cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማዕደ ፡ ጥበብ ፡፡

የተደከመባቸው ፣ የተለፋባቸው ፣ በግርጌ ማስታውሻ የታገዙ ፣ "አንቱታ"ን ካገኙ የቤ/ክ መጽሓፍት ጀምሮ ልዩ ልዩ መጽሓፍትን እንደ ማጣቀሻ በመጠቀም የተቀመሙ መካሪ አስተማሪ ጽሑፎች ዳግመኛም የድምጽ ወምስል ውጤቶች ይቀርባሉ! ይምጡና ይጎብኙን! “ለንባብ ክብርን ስጥ። ራስኽን ለንባብ አስገድድ። ከቻልኽ ፥ ከምትጸልየው አስበልጠኽ አንብብ። የጥሩ ጸሎት ምንጩ ንባብ ነውና" (አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ)

Show more
Advertising posts
1 427
Subscribers
-224 hours
-67 days
-2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

<< መቃብር ጾመኛ ሴትን መሰለ! >>         በጾም ቀን ወጥ የምትሠራ ሴት፥ ቀምሳ ጢቅ ትለዋለች፤ አትውጠውም፡፡ እንደዚኹም ኹሉ፥ ጌታችን ክርስቶስን መቃብር ቀመሰው[ሞቶ ተቀበረ]፡፡        ያቺ ጾመኛ ሴት፥ ቀምሳ ጢቅ ትለዋለች እንጂ እንደማትውጠው ፥ መቃብርም ክርስቶስን ውጦ ያስቀረው ዘንድ አልቻለም፡፡ የክርስቶስ ሥጋ ዐለት ኾነበት፡፡         በዚኽ ዐለት ምክንያት የመቃብር ጥርስ ረገፈ! ይኽን ያየን እኛም 'ሞት ሆይ መውጊያ የት አለ?' እያልን ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር ዘመርን። ለአማኞች 'የሕይወት እንጀራ ነኝ' ያለ ጌታ፥ ለሞት ግን ሕያው ድንጋይ ኾነበት፡፡ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የቆየ የሞት ሥልጣን፥ በሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ድል ተነሣ!         ጾመኛዋ ሴትና መቃብር የተገኙት "አኀዘ ይጥዐሞ ለሞት በፈቃዱ ዘእንበለ ግብር፤ ሞትን በፈቃዱ ቀመሰ" ከሚለው የአፈወርቅ ንባብ ነው።           ሀገራችንም የደምና የጦርነት ጾመኛ  ኾና፥እንደ አገርም 'እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሓ ወሰላም' ለማለት ያብቃን፡፡ © ሊቀ ሊቃውንት ሥሙር አላምረው
Show all...
<< መቃብር ጾመኛ ሴትን መሰለ! >> በጾም ቀን ወጥ የምትሠራ ሴት፥ ቀምሳ ጢቅ ትለዋለች፤ አትውጠውም፡፡ እንደዚኹም ኹሉ፥ ጌታችን ክርስቶስን መቃብር ቀመሰው[ሞቶ ተቀበረ]፡፡ ያቺ ጾመኛ ሴት፥ ቀምሳ ጢቅ ትለዋለች እንጂ እንደማትውጠው ፥ መቃብርም ክርስቶስን ውጦ ያስቀረው ዘንድ አልቻለም፡፡ የክርስቶስ ሥጋ ዐለት ኾነበት፡፡ በዚኽ ዐለት ምክንያት የመቃብር ጥርስ ረገፈ! ይኽን ያየን እኛም 'ሞት ሆይ መውጊያ የት አለ?' እያልን ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር ዘመርን። ለአማኞች 'የሕይወት እንጀራ ነኝ' ያለ ጌታ፥ ለሞት ግን ሕያው ድንጋይ ኾነበት፡፡ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የቆየ የሞት ሥልጣን፥ በሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ድል ተነሣ! ጾመኛዋ ሴትና መቃብር የተገኙት "አኀዘ ይጥዐሞ ለሞት በፈቃዱ ዘእንበለ ግብር፤ ሞትን በፈቃዱ ቀመሰ" ከሚለው የአፈወርቅ ንባብ ነው። ሀገራችንም የደምና የጦርነት ጾመኛ ኾና፥እንደ አገርም 'እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሓ ወሰላም' ለማለት ያብቃን፡፡ © ሊቀ ሊቃውንት ሥሙር አላምረው
Show all...
