Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
@telemetr_io_bot
Telegram analytics bot

The bot can:

  • analyze channel audience
  • channels intersections
Category
Channel location and language
🇪🇹እንኳን ወደ እውነት ሚድያ በሰላም መጣችሁ🇪🇹 ✅ በዚህ ቻናል እውነተኛ ዜናዎች አስገራሚ ክስቶች የስራ ማስታወቂያዎች እንዲሁም ጥንቃቄ የሚሹ ጉዳዮችን የምናጋራችሁ ይሆናል። ✅ሀሳብ፣አስተያየት፣መረጃ ወይም ከኛ ጋር መስራት ከፈለጉ በአድራሻችን  @Ewuneta_bot   @Ewuneta_bot  
Show more
37 737-39
~5 943
~53
15.74%
Telegram general rating
Globally
46 358place
of 3 824 617
66place
of 899
In category
307place
of 2 433

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

‼️ሰበር ዜና‼️ ✅የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ። 👉ከንቲባው በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ተጠርጥረው እንደሆነ የኢሳት የደህንነት ምንጮችን ገልጸዋል። 👉ከንቲባው በፌዴራል ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ፣በብሔራዊ እና መረጃ ደህንነት ግብረኃይል በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮቻችን አክለዋል። 👉ከንቲባው አቶ ደስታ አንዳርጌ እስከ ሕዳር 18 ምሽት ድረስ ኃላፊነታቸው ላይ የነበሩ ቢሆንም ትላንት ሕዳር 18 ሌሊት ላይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። ESAT @EthioEwuneta @EthioEwuneta
4 491
9
✅መቀሌ ዛሬ ጧት በድሮን ጥቃት ደረሰ✅ 👉የኢትዮጵያ መንግስት ጦር የትግራይ ክልል መስተዳድር ርእሰ-ከተማ መቀሌን ዛሬ ጧት በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተነገረ። 👉 የዓይን ምስክሮች እንዳስታወቁት በልማዱ ዲያስፖራ ተብሎ የሚጠራዉ የሐድነት ክፍለ ከተማ የደረሰዉ ጥቃት ሁለት መኖሪያ ቤቶችን አፍርሷል ወይም አቃጥሏል። 👉 ነዋሪዎቹ እንዳሉት ሌሎች ቤቶችም መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በሰዎች ላይ ግን ፍርስራሽና የመስተዋት ስብርባሪና ካደረሰዉ አነስተኛ ጉዳት በስተቀር የደረሰ ነገር የለም። 👉 የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቃል አቀባይ ጌታቸዉ ረዳ የዛሬዉን ጥቃት ተስፋ ከቆረጠ ሥርዓት የተሰነዘረ የተስፋ መቁረጥ ርምጃ በማለት ነቅፈዉታል። 👉 መቀሌ ባለፈዉ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያም በድሮን ተመትታ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ስለዛሬዉ ጥቃት እስከአሁን ምንም ያለዉ የለም። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 745
5
✅ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በግንባር✅ 👉 ከእኔ ጀርባ የምታዩት ጠላት እስከትናንትና ድረስ ሙሉ በሙሉ የያዘው ተራራ ነው፤ ዛሬ አስለቅቅናል፤ 👉 ካሳጊታን ይዘናል ዛሬ ጭፍራንና ቡርቃን እንይዛለን፤ 👉 የሰራዊቱ ሞራል እጅግ ደስ ይላል፤ ጦርነቱ በከፍተኛ ድል ነው እየተከናወነ ያለው፤ 👉 የኢትዮጵያ ነጻነት እስኪረጋገጥ ወደኋለ አንልም፤ 👉 የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆም ኢትዮጵያን ማየት ነው 👉 የምንፈልገው ኢትዮጵያዊ መሆን አሊያም ኢትዮጵያ መሆን ነው፤ 👉 ሁሉንም በድል እንደምናሳካ በጣም እርግጠኛ ነኝ፤ 👉 ህዝብችን ከጎናችን ነው፤ 👉 በውጭ ያሉ ወገኖቻችን ባላቸው አቅም እየጮሁ ነው፤ የእኔ ስራ ደግሞ በግንባር ሆኖ ጦርነቱን መምራት ነው፤ 👉 በጣም ትላልቅ ድሎች አሉ፤ ይቀጥላል፤ 👉 ጠላት ከእኛ ጋር ሊስተካከል የሚችል ቁመና የለውም እናሸንፋለን፤ 👉 ነጻ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናሸጋግራለን፤ ውጤቱ በጣም ጥሩ ነው በርቱ፤ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 276
3
🪧በብሔር ስም እየነገዱ ኢትዮጵያን ማሸበር ፈጽሞ አይቻልም🪧- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ✅"ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በመንዛትና በብሔር ስም በመነገድ ኢትዮጵያን ማሸበር ፈጽሞ አይቻልም" ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። 👉የአሸባሪ ቡድኖችን የሽብር ተልዕኮ ማክሸፍ የኢትዮጵያዊያን የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። 👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከኢትዮጵያ ባለፈ የአፍሪካ ርዕሰ መዲናና ፤የዓለም ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ማዕከል የሆነችውን አዲስ አበባ በፕሮፓጋንዳ ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች የሕልውና ዘመቻው ከመጀመሩ በፊት የነበሩ ናቸው ብለዋል። አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
3 970
0
🪧የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻውን ተሰብስቦ፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተመለከቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ገምግሟል። 🪧 ✅የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተያዘለት ዓላማ አኳያ አፈጻጸሙ በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን አረጋግጧል። 👉በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከርና ዕንቅፋት የሚሆኑትን ችግሮች ለማስወገድ የሚከተሉትን 4 ትእዛዞች አስተላልፏል። 1. የመለዮ ለባሾች ዩኒፎርም የራሱ የሆነ የአለባበስ ሕግና ሥርዓት አለው። ከዚህ ሕግና ሥርዓት ውጭ የመለዮ ለባሾችን ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት የተልእኮ አፈጻጸሙን እያወከ ይገኛል። 👉 በመሆኑም በማንኛውም ሁኔታ፣ ቦታና ጊዜ የመከላከያ ሠራዊትን፣ የፌዴራል ፖሊስን፤ የክልል ልዩ ኃይሎችንና የመደበኛ ፖሊስን ዩኒፎርሞች፣ የጸጥታ አካላት አባል ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለብሶ መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው። 👉የተቋማቱ አባል ሳይሆንና የታደሰ መታወቂያ ሳይዝ ዩኒፎርሙን ለብሶ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ፣ የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። 2. አሁን ያለንበት ሀገር የማዳን የህልውና ዘመቻ በጥብቅ ዲሲፕሊንና በከፍተኛ ጥንቃቄ መፈጸም የሚገባው ነው። ስለሆነም ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችንና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው። 👉በየግንባሩ የሚገኙ የሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች ከተሰጣቸው ሥምሪትና ተልእኮ ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችንና ውጤቶችን የሚመለከቱ መግለጫዎች መስጠት የተከለከለ ነው። 👉የጸጥታ አካላትም ይሄን ተላልለፈው በሚገኙት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። 3. በሀገራችን ህልውና ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመቀልበስ መንግሥትና ሕዝብ ተቀናጀተው ወቅታዊና ሕጋዊ ርምጃን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። 👉ሆኖም ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ከሚፈቅደው ውጪ የሽግግር መንግሥት ወይም ሌላ ሕገ ወጥ ቅርጽ ያለው መንግሥት እንመሠርታለን ብለው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ አካላት ላይ የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። 4. በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያውያን ግንባር ቀደም አጀንዳ ሀገርን መታደግ መሆኑ ይታወቃል። ማንኛውም የሐሳብና የተግባር እንቅስቃሴ ሁሉ ይሄንን ግንባር ቀደም የኢትዮጵያውያን ዓላማ የማያሰናክል መሆን አለበት። 👉በመሆኑም የሐሳብ ነጻነትን ሰበብ በማድረግ ልዩ ልዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም፣ የሽብር ቡድኑን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በመደገፍ በህልውና ዘመቻው ላይ ዕንቅፋት የሚፈጥሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአስቸኳይ ጊዜ ዕዝ ያስጠነቅቃል። 👉ይሄንን ማስጠንቀቂያ ተላልፈው ከድርጊታቸው በማይቆጠቡ አካላት ላይ የጸጥታ ኃይሎች ተገቢውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ህዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 268
