health Issues with An Impact " Registration Link here https://us02web.zoom.us/webinar/register/WN_oBSGxlpURcK
  " Communicating Health Issues with An Impact "  Registration Link here https://us02web.zoom.us/webinar/register/WN_oBSGxlpURcKlxP_76OFC6w

" Communicating Health Issues with An Impact " Registration Link here https://us02web.zoom.us/webinar/register/WN_oBSGxlpURcK
  " Communicating Health Issues with An Impact "  Registration Link here https://us02web.zoom.us/webinar/register/WN_oBSGxlpURcKlxP_76OFC6w

የቅድመ ወሊድ ክትትል (በተስሊም ሰዒድ- የህክምና ተማሪ, SPHMMC) 🔶 የቅድመ ወሊድ ክትትል ምንድን ነው? የቅድመ ወሊድ ክትትል ማለት አንዲት ነፍሰ ጡር እናት በእርግዝና ወቅት በጤና ተቋም ውስጥ ማግኘት ያለባት የጤና አገልግሎቶች ጥቅል ነው። 🔶 የቅድመ ወሊድ ክትትል ዋና ዋና አላማዎች 🔸 የእናትና እና የጽንሱን ጤና ለመጠበቅ ፣ 🔸 ከእርግዝና ጋር ተያያዥ ያልሆኑ የጤና እክሎች (ለምሳሌ የስኳርና ደም ግፊት በሽታዎች) ካሉ ቀድሞ ለመለየትና በእርግዝናው ላይ ልያሳድሩ የሚችሉትን ተጽኖ ለመቀነስና ለመከላከል ፣ 🔸 በእርግዝና ጊዜ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማንኛውም ተያያዥ የጤና እክሎችን ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ ለመከላከልና፤ ከተከሰቱም በኋላ በጊዜ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማስቻል፣ 🔸 በወሊድ እና በድህረ ወሊድ ወቅት ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ተያያዥ የጤና እክሎች ቀድሞ ለመዘጋጀት፣ 🔸 እናቶች ከወሊድ በኋላ ማድረግ ስለሚኖርባቸው ጥንቃቄዎችና ልጇን እንዴት ጡት ማጥባትና መንከባከብ እንዳለባት ግንዛቤ ለማስጨበጥ   🔶 አንዲት ነፍሰጡር እናት የቅድመ ወሊድ ክትትል መቼና የት ነው መጀመር ያለባት? አንዲት እናት ነፍሰጡር  መሆኗን ካወቀችበት ወይም ከጠረጠረችበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ሶስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ ባቅራቢያዋ በሚገኝ ጤና ጣብያ በመሄድ ክትትል መጀመር ይኖርባታል። 🔶አንዲት ነፍሰጡር እናት ክትትል ከጀመረች በኋላ ወደ ጤና ተቋሙ ስንት ጊዜ መመላለስ ይኖርባታል? የአለም የጤና ድርጅት ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት አንዲት እናት በቅድመ ወሊድ ክትትል ወቅት (በሚሰጣት ቀጠሮ መሰረት) ቢያንስ ለስምንት ጊዜ ወደ ጤና ተቋሙ መመላለስ ይኖርባታል።   🔶 በቅድመ ወሊድ ክትትል ወቅት የሚሰጡ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች ምን ምንድን ናቸው? 🔸እርግዝና መኖሩን በምርመራ ማረጋገጥ 🔸የደም ግፊትና ስኳር ምርመራ 🔸የደም አይነት ልየታ እና የደም ማነስ ምርመራ 🔸የኤችአይቪ ምርመራ 🔸የጉበት በሽታ ምርመራ 🔸የሽንት ምርመራ 🔸የአባላዘር በሽታ ምርመራ 🔸የአልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ የጽንሱን ጤንነት ማረጋገጥ 🔸የመንጋጋ ቆልፍ(TETANUS) ክትባት 🔸ደም ማነስን የሚከላከሉ የአይረን እንክብሎች መስጠት 🔸በእርግዝና ወቅት መወሰድና መደረግ ስለሌለባቸው ነገሮች የምክር አገልግሎት መስጠት(ለምሳሌ፡ አልኮል መጠጣት እና ሲጋራ ማጨስ) 🔸በአመጋገብ ስርዐትና በአካላዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ግንዛቤ መስጠት 🔸አንዳንድ (እንደ ሃይለኛ ራስ ምታት፣ የአይን ብዥ ማለት፣ከማህጸን ደም መፍሰስ፣ ማህጸን አካባቢ የመግፋት ስሜት የመሳሰሉ) የተለዩ ስሜቶች ሲኖሩ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንዳለባቸው ግንዛቤ መስጠት   በተጨማሪም አንዲት ሴት ከእርግዝና በፊት ብቻዋን ወይም ከትዳር አጋሯ ጋር አንድ ጤና ተቋም ሄዳ ስለ እርግዝና አና ከእርግዝና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሁነቶችን ከጤና ባለሙያዎች መረጃ ማግኘት ትችላለች።