<<ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን >>           "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን"፦ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ፥ የትንሣኤ ባለ ቤት ነውና አንድም 'ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ' ብሏልና አንድም በአዳም የቀደመ ኃጢአት ምክንያት ይዛ ታስቀር ወይም ታበሰብስ የነበረችውን መቃብር እርሱ ገብቶ ለወጣትና የትንሣኤ ቦታ አድርጓታልና ፤ 'ሞቶ መቅረት በእርሱ ሞት ተሽሮ ትንሣኤ በእርሱ ታወጀ' ለማለት በክርስቶስ ትንሣኤ በኩል ለኹላችንም ትንሣኤ የተሰጠን መኾኑን ነገረን።         "በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን" አለ፦ ሞት የተሻረችው ትንሣኤ የተሰጠችው ሥልጣኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በኾነለት በሥግው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ ነውና፤ አንድም በአምላክነት ክብሩና ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መበስበስን አስቀርቶ ተነሥቷልና።         "አሠሮ ለሰይጣን"፦ ሰይጣንን አሠረው አለ፥ ሰይጣን ግዙፍ ኾኖ በገመድ የሚታሠር ኾኖ ሳይኾን የቀደመ ኃይሉን አድክሞበት ተነሣ አንድም ፥ የሠይጣን የቀደመ ሥልጣኑ ተወሰደበት (ጻድቃንን እንኳ ሳይቀር ወደ ሲኦል ያስገባ ነበርና) አንድም በአዳም ላይ ገዢ ኾኖ "አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ" የሚል ደብዳቤ አጽፎ አዳምና ሔዋንን ባሪያው አድርጎ የሚገዛበት ኃይሉ ተወስዶበታልና። አንድም 'ሰይጣን ታሠረ!' አለ እንደ ቀደመው በሙሉ ነጻነትና ሥልጣን እንዳያስት በቅዱስ መስቀሉ ተቀጥቅጦ ደክሞልና አንድም ምእመናን የመስቀሉን ምልክት ቢያሳዩት በርሮ ይጠፋልና።         "አግአዞ ለአዳም"፦ አዳምን ነጻ አወጣው አለ ለምን ቢሉ በዲያብሎስ ባርነት ነበርና ከዚያ መውጣቱን ሲያይ አንድም የሞት ተገዢ ኾኖ ነበርና ከዚያ መውጣቱን ሲያይ አንድም ከባሕርይ መጎስቆል ከጸጋ መገፈፍ ከርግማን ኹሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነጻ አውጥቶታልና አንድም ከሲኦል ወጥቶ ወደ ቀደመ ስፍራው ወደ ገነት ተመልሷልና።        "ሰላም፣ እም ይእዜሰ፣ ኮነ፣ ፍስሐ ወሰላም"፦ ከእንግዲህ ወዲህ ሰላም ፍጹም ደስታና ሰላም ኾነ፦ ይኸውም በክርስቶስ የተገኘች አዲስ ሕይወት ናት። እርሱ "የሰላም አለቃ" ተብሏልና በእርሱ የሚያምኑ ከእርሱ የምትገኘውን የእውነት ሰላም ደስታ ይወስዷታልና። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰዎች ዘንድ የጠፋችውን ደስታና ሰላም መልሶ ሰጥቷቸዋልና አንድም በእያንዳንዱ አማኝ ሰውነት ውስጥ የክርስቶስ ሰላምና ደስታ ከእንግዲህ ትገለጣለችና። አንድም ጥላቻ ርቃ የክርስቶስ ፍቅር በክርስቲያኖች ዘንድ ትታያለችና አንድም ራሱ ክርስቶስ ራሱን ሰላምና ደስታ አድርጎ ለክርስቲያኖች ሰጥቷልና 'በእርሱ የሚኖሩ ይኾናሉ' ሲል አንድም ቅ.ዮሐንስ አፈ ወርቅ ኢየሱስ ክርስቶስን 'ኹሉን የሚጠቀልል ፍቅር' ይለዋልና ፥ ያን ሲያስታውስ፥ ይህ እንዴት ነው ቢሉ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስፈልገንን መልካም ነገር ኹሉ መኾኑን የሚገልጥ ነው። እውነተኛ ብርሃን፣ እውነተኛ ሕይወት፣ እውነተኛ ምግብና መጠጥ፣ እውነተኛ ሰላምና ደስታ፣ እውነተኛ ዕረፍትና እርካታ እርሱ ነውና። © ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው እንኳን አደረሰኝ አደረሳችኹ!
