cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ewunet Media(እውነት)

🇪🇹እንኳን ወደ እውነት ሚድያ በሰላም መጣችሁ🇪🇹 በውስጥ መስመር ከፈለጉን @Ewuneta_bot YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtube.com/channel/UCjiq4hREIdyVsnPPKfSOkcg

Show more
Advertising posts
16 514
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
‼️በአዲስ አበባ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ተባለ፡፡ ✅የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ 👉የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳዊት የሺጥላ እንዳሉት በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የአዉቶብስም፣ የታክሲም የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡ 👉የማሻሻያ ዋጋዉም የታክሲ ትንሹ የ 50 ሳንቲም ጭማሪ ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ የ2 ብር ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን ቢሮው አስታውቋል፡፡ 👉በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ከተደረገ ወዲህ በተለይም ታክሲዎች በራሳቸዉ ታሪፍ እየጨመሩ ከተሳፋሪዎች ጋር አላስፈላጊ እስጠገባ ዉስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡ ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
‼️ወለጋ ከሞት የተረፉት ጭንቅ ✅ መንግስት የደርድሩን ስራ ጀመረው ✅ በኮንደሚኒየሙ ተያዙ የተባሉት ስራ ላይ ናቸው ✅ግብጽን ያስደነገጠው =================== 06/11/2014 እሮብ (16:24 min) 7.5 MB ===================== መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
ወለጋ_ከሞት_የተረፉት_ጭንቅ_መንግስት_የደርድሩን_ስራ_ጀመረው_በኮንደሚኒየሙ_ተያዙ_የተባሉት_ስራ_ላይ.mp37.51 MB
‼️ኮሚሽነር #ምትኩ #ካሳ በሙስና ተጠርጥረው ተያዙ  ✅የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ። 👉ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት። 👉በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቲቪ እንዳሉት ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት "ኤልሻዳይ" ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው። 👉ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ እና በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት። 👉ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።(EBC) ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
‼️ህወሓት፤ ትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት የተፈረመው ስምምነት “አልገባኝም” ብሏል ✅የኢትዮጵያ መንግስት በህሓት ኃይሎች እና በፌደራል መንግስት መካከል በተፈጠረ ግጭት የወደመውን መሰረተ ልማት መልሶ ለመገንባት ከተባበሩት መንግስታት ጋር የሶስተኛ ወገን ትግበራ ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል። 👉በኢትዮጵያ በኩል መንግስትን በመወከል ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ሲሆኑ በተመድ የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ (ዩኤንኦፒኤስ) በኩል ደግሞ ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮንን ናቸው፡፡ 👉መንግስት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይደርስ አስተጓጉሏል ሲል ህወሓትን ከሰሰ 👉የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ብሄራዊ የማገገሚያ መርሃ ግብሩ" የመሰረተ ልማት መልሶ የመገንባት፣ የአስፈላጊ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለማሻሻል እና የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ለመርዳት ያለመ ነው ብሏል፡፡ 👉"በትግራይ ያሉ ሁኔታዎች እስኪሻሻሉ እና መንግስት ፕሮጀክቱን በራሱ መዋቅር ለማስፈጸም እስኪችል ድረስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ ፕሮጀክቱን በትግራይ ተግባራዊ ያደርጋል" ሲልም መግለጫው አክሏል። 👉ከመንግስት ጋር ስምምነቱን የተፈራረመው የተመድ የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ (ዩኤንኦፒኤስ)፤ ጦርነት በተጎዳው የሰሜኑ ክፍል እና ባብዛኛው በህወሐት ስር በሚገኘው የትግራይ ክልል የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ እንደሚገነባ መግለጹም ሚኒስተሩ አስታውቋል፡፡ 👉ከጾታዊ ጥቃት የተረፉ ሰዎችን የሚረዳበት ሌላው የፕሮግራሙ ክፍል በሌላ አካል የሚተገበር ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ ድርድር እየተካሄደ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። 👉መንግስት በጦርነት የወደመው የትግራይ ክልልን መሰረተ ልማት መልሶ ለመገንባት ይህን ይበል እንጂ፤ ጉዳዩ በህወሐት በኩል ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም፡፡ 👉የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ፤ “ይህ ነገር ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት እንደሚሰራ አልገባኝም” ብለዋል፡፡ 👉“መልስ ለማግኘት እየጮህኩ ነው!” ሲሉም ስምምነቱ ያልጠበቁትና የማይቀበሉት በሚመስል መልኩ ገልጸውታል፡፡ 👉እንደረፈረንጆቹ በህዳር 2020 በመንግስት እና በህወሓት መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ብዙ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋሮች ቀደም ሲል ሲሰጡት የነበረን እርዳታ ቀንሰው እንደነበረ ይታወቃል። 👉የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች እርዳታ ጭነው ትግራይ መግባታቸውን ህወሓት አስታወቀ 👉መንግስት በሚያዝያ ወር የእርዳታ ወደ ትግራይ የመላክ ሂደት እንደገና በመፍቀድ እርዳታ የጫኑ መኪናዎች ወደ ክልሉ እንዲመለሱ መፍቀዱም ተከትሎ ወደ ትግራይ ሚገባው እርዳታ በእጅጉ የተሻሻለ መምጣ ይታወቃል። 👉ትግራይ አሁንም እንደ መብራት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና ባንክ ያሉ አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሌሉበት እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙበት ክልል እንደሆነ የተመድ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ 👉ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባው የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት እና በአሰቃቂ ድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 715 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እና ብድር ለመስጠት ባለፈው ወር መስማማቱ አይዘነጋም። ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