2
🪧ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችንና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው።🪧 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
3 851
0
✅“በሰላም የኢትዮጵያ ብልጽግና ሚረጋገጥበትን መንገድ መስራት ብቻ ነው ምፈለገው... ተላላኪ መንግስ ኢትዮጵያ ውስጥ አይፈጠርም።”✅ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ @EthioEwuneta @EthioEwuneta

file

4 392
11
🪧ከህወሓትና ሸኔ ጋር አገር በማተራመስና በማፍረስ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው🪧 ✅ከሽብርተኞቹ ህወሓትና ሸኔ ጋር የህቡዕ ትስስር በመፈፀም አገር በማተራመስና በማፍረስ ሴራው ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር የማዋሉ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። 👉ከህወሓትና ሸኔ የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ ከተማ ሁከት፣ ግርግርና ሽብር ለመፈፀም ዝግጅት እያደረጉ ባሉ ተጠርጠሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሰነዶችን መያዝ መቻሉን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ 👉በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ከጁንታው ጋር ትስስር አላት በሚል ከአካባቢው ህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ በመኖሪያ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከ60 መሰል ጥይቶች ጋር እንዲሁም ሁለት ሽጉጦች ከ20 መሰል ጥይቶች ጋር በፀጥታ አካላት መያዛቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁት የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ 👉በተመሳሳይ በዚሁ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወራዳ ሁለት በሚገኘው አትላስ ሆቴል ውስጥ ለሶስት አመታት ያህል አልጋ በመያዝ ከሽብርተኛው ሸኔ ጋር በህቡዕ በመገናኘት ተልዕኮዎችን ሲያስተባብር የነበረ አንድ ተጠርጣሪ ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ 👉ተጠርጣሪው ባረፈበት ሆቴል ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አድንዛዥ ዕፅ፣ ሶስት ኮምፒዩተሮች፣ ሁለት ፕሪንተሮች፣ ሰባት የተለያዩ ማህተሞች፣ አንድ ላፕቶፕ እና አንድ ትልቅ ማይክ ተይዟል። 👉ከዚህ ባለፈም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለመልቀቅ ያዘጋጀቸው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰነዶች ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን በማስረጃነት የተያዙ ፎቶዎችን አያይዘው ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ልከውልናል። አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 322
2
3 699
0
🪧የአሜሪካ ኤምባሲ ከሽብር ፈጣሪ መግለጫዎቹ እንዲቆጠብ መንግሥት አሳሰበ🪧 ✅የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ዜጎቻቸውን ለማውጣት ያደረጉት ሙከራ ስህተት መሆኑ ሲገባቸው ሀሳባቸውን እየቀየሩ ነው ሲል መንግሥት አስታወቀ፡፡ 👉በዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የሚደረገው ሙከራ ፍጹም ስህተት መሆኑ ተገልጿል፡፡ 👉የአሜሪካ ኤምባሲ እንደዚህ ዓይነት መግለጫ ከማውጣት እንዲቆጠብ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ አሳስበዋል፡፡ 👉የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤምባሲዎችን የማስፈራራት ስራ ከመስራት እንዲቆጠቡም በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
4 363
2
‼️የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮ/ር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️ ✅ 'የደህንነት ስጋት ናቸው' ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ከእስር በመፍታት የተጠረጠሩት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ። 👉የከተማው ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪው ህውሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ያለ ኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ከማቆያ እንዲወጡ አድርገዋል በሚል ነው። 👉በዚህ ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች አመራሮች መኖራቸውን በተመለከተም ከህዝብ ጥቆማዎች እየደረሳቸው እንደሚገኝም አቶ ዳንኤል ገልፀው÷ መረጃውን ለማጥራት እየተሠራ ነውም ብለዋል፡፡ አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 084
4
🪧የሰርግ ፕሮግራም ሰርዠ ወደ ግንባር ለመዝመት ወስኛለሁ🪧 - ረ/ፕሮፌሰር አክሊሉ አይዛ ✅ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለተዘጋጀው የአሸባሪ ህወሓት ቡድን ምላሽ ለመስጠት በጥር ወር የያዙትን የሰርግ ፕሮግራም ሰርዘው ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰናቸውን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ አይዛ ገለጹ። 👉በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ወራሪ ኃይል ጥቃት እየደረሰባት ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ለማፍርስ ለተዘጋጁት የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጥቃት ከዜጎቿ ምላሽ እንደሚያስፈልጋት ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡ 👉ከዚህ ቀደም በዘመቻው ላይ ለመሳተፍ ያቀዱ ቢሆንም÷ የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ሲያግዙ የቆዩና አሁን ተማሪዎቹ እንደተመረቁ የዘመቻ ደብዳቤ ለዩኒቨርስቲው አቀርበው ዝግጅት ላይ መሆናቸውንም መምህሩ ተናግረዋል፡፡ 👉በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ሀገርን እንዳይመራ እያደረገ ያለውን ጠላት ለመመከት በጥር ወር የያዙትን የሰርግ ፕሮግራም ሰርዘው ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰናቸውን አብራርተዋል፡፡ 👉እናቱን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ እንደማይኖር የገለፁት መምህሩ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሴራ የሚያምን በመሆኑ ከመንግስት ጎን በመቆም ጦርነቱን በድል ተወጥተን ወደ አንድ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ 👉የውጭ ሚዲያዎች የሚያደርጉት ዘመቻ ከዚህ ቀደም ከአሸባሪው ህወሓት የሚያገኙትን ጥቅም የሚያስቀርባቸው በመሆኑ÷ የውሸት ፕሮፓጋንዳቸውን ቢያሰራጩም ይህ በኢትዮጵያዊያን አንድነት እንደሚቀለበስ ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ተናግረዋል ሲል ዴሬቴድ ዘግቧል። አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
3 894
2
🪧የኢትዮጵያ የውጭ ጫናውን አሸንፎ መውጣት ለአፍሪካም ማሸነፍ ነው 🪧- ዶ/ር ምህረት ደበበ 👉 ኢትዮጵያ አሁን የተከፈተባትን የውጭ ጫና አሸንፎ መውጣት ለአፍሪካም ጭምር ማሸነፍ እንደሆነ መገንዘብ እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዶክተር ምህረት ደበበ ገለጹ፡፡ 👉ዶክተር ምህረት እንደገለጹት ÷ ኢትዮጵያ አሁን የተከፈተባትን የውጭ ጫና አሸንፎ መውጣት ለአፍሪካም ጭምር ማሸነፍ እንደሆነ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ 👉በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ትልቅ እና ታሪካዊ ጊዜ ላይ ነን ፤ አፍሪካውያን ከጎናችን እንደሚቆሙ እያሳዩን ነው ፤ ስለሆነም ጦርነቱን ከማሸነፍ ውጪ ሌላ ምርጫ የለንም ብለዋል፡፡ 👉በታሪካችን ኢትዮጵያ ብቻዋን ነፃነቷን አስከብራ ሌሎችንም ወደ ነፃነት ስትመራ ይሄ ሁለተኛው የነፃነት ጥሪ መሆኑን ጠቁመው ÷ ይሄንን ጦርነት በማሸነፍ የአሁኑ ትውልድ ታሪክ መጻፍ እንዳለበትም ነው የገለጹት፡፡ 👉ምዕራባውያን የአፍሪካን አገራት እንደ አገር ማየት እና ማክበር አይፈልጉም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ውስጥ ያልገባች በአጭር ጊዜ ውስጥም ቢሆን በጣልያን ወረራ አባቶቻችን እጅ ሳይሰጡ የኢትዮጵያን ነፃነት እንዳስጠበቁ ገልጸዋል፡፡ 👉ኢትዮጵያን ትልቅ እናደርጋታለን ብለው ዜጎቿ ሲነሱ ምዕራባውያን ደግሞ እንዳንሆን በአሁኑ ወቅት ተነስተውብናል ብለዋል፡፡ 👉ይህንን እንዳይሳካ ለማድረግ እንደ ሁነኛ መሣሪያ ሆኖ ያገኙት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት እንደሆነ ጠቅሰው ÷ የአሸባሪውን ህወሓት ኃይል ለዚህ መጠቀሚያ ስለማድረጋቸውም ነው ያነሱት፡፡ 👉በግብጽና በሱዳን በኩልም በዓባይ ዙሪያ ያለው ፍላጎት ቀላል እንዳልሆነ ማንሳታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡ 👉ስለሆነም በጦር መሣሪያ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው የአገሩ አምባሳደር መሆን ይጠበቅበታልም ነው ያሉት፡፡ 👉አሸናፊነት ከድል በኋላ የሚመጣ አይደለም የሚሉት ዶክተር ምህረት ÷ ሰው ሳይዋጋ በፊት የአሸናፊነት ሥነ ልቦና ሊላበስ ይገባልም ብለዋል፡፡ ጦርነቱን ቀላልና በአገር ውስጥ የተለያየ እይታ ያላቸው የአንድ አገር ሰዎች እየተዋጉ እንዳሉ አድርጎ ማሰብ አያስፈልግም፡፡ 👉ይልቁንም የምዕራባውያን ትልቅ እጅ ያረፈበት እጅግ ውስብስብ ጦርነት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ 👉አገር ከገባችበት እንድትወጣ ጦርነቱን አቅልሎ አለማየትና የኔ ነው ብሎ በመነሳት ሁሉም የሚችለውን ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ 👉ለዚህ ቆራጥ በመሆን እኛ ባንጠቀም ቀጣዩ ትውልድ ይጠቀማል ብሎ መነሳት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ 👉በተሳሳተ አቅጣጫ ያሉ ኢትዮጵያውያንም መንቃት እንዳለባቸው ያነሱት ዶክተር ምህረት ÷ ምን እያደረጉ እንዳሉና መጨረሻ ላይ ማግኘት የሚፈልጉት ነገር ምን እንደሆነ በማወቅ አገራቸውን ከማፍረስ እንዲመለሱ ዶክተር ምህረት መክረዋል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 716
4
‼️የኛ ቲቪ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው‼️ ✅የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት እና ወቅቱን ያላገናዘበ ዘገባ ሰርቷል ለተባለው ለየኛ ቲቪ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። 👉ባለስልጣኑ የኛ ቲቪ በተሰኘው ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ከዜጎች በቀረበ ጥቆማ እና በተደረገ ምርመራ መሰረት ማረጋገጥ እንደቻለ ገልጿል፡፡ 👉በዚህ መነሻም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለቴሌቭዥን ጣቢያው የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አስታውቋል፡፡ 👉መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣኑ÷በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የመገናኛ ብዙኃን ሀሰተኛ መረጃ እና ወቅቱን ያላገናዘበ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ማሳሰቡን ከመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
6 155
1
🪧ሲ ኤን ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃ እያወጣ መሆኑ ተጋለጠ🪧 ✅ሲ ኤን ኤን የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃ እያወጣ እንደሆነ ተጋለጠ። 👉ጣቢያው ኢትዮጵያን በተመለከተ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን እየሰራ ቢገኝም፥ የሚሰራቸው ዘገባዎች በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረቱ ሐሰተኛ፣ የተዛቡና ሚዛናዊነት የጎደላቸው ናቸው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል። 👉የቴክኖሎጂ አማካሪና ስትራቴጂስት የሆነው የቴክቶክ ዋና አዘጋጅ ሰሎሞን ካሳ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ እንዳደረገው፥ ሲ ኤን ኤን በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት በሰራው አንድ ዘገባ ላይ ሀሰተኛ ምስል መጠቀሙን አጋልጧል። 👉“ምንም ነገር ተሸሽጎ ለዘላለም አይቆይም” በሚለው መርሁ የሚታወቀው ኡጋንዳዊው የምርመራ ጋዜጠኛው ዳኒኤል ሉታያ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ከማቅናቱ በፊት የሲ ኤን ኤን ዘገባዎችን ተመልክቶ እንደነበር ገልጿል። 👉በዘገባው መሰረት ወደለየለት የጦር ቀጠና እየገባ እንደሆነ ተሰምቶት እንደነበር በትዊተር ገጹ አስነብቧል። 👉ነገር ግን ኢትዮጵያ ሲደርስ ያጋጠመው የሲ ኤን ኤን ዘገባ ከፈጠረበት ምስል ተቃራኒ እንደሆነም ጋዜጠኛው አስታውቋል። አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
11 554
22
🪧የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ጥቅምት 27 ቀን ተራዘመ🪧 ✅በተለያዩ ምክንያቶች የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም መራዘሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 👉የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በ11ዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በአካል በመገኘት እንዲያስመዘግብ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች በእጃቸው ላይ የሚገኝን የጦር መሳሪያ ለተከታታይ 3 ቀናት አስመዝግበዋል፡፡ 👉ሰዎች የማስመዝገብ ፍላጎቱ እያላቸው የምዝገባ ቀኑ በማጠሩ፣ያላቸውን የጦር መሳሪያ ሌላ ቦታ በማስቀመጣቸው እና ማስመዝገብ እንደሚቻል በቂ መረጃ ያልሰሙ ግለሰቦች በመኖራቸው ምክንያት ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡ 👉ስለሆነም ማንኛውም ግለሰብ በእጁ ላይ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ያላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ የተጨመረውን ቀን ተጠቅሞ እንዲያስመዘግብ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡ 👉የጦር መሳሪያ የማያስመዘገቡ ግለሰቦች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆኑ እና የጦር መሣሪያው ለመንግስት ገቢ እንደሚደረግም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 657
7
👆 🪧በመላ ኦሮሚያ የሽብርተኞቹን ወያኔና የሸኔን አገር የማፍረስ ሴራ በማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ እየተካሄደ ነው🪧 ✅በመላ ኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ሽብርተኞቹ ወያኔና ሸኔ ኢትዮጵያያን ለማፍረስና ህዝቦቿን ለማጥፋት እያካሄዱ ያሉትን እንቅስቃሴ በማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ በመካሄድ ላይ ነው ። 👉ሠልፈኞቹ የወያኔ አሽከር ሆኖ የሚያገለግለው ሸኔ እና ጨፍጫፊውና ዘራፊው ወያኔ የሚያካሂዱት አገርና ህዝብን የማጥፋት ሴራ እኛ በህይወት እያለን ሊሳካ አይችልም፥የክተት ጥሪውን ተቀብለን በመዝመት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እናስከብራለን ብለዋል። 👉በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን ባደረሱን መረጃ መሠረት፥ ታጋሽና ሰላማዊ የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች ኢትዮጵያ - ጠል የሆነውን የባዕዳን ተልዕኮ ለማስፈጸም እያካሄዱ ያሉትን እንቅስቃሴ በጥብቅ እንደሚያወግዙ ሠልፈኞቹ ገልጸዋል። 👉ሰልፈኞቹ ይዘዋቸው ከወጡት መፈክሮች መካከልም “ወያኔ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ናት! እኔ እያለሁ ወያኔ ዳግም በህዝባችን ትከሻ ላይ የጭቆና ቀንበር አትጭንም ወያኔን ማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው! አልረሳም! ወያኔ የኦሮሞ ቄሮና ቃሬ ጠላት ናት! እዘምታለሁ! የኢትዮጵያን ሉሃላዊነት አስከብራለሁ! በአንድ እጃችን ልማታችንን፣ በሌላ እጃችን ጠላቶቻችንን ለመቅበር ተግተን እሠራለን! “ የሚሉ ይገኝበታል። አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 217
2
3 163
0
3 633
0
3 512
1