Show all...
<< ሕማማተ መስቀል ዘእግዚእነ >>            "ወኀለፈ እግዚእ ኢየሱስ ፲ተ ወ፫ተ አናቅጸ ሕማማት" እንዲሉ ሐዋርያት በሲኖዶስ ፥ ጌታችን የተቀበላቸው ሕማማት ፲፫ ናቸው። " 'የለም ፲፰ ናቸው' የሚል አብነት ይገኛልሳ? ይኽ እንድምንድን ነው?" ቢሉ ፣ ፭ቱን ቅንዋት ለየብቻቸው ቆጥረው ወሪቀ ምራቅን (ምራቅ መተፋትን) ይጨምራሉን ስለዚኽ ነው። ያም ኾነ ይኽ ፣ እሊኽ ሕማማተ መስቀል ማን ማን ናቸው?" ቢሉ ከዚኽ ይናገሯቸዋል፦ ፪ . ተስህቦ በሐብል በማእከለ ዓምድ - በሐብል ታስሮ በዓምድ መኻከል መጎተት ፫. ወዲቅ ውስተ ምድር - በምድር ላይ መውደቅ ፬. ተከይደ በእግረ አይሁድ - በአይሁድ እግር መረገጥ ፭ .ተጸፍዖ መልታሕት - በጥፊ መመታት ፮. ተቀስፎ ዘባን - ጀርባውን መመታት ፰. አክሊለ ሦክ - የሾኽ አክሊል በራሱ ላይ መደፋቱ ፱. ተዐርቆተ ልብስ - ከልብስ መራቆት ፲ .ፀዊረ መስቀል - መስቀል መሸከም ፲፩. ተቀንዎ ቅንዎት - እጆቹን እግሮቹን መቸንከሩ ፲፪. ተሰቅሎ በዕፅ - በመስቀል መሰቀል ፲፫. ሰሪበ ሐሞት - ሐሞት መጠጣት ናቸው።      "ፅርፈተ - አይሁድ" ፣ "ወሪቀ ምራቅ" ና "ርግዘተ - ገቦ" ከንዑሳኑ ገብተው ይቆጠራሉ እንጂ ከዐቢያኑ ገብተው አይቆጠሩም። "ስለምን አይቆጠሩም?" ቢሉ ፣ ፅርፈተ - አይሁድን ቢያነሱ አይሁድ ጌታችንን "ዕሩቅ ብእሲ ወልደ ዮሴፍ - የዮሴፍ ልጅ አምላክ ያይደለ እንደኛ ሰው ነው" ብለው ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስቅዱስ ለይተውታልና ይኽ ስድባቸው ነው። ሰውን ቢሰድቡት ይቆጣል ይናደዳል እንጂ ስድብ ሕማም ኾኖ አይገድለውና ስለዚኽ አይቆጠርም።         "ወሪቀ ምራቅ - ምራቅ መተፋት" የተባለውን ቢያነሱ ፣ ሰውን ቢሰድቡት ይጸየፋል እንጂ ምራቅ ሕማም ኾኖ አይገድለውምና ስለዚኽ ነው። (ምንም እንኳን ቀደም ስንል እንደተመለከትነው ፣ ሠለስቱ ምእት ከ፲፫ቱ ሕማማት ቢቆጥሩትም)። "ርግዘተ - ገቦ - ጎኑን መወጋት" የተባለውን ቢያነሱ ፣ ጌታችን ጎኑን የተወጋው ነፍሱ ከሥጋው ከተለየች በኋላ ነው። ሰውን ከሞተ በኋላ ቢወጉት ከባሕር ከገደል ቢጥሉት በእሳት ቢያቃጥሉት አይሰማውምና "ርግዘተ - ገቦ" ስለዚኽ ምኽንያት አይቆጠረም። ይቆየን! ዲያቆን ዳዊት ሰሎሞን። ------------ ምንጭ፦  ፩. ወንጌል ትርጓሜ ፪. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል አንድምታ (አሳታሚ ፦ ኃ/ሚካኤል ብርሃነ መስቀል ፣ የካቲት 19/2010 ዓ.ም.) ፫. ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘሰሙነ ሕመማት ከሕመማት መስቀሉ ታሪክ ጋር (መጋቢት 2008 ዓ.ም)
Show all...