‼️ ነገ መብራት ይጠፋል ✅የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት 👉ረቡዕ ሀምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል በጆሞ 2 ኮንደሚኒየም፣ በየስ ውሃ፣ በአለም ገና ማርስ ብስኩት እና አካባቢዎቻቸው ኤሌክትሪክ ይቋረጣል፡፡ 👉በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️በደሴ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ ሐምሌ 5፣ 2014 (ማክሰኞ) ✅ በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ 👉በደሴ ከተማ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር አለባቸው መለሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ዛሬ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ሳላይሽ በግ ተራ አካባቢ የቆራሌ ዕቃ በሚራገፍበት ሰዓት ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ፈንድቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ 👉በፍንዳታው በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሠራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን÷ ተጎጂዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ 👉እስከ አሁን የሞተ ሰው እንደሌለ ጣቢያችን ያረጋገጠ ሲሆን፥ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ፖሊስ መረጃ እሰጣለሁ ብሏል፡፡ በከድር መሀመድ ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
‼️የአማራ ልዩ ሃይል በሸኔ ከጀርባ ተመቷል ✅ ኮንደሚኒየሙ ጉድ አመጣ ✅ ህወሃት በኤርትራና ሶማሊያ ዘመቻ ✅ከፍቷል በጎንደር የቅማንት ታጣቂ =================== 05/11/2014 ማክሰኞ (17:00 min) 7.8 MB ===================== መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
የአማራ_ልዩ_ሃይል_በሸኔ_ከጀርባ_ተመቷል_ኮንደሚኒየሙ_ጉድ_አመጣ_ህወሃት_በኤርትራና_ሶማሊያ_ዘመቻ_ከፍቷል.mp37.79 MB
‼️ላልቆጠቡ ሰዎች የቤት እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች በመገኘቱ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን አስተዳደሩ አስታወቀ (ኢ.ፕ.ድ) ✅ሀምሌ 01 ቀን 2014 የወጣው የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ላይ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች በመገኘቱ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን አስተዳደሩ አስታወቀ። 👉በዚህ ዙሪያ አስተዳደሩ ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል። 👉የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል ብሏል አስተዳደሩ በመግለጫው። 👉ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን ሲልም ገልጿል፡፡ 👉አስተዳድሩ.ማምሻውን ያወጣው መረጃ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፤ 👉ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ይመለከታል:: 👉በከተማችን አዲስ አበባ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል አንዱ የቤት አቅርቦት እጥረት ሲሆን ይህንኑ ደረጃ በደረጃ ለማቃለል አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ 👉የዚህ ሂደት አካል የሆነው የነባሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ወስብስብ ችግር ለይቶ በመፍታት ተመዝጋቢዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ እና የቤት እጥረት ጫና ለመቀነስ የተደረገው ሰፊ ጥረት ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ ሂደት በግንባታ ላይ የነበሩ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል 25,491 ያህሉ በቅርቡ ለባለ እድለኞች የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት መካሄዱ ይታወቃል፡፡ 👉ይህ የቤት ማሰስተላለፍ ስራ እንደ ከዚህ በፊቱ በቆጣቢወች መካከል አድሎና ብልሹ አሰራር እንዳይኖር ለማድረግ ግልፅነት በሚያሰፍን አግባብ ለማስተላለፍ ሲባል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ በመስራት ሂደቱን ግልጽና አሳታፊ ለማድረግ የተደረገው ተነሳሽነትና ጥረት እንዲሁም የባልሙያዎችን ሙያዊ ነፃነት አክብረን አስፈላጊውን ሂደት ተከትለን ተዓማኒነቱን እንዲያረጋግጡልን አድርገን ነበር:: በዚህ ሂደት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ አዲስ ሶፍትዌር እንዲበለፅግ እና ስለሶፍትዌሩ ታአማኒነት የኢኖቬንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር እንዲያረጋግጥልንም ተደርጓል:: 👉በቀጣይም ከሁለት ጊዜ በላይ ታዛቢወች እና ባለሙያወች ፊት ቀርቦ እንዲያረጋግጡልን ተደርጎ ማረጋገጫ ሰጥተዋል:: ይህ ሁሉ ሂደት ከእለት ጉርሱ የቆጠበዉን እና በከፍተኛ ጉጉት የሚጠባበቀውን ሕዝብ በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ቀና ሃሳብ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል:: 👉ይሁን እንጂ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል:: ‼️በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ 👉ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል:: 👉ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡ 👉ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 4/2014 ዓ/ም ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
‼️የተከበራችሁ የእውነት ሚዲያ ቤተሰቦች ✅የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች በዛሬ ዕለት ይፋ መደረጉ ይታወቃል። 👉በዚሁ መሰረት የዕጣ ዕድለኞችን ስም ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃዎችን በዚህ የቴሌግራም ይቀርባል። ‼️የቴሌግራም ቻናላችንን ሰብስክራይብ አድርገው ይከታተሉ።
Show all...
‼️ ደብረጺዮን እንቢ ያሉት የኢሳያስ ምክር ✅ክልሉ ለሁለት ሊከፈል ነው ✅ኢትዮጵያ ወደቧን አስመለሰች ✅ ህወሃት በአማራ ተወካዮች ላይ ዘመቻ ከፈተ =================== 02/11/2014 ቅዳሜ (15:14 min) 7.0 MB ===================== መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
ደብረጺዮን_እንቢ_ያሉት_የኢሳያስ_ምክር_ክልሉ_ለሁለት_ሊከፈል_ነውኢትዮጵያ_ወደቧን_አስመለሰች_ህወሃት.mp36.98 MB