🪧የዩኒቨርሲቲ ምደባ🪧 ✅ለመቐለ ፤ አክሱም ፤ አዲግራት ፤ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ ከላይ በተጠቀሱት ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በፀጥታ ምክንያት ትምህርታችሁን መቀጠል ያልቻላችሁ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በወሰነው መሰረት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በጊዜያዊነት የተመደባችሁ ስለሆነ በተቀመጠዉ አድራሻ https://www.placement.ethernet.edu.et/ የተመደባችሁበትን ዩኒቨርስቲ ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ጥሪ ሲያደርግላችሁ ብቻ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡ #ማሳሳቢያ 1. ምደባዉ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረዉን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡት ተማሪዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡ 2. ምደባዉ የተካሄደዉ መረጃዎችን በትክክል ላሰገቡ ተማሪዎች ሲሆን፣ በተጠየቀዉ መሰረት መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ ተማሪዎችና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻላችሁ ተማሪዎች ስማችሁን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላታገኙ ስለምትችሉ፣ በነበራችሁበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት ስለተመዳባችሁ፣ የተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ፡፡ 3. ተመዝግባችሁ ሳትመደቡ የቀራችሁ ተማሪዎች በቂና ግልፅ መረጃ ያላቀረባችሁ በመሆኑ ያልተመደባችሁ መሆኑን በመገንዘብ ትምህርት ክፍላችሁ የተመደበበትን ዩነቨርስቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳዉቃለን፡፡ 4. ያልተመዘገባችሁ እና ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላችሁ ተማሪዎች በተቀመጠዉ የቴሌግራም ቦት አድራሻ(@moeplacementbot) አቤቱታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን አቤቱታዎችን በአካል የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ 5. በዩኒቨርስቲዎቻችሁ ተፈቅዶላችሁ እረፍት(Withdrawal) ላይ የነበራችሁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍላችሁ ለተመደበበት ዩኒቨርስቲ ማስረጃቻዉን አቅርባችሁ የሚታይላቸዉ ይሆናል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
4 848
7
🪧ስራ አዋሽ ባንክ🪧 Share ያድርጉ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
4 743
20
አርማሽ (ቀና በል) ➖➖➖➖➖➖ አዝማች: አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ ቀን እየሄደ ቀን መጣ ልቤ ከሀሳብ ሳይወጣ መጥታ ታብሰው እንባዬን ሀገሬን ጥሯት አርማዬን መቼም ከዚህ ምድር ላይ ሄዶ ነው ሁሉም ቀሪ አገር ናት ቋሚ ሰንደቅ ለዘላለም ኗሪ ትላንትም እንደ ጀምበር እያዩት ካይን ይርቃል ኢትዮጵያ እንድትመጪ ስንት ቀን ይበቃል እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ ግን ባባሁ ናፈኩሽ እና ዕምባ ቀደመኝ እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ ወጥተሽ በምሥራቅ አንቺ ያለም ጀምበር አንድ አርጊንና ጠላትሽ ይፈር የቦረኩበት በልጅነቴ የያኔው መልክሽ ብቅ ሲል ፊቴ እየመለሰኝ ወደ ትላንቱ ናፍቆኝ በብርቱ ትዝ አለኝ የጥንቱ እ ... እ ... እ አዝማች: አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ አገር ለክብሩ ሲጣራ ከፍ ያደረግነው ባንዲራ ዘመም ሳይል ቀን ጎሎ ባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ ብዙነሽ አንቺ አገሬ የሞላሽ ታምራት ምኩራብሽ የተፈራ የነጻነት ቤት የአርበኞች የድል ችቦ ለትውልድ እንዳበራ መኖር ላገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ እኔማ ................. ዓመት አውዳመት ድገመን ሲሉ ልጆች በቀዬው ችቦ እያበሩ መስቀል ፋሲካው ዒድ እንቁጣጣሽ አውዳመት አይሆን አንቺ ካልመጣሽ ዘመን አድሰሽ በፍቅር ቀለም ብቅ በይ ኢትዮጵያ ሁኚና መስከረም ሆነሽ መስከረም ……. አስዮ ብቅ በይና ……. ቤሌማ እንበል አሲዮ ……. አስዮ ናና ቤሌማ ……. ቤሌማ ብቅ በይና ……. .አስዮ ሆነሽ ሙሽራ ……. ቤሌማ ይብቃን ስደቱ ……. አስዮ ስቃይ መከራ ……. ቤሌማ ቤሌም ቤሌማ ……. አስዮ ናና ቤሌማ ……. ቤሌማ ዘር ያበቀለው ……. አስዮ ታጭዷል መከራው ……. ቤሌማ የኢትዮጵያዊነት ……. አስዮ አሁን ነው ተራው ……. ቤሌማ አሲዮ .......አሲዮ......... ዘመን አድሰሽ ……. አስዮ በፍቅር ቀለም ……. ቤሌማ ብቅ በይ ኢትዮጵያ ……. አስዮ ሆነሽ መስከረም……. ቤሌማ እኛስ ከመንገድ ላይ ጠፍተን መች አወቅነው ብንሄድ ብንሄድ አንደርስም ገና ነው በመባረኪያችን ከመንገድ ላይ ዝለን አይበቃም ወይ ማሳል በዘር ጉንፋን ታመን ቀን አለ በሉ | 2✖ ቀን አለ ገና ለኢትዮጵያዊነት ቀን አለው ገና ስምሽን በክፏ ያነሳሽ ጠፍቶ አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወጥቶ እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል ቀን አለ በሉ | 2✖ ቀን አለ ገና ስንቱ ተሰደደ ይብቃን ሐዘን ለቅሶ አንድ ሆነሽ ኢትዮጵያ ባዬን ፍቅር ነግሦ ዘር ያበቀለው ታጭዷል መከራው የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራው ቀናበል አሁን | 2✖ ቀና በል ቀና የጀግኖቹ ልጅ አንተ ነህና ካገር ወዲያ ሞት ሞት የለምና ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት ማንም አይገታው የተነሳለት ቀናበል አሁን ቀናበል ቀና ጥንት አባቶችህ ያቆዩትን ከፍ አርገህ ይዘህ ባንዲራህን ቀናበል አሁን ቀናበል ቀና -----------------------------//---------------------- 🟩 🟨 🟥 (https://youtu.be/PkOstq4GuLk) ግጥም - ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ዜማ - ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ቆየት ያለ የሀገረሰብ ባህላዊ ዜማ ተጨማሪ ድምፅ ግብዐት - ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ሙዚቃ ቅንብር : ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ: ማሩ ዓለማዬሁ/አቡጊዳ እና ማርቭን ስቱዲዮዎች ሳክስ - ያሬድ ተፈራ ሊድ ጊታር - በረከት ተስፋዝጊ መሰንቆ - ማንደፍሮ ካሳ (ቤቢ) ተቀባዮች - ምኞት ኃይሉ ( ዲጄ ዊሽ) እና ክንዴነህ ወንድሙ ምስጋና - ይህ ሥራ የተሳካ እንዲሆን በተለያየ መንገድ አስተዋፅዖ ላደረጋችሁ ወገኖች በሙሉ :: @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
6 223
57

TEDDY_AFRO_አርማሽ_ቀና_በል_New!_Official_Single_2021_With_Lyrics128k.m4a

5 376
65
🪧መከላከያ ሠራዊቱ በሁሉም ግንባሮች የአሸባሪውን ወራሪ ሃይል እየደመሰሰ ነው🪧 ✅ የአገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች አሸባሪውን ወራሪ የህወሃት ሃይል በመደምሰስ ላይ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። 👉የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ሠራዊቱ ኢትዮጵያን የማዳን ተልዕኮውን በጀግንነትና በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 👉ትናንት በደሴ ግንባር አሸባሪው ቡድን ቀድሞ ባስገባቸው ሰርጎ ገቦችና ሲቪል ለብሰው ከተማዋ ውስጥ በነበሩ ባንዳዎች አማካኝነት ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም መሞከሩን ገልፀዋል። 👉የመከላከያ ሠራዊቱ የተከፈተበትን ጥቃት በከፍተኛ ተጋድሎ መክቶ የማጥቃት ዘመቻ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል። 👉ሠራዊቱ ትናንት በደሴ ግንባር ታላቅ ተጋድሎ መፈጸሙን እና ሕዝቡም ደጀንነቱን በተግባር ማስመስከሩን ነው የገለጹት። 👉የመከላከያ ሠራዊቱ በጭፍራ፣ በጋሸና እና በሌሎች ግንባሮች እያደረገ በሚገኘው ተጋድሎ ይዞታውን በማስፋት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
8 226
16
🪧ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ🪧 👉እጅግ የተከበርከው የአማራ ክልል ሕዝብ ሆይ! በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን ማፍረስ ዋነኛ ቀዳሚ ዓላማ አድርጎ ይህንኑ ፍላጎቱን ለማስጠበቅ በአይነቱ የተለየ፣ በተሳሳተ ትርክትና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተጠለፈ ሕዝባዊ አሰላለፍ በመፍጠር መጠነ ሰፊ ወረራ መፈፀሙና እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል። እድሜያቸው ከ12 እስከ 65 ዓመት የሚደርሱ ወንድና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ነፍሰ ጡሮች፣ ካህናትና ሸኮች ሳይቀር እያስገደደ በማሰማራት ወደ አማራና አጎራባች የአፋር ክልሎች አዝምቷል። 👉በዚህ ወረራ ወደር የሌለው ጭካኔ በመላበስ አማራን እስከወዲያኛው አንገት ለማስደፋት በየደረሰበት አካባቢ ሴቶችን በመድፈር፣ ንጹሐንን በመረሸን፣ መሰረተ ልማቶችን በማውደም፣ የመንግሥትና የግለሰብ ሀብቶችን በመዝረፍ፣ የቤት እንሰሳትን በጥይት በመግደል ሕዝብን እያሸበረ ከቀየው እንዲሰደድ በማድረግ ላይ ይገኛል። 👉የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን የማፍረስና አማራን እንደ ሕዝብ የማጥፋት ዘመቻው ከመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት በተጨማሪ በሕዝባዊ ማዕበል መቀልበስና መደምሰስ እንዳለበት ግድ የሚል ሁኔታ ስለተፈጠረ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል። 