<< ይሁዳ - የድል አጥቢያ አርበኛ! >> አንዳንድ መናፍቃን  “ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ባይሰጠው ድኅነትን ባልተፈጸመም ነበር” በማለት ይሁዳን ለድኅነታችን አስተዋጽዖ እንዳደረገ እንደ አንድ ጻድቅ ሰው ሊቈጥሩት ይዳዳቸዋል። እንደነርሱ አባባል አይሁድ ክርስቶስን ባይስቅሉት ድኅነታችን ባልተፈጸመም ነበር።¹ እንዲኽ ከኾነ ዘንድ አይሁድ በመስቀላቸው ይሁዳም አሳልፎ መስጠቱ እሰይ! ደግ አደረጉ! ነገር ግን ነገሩ እንዲኽ አይደለምና  ይሁዳም አይሁድም ደግ አላደረጉም! በሥራቸው ጠፍተውበታል። ይሁዳን እንደ ደኅነት ምክንያተ ድኅነት ለሚያዩት መናፍቃን ግን አንድ እንበላቸው። ኹለት ነጥቦች ብቻ፦ አንደኛው ፥ የይሁዳ ሚና የድል አጥቢያ አርበኛ ሚና ነበር። የድል አጥቢያ አርበኛ ጦርነቱ 'ኦልሞስት' ካለቀ ነገርዬው 'ኦልሞስት' ከደቀቀ በኋላ መጥቶ ትንሽ ወዲያ ወዲኽ እያለ ያሽላላና ድሉ በስማቸው ከተጻፈላቸው አርበኞች ተርታ ሊመደብ ይዳዳዋል። ለድሉ ሳይኾን ድሉን ለማክበር የሚገኝ በሉት! ለውጊያው ሳይኾን ለሽብሸባውና ለጭብጨባው ዋዜማ የሚገኝ ማለት ነው። የይሁዳም ሚና እንዲኹ ነበር።  ስለዚኽ በገዛ ፈቃዶ ኼዶ ‘ማኖ’ ነክቶ ቀይ ካርዱ ተረፈው እንጂ ጎሉስ መግባቱ አልቀረም። ደግሞ እኮን በደሉን ንስሓ በተባለ ‘VAR' መሻር እየቻለ.. ‘ጥፊ ያላት ከተማ...’ አይሁድ ጌታችንን ለመግደል ወስነው ጨርሰው ሸንጎው ከተበተነ ከሰዓታት በኋላ ነበር ይሁዳ የተከሰተው። የእርሱ ሚና ከኾነም የሚኾነው የእቅዳቸውን አፈጻጸም ያለ ሁካታ ማስፈጸም ነበር።²  ኹለተኛ ፥ ይሁዳ እንደ አይሁድ ከ ሀ - ፐ ሙሉ ሚና ቢኖረው እንኳን ኲነኔውን ቢጨምርበት እንጂ የጌታችን መሰቀል ለእኛ ድኅነት ኾኗልና ጻድቅ አያሰኘውም። ጌታችን በወንጌል "መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም ፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት”³ ሲል እንደተናገረ ፥ ጌታችን ሲጀመር እንደ ሰው ልጆች ለመኖር ያይደለ ለመሞት የተወለደ ነው። መሰቀሉም የማይቀር ነው። ይሁዳም ኾነ አይሁድ ባይኖሩ መሰቀሉ አይቀርም! ምክንያት ለሚኾኑት ፥ ለሚያሰቅለው ለሚያሰቅሉት ግን ወዮ ለእርሱ ወዮ ለአነርሱ!   