‼️ኢሰመኮ፤ ኢትዮጵያ አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ቀውስ ውስጥ መሆኗን አስታወቀ ✅የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኢትዮጵያ አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ አስታወቀ። ኮሚሽኑ ይህን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። 👉ኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርቱን ዛሬ አርብ ሐምሌ 1፤ 2014 ይፋ ያደረገው መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። በዚሁ መግለጫ ላይ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ሀገሪቷ ያለችው ምንም የማይካድ አሳሳቢ የሆነ ሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ ስለሆነ፤ በርካታ አሳሳቢ ጉዳዮች በየዘርፉ አሉ” ሲሉ የሀገሪቱን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ግምገማ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።  👉በኮሚሽኑ የሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች ኮሚሽነሩ ዶ/ር አብዲ ጂብሪል፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን አሳሳቢ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል አንዱ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ “መንግስታዊ ባልሆኑ ተዋናዮች” የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየጨመሩ መምጣታቸውንም ጠቁመዋል።  👉የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት “በዋናነት መንግስታዊ ካልሆኑት ከታጣቂ ቡድኖች መምጣታቸው” ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር አስቸጋሪ እንዳደረገው ዶ/ር አብዲ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በዛሬው መግለጫ ላይ ይፋ በተደረገው የኢሰመኮ ሪፖርትም ይኸው እውነታ ተደጋግሞ ተስተጋብቷል።  👉ለሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቅድሚያ የሰጠው ሪፖርቱ፤ በህይወት የመኖር መብትን በዳሰሰበት ክፍል “ባለፉት 12 ወራት በህይወት የመኖር መብት እጅግ የከፋ አደጋ ውስጥ እንደወደቀ ቀጥሏል” ሲል አትቷል። ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም በኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ሶማሌ ክልሎች የተፈጸሙ የሲቪል ሰዎች ግድያን በማሳያነት ጠቅሷል። 👉ኢሰመኮ በአማራ እና በአፋር ክልል ለተፈጸሙ ግድያዎች በሁሉም ወገኖች ያሉ የጦርነቱን ተሳታፊዎች ተጠያቂ ሲያደርግ፤ በኦሮሚያ ክልል ለተፈጸሙት ግድያዎች ደግሞ “ኦነግ ሸኔ” የተባለው ቡድንን ወንጅሏል። በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከጭካኔ፣ ኢ-ሰብዓዊ እና አዋራጅ አያያዝ ቅጣት ነጻ የመሆን መብቶች መጣሳቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።  👉መብታቸው የተጣሰባቸው አብዛኛዎቹ ሲቪል ሰዎች መሆናቸውን እና በጦርነቱ ተሳትፈው የተማረኩ ተዋጊዎችም ለዚህ መብት ጥሰት መጋለጣቸውን አስታውቋል። ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቆየችባቸው ከጥር እስከ የካቲት ባሉት ሶስት ወራት ገደማ “መጠነ ሰፊ የዘፈቀደ እስር፣ ብሔርን መሰረት ያደረገ አድሏዊ አሰራር፣ እስራት እና ያለ አግባብ ከስራ እና ከደመወዘ መታገድ ተፈጽሟል” ብሏል። 👉የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትግራይ ክልልም ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት መሆኑን ኢሰመኮ አስታውቋል። ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ደንብ በማውጣት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ መሆኑን ያስታወቀው ኮሚሽኑ፤ ህወሓት ያወጣው አዋጅ “የሰዎችን መብቶች በከፍተኛ ሁኔታ የገደበ እና ከኢትዮጵያ ህገ መንግስት እና የወንጀል ህግ ጋር የሚጣረስ ነው” ሲል ነቅፎታል። 👉አዋጁ ከፌደራል መንግስት ጋር የሚደረግ የስራ ግንኙነት በወንጀል የሚያስጠይቅ እና ወላጆች በግዳጅ ልጆቻቸው የህወሓትን ሰራዊት እንዲቀላቀሉ የሚያስገድ መሆኑን ኢሰመኮ ገልጿል። በአስር ዘርፎች ተከፋፍሎ የቀረበው ዓመታዊ ሪፖርቱ፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በነበሩ ግጭቶች የሴቶች እና ህጻናት መብቶች መጣሳቸውንም አመልክቷል።   👉በግጭቶቹ “በርካታ ሴቶች እና ህጻናት ላይ መጠነ ሰፊና ስልታዊ በሆነ መንገድ በተናጠል እና በቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች መፈጸማቸውን” ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። ጥቃቶቹ “ሰብዓዊ ክብርን ለማዋረድ ሆነ ተብሎ ታቅዶ በግልጽ የበቀል ስሜት የተፈጸሙ” መሆናቸውን የገለጸው የኮሚሽኑ ሪፖርት፤ ጥቃቶቹ በጦርነት አውድ ውስጥ በመፈጸማቸው የጦር ወንጀል ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል።  👉በመቶ ገጾች የተዘጋጀው ዓመታዊው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም ዳስሷል። ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ካለፈው ዓመት ሐምሌ እስከ ግንቦት 2014 ባሉት ጊዜያት፤ 54 የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከቀናት እስከ በርካታ ወራት በእስር ላይ መቆየታቸው በሪፖርቱ ተገልጿል። ከእነዚህ መገናኛ ብዙሃን መካከል 15ቱ በትግራይ ባለስልጣናት በክልሉ የተያዙ መሆናቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል። 👉በትግራይ ክልል የታሰሩ የመገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በክልሉ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ኮሚሽኑ መረጃ ስላገኘበት መንገድ፤ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ጥያቄው የቀረበላቸው የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ መቀሌ የሚገኘው የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ ላይ እንደነበር ገልጸዋል።  