👉ይህ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ እንደተጠበቀ ኾኖ በአማራ ክልል ደረጃ ፈጣንና የተደራጀ ሁሉ አቀፍ ሕዝባዊ ዘመቻ ማካሄድ ጊዜ የማይሰጠው እጅግ አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም እድሜውና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የክልላችን ሀገር ወዳድ ዜጋ ኹሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ማንኛውንም መሳርያና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከላት የክተት ጥሪውን ተቀብሎ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ታላቅ የሕልውና ዘመቻ ጥሪ አቅርቦልሃል። 👉ሁሉ አቀፍ የሕልውና ዘመቻውን የተደራጀ አመራር፣ በሕዝባዊ ማዕበል ተመስርቶ በእልህና በወኔ ለማከናወን የሚያስችል ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመርያ በየአካባቢው ይደርስሃል። 👉የዚህ ክተት ዘመቻ ዋነኛ ኃይላችን ለመስዋእትነት የተዘጋጀ ሕዝባችን መሆኑን የክልላችን መንግሥት ያምናል። በመሆኑም አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል የከፋ ምኞች ማምከን ብሎም የገባበት ገብቶ ለመደምሰስ የቀረበውን የጀግንነት ጥሪ በመቀበል ኢትዮጵያን ለማዳን እንዲሁም የአማራ ክልልን ሕዝብ ከውርደት ለመታደግ እንድንዘምት የክልሉ መንግሥት ጥሪውን በድጋሜ ያስተላልፋል። 👉ህልውናችንን በትግላችን እናረጋግጣለን! እናሸንፋለን! የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም ባሕርዳር፣ ኢትዮጵያ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
8 368
14
🪧ቅዳሜ ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች🪧 ✅ የመንግሥት ኮምንኬሽን አገልግሎት ከቀትር በኌላ ባወጣው መግለጫ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ ደሴ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር መሆኗን አስታውቋል። 👉 ዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች አማጺዎች ከተማዋን ተቆጣጥረዋል በማለት ያሠራጩት መረጃ ሐሰት እንደሆነም መግለጫው አክሎ ገልጧል። 👉መከላከያ ሠራዊት ደሴን ለመቆጣጠር ከኩታበር፣ ቦሩ ሥላሴ እና ሐይቅ አቅጣጫ ከተንቀሳቀሱ የሕወሃት ተዋጊዎች ጋር እየተፋለመ እንደሚገኝ የገለጠው መግለጫው፣ ስለ ውጊያው ያልተጣራ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል። ❗️ዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች የከተማዋን አንዳንድ ነዋሪዎች በእማኝነት በመጥቀስ፣ አማጺዎቹ ወደ ከተማዋ እንደገቡ፣ የመንግሥት ወታደሮች ከማለዳ ጀምሮ በከተማዋ እንደማይታዩ እና የከተማዋ ኤሌክትሪክ አቅርቦት እንደተቋረጠ ዘግበው ነበር። ✅ የመንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት የኮምንኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ ለገሠ ቱሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በወገን ጦር ውስጥ የሠራዊቱን እንቅስቃሴ በማገድ ለሕወሃት የሚሰሩ ቅጥረኛ ወይም "ባንዳ" ኃይሎች አሉ ሲሉ ከሰዋል። 👉መከላከያ ሠራዊት ከሚመራው የዕዝ ሰንሰለት ውጭ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ውጤት ሊያስገኙ እንደማይችሉ ተገንዝበው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት ቃል አቀባዩ፣ ሁሉም ወገን በመንግሥት ዕዝ ስር ውስጥ ገብቶ ሕወሃትን እንዲፋለም አሳስበዋል። ✅ አማጺው ሕወሃት ተዋጊዎቹን ከአማራ እና አፋር ክልል እንዲያስወጣ እና ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ የሚያደርገውን ግስጋሴ እንዲገታ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። 👉የሕወሃት ተዋጊዎች በከተሞች ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ከመተኮስ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መግለጫው፣ ሁሉም ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል። 👉 ለትግራይ ክልል ተረጅዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይቀርብ መንግሥት እገዳ እንደጣለ ቀጥሏል ሲል የወቀሰው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ፣ አሁንም ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ሰብዓዊ ዕርዳታ ለተረጅዎች እንዲገባላቸው እንዲፈቅዱ ጠይቋል። ✅ ፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ውጤት በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። 👉ምክር ቤቱ የሕዝበ ውሳኔውን ውጤት ያጸደቀው፣ ምርጫ ቦርድ ስላካሄደው ሕዝበ ውሳኔ እና ስለ ውጤቱ የሰጠውን ማብራሪያ አዳምጦ ከመረመረ በኋላ እንደሆነ ምክር ቤቱ አክሎ ገልጧል። 👉በሕገ መንግሥቱ መሠረት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፌደሬሽኑ 11ኛ አባል ክልል የሚሆነው፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት በመጭው ሰኞ በሚያካሂደው አስቸኳይ ጉባዔ ሥልጣኑን ሲያስረክብ ነው። የሥልጣን ርክክቡ ሲጠናቀቅ፣ አዲሱ ክልል ከደቡብ ክልል ተነጥሎ ራሱን የቻለ ክልል በመሆን ከሲዳማ ክልል ቀጥሎ ሁለተኛው ይሆናል። ✅ ፌደሬሽን ምክር ቤት በዛሬው ስብሰባው የፌደራሉን የድጎማ በጀት ድልድል እና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ቀመር ዝግጅትን በሚመለከት የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ እንዳጸደቀ ምክር ቤተ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። 👉ምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳቡን ያጸደቀው፣ የድጎማ በጀት እና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ቋሚ ኮሚቴዎች ባቀረቡት የ2014 ዓ.ም ዕቅዶች ላይ ከተወያየ በኋላ ነው። 👉ምክር ቤቱ አሁን በሥራ ላይ ያለው የድጎማ በጀት እና የጋራ ሃብት ክፍፍል ቀመርም ማሻሻያ ሳይደረግበት ባለበት እንዲቀጥል በአብላጫ ድምጽ መወሰኑንም አመልክቷል። ✅ የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል በኢትዮጵያ እንዳይንቀሳቀስ የተጣለበት እገዳ ለሁለት ወራት እንደተራዘመ ድርጅቱ በድረገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። 👉ረድዔት ድርጅቱ በመንግሥት ውሳኔ ማዘኑን ገልጦ፣ እገዳው ለምን እንደተራዘመ ለመረዳት ከባለሥልጣናት ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ ገልጧል። 👉መንግሥት ባለፈው ሐምሌ በድርጅቱ ላይ የሦስት ወር እገዳውን የጣለው፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዳሰራጨ እና ለአንዳንድ የውጭ ሀገር ዜግነት ላላቸው ሠራተኞቹ አስፈላጊውን ሕጋዊ የሥራ ፍቃድ እንዳላሟላ በመጥቀስ ነበር። ✅ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጌታ ፓሲ ዛሬ የሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክን እንደጎበኙ ኢምባሲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። 👉 አምባሳደሯ የፓርኩ ባለሃብቶች ማኅበር አመራሮችን እና የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች ሠራተኞችን ያነጋገሩ ሲሆን፣ የፋብሪካዎቹ ሠራተኞች የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ አሜሪካ የሰጠችው ዕድል ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው ለአምባሳደሯ ነግረዋቸዋል። 👉 አምባሳደር ባሲ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎቹን የጎበኙት፣ መንግሥታቸው ኢትዮጵያን ከአፍሪካው የቀረጥ ነጻ ዕድል (አጎዋ) እንደሚያግድ እያስጠነቀቀ ባለበት ወቅት ነው። ✅ ዛሬ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናዊያን ባለፈው ስምንት የተደረገውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም በመላ ሀገሪቱ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ዓለማቀፍ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። 👉ሰልፈኞቹ ከሥልጣኑ የተወገደው ሲቪል የሽግግር መንግሥት ወደ ቦታው እንዲመለስ የጠየቁ ሲሆን፣ ጸጥታ ኃይሎች ሁለት ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በጥይት እንደገደሉ ታውቋል። 👉በሰልፉ ሳቢያ በሀገሪቱ የስልክና ኢንተርኔት መስመሮች በሙሉ ተቋርጠው ውለዋል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 126
8
🪧ህወሃት ደሴን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሪያለው አለ🪧 @EthioEwuneta @EthioEwuneta
6 224
12