ነገሥታት ባይኖሩ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዙ ያሸበረቁ ሰማእታት ባልኖሩም ነበር። ይኽ ከኾነ ፥ “ዓላውያን ነገሥታቱ ሰማእታትን አፍርተዋልና አብዝተዋልና በሥራቸው ይሹመበት ይሸለሙበት!” ያሰኛልን? አያሰኝም! “ምነው?” ቢሉ ፥ እነርሱስ ሥራቸው ጽድቅ ሊኾን ቀርቶ የክፉ ክፉ ነው። ነገር ግን መከራን በአኰቴት ለተቀበለው የክብር ክብር ይኾንለታልና ፥ ስለዚኽ ነው እንጂ ሥራቸውስ የከፋ ነበር። እኛ የሰማእታትን ዜና ብቻ ስለምንሰማ ነው እንጂ እኮን ፥ መከራውን ተሰቅቆ የካደም አይጠፋም። ቅዱሳኑ ትሕትናን ገንዘብ ያደርጉ ዘንድ መሰደብን መሰደድን መዋረድን መገፋትን ይሻሉ። እንዲኽ የሚያደርጋቸው ከጠፋ እንኳን  ገንዘብ እየከፈሉ ምግብ እየመገቡ እንዲሰድቧቸው ያደርጉ የነበሩ ቅዱሳንም ነበሩ። “ስድቡ ውርደቱ ለትሕትና ከኾናቸውማ ሰዳቢዎቹ አዋራጆቹ የጽድቅ ምክንያት ኾነዋልና በእውነት ደግ አደረጉ። እግዚአብሔር በሰማይ በጎ ዋጋቸውን ይክፈላቸው” ይባላልን? አይባልም! ለምን? ምክንያቱም ፥ ነገሩን ጽድቅ ያደረገው ቅዱሳኑ ስድቡን “ይገባኛል! አንድም ፥ ለትሕትና ይኾነኛል ፣ ወደ ጽድቅ ይመራኛል ፣ መንግሥቱን ያወርሰኛል” ብለው በአኰቴት ስለተቀበሉት ነው እንጂ እነርሱ ስለሰደቧቸው ብቻስ አይደለም። ተሰድበው መልሰው ቢሳደቡ የጥፋት ምክንያት ይኾንባቸዋልና። ጌታችንን የሰውን ክፋት ፣ ተንኮል ወደ በጎ መቀየር ልማዱ ስለኾነ ነው የሰዉ ስድብ ለእነርሱ ጽድቅ ኾነላቸው እንጂ ሳዳቢዎቹስ ይኰነኑበታል።  በአንድ ወቅት አረጋዊ መንፈሳዊን ያልተገባ ቃል ይናገረው ስለነበረው አንድ ሰው ‘እኔ ያንተን ስድብ መታገሴ ዋጋ ይኾንልኛል። ይኽ ማለት ግን አንተ በመሳደብኽ ደግ አደረግኽ ማለት አይደለም’ እንዳለው። መናፍቃን ባይበዙ ሊቃውንቱም ባልበዙ ነበር። ብዙ ጥያቄወቻችንም ባልተመለሱልን ነበር። ብርሃን የኾኑ ሥርዐት ባልተደነገጉልንም ነበር። አርዮስ ባይ‘ነሣ ሠለስቱ ምእትን ባለወቅናቸው ፣ ሕንጻ መነኰሳትን ባልተረከብን ፣ በሃይማኖተ - አበው የደነገጉትን ፣ ሌሎችን ድንጋጌያት ኹሉ ባለገኘንም ነበር። ነገሩ እንዲኽ ከኾነ ፥ “አርዮስ በጎ አደረገ እንጂ ምን አደረገ? በሥራው ይጽደቅበት እንጂ ይኮነንበት?” ማለት ይገባልን? አይገባም! ለምን? ምንፍቅናውስ በጎ አልነበረም ፥ እግዚአብሔር ግን ከአናብስት አፍ እንኳን ማር ማውጣት ያውቅበታልና ፣ ከመረረ ነገር የጣፈጠ ነገር ማውጣት ያውቅበታልና ፣ ነገርን ኹሉ ወደ በጎ መለወጥ ያውቅበታልና ፥ ስለአርዮስ መነሣት ምክንያት ሊቃውንትን ያስነሣልን እግዚአብሔር ይመሰገንበታል ይደነቅበታል እንጂ አርዮስን “እሰይ! ደግ አደረገ” ለማለት የሚደፍር እርሱ ማን ነው? የይሁዳም ጉዳይ እንዲኹ ነው! በፈቃዱ ማኖ ነክቶ ከምክንያተ ስቅለቱ ቢካተትም ስቅለቱ ምንም ድኅነት ቢኾነንም በሥራው ግን የሲኦል ፈር ቀዳጅ በር ከፋች ኾኖበታል።  ብቻ ያሳዝናል - ማርያም ኃጥእት በ300 ዲናር ሽቶ ኃጢአቷን ስታረግፍ ይሁዳ በ30 ብር ገዝቶት ኼደ! አንዱ ባለቅኔ ነው ያለው። እኔ አይደለኹም። የአይሁድም ጉዳይ እንዲኹ ነው! ይቆየን! ዲያቆን ዳዊት ሰሎሞን። ------- ¹ ዲያቆን ሄኖክ ኀይሌ። ሕማማት። ገ.32 ² ዝኒ ከማሁ። ገ.33-34 ³ ሉቃ.፲፯ ፥ ፩