👉ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም “ከተወሰኑ ወራቶች በፊት የትግራይ ባለስልጣናት መቀሌ ላይ ያለውን ጽህፈት ቤታችንን ዘግተውብናል። ያ ቢሮ ስለተዘጋ ከዚህ በፊት የነበረንን አይነት ክትትል ለማድረግ እንቅፋት ፈጥሮብናል” ብለዋል። ይሁን እንጂ ኮሚሽኑ አሁንም የርቀት ክትትል በማድረግ መረጃዎችን እንደሚያገኝ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️የአርብ የሚድያ ዳሰሳ ✅ አጭበርባሪዎች የግለሰቦች ስልክ ላይ በመደወል እና ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ሽልማት ደርሷችኋል፣ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታችሁን አስተካክሉ እና ሌሎች መሰል መልእክቶችን በማስተላለፍ ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማዎች ደርሰውኛል ሲል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በሳምንቱ መጀመሪያ አስታውቋል። ግለሰቦች እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች በሚደርሳቸው ወቅት አቅራቢያቸው በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከማረጋገጣቸው በፊት ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመጠንቀቅ እራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ አገልግሎቱ አሳስቧል። ✅ ቻይና በማህበራዊ ሚዲያ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች በተወሰኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለመናገር የብቃት ማረጋግጫ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ደንብ አውጥታለች። የቻይና ብሔራዊ የሬዲዮና ቴሌቪዥን አስተዳደር ረዕቡ እለት ይፋ ያደረገው አዲስ ደንብ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የቀጥታ ስርጭት የሚያቀርቡ ተጽኖ ፈጣሪዎችን የሚመለከት ሲሆን ስለ ህግ፣ ጤና፣ ትምህርትና ፋይናንስ ትንታኔ፣ ማብራሪያና ሃተታ ለማቅረብ በዘርፉ የብቃት ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ያስገድዳል። ✅ ዩትዩብ ቻናሎች የደንበኞቻቸውን ብዛት (subscribers number) እንዳይታይ የሚያደርጉበትን አሰራር በሐምሌ ወር መጨረሻ ከአገልግሎት እንደሚያስወጣ አስታውቋል። ዩትዩብ ይህን እርምጃ የሚወስደው ከታዋቂ ቻናሎች ጋር ተመሳስለው የሚከፈቱ ቻናሎችን ተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲለዩ ለማስቻል መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም የታዋቂ ቻናሎችን ስም አስመስሎ ለመክፈት ተግባር ላይ በሚውሉ ልዩ ሆህያት (special characters) አጠቃቀም ላይ ገደብ መጣሉን ዩቱዩብ አስታውቋል። በቪዲዮች ስር የሚሰጡ አስተያየቶችም ከመጋራታቸው በፊት በቻናሉ አስተናባሪዎች ግምገማ የሚደረግበትን ስርዐት መዘርጋቱንም አስነብቧል። ✅ እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም በዩናይትድ ኪንግደም በተፈጸሙ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ የማጭበርበር ድርጊቶች 1.3 ቢሊዮን ፓውንድ በአታላዮች እጅ መግባቱን ዩኬ ፋይናንስ (UK Finance) የተባለ ተቋም ያወጣው ሪፖርት አስነብቧል። ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ በአታላዮች እጅ የገባው በዓመቱ በተፈጸሙ 195,996 ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ የማጭበርበር ድርጊቶች መሆኑ ተገልጿል። ይህም ቀደም ካለው ዓመት ጋር ሲወዳደር የ27 ፐርሰንት ብልጫ አለው። ✅ ትዊተር ኩባንያ አካውንቶችን እንድዘጋ እንዲሁም ትዊት የተደረጉ ይዘቶችን እንድሰርዝ እያስገደደኝ ነው ሲል የህንድን መንግስት በፍርድ ቤት መክሰሱን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ትዊተር ክስ የመሰረተው የሀገሪቱን ህግ ተላልፈዋል የተባሉ አካውንቶችና ይዘቶች ላይ እርምጃ እንዲወስድ በህንድ መንግስት ከታዘዘ በኋላ ነው። የህንድ መንግስት ከዓመት በፊት ትዊተር የራሱን መመሪያዎች ሳይሆን የሀገሪቱን ህግ መሰረት አድርጎ እንዲሰራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ ✅ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ጥሪ አቀረቡ። 👉ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ 1443ኛውን የኢድ አል አደሀ/አረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 👉ህዝበ ሙስሊሙ ነገ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን ታላቁን የኢድ አል አደሀ /የአረፋ በዓል በሰላም ወጥቶ አክብሮ በሰላም እንዲመለስ ጠይቀዋል፡፡ 👉ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ሰላም የሁሉም መሰረት በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 👉ታላቁ የኢድ አል አደሀ /አረፋ በዓል በፍቅር፣ በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡ 👉አገር፣ ቤተሰብ፣ ልማትና እድገት የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሰላም ከፍ ያለ ዋጋ በመስጠት በሰዎች መካከል የትብብርና ወንድማማችነት መንፈስ ማስፈን ይገባል ብለዋል፡፡ 👉ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁን የአረፋ በዓል ሲያከብር አቅመ ደጋሞችን በመጠየቅ፣ የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡ 👉ሀይማኖት የሚኖረው ሀገር ሲኖር መሆኑን በመረዳት በዓሉን ስናከብር በመተዛዘን፣ በመረዳዳትና አንድነትን በማጠናከር መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ 👉የሀይማኖት አባቶቹ 1443ኛው የኢድ አል አደሀ/አረፋ በዓል የሰላም የደስታ የብልጽግናና የመከባበር ይሆን ዘንድ የትብብር መንፈስ መጎልበት አለበት ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ ማሳሰቢያ ✅ሰሞኑን የተለቀቀው ቪዲዮ ላይ የተገለፀው የሐዋሳ ዩንቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ተማሪም ተመራቂም አለመሆኑን እናሳውቃለን። ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️ የአቶ ደመቀ መኮንን ተማጽኖ ✅ ህወሃቶች ድንገት ተለያይተዋል ✅ የጠቅላዩ ንግግር ያስነሳው አቧራ ✅ ተመስገን ያልተፈታበት ምክንያት ‼️ አሁን ላይ ሽንዞ አቤ ህይወታቸው አልፏል =================== 01/11/2014 እሮብ (16:28 min) 7.5 MB ===================== መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
የአቶ_ደመቀ_መኮንን_ተማጽኖ_ህወሃቶች_ድንገት_ተለያይተዋል_የጠቅላዩ_ንግግር_ያስነሳው_አቧራ_ተመስገን.mp37.55 MB
‼️ለእስልምና እምነት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️የ2015 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር ኾኖ አጸደቀ። ✅ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2015 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር አጸደቀ። ➡️ 345 ቢሊየን ብር ለፌደራል መንግስት ወጭ የተመደበ በጀት ሲኾን 44 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል ፡፡ ➡️ ለካፒታል ወጭ 218 ቢሌን ብር የተመደበ ሲኾን ይህም 28 በመቶ ኾኖ ጸድቋል፡፡ 👉በበጀት አመቱ ከፍተኛውን ድረሻ የያዙት ለመደበኛ ወጭና ለካፒታል የተመደበው መኾኑም ታወቋል፡፡ 👉ከአጠቃለይ የፈደራል መንግስት መደበኛና ካፒታል በጀት ውስጥ 37 ነጥብ 6 በመቶ በ10 አመት ፍኖተ ብልጽግና እቅድ መሰረት ትኩረት ለተሰጣቸው ድህነት ተኮር ፕሮግራሞች ትኩረት ለተሰጣቸው ለትምህርት፤ ለጤና መሻሻሎች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡ 👉የ2015 በጀት ከተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ጠቅላላ በጀት ጋር ሲነጻጸር የ16 ነጥብ 59 እድገት እንዳለው ታወቋል፡፡ 👉የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና የመልሶ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የተሰራ ነው ተብሏል፡፡ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ስብሰባ እየተካሄደ ነው ✅የምክር ቤት አበላት ጥያቄ እያቀረቡ ነው፤ የቀረቡ ጥያቄዎች ዋና ዋናዎቹ  👉የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ከትምህርት ምዘና ይልቅ ፖለቲካዊ ቅርጽ እየያዘ አገራዊ አደጋ እየሆነ መጥቷል፤ ፈተናውን ኦንላይን ለመስጠት ምን ታስቧል፤ 👉 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአገር አልፎ ለአፍሪካ ኩራት የሆነ የተመሰከረለት ሰራዊት ነው፤ ለዓለም ሰላም ዋጋ ከፍሏል፤ ነገር ግን ዓለም ይሄንን ውለታ ክዷል፤ 👉 ምዕራባዊያን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጎን ቆመዋል፤ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ገብተዋል፤ ይህ ለምን ይሆናል፤ 👉 የሱዳን መንግስት ዜጎቻችንን ከሚጨፈጭፉ ቡድኖች ጋር ይተባበራል፤ ትግስትም ልክ አለውና መንግስት የሱዳንን ወረራና ትንኮስ እንዴት እያየው ነው፤ በሲቃ ውስጥ ላሉ ለታፈኑ የትግራይ ዜጎች መንግስት ምን እገዛ እያደረገ ነው፤ ምን ሊያደርግላቸው ይችላል፤ 👉 ለውጡን ያልፈለጉ አካላት ለለውጡ ትልቅ ፈተና ቢሆኑም ህዝቡ እንቢ በማለት ዳግም አድዋን ፈጽሟል፤ የመንግስት የቅድሚያ ቅድሚ ስራው የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ነው፤ ለ50 አመት የተዘራው የሀሰት ትርክትና የጥላቻ ፖለቲካ ፍሬ አፍርቶ በዜጎች ላይ በአሸባሪው ሸኔ እና ህወሓት እየተገደሉ ነው። 👉በለውጡ ስም የገቡ ከላይ እስከታች ያሉ ቀን ቀን መሪ ማታ ማታ አሸባሪ የሆኑ ሰዎች አሉ፤ እነዚህ ሽብርተኞች በፈጸሙት ወንጀል ልክ ምን እርምጃ ተወሰደ፤ ለወደፊቱስ ጭፍጨፋው እንዳይፈጸም ምን ታስቧል፤ 👉 በሶማሌ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርክ የለምና ምን ታስቧል፤ 👉 በውጭ አገራት ያሉ ዜጎቻችን መብት እንዲከበር፤ በመላው ዓለም ያላቸው ተፈላጊነት እንዲጨምር ለማድረግ ምን ታስቧል፤ 👉 በቅርቡ በአገሪቷ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን ለመከላከል የአገሪቷ የደህንነት ተቋም ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ ምን እየሰራ እንደሆነ ማብራሪያ ቢሰጥ፤ 👉 በአገራችን ለአርሶ እና አርብቶ አደሮች ምርጥ ዘር፣ ማደበሪያና የውሃ ፓምፕ እጥረተ አጋጥሟልና ችግሩን ለመፍታት ምን ታስቧል፤ 👉 አሁንም ድረስ ትህነግ በአገራችን በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ ያለው ስጋት፤ በአሸባሪው ሸኔም ዜጎቻችን እየተጨፈጨፉ ነው፤ መንግስት ሁሉም ሸኔን ተደመሰሰ ይላል፤ ጥቃቱ ግን ቀጥሏል፤ ይሄ ዛሬ የተፈጠረ ሳይሆን ለበርካታ አመታት የተዘራ መሆኑን እንረዳለን፤ የመንግስት ቀዳሚ ስራ ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ ነው፤ ይህ ግን አልሆነም፤ መንግስት የዚህን ዘር ተኮር ጥቃት ማስቆም ያልቻለው ለምንድን ነው፤ የወገኖቻችን ሲቃና መከራ የሚቆመው መቼ ነው፤ 👉 የክልል መንግስታት በክልላቸው የሚኖሩ ዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ካልቻሉ ለምን አይጠየቁም፤ 👉 ከአዋሽ ወደ አፋር ያለው መንገድ ደህንነትን ለማስጠበቅ ምን እየተሰራ ነው፤ 👉 በዜጎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ ይከለከላል፤ በወጡ ዜጎች ላይም ጥቃት ተፈጽሟል ለምን፤ 👉 ባለፉት አራት አመታት በዜጎች ላይ በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት ብሄራዊ ስጋት አይደለም ወይ፤ በዚህ ድርጊት የተሳተፉት ላይ ለምን እርምጃ አልተወሰደም፤ 👉 ከትህነግ ጋር ለመወያየት ሰው መመደቡን ሰምተናል፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቡድኑን ሽብርተኝነት ስያሜ ባላነሳበት ሁኔታ መደራደር ወንጀል አይደለም ወይ፤ 👉 በምክር ቤት ሽብርተኝነት የተሰየመን ቡድን ኢ መደበኛ ብለው ይጠሩታል፤ ዘር ፍጅት ወንጀሉንም ግጭት ብለው ይጠሩታልና ለዚህ ወቀሳ ያለዎት መልስ ምንድን ነው፤ 👉 ሚዲያ አራተኛ መንግስት እንደሆነ ይታመናል፤ ነገር ግን ከአዎንታዊው ይልቅ አሉታዊው እየበዛ መጥቷል፤ የህዝብን አንድነትና አብሮነት የሚሸረሽሩ ሚዲያዎች አሉ፤ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ምን መደረግ አለበት ይላሉ ፤ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ማቅረብ ቀጥለዋል። ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን። ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️ምክር ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዛሬ ይወያያል። ✅ሰኔ 30/2014 ዓ.ም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሚያካሂደው 16ኛ መደበኛ ጉባዔ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጋር ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ይወያያል። 👉ምክር ቤቱ በዚህ መደበኛ ጉባዔው፤ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ላለው የዜጎች የፀጥታ እና ደኅንነት ጉዳይ ዐቢይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ይጠበቃል። 👉በሌሎች ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ-ሀብታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ውይይት ያካሂዳል። 👉ምክር ቤቱ በተጨማሪም በአዲሱ የ2015 የበጀት ድልድል ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል። 👉በተያያዘ ዜናም የፌዴራል መንግሥት አጠቃላይ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትም ይቀርባል። በዚሁ ሪፖርት ላይም ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጋር ይወያያል። ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️ከጭፍጨፋ የተረፉ እና የአጎራባች አካባቢ ነዋሪዎች ሰቆቃና ስጋት 👉ከሰሞኑ ጭፍጨፋ ከተፈፀመባቸው የምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ አካባቢዎች ከጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች አሁንም ስጋት እንዳላቸው ገለጹ። 👉ቢቢሲ ያነጋገራቸው በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ እና በምሥራቅ ወለጋ፣ ሃዋ ገላና ወረዳ፣ ለምለም ቀበሌ ነዋሪዎች አሁን የፌደራል የፀጥታ አካላት በአካባቢው ቢኖሩም ጥቃት ባልተፈፀመባቸው አካባቢዎች ተመሳሳይ ጭፍጨፋ ሊፈፀም ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል። 👉ቢቢሲ ለደኅንነታቸው ሲል ስማቸውን የማይጠቅሳቸውና በቄለም ወለጋ፣ ሃዋ ገላና ወረዳ፣ መቻራ በምትባል የገጠር ከተማ የሚኖሩ ግለሰብ በእነርሱ አዋሳኝ ባሉ መንደሮች የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ፣ ከጥቃቱ ለተረፉ መንደሮች ነዋሪዎች ስጋት ነው ብለዋል። 