🪧ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ!🪧 👉በሀገር መከላከያ ሠራዊት እየተመራ ወራሪውን የሽብር ቡድንና ያሰለፈውን መንጋ እየመከተ የሚገኘው መላው የፀጥታ ኀይላችን በፀረ ማጥቃት እርምጃው ቀጥሏል። 👉በተለይ ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ወራሪ ኀይል በመመከት አኩሪ ገድልን እየፈፀመ ይገኛል። 👉ሌሊቱን ሙሉ ከተለያዩ ግንባሮች ጠጋግኖ በማሰባሰብ ደሴን ለመያዝ በኩታበር፣ ቦሩ ስላሴና በኀይቅ መስመር የመጣውን ወራሪ መንጋ የፀጥታ ኀይላችን በታላቅ ጀብዱ መክቶታል። አሁንም ደሴና አካባቢዋ በፀጥታ ኀይላችን ስር ነው። 👉ቀደም ብለውም ስደተኛ በመምሰልና የመከላከያ ኀይላችንን ወታደራዊ አልባሳት ለብሰው ሊዘርፉ የሞከሩ ቡድኖችና በከተማዋ የሚኖሩ ለጥፋት ኀይሉ የሚሰሩ ባንዳዎች ከትናንት ጀምሮ የጁንታውን ዓላማ ለማስፈፀም ከግንባር ውጊያው ባልተናነሰ ሲሰሩ ውለዋል። 👉የደሴ ወጣቶችና መላው የፀጥታ ኀላችንም ይህንን ኀይል በተደራጀ መንገድ እየመከቱት ይገኛሉ። የከተማዋ ወጣቶችም በጀመሩት መንገድ ከተማቸውን ከባንዳ የመጠበቅ ተግባራቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል። 👉ያለውን ኀይል ሁሉ አሰባስቦ በዚሁ ግንባር ያመጣው የሽብር ቡድኑ በጦር ግንባር ያቃተውን በወሬ ለማግኘት አሁንም መፍጨርጨሩን ቀጥሏል። አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙኀንም የሽብር ቡድኑን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ። 👉በወሬ የሚያዝ ከተማ የለም ሊኖርም አይችልም ብሎ መላው ሕዝብ በደሴ ከተማ ዙሪያ ለሚነሳው አሉባልታ ጆሮ ሳይሰጥ አሁንም የሀገሩን ህልውና ለማስከበር የሚያደርገውን ተጋድሎ ቀጥሏል። 👉በዚሁ አጋጣሚ በተለይ ያልተጣራ መረጃን በመያዝ ሕዝብን ለማሸበር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙና የሽብር ቡድኑ መጠቀሚያ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግሥት ያሳስባል። የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
5 644
5
🪧በመዲናዋ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ የእሳት አደጋ ደርሷል🪧 ✅በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ጸጋ አብ ህንጻ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል። 👉የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች አካባዎች እንዳይዛመት÷ የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ወጣቶች ከፍኛ ርብርብ እያደረጉ ነው፡፡ 👉የእሳት አደጋውን መንስኤ እንዲሁም በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ እንደሚገልጽ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
5 425
0
🪧ዓርብ ጥቅምት 19/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች🪧 ✅ የፌደራል እና ክልል መንግሥታት የሕግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ ዛሬ በባሕርዳር ከተማ ተወያይቶ ባወጣው መግለጫ የአማጺው ሕወሃትን መጠነ ሰፊ ጥቃት በመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት መቀልበስ እንደማይቻል አስታውቋል። 👉የሕወሃትን መጠነ ሰፊ ጥቃት በሕዝባዊ ኃይል እንዴት መመከት እና መቀልበስ እንደሚቻል በጥልቀት መወያየቱን የገለጠው መድረኩ፣ ሕወሃት-መራሹ ጦርነት ሕዝባዊ ጦርነት በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት እና ከክልል ልዩ ኃይሎች ጎን ተሰልፎ ለሀገሪቱ ሕልውና እንዲታገል ጠይቋል። 👉መድረኩን የመሩት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሲሆኑ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች ባለሥልጣናት ተሳትፈውበታል። ✅ ከአማጺው ሕወሃት ተዋጊዎች ከደሴ ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘውን የወሎ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንደተቆጣጥሩ አድርገው ያስወሩት ወሬ ሐሰት ነው ሲል የመንግሥት ኮምንኬሽን አገልግሎት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። 👉 ቦሩሜዳን ጨምሮ ከደሴ ከተማ ራቅ ያሉ አንዳንድ ቦታዎች በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር እንደሆኑ መግለጫው አክሎ ገልጧል። 👉 በደሴ ከተማ አቅራቢያ ከባድ ውጊያ እየተደረገ እንደሆነ ዓይን እማኞችን ጠቅሶ የዘገበው ደሞ ዶይቸቨለ ነው። 👉ውጊያው ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው ወሎ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንደሆነ እና የተኩስ ልውውጡ እስከ ከተማዋ ድረስ እንደሚሰማ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ✅ የአማጺው ሕወሃት ተዋጊዎች በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ ደሴ በመኖሪያ ሠፈሮች ላይ ትናንት ከቀትር በኋላ በተኮሷቸው መድፎች አንድ ሰው እንደሞተ የደሴ ከተማ ከንቲባ አበበ ገ/መስቀል ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል። 👉አማጺዎቹ በሦስት የተለያዩ የከተማዋ ሠፈሮች ላይ የተኮሱት አምስት መድፎችን ሲሆን፣ በጥቃቱ ሌሎች ሦስት ሰዎች እንደቆሰሉ ከንቲባው አስታውቀዋል። ✅ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን የሀገር ውስጥ ኤፍኤም ሬዲዮዎች በውጭ ሀገራት የሚዘጋጁ የሬዲዮ ሥርጭቶችን በትስስር ዘዴ በሀገር ውስጥ ማሰራጨት እንዳይችሉ ከዛሬ ጀምሮ እገዳ እንደጣለ ለኢዜአ ተናግሯል። 👉 እገዳው የተጣለው፣ በውጭ ሀገራት የሚዘጋጁ የሬዲዮ ፕሮግራሞች የሀገሪቱን ሕጎች እና ደንቦች ተከትለው እንደማይሰሩ እንዲሁም የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም እና ነባራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ከግምት እንደማያስገቡ በመግለጽ ነው። 👉 በሕጉ መሠረት ለጣቢያዎቹ ግብረ መልስ እና እርምቶችን መስጠት የሚችልበት ሁኔታ አለመኖሩም ሌላኛው የእገዳው ምክንያት እንደሆነ ባለሥልጣኑ አክሎ ገልጧል። ✅ ፍትህ ሚንስቴር እና ፌደራል ፖሊስ የሕወሃት ተዋጊዎች በአማራ እና አፋር ክልሎች ነዋሪዎች ላይ የፈጸሟቸውን ወንጀሎች የሚመለከት ሪፖርት ዛሬ ይፋ እንዳደረጉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። 👉 አማጺዎቹ ከተቆጣጠሯቸው በኋላ በኃይል በለቀቋቸው የሰሜ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እና የአፋር ክልል አንዳንድ ወረዳዎች ከሐምሌ ጀምሮ 482 ሰዎችን እንደገደሉ፣ በ165 ሰላማዊ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንዳደረሱ እና 109 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን እንደፈጸሙ በመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ እንደተረጋገጠ መግለጫው አመልክቷል። 👉ከተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች መካከል ጨቅላ ሕጻናት፣ ሴቶች እና ሽማግሌዎች ይገኙበታል ተብሏል። ✅ ትናንት በመቀሌ ከተማ አቅራቢያ በተፈጸመው የአየር ድብደባ የሟቾች ቁጥር ወደ 10 እንዳሻቀበ ዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች የሕወሃት ምንጮችን ጠቅሰው ዘግበዋል። 👉 በጥቃቱ የቆሰሉት ሰዎች ደሞ 21 ናቸው ተብሏል። የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ በበኩላቸው፣ የአየር ድብደባው መኖሪያ ሠፈሮችን ዒላማ እንዳላደረገ ለአዲስ ስታንዳርድ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። 👉 በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚዘዋወሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ የሚታዩ የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች ምስሎች በትክክል ከመቀሌ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ አይቻልም- ብለዋል ቃል አቀባዩ። ✅ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም የዓለም ጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር በዋና ዳይሬክተርነት ለመምራት ብቸኛ ዕጩ መሆን መቻላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። 👉ዶ/ር ቴዎድሮስ ድጋሚ ዕጩ እንዲሆኑ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ኬንያን ጨምሮ 28 ሀገራት እንደጠቆሟቸው ዘገባው አመልክቷል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ምርጫ የሚካሄደው በቀጣዩ ግንቦት ነው። ✅ በሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ (አሚሶም) በማዕከላዊ ሱማሊያ "አህሉ ሱና ዋልጃማ" የተባሉት የሱፊ እስልምና ተከታይ ሚሊሻዎች ከመንግሥት ወታደሮች ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ለመንግሥት ወታደሮች ድጋፍ አድርጓል መባሉን አስተባብሏል። 👉የቀጣዩን ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊነት ለማረጋገጥ በጋልሙዱግ ክልል ዱሳመረብ ከተማን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ጸጥታ ኃይሎቹን ማሠማራቱን ባወጣው መግለጫ የጠቆመው አሚሶም፣ ለሱማሊያ መንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ወታደራዊ ድጋፍ የማደርገው የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት እና አፍሪካ ኅብረት አልሸባብን እንድዋጋ በሰጡኝ የሥልጣን ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ ነው ብሏል። 👉 ሚሊሻዎቹ ከሱማሊያ መንግሥት እና ከጋልሙዱግ ክልል ታጣቂዎች ጋር ከዕሁድ ጀምሮ ለ3 ቀናት ባካሄዱት ውጊያ 120 ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ዓለማቀፍ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