photo content

ስለ እንቅርት በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች (በአህላም አህመድ - የህክምና ተማሪ, SPHMMC) በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ እጢዎች የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በማምረት ለሰውነታችን ስርዓት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። ከእነዚህ እጢዎች መካከል፡- ታይሮይድ የሚባለው እጢ አንደኛው ነው። ከእነዚህ እጢዎች የሚመረተው ንጥረ ነገር በሚበዛበት ወይንም በሚያንስበት ጊዜ ሰውነታችን የተለያዩ ምልክቶችን ያሳያል። ለዛሬ በታይሮይድ ንጥረ ነገር መብዛት የሚከሰተውን እንቅርት በመባል የሚታወቀውን የህመም አይነት እንመለከታለን። የታይሮይድ ዕጢ በፊተኛው የአንገት ክፍል የሚገኝ ሲሆን የቢራቢሮ ዓይነት ቅርፅ አለው። ይህ እጢ የተለያዩ ሆርሞኖች (ንጥረ ነገሮችን) የሚያመርት ሲሆን በዋናነት T3 እና T4 የተባሉ ኬሚካሎችን ያመርታል።እነዚህ ኬሚካሎች የሰውነታችን ሥርዓት (ዑደት) የሚቆጣጠሩ ናቸው። እንደ የምግብ መፍጨት ስርዓት፣የልብ ምት የእንቅልፍ ስርዓትን፤ የካርቦ ሐይድሬት (ስኳር) እና የፕሮቲን ምርት እና አጠቃቀምን፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ባህሪያችንን ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል። መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው? የአዮዲን እጥረት በዋነኝነት የሚጠቀስ የእንቅርት መንስኤ ነው ። ሌሎች እንደ ካንሰር፤ የታይሮይድ እጢ መቆጣት ወይም ኢንፌክሽን የሚያመጡ ቢሆንም፤ የመከሰት ዕድላቸው ግን በጣም አናሳ ነው። በተጨማሪም በተፈጥሮ የሚከሰቱ (በአፈጣጠር ችግር ) የሚከሰቱ የእንቅርት (Hyperthyroidism) ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። እንደ እርግዝና እና በአፍላ የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆንም ለህመሙ መምጫ መንስኤ ተብለው ይጠቀሳሉ። እንቅርት ያላቸው ሰዎች ከመጠን ያለፈ የታይሮይድ ሆርሞን በሚያመነጩበት ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ። 🔷 የልብ ምት መጨመር 🔷 ማስቀመጥ 🔷 የሙቀት ስሜት(ብርድ በሆነ ወቅት) 🔷 ከፍተኛ የማላብ ስሜት 🔷 የምግብ ፍላጎት መጨመር 🔷 የክብደት መቀነስ 🔷 የወር አበባ ዑደት መዛባት ከመጠን ያነሰ የታይሮይድ ሆርሞን በሚመነጭበት ጊዜ ደግሞ የሚከተሉት ምልክቶች ይስተዋላሉ። 🔷 የልብ ምት መቀነስ 🔷 የሆድ ድርቀት 🔷 የብርድ ስሜት(ሙቀት በሆነ ወቅት) 🔷 የምግብ ፍላጎት መቀነስ 🔷 የክብደት መጨመር 🔷 የወር አበባ ዑደት መዛባት አጋላጭ ነገሮች ምንድን ናቸው? 🔹 አዮዲን የሌለው ጨው መጠቀም 🔹 ፆታ: ሴቶች ከወንዶች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸዉ ። 🔹 እድሜ: እድሜ እየገፋ ሲሄድ ተጋላጭነት ይጨምራል። 🔹በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ የታይሮይድ ችግር ካለ 🔹 የጨረር ህክምና: አንገት እና ደረት አካባቢ የጨረር ህክምና ከነበረ 🔹 እርግዝና 🔹 ማረጥ የሚደረጉት ምርመራዎች ምንድን ናቸው? ከሚደረጉ ምርመራዎች ውስጥ የ T3 እና T4 መጠንን በደም ውስጥ መለካት እንዲሁም እነዚህን እንዲመረቱ የሚያደርግ ሆርሞንን (TSH) መጠኑን በደም ውስጥ መለካት ዋነኛዎቹ ናቸው። በመቀጠል እንደ አልትራሳውንድ፤ ሲቲ ስካን፤ የመሳሰሉት የምስል ምርመራዎች ደጋፊ ይሆናሉ። የእንቅርት ህመም ህክምናውን እንደ ላብራቶሪ ውጤት እና እንደ በሽተኛው የሚያሳየው ምልክት የሚወሰን ይሆናል። የህክምናው አማራጮች ውስጥ የሚዋጥ መድኃኒት አንስቶ እስከ ቀዶ ጥገና ድረስ የሚሄድ ይሆናል። የእነዚህ የህክምና አማራጮች የሚወሰነው በሐኪምዎ ይሆናል።

photo content

Welcome to AFYET, your source of health related articles on a variety of topics and suggestions on how to get on the road to your ultimate health. No matter your age, our channel offers plenty of information on various health conditions, diseases, their symptoms and methods of treatment in an easy to understand format and language. Our main goal is to provide information that helps to practice a healthy lifestyle with choices people make both at home and healthcare institutions. We hope that our health articles will be able to provide answers to your health conditions and steer you in the right direction of taking charge of your own health. Join us on our journey of creating a medically informed society! t.me/Afyet_Health