👉ከ1977 ዓ.ም አንስቶ ነዋሪነታቸው እዚያ እንደሆነ የሚናገሩት እኚህ ግለሰብ፣ በሟቾች የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ገልጸው፤ “ዘግናኝ” ያሉትን ጭፍጨፋ የተመለከቱና ከጥቃቱ የተረፉ ሕጻናትም ሆኑ አዋቂዎች በተረበሸ ስሜት ውስጥ እንዳሉ አክለዋል። 👉“ሕጻናቱም፣ ከብቱም፣ ንብረቱም ብትንትን ብሎ ሜዳ ላይ ነው የቀረው። ለተመለከተው ልብ ይሰብራል” ይላሉ ነዋሪው። 👉እርሳቸው የሚኖሩበት መቻራ ከተማም “ጥቃት ከተፈፀመባቸው፣ መንደር 20፣ መንደር 15፣ መንደር 16 አካባቢዎች በተፈናቀሉ እናቶች እና ሕጻናት ተጥለቅልቃለች” ብለዋል። 👉እርሳቸው እንደሚሉት ሰኔ 27/2014 ዓ.ም. እናቶችና ሕጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች የተጨፈጨፉበትና በለምለም ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው መንደር 20 ከመቻራ በእግር አንድ ሰዓት ቢያስጉዝ ነው። 👉በጭፍጨፋው መንደር 20 ክፉኛ መጎዳቱን የገለጹት ነዋሪው፣ “ንብረት ተዘርፏል፤ ተቃጥሏል። ከብት ተነድቷል። በሕይወት ያለው ነዋሪ መንከራተት ይዟል” ብለዋል። 👉ወደ ከተማዋ ጥቃት ሸሽተው የሄዱት ነዋሪዎችም “በዚህ የክረምት ወቅት ያለመጠለያ በየበረንዳው፣ መንገድ ላይ፣ ዘመድ ያለው በየዘመድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ” ሲሉም ስላሉበት ሁኔታ ተናግረዋል። 👉“አነስተኛ ቁጥር ያላቸው በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ሁሌም ስጋት ላይ ናቸው” ያሉት ነዋሪው፣ አካባቢውን ለቀው የሚወጡ ሰዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል። 👉“እስካሁን ቤት ንብረቱን ላጣውና ወደ መቻራ ከተማ ለተፈናቀለው ሰው፣ በመንግሥት በኩል የሚደረግ ድጋፍ አላየሁም፤ ሰው ሲንከራተት ብቻ ነው የማየው” ብለዋል። 👉ሌላኛው ያነጋገርናቸው የሃዋ ገላና ነዋሪም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች መግባታቸውን ገልጸው፣ ነዋሪዎች ግን አሁንም አለመረጋጋታቸውን ገልጸዋል። 👉“እነዚህ ሰዎች ካለቁ ጀምሮ ሰው መረጋጋት አልቻለም። ጥቃቱ ድጋሜ ይፈፀማል በሚል ስጋት ውስጥ ነው ያለነው” ሰው በመንገድ ላይ ሲንከራተት ነው የሚታየው ብለዋል። “ተረጋግተን እንኖራለን የሚል ተስፋ የለንም” 👉በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን፣ ሃዋ ገላና ወረዳ ሰኞ፣ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም በተፈፀመ ጭፍጨፋ ከ150 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ገልጸዋል። ከተገደሉት መካከል አብዛኞቹም ሕጻናትና ሴቶች መሆናቸው ተነግሯል። 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥቃቱ በተፈፀመበት ዕለት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ መንግሥት ሸኔ በሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቡድን በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈፅሞባቸዋል ብለዋል። 👉የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኦዳ ተርቢ በበኩላቸው በቄለም ወለጋ መቻራ ሰላማዊ ሰዎች የተገደሉት “በአገዛዙ ታጣቂዎች ነው” ሲሉ ክሱን አጣጥለዋል። 👉“ሥፍራውን የተቆጣጠሩት የመከላከያ ሠራዊት እና አጋር ኃይሎች ምንም አላደረጉም” ሲሉ በመውቀስም የአገር ውስጥም ሆኑ የውጭ አካላት ገለልተኛ ምርመራ እንዲያደርጉ አፅንኦት ሰጥተዋል። 👉ከሁለት ሳምንት በፊት ጭፍጨፋ በተፈፀመበትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት ምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ ነዋሪው በበኩላቸው የአካባቢው ሰው በሐዘን በመጎዳቱ መረጋጋት ባይችልም የፀጥታ አካላት ግን በሥፍራው እንደሚገኙ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። 👉“መንግሥት እርምጃ እየወሰደ ነው። ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም. ማርፈጃውን ከፍተኛ ተኩስ ነበር” ብለዋል ነዋሪው። 👉“የተፈፀመው የሚዘገንን ድርጊት ስለሆነና ከአንድ ቤት በርካታ የቤተሰብ አባላት ስለተገደሉ፣ ተረጋግተን እንኖራለን የሚል ተስፋ የለንም” ሲሉም ያላቸውን ስሜት አጋርተዋል። 👉ምንም እንኳን አሁን የፌደራል ኃይሎች በአካባቢው በመኖራቸው ለጊዜው የጥቃት ስጋት እንደሌላቸው የሚገልጹት ነዋሪው፣ “የፀጥታ ኃይሎቹ መቼ ጥለው እንደሚወጡ ስለማናውቅ አሁንም ስጋት ላይ ነን” ብለዋል። 👉አሁንም ከታጣቂዎቹ [ሸኔ] “አንምራችሁም!” የሚል ዛቻ እንደሚደርሳቸውም አክለዋል። በስልክ ጭምር እየተደወለ ማስፈራሪያ እንደሚደርሳቸው ቢቢሲ ያናገራቸው ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ይናገራሉ። 👉“መውጣት የሚችለው ነዋሪ ተወልጄበታለሁ ወዳለው አካባቢ [ወደ ከሚሴ ዙሪያ] እየወጣ ነው” ሲሉም ለአስርት ዓመታት ኖረው፣ ወልደው ከብደው ከኖሩበት አካባቢ ለመውጣት መንገድ የጀመሩ መኖራቸውንም አስረድተዋል። 👉በጊምቢ በተፈፀመው ጭፍጨፋ 338 ሰዎች መገደላቸውን መንግሥት የገለጸ ሲሆን የዐይን እማኞች እና በአሜሪካ የአማራ ማኅበር አሰባሰብኩት ያለውን መረጃ ጠቅሶ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 600 እንደሚጠጋ እና 455 የሚሆኑትን በስም እንደለየ መግለጹ ይታወሳል። 👉ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ በነበሩ ጥቃቶችን ሸሽተው የተፈናቀሉ የአማራ ብሔር ተወላጆች በየስፍራው ተጠልለው ይገኛሉ፤ ከነዚህም መካከከል የደብረ ብርሃን ከተማ ተጠቃሹ ነው። 👉የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻድቅ በተለያየ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈፀሙ ጥቃቶችን ተከትሎ 70 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ እንደሚገኙ መግለጻቸው ይታወሳል። ከእነዚህ መካከል 17 ሺህ የሚሆኑት ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል። 👉ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ውጭ ካሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች የተወሰነ መረጋጋት ባለባቸው አካባቢዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውንም አስተዳዳሪው አክለዋል። 👉ከሰሞኑ የተፈፀሙትን እነዚህ ጥቃቶች ተከትሎ ከምዕራብ ወለጋ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን የገቡ ተጨማሪ ሰዎች መኖራቸውንም የከተማዋ ከንቲባ አቶ ካሳሁን እምቢአለ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ምንጭ፦BBC ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅ መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ጥቆማ "ሀዋሳ ነዳጅ በጉቦ ሁኗል" #Fitse ከሃዋሳ ስለሰጠኸን ጥቆማ እናመሰግናለን 👉የሚመለከተው አካል ተገቢውን የሆነ እርምጃ በመውሰድ ማስተካከል አለበት እንላለን ✅ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካለዎት በዚህ ይላኩልን @Ewuneta_bot ✅መረጃዎችን ለማግኘት @EthioEwuneta
Show all...