6 403
17
✅በምግብ አልተመረዙም 🪧በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በምግብ ተመርዘዋል ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰት ነው ተባለ።🪧 ✅ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው የወደቁ ሲሆን ሌሎች ተማሪዎች ልጆቹን በማየታቸው የህመም ስሜት ተሰምቷቸዋል። 👉የወደቁትንና ሌሎች ተማሪዎችን ጨምሮ ወደ ህክምና በመውሰድ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ የምግብ መመረዝም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ህመም ስላልተገኘባቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። 👉ከምግብ መመረዝ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ችግር የሌለ በመሆኑ የተማሪ ወላጆች እንዲረጋጉ እና በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለሉ እንገልፃለን ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። 👉ጡሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በበኩሉ ለህክምና 98 ተማሪዎች የመጡ ሲሆን ምርመራ ከተደረገላቸዉ ሴት 47 እና 51 ወንድ በአጠቃላይ 98 ተማሪዎች የመደንገጥና ከመጠነኛ ማስታወክ ስሜት ዉጭ የከፋ ኬዝ አለመኖሩን ነገር ግን ሁለት ተማሪዎች ብቻ መጠነኛ ህመም እንዳጋጠማቸው አሳውቋል። 👉የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሳምሶን ጉታ እንደገለጹት ክስተቱ ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ አለመሆኑን እና የሞተ ተማሪ አለመኖሩን ገልፀዋል። 👉ዶ/ር ሳምሶን ወደ ሆስፒታሉ የገቡ ተማሪዎች ምርመራ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ሁሉም ተማሪዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
6 480
6
🪧ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።🪧 ✅ይህ የሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም የፌስቡክ ገፅ አይደለም! 👉ከ9,900 በላይ ተከታዮች ያሉትና በሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈተ የፌስቡክ ገጽ መኖሩን ተመልክተናል። 👉"ብናልፍ አንዷለም - Binalf Andualem Official” የሚል ስያሜ ያለው ይህ ገጽ የተለያዩ መልዕክቶችን የሚለጥፍ ሲሆን በርከት ያሉ ሰዎች የመልዕክቶችን የስክሪን ቅጅ (screenshots) በትዊተርና በፌስቡክ አካውንቶቻቸው ሲያጋሩም አስተውለናል። 👉ገፁ በትናንትናው እለትም " ዘማቾችን በተመለከተ" የሚል በምስሉ ላይ የሚታየውን አነጋጋሪ ፅሁፍ አጋርቶ ብዙዎችን ግራ እያጋባ ይገኛል። 👉በፌስቡክ የገጽ ግልጽነት (Page Transparency) አገልግሎት እንደተመለከትነው ይህ የፌስቡክ ገጽ በታህሳስ ወር 2013 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ግለሰቦች ይቆጣጠሩታል። 👉ኢትዮጵያ ቼክ የገጹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አቶ ብናልፍ አንዷለምን የጠየቀ ሲሆን ገጹ የእርሳቸው አለመሆኑን አስታውቀዋል። ገፁ የርሳቸው እንዳልሆነ ከሁለት ሳምንት በፊት ኢትዮጵያ ቼክ መረጃ አጋርቶ ነበር። አቶ ብናልፍ ምንም አይነት የፌስቡክ አካውንት እንደሌላቸውም ጨምረው ገልጸዋል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
5 866
3
🪧ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ የዘረፉ ሶስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ🪧 ✅ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ የዘረፉ ሦስት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን በፈፀሙ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ 👉ተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም ተገልጿል፡፡ 👉የተደራጁ ዘራፊዎች ጥቅምት 17 ቀን ለ18 አጥቢያ 2014 ዓ.ም ሌሊት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ከሚገኝ የሕብረት ባንክ ሲ ኤም ሲ ቅርጫፍ ውስጥ ነው ከአንድ የባንኩ የጥበቃ ሰራተኛ ጋር በመመሳጠር አንደኛውን ጥበቃ በመደብደብ ፣ በማፈን እና እጅና እግሩን በማሰር የዘረፋ ወንጀል ፈፅመው የተሰወሩት፡፡ 👉ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት አስፈላጊውን መረጃ በመለዋዋጥ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ በተፈፀመ በሰአታት ጊዜ ውስጥ ሦስቱን ወንጀል ፈፀሚዎች ከዘረፉት 2 ሚሊየን 100 ሺህ 969 ብር ፣ 900 ዶላር ፣ 65 ድርሃም እንዲሁም 8 ሞባይሎች እና ግለሰቦቹ ለወንጀል ድርጊት ከተጠቀሙበት ኮሮላ መኪና ጋር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ 👉የሕብረት ባንክ የሲ ኤም ሲ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አቤኔዘር ጥሩነህ÷ ለአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
6 655
5
🪧መቀሌ ኵሃ አካባቢ የሚገኘው የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም በአየር ኃይል ተመታ🪧 ✅ዛሬ መቀሌ ኵሃ አካባቢ የሚገኘው የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም በአየር ኃይል ተመቷል፡፡ 👉ይህ ተቋም በአሁኑ ወቅት በርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እየሰለጠኑበት ያለ ተቋም መሆኑን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
10 100
10
🪧በምዕራብ ግንባር የጠላት ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በአየር ተመታ🪧 ✅በምዕራብ ግንባር የጠላት ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በዛሬው ዕለት መመታቱን ምንጮች መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ምንጭ፦ ኢዜአ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
11 070
15
🪧የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ ሆነ።🪧 ✅የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ መሆኑን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል። 👉ማዕከሉ ለአሸባሪው ቡድን ወታደራዊ ሥልጠና ከመዋሉ በፊት የኢፌዴሪ መከላከያ ማሠልጠኛ ማዕከል እንደነበርም ተገልጿል። 👉በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ቡድን በዚህ ተቋም ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የሚሠጥበት፤ የውጊያ ግንኙነት ኔትወርክ ያለበት መሆኑን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አመላክቷል። 👉ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
12 579
11