Show all...
<< ሕማማተ መስቀል ዘእግዚእነ >> "ወኀለፈ እግዚእ ኢየሱስ ፲ተ ወ፫ተ አናቅጸ ሕማማት" እንዲሉ ሐዋርያት በሲኖዶስ ፥ ጌታችን የተቀበላቸው ሕማማት ፲፫ ናቸው። " 'የለም ፲፰ ናቸው' የሚል አብነት ይገኛልሳ? ይኽ እንድምንድን ነው?" ቢሉ ፣ ፭ቱን ቅንዋት ለየብቻቸው ቆጥረው ወሪቀ ምራቅን (ምራቅ መተፋትን) ይጨምራሉን ስለዚኽ ነው። ያም ኾነ ይኽ ፣ እሊኽ ሕማማተ መስቀል ማን ማን ናቸው?" ቢሉ ከዚኽ ይናገሯቸዋል፦ ፪ . ተስህቦ በሐብል በማእከለ ዓምድ - በሐብል ታስሮ በዓምድ መኻከል መጎተት ፫. ወዲቅ ውስተ ምድር - በምድር ላይ መውደቅ ፬. ተከይደ በእግረ አይሁድ - በአይሁድ እግር መረገጥ ፭ .ተጸፍዖ መልታሕት - በጥፊ መመታት ፮. ተቀስፎ ዘባን - ጀርባውን መመታት ፰. አክሊለ ሦክ - የሾኽ አክሊል በራሱ ላይ መደፋቱ ፱. ተዐርቆተ ልብስ - ከልብስ መራቆት ፲ .ፀዊረ መስቀል - መስቀል መሸከም ፲፩. ተቀንዎ ቅንዎት - እጆቹን እግሮቹን መቸንከሩ ፲፪. ተሰቅሎ በዕፅ - በመስቀል መሰቀል ፲፫. ሰሪበ ሐሞት - ሐሞት መጠጣት ናቸው።      "ፅርፈተ - አይሁድ" ፣ "ወሪቀ ምራቅ" ና "ርግዘተ - ገቦ" ከንዑሳኑ ገብተው ይቆጠራሉ እንጂ ከዐቢያኑ ገብተው አይቆጠሩም። "ስለምን አይቆጠሩም?" ቢሉ ፣ ፅርፈተ - አይሁድን ቢያነሱ አይሁድ ጌታችንን "ዕሩቅ ብእሲ ወልደ ዮሴፍ - የዮሴፍ ልጅ አምላክ ያይደለ እንደኛ ሰው ነው" ብለው ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስቅዱስ ለይተውታልና ይኽ ስድባቸው ነው። ሰውን ቢሰድቡት ይቆጣል ይናደዳል እንጂ ስድብ ሕማም ኾኖ አይገድለውና ስለዚኽ አይቆጠርም። "ወሪቀ ምራቅ - ምራቅ መተፋት" የተባለውን ቢያነሱ ፣ ሰውን ቢሰድቡት ይጸየፋል እንጂ ምራቅ ሕማም ኾኖ አይገድለውምና ስለዚኽ ነው። (ምንም እንኳን ቀደም ስንል እንደተመለከትነው ፣ ሠለስቱ ምእት ከ፲፫ቱ ሕማማት ቢቆጥሩትም)። "ርግዘተ - ገቦ - ጎኑን መወጋት" የተባለውን ቢያነሱ ፣ ጌታችን ጎኑን የተወጋው ነፍሱ ከሥጋው ከተለየች በኋላ ነው። ሰውን ከሞተ በኋላ ቢወጉት ከባሕር ከገደል ቢጥሉት በእሳት ቢያቃጥሉት አይሰማውምና "ርግዘተ - ገቦ" ስለዚኽ ምኽንያት አይቆጠረም። ይቆየን! ዲያቆን ዳዊት ሰሎሞን። ምንጭ፦  ፩. ወንጌል ትርጓሜ ፪. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል አንድምታ (አሳታሚ ፦ ኃ/ሚካኤል ብርሃነ መስቀል ፣ የካቲት 19/2010 ዓ.ም.) ፫. ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘሰሙነ ሕመማት ከሕመማት መስቀሉ ታሪክ ጋር (መጋቢት 2008 ዓ.ም)