‼️እጣው ወደ አርብ ተዛውሯል ✅ነገ ሊወጣ የነበረው የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ ወደ አርብ ተዛውሯል 👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ14ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ለማካሄድ በበነገው እለት ፕሮግራም ተይዞ እንደነበር ይታወቃል፡፡ 👉ነገር ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ምክንያት የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት ወደ ፊታችን አርብ ሃምሌ 1/2014 የተዛወረ መሆኑን አስተዳደሩ ማምሻውን አስታውቋል፡፡ 👉"ታዛቢዎች ባለእድለኞች እና ሌሎችም በክብር እንግድነት የምትገኙ እንግዶችና የሚድያ አካላት በሙሉ ለተፈጠረው የፕሮግራም ለውጥ ይቅርታ እየጠየቅን በተለዋጩ ፕሮግራም መሰረት እንድትገኙልን ከወዲሁ እናሳስባለን" ሲልም አስተዳደሩ ገልጿል። @EthioEwuneta
Show all...
‼️ ወሀ ይቋረጣል ✅ለአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ደንበኞች ! 👉የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቅዳሜ ሐምሌ 9 እና ዕሁድ ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት በገፈርሣ ውሃ ማጣሪያ ጣቢያ የገንዳ አጠባ ያከናውናል፡፡ በመሆኑም፡- × በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከወረዳ 4 እስከ 10፣ × በጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 8፣ × ቂርቆስ ክ/ከተማ ከወረዳ 1፣ 8፣ 9 እና 10፣ × በኮልኤ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከወረዳ 9 እስከ 15፣ 👉የውሃ አገልግሎት በከፊል ስለሚቋረጥ የባለሥልጣኑ ደንበኞች ተገቢውን ጥንቃቄ ከወዲሁ እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን @EthioEwuneta
Show all...
‼️በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ በመምሰል በተለምዶ ሿሿ የተባለውን የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 3 ተሽከርካሪዎች እና 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ✅ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን የፈፀሙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በተለያዩ ቀናት እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ -3-14407 ኦሮ ፣ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-13314 አ.አ እና ኮድ 1- 10635 አ.አ ሚኒባስ ታክሲዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መስለው የተለያዩ የማታለያ ስልቶችን በመጠቀም የግል ተበዳዮች ወደየት እንደሚሄዱ ጠይቀው ከጫኗቸው በኋላ አቅጣጫ በመቀየር ነዳጅ ልንቀዳ ነው ፣ የመኪና መስታወት ልናስገጥም ነው እንዲሁም ትራፊክ ፖሊስ እያየን ነው ውረዱልን በማለት እያዋከቡ ወንጀሉን መፈፀማቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡ 👉በወንጀሉም የ4 የግል ተበዳዮች ሞባይል ስልኮች የተወሰዱ ሲሆን በህብረተሰቡ እና በፖሊስ ትብብር ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ከነ ተሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ እና ከተወሰዱት 4 የሞባይል ስልኮች ውስጥ 2 ሞባይሎች ለግል ተበዳዮች ሊመለስ መቻሉን በተጠርጣሪዎቹ ላይም አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅሷል፡፡ 👉የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው ህዝብ በሚበዛበትና የትራንስፖርት እጥረት ባለበት ቦታ በመንቀሳቀስ ተሳፋሪዎችን መኪና ውስጥ አስገብተው የስርቆት ወንጀሎችን የሚፈፀሙ ግለሰቦችን ለመከላከል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በእንደዚህ አይነት ህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው ህዝብን የሚያስመርሩና ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦችን በህግ ለማስጠየቅ ሁሉም ሰው የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት አስተላልፏል። ዘጋቢ፡- ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ @EthioEwuneta
Show all...
‼️አስገዳዩ ሽመልስ በፍጥነት ይታሰር” የፓርላማው ሃንጋሳ ያወጣው ሚስጥር ሲገለጥ =================== 29/10/2014 እሮብ (9:24 min) 3.2 MB ===================== መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
አስገዳዩ_ሽመልስ_በፍጥነት_ይታሰር”_የፓርላማው_ሃንጋሳ_ያወጣው_ሚስጥር_ሲገለጥ.mp33.23 MB
‼️የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ። ✅በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ተደጋጋሚ አሰቃቂ ጥቃት ተፈፅማል ብሏል ንቅናቄው። 👉ይህ ጥቃት በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም አዲስ አይደለም ይልቁንስ የተሳሳተው ትርክት አንዱ ቅርንጫፍ መኾኑንም አብን አስታውቋል። 👉አማራ ጠል ትርክት ከውጭም ከውስጥም ጠላት አፍርቶልናል እናም በዚህ ደግሞ እየተጎዳ ያለው ምስኪን ራሱን መከላከል የማይችል ሕዝብ ነው፤ የአሁኑን ጨምሮ ተከታታይ ችግሮችን ለማስቆም የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ የንቅናቄው ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አሳስበዋል። 👉በአማራ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ዘር የማጥፋት ጥቃት የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ ዶክተር በለጠ አሳስበዋል። 👉ንቅናቄው በአማራ ሕዝብ ላይ አየተፈፀመ ያለው ስልታዊ ዘር ማጥፋት ነው ብሎ አብን ያምናል ብለዋል ዶክተር በለጠ በመግለጫቸው። 👉የአማራ ሕዝብ ተከታታይ ግድያ ግድ ሊለው የሚገባው የመንግስት መዋቅር ችላ ማለቱን እንዲያቆም እና ባስቸኳይ ሕዝብን እንዲጠብቅ ሲል አብን አሳስቧል። 👉ጥቃቱን እየተከታተለ እርምጃ ያልወሰደው መንግስት ይህንን ጥቃት እየሸፈኑ ያሉ እንዲሁም ሕዝብን መጠበቅ ያለባቸው ከክልል እስከ ፌደራል ቢሮዎች ተጠያቂ ናቸው ሲልም አብን አስታውቋል። 👉ጥቃቱን ለማስቆም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅና የአካባቢው ነዋሪዎች በፀጥታ አካልነት ተካትተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል ሥራ እንዲሰራ አብን ጠይቋል። 👉አጥቂዎች በግልፅ ፍርድ እንዲበየንባቸው፤ ይህን ችላ ያሉ፣ እንዲባባሱ ያደረጉ ሚዲያዎች፣ ፓለቲከኞች እና ግለሰቦችን መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርግ አብን ጠይቋል። ‼️ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅም አብን ጠይቋል። 👉አማራ የመጣበትን ችግር ለመመከት እንደ ሕዝብ በአንድነት ለመመከት አንድነቱን ጠብቆ የመጣውን የዘር ማጥፋት ጥቃት ለመመከት እንዲሠራ አብን ጥሪ አቅርቧል። 👉በቀጣይ ሀሙስ የሀዘን ቀንን ለማሰብ የሻማ ማብራት፣ የፓናል ውይይት እና ሌሎች ዝግጅትን ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አብን ገልጿል። @EthioEwuneta
Show all...
‼️የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ ✅የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ። 👉የዕለቱን መርኃ-ግብር በግፍ ለተጨፈጨፉት ዜጎች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በማድረግ የጀመረው ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን የውሳኔ ሐሳቦች አስተላልፏል፡፡ @EthioEwuneta
Show all...
‼️ ስለመንግስትና ሸኔ ሌላ የስልክ ንግግር ወጣ ✅ አስደንጋጩ የአቶ አንጋሳ ንግግር ትርምስ ፈጠረ ✅ባለስልጣናት ወለጋ ገቡ- ፍጋው ቀጥሏል =================== 29/10/2014 እሮብ (16.47 min) 7.7 MB ===================== መረጃው የ #Feta_Daily_News ነው ===================== ✅YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ 👇 https://youtu.be/M_5e2uxf4HQ ✅ ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ @Ewuneta_bot ይላኩልን መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው 🙏 ===================== @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show all...
ሰበር_ስለመንግስትና_ሸኔ_ሌላ_የስልክ_ንግግር_ወጣ_አስደንጋጩ_የአቶ_አንጋሳ_ንግግር_ትርምስ_ፈጠረባለስልጣናት.mp37.69 MB
Photo unavailableShow in Telegram
‼️አሜሪካ በኦሮሚያ ክልል ለደረሰዉ ጥቃት ተጠያቂነት እንዲኖር ጠየቀች፡፡ ✅በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ እንዳስታወቀዉ፣ ለደረሰዉ ሰብአዊ መብት ጥሰት ሙሉ ተጠያቂነት እንዲኖር እንጠይቃለን ብሏል፡፡ 👉በኦሮሚያ ክልል በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት አዝነናል ያለዉ ኢምባሲዉ ፤ ለተጎዱት ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡ 👉ኢትዮጵያዉያን ሁከትን እንዲተዉ፣ በአገሪቱ የሚነሱትን የትጥቅ ግጭቶችን ሁሉ ለማስቆም ውይይት እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡ 👉የአሜሪካ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ለደረሰዉ ሰብአዊ መብት ጥሰት ሙሉ ተጠያቂነት እንዲር እንደሚፈልግም ኢምባሲዉ አስታዉቋል፡፡ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም @EthioEwuneta
Show all...
‼️ የተወካዮች ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በልዩ ስብሰባ እየመከረ ነው ✅የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “በወቅታዊ የሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ እና በንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ” ላይ ለመወያየት ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 29፤ 2014 ልዩ ስብሰባ እያካሄደ ነው። ፓርላማው በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ “የውሳኔ ሃሳብ” ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድ የፓርላማ አባል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።  👉የተወካዮች ምክር ቤት ቀደም ሲል ለዛሬ ይዞት የነበረው መርሃ ግብር በፓርላማ አባላት አማካኝነት የችግኝ ተከላ ማካሄድ ነበር። ነገር ግን ከአማራ ክልል የተወከሉ የምክር ቤት አባላት ኮሚቴ አዋቅረው ባቀረቡት ጥያቄ የዛሬው ልዩ ስብሰባ መጠራቱን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የፓርላማ ምንጭ ተናግረዋል።  👉በኮሚቴው ውስጥ ከአማራ ክልል የተወከሉ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዮች መካተታቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የፓርላማ አባል አስረድተዋል። በኮሚቴው ጥያቄ በተጠራው በዛሬው ስብሰባ የተወካዮች ምክር ቤት “ጭፍጨፋውን ያወግዛል ተብሎ እንደሚጠበቅ” እኚሁ የፓርላማ አባል ገልጸዋል። 👉ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሰኔ 27 በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ዜጎች “ጭፍጨፋ” እንደተፈጸመባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታውቀው ነበር። በቄለም ወለጋ ዞን በሀዋ ገላን ወረዳ መንደር 20 እና 21 በተባሉ አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም አረጋግጧል።  👉የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ ምሽት ባወጣው መግለጫ “በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎቻችን ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ በእጅጉ የሚወገዝ ነው” ብሎ ነበር። ምክር ቤቱ በዛሬው ልዩ ስብሰባው ድርጊቱን በይፋ ከማውገዝ ባለፈ “ጉዳዩን ገምግሞ ሪፖርት የሚያቀርብ ቡድን” ሊያወቅር እንደሚችልም የፓርላማ አባሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ምክር ቤቱ ሊያሳልፈው በሚችለው የውሳኔ ሀሳብ መሰረትም “ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሊታወጅ” የሚችልበት ዕድል እንዳለም ጠቁመዋል።  👉በዚህ ጉዳይ ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። የዛሬውን የፓርላማ ልዩ ስብሰባን የመዘገብ ፍቃድ የተሰጠው ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ብቻ በመሆኑም ሂደቱን በተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ተገኘቶ ለመከታተልም አልተቻለም።  👉የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢን ጨምሮ ዛሬ በፓርላማ ሊካሄድ የነበረን ሌላ ስብሰባ ለመዘገብ በስፍራው የተገኙ የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች “መግባት አትችሉም” ተብለው ተመልሰዋል። የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በፓርላማው የተገኙት፤ በተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚገመግምበትን ስብሰባ ለመዘገብ ነበር።  👉ይህ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ በልዩ ውይይቱ ምክንያት መሰረዙን የፓርላማ ምንጮች አስረድተዋል። የተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ማክሰኞ ሰኔ 28፤ 2014 ሊካሄደው የነበረው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ እንዲሁ ሳይካሄድ ቀርቷል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የፓርላማ አባላት፤ የትላንቱ መደበኛ ስብሰባ የተሰረዘበት ምክንያት አልተገለጽልንም ብለዋል።  @EthioEwuneta
Show all...