Show all...
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ኾነ ወደ ዐማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ እነሆ የተወሰኑትን እንመልከት፦ ~ ኪሬዬ ኤላይሶን ~ ቃሉ የግሪክ ሲኾን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነው፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ" ማለት ሲኾን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ" ማለት ነው፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጒሙ "አቤቱ ማረን" ማለት ነው፡፡ "ኪርያላይሶን" የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ~ ናይናን ~ የቅብጥ ቃል ሲኾን ትርጉሙ "መሐረነ፣ ማረን" ማለት ነው፡፡ ~ እብኖዲ ~ የቅብጥ ቃል ሲኾን ትርጒሙ "አምላክ" ማለት ነው፡፡ "እብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው። ~ ታኦስ~ የግሪክ ቃል ሲኾን ትርጒሙ "ጌታ፣ አምላክ" ማለት ነው፡፡ "ታኦስ ናይናን" ማለትም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነው፡፡ ~ ማስያስ ~ ~ ትስቡጣ ~ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲኾን ትርጉሙም "ደግ ገዥ" ማለት ነው። ~ አምነስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ ~ የቅብጥ ቃል ሲኾን ትርጒሙም "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ - አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ" ማለት ነው፡፡ የቅብጥ ቃል ሲኾን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡ ~ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ ~ የቅብጥ ቃል ሲኾን ትርጒሙም "ተዘከረነ እግዚአ ኲሉ በውስተ መንግሥትከ - የኹሉ የበላይ የኾንኽ ሆይ በመንግሥትኽ አስበን" ማለት ነው፡፡ Source: @Amon_0721
Show all...
3👍 1
<< ያለ ፈጣሪ አንተ አህያ ነኽ! >> አንድ ጊዜ እንዲህ ኾነ፦ አንድ አህያ በደስታና በኩራት ወደ እናቱ ይመጣል፡፡ እናቱም ምን አግኝቶ እንደኾነ ትጠይቀዋለች፡፡ እርሱም እንዲኽ ሲል ይመልሳል፦ " እናቴ! ክርስቶስ የሚባል አንድ ሰው በላዬ ላይ ተቀምጦ ወደ መቅደስ ስገባ ፣ ሰው ኹሉ ተሰብስቦ በታላቅ ድምጽ " ' በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው! ጌታን በዙፋኑ አመሰግኑት! ሆሳዕና በአርያም! ሆሳዕና በአርያም! ' እያሉ እያመሰገኑ ከፊቴ ልብሶቻቸውን የሚያነጥፉ ነበሩ፡፡ የዘንባባ ዝንጣፊም የሚያነጥፉ ነበሩ፡" እናቱም ፥ "እስኪ ወደ ከተማው ብቻኽን ጎራ ብለኽ ና" ስትል ትመልስለታለች፡፡ እርሱም ተስማማና በማግስቱ ወደ ከተማው ብቻውን ደርሶ መጣ፡፡ በዚኽ ጊዜ ግን ሲመለስ በብስጭት ነበር፡፡ እንዲኽ ሲልም እናቱ ፊት ያጉረመርም ነበር ፦ "እናቴ! እንዲኽማ አይኾንም! ማንም ሰው ትኩረት አልሰጠኝም፡፡ ባሰተዋሉኝ ጊዜም እየመቱ ከከተማ አስወጡኝ" እናቱም ስታዳምጠው ከቆየች በኋላ እንዲህ ስትል መለሰችለት፦ " ልጄ! ያለ ክርስቶስ አንተ እንዲኹ አህያ ነኽ!"       Source: Orthodox parables and short stories (Posted on may 16, 2019) ከሆሳዕና በዓል ጋር እንዲስማማ ተደርጎ የተተረጎመ ትርጒም፦ ዲ/ን ዳዊት ሰሎሞን
Show all...
Show all...
MK TV || ዐውደ ስብከት || መፃጕዕ እና ኒቆዲሞስ || ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

<< ላለው ይጨመርለታል >> ከጸጋው ሰዎች በሚችሉት መጠን ይቀበላሉ። በጸጋው በመጽናት ደስ ብሎት የሚኖር ክርስቲያን ሌላ ተመሳሳይ ጸጋን እንደሚቀበል ቃል ተገብቶለታል ። የተሰጠውን ጸጋ ለሚጠቀምበት ክርስቲያን “ላለው ይጨመርለታል”ተባለለት። ዛሬ ማንኛውንም ነገር ለመቀበል የበቃን ከኾንን ይጨመርልናል። የበቃን ካልኾንን ግን አይጨመርልንም።     የጽድቁ ብርሃን በእርሱ ይነቀፋልና በአመለካከቱ ሰነፍ ለኾነ ሰው ጥበብን የሚገልጥ መንፈስ ቅዱስ አያድርበትም። ምሥጢርን የሚገልጥ መንፈስ ቅዱስ ብሩሃነ አእምሮ ለኾኑት ይሰጣል እንጂ። ስለዚኽ ፥ ጥበብ በእርሱ አብባ ትሰፋለች:: ደስ የሚያስኘውን ቃሉን በመስበክ በዙሪያው ያሉ ኹሉ በሐሴት ይሞላሉ። እኛ ተበዳሪዎች ነን። ከዕዳችን ነጻ የወጣን እንሁን።       እኛ ምን እንደተቀበልን የምናውቅ ከኾነ ከተቀበልነው ላይ ተጨምሮ ይሰጠናል። ነገር ግን በእርሱ የማይገባ ሥራን ከሠራንበት ያለ ጥርጥር ከእርሱ አንዳችም ነገር የምንቀበለው እንደሌለ እንወቅ። እኛ ከሠራንበት ሀብት ይኾነን ዘንድ የተቀበልነው ጸጋ ከእኛ ዘንድ ይቀራል። ሀብት ኾኖ የተሰጠንን አምነንና ስጦታውን በምስጋና ከተቀበልን እንዲሁ ሀብቱ በእኛ ጸንቶ ይቆያል።... ምንጭ፦ መምህር ሽመልስ መርጊያ (ተርጓሚ)። ኅብረ ወንጌል - ዲያቴሳሮን ትርጓሜ (በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)። የመጀመሪያ ኅትም። ፳፻፲፫ ዓ.ም. ገ.118 @Tibebsenayit Comment @Dndawitsol
Show all...