🪧 ሐሙስ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች🪧 ✅በትግራይ ክልል ባሉ ባንኮች የባንክ ሒሳብ የከፈቱ ግለሰቦች ሒሰባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ተሰማ። 👉 የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው ደንበኞች ወደ ንግድ ባንኮች በመሄድ፣ ማመልከቻ በመጻፍ፣ ቅጽ በመሙላት እና መታወቂያና የባንክ ደብተራቸውን በማቅረብ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ አንድ የንግድ ባንክ ሃላፊ ተናግረዋል። 👉 የአንድ የግል ባንክ ሃላፊ ግን ስለጉዳዩ እስካሁን መረጃ እንደሌላቸው ገልጠዋል። 👉የትግራዩ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ እገዳው የተጣለው፣ ለጸጥታ ስጋት የሚሆን ገንዘብ እንዳይዘዋወር ለመግታት ሲባል እንደሆነ ተገልጦ ነበር። ✅ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ በመቀሌ ከተማ ሌላ የአየር ድብደባ እንደፈጸመ የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። 👉የዛሬው ድብደባ ዒላማ ከመቀሌ አቅራቢያ የሚገኘው እና የሕወሃት ታጣቂዎች ማሰልጠኛ የሆነው የቀድሞው የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ጣቢያ እንደሆነ ለገሠ አክለው ገልጸዋል። 👉 የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ግን አውሮፕላኑ በከተማዋ ላይ በተደጋጋሚ ቢያንዣብብም ምንም ዒላማ ሳይመታ ቀርቷል በማለት አስተባብለዋል። ✅ ለሀገራት የውጭ ዕዳ የመክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣው "ሙዲ" የተባለው ዓለማቀፍ ኩባንያ የኢትዮጵያን ደረጃ እንደገና ባንድ ደረጃ ዝቅ እንዳደረገው ብሉምበርግ ዘግቧል። 👉ለሀገሪቱ ደረጃ ዝቅ ማለት ምክንያቱ፣ በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና በሀገሪቱን የዕዳ ስረዛ ወይም መክፈያ ጊዜ ላይ የታሰበው ሽግሽግ በመዘግየቱ እንደሆነ ድርጅቱ ገልጧል። 👉ከ5 ወር በፊት ድርጅቱ የሀገሪቱን ደረጃ Caa1 በተባለው ምድብ ውስጥ አስቀምጦት የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ወደ Caa2 ዝቅ አድርጎታል። ✅ የሕወሃት ተዋጊዎች የከፈቱትን መጠነ ሰፊ ወረራ መመከት የሚቻለው የተደራጀ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር ነው ሲል የመንግሥት ኮምንኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። 👉ሕወሃት በአማራ ክልል በውጫሌ፣ ተሁለደሬ፣ ወረባቦ፣ ድላንታ እና ጭፍራ በተባሉ አካባቢዎች ጦርነት እንደከፈተ የገለጸው መግለጫው፣ ከጦርነቱ ቀጠና ውጭ ያለው ኅብረተሰብ በግንባር ለሚደረገው ተጋድሎ አጋርነቱን እና ደጀንነቱን እንዲያሳይ ጠይቋል። 👉በተያያዘ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የክልሉ የመንግሥት እና የግል ታጣቂዎች በሙሉ ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጥሪ ማድረጋቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። 👉የሕወሃት ጥቃት በአማራ ክልል ላይ ብቻ ተገድቦ እንደማይቀር የጠቀሱት ይልቃል፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሕልውናው እንዲረባረብ ጠይቀዋል። ✅ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የምትገኘው ሐይቅ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር እንደሆነች የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። 👉ከተማዋን የሕወሃት ታጣቂዎች ትናንት እንደተቆጣጠሯት ገልጸው ነበር። ✅ ዓቃቤ ሕግ በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ላይ ለሁለተኛ ቀን ሊያሰማ የነበረውን የምስክር ማሰማት ሂደት ዛሬ እንዳላካሄደ ሪፖርተር ዘግቧል። 👉የምስክር ማሰማት ሂደቱ ሊቀጥል ያልቻለው፣ እስክንድር በወህኒ ቤት ውስጥ ድብደባ ስለተፈጸመበት እና ችሎት ለመቅረብ ፍቃደኛ ባለመሆኑ እንደሆነ የወህኒ ቤቱ የፈረቃ ሃላፊ ለችሎቱ ተናግረዋል። 👉 የምስክር ማሰማቱ ሂደት ሰኞ እንደሚቀጥል ችሎቱ ገልጧል። ✅ የኔዘርላንድ ዓቃቤ ሕግ ኤርትራዊውን ሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪ ኬዳኔ ዘካሪያስን ከተፈላጊ ወንጀለኞች ዝርዝር ውስጥ እንዳካተተው የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል። 👉ተፈላጊው ኪዳኔ ኤርትራዊያን ስደተኞች በሕገወጥ ደላሎች አማካኝነት በሜድትራኒያን ባሕር በኩል በጀልባ ወደ አውሮፓ እንዲሻገሩ በማስተባበር ወንጀል የሚጠረጠር ሲሆን፣ በሊቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የሚታጎሩበትን ጣቢያ እንደሚመራም ይነገራል። ኪደኔ አምና ከኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ካመለጠ ወዲህ የት እንደገባ እስካሁን አልታወቀም። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
9 894
15
🪧በመቀለ በቀናት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ የአየር ድብደባ መፈጸሙ ተነገረ🪧 ✅በሁለት ቀናት ልዩነት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የአየር ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ። 👉 ከዓይን እማኞች እንዳተጣራው ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ከአራት ሰዓት በኋላ የተፈጸመው የአየር ድብዳባ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ በተባለው ተቋምና በአንድ የአውቶብስ መናኸሪያ አቅራቢያ እንደሆነ ተናግረዋል። 👉ሮይተርስ የዜና ወኪል በክልሉ የሚገኝ ቴሌቪዥን ጣቢያን እንዲሁም አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ደግሞ የረድኤት ተቋማት ምንጮችን ጠቅሰው የአየር ጥቃት ስለመፈጸሙ ዘግበዋል። 👉 ከአገር መከላከያ ቃል አቀባይ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። 👉በተመሳሳይ ሮይተርስ የዜና ወኪል በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናትን አስተያየትን ለማካተት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት አመልክቷል። ✅ይሁን እንጂ የመንግሥት የወቅታዊ መረጃ አጣሪ በትዊተር ገጹ ላይ የአገር መከላከያ የአየር ጥቃት ዒላማዎች የህውሓት ጦር መሳሪያ ማምረቻ እና መጠገኛ ስፍራዎች ናቸው ብሏል። 👉መረጃ አጣሪ ቡድኑ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ባጋራው መረጃ መከላከያ ኦፕሬሽኖች ዒላማ ከባድ መሳሪያ ማከማቸው ስፍራዎችን ማውደም ነው ብሏል። 👉በህወሓት የሚተዳደረው ቴሌቪዥን ጣቢያም ረቡዕ ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ ተዋጊ ጀቶች በመቀለ ከተማ የአየር ድብደባ ማድረጋቸውን ዘግቧል። 👉ከዚህ በተጨማሪም በመቀለ ከተማ የአየር ድብደባ መፈጸሙን ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት ክንደያ ገብረሕይወት በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፈረዋል። 👉የአየር ድበደባውን የሚያሳዩ ናቸው የተባሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በስፋት እየወጡ ይገኛሉ። 👉የዛሬው የአየር ጥቃት ኢላማ ነበሩ ከተባሉት አንዱ መስፍን ኢንደስቱሪያል ኢንጂነሪንግ ኤፈርት የተባለው ኢንዶውመንት ፈንድ አካል በመቀለ ከተማ የሚገኝ ግዙፉ ተቋማ ነው። 👉ምንጮች ዛሬ በቀናት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ ተፈጽሟል በተባለው የአየር ጥቃት የደረሰውን ጉዳት በተመለከተም እስካሁን ያሉት ነገር ባይኖርም የህውሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በአየር ጥቃቱ መኖሪያ ስፍራዎች ዒላማ ተደርገዋል ብለዋል። 👉ከትናንት በስቲያ ሰኞ በተመሳሳይ የኢትጵያ አየር ኃይል በመቀለ የአየር ድበደባ አድርጎ እንደነበረ ይታወሳል። 👉በዚህ የአየር ጥቃት የ3 ሰዎች ሕይወት ስለማለፉ የህወሓት ባለስልጣን፣ የረድኤት ሠራተኛ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጸው ነበር። 👉ይህን የአየር ድበደባ በተመለከተ የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ሐሰት ነው ቢሉም ዘግይቶ መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አየር ኃይሉ ድበደባ መፈጸሙን ዘግቧል ነበር። 👉የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዘገባው የአየር ኃይሉ ዒላማዎች ህወሓት ይጠቀምባቸዋል ያላቸው የመገናኛ አውታሮችና መሳሪያዎች መሆናቸውን እና በጥቃቱ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል ብሏል። 👉በሰኞው ዕለት የአየር ጥቃቱ ዒላማ የነበሩት ህወሓት ይጠቀምባቸዋል የተባሉ የመገናኛ አውታሮችና መሳሪያዎች መሆናቸውን እና በጥቃቱ "ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎ ይህም በተሳካ ሁኔታ ተፈጽሟል" ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቦ ነበር። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
9 395
12
🪧በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡🪧 ✅በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ 👉በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡ 👉በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ 09/02/21014 ዓ.ም እስከ 12/ 02/2014ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ✅ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
8 953
18
🪧ስራ Berhan Insurance🪧 ✅JUNIOR ACCOUNTANT ✅JOB OVERVIEW 👉Salary Offer:As per Company Scale 👉Experience Level: Junior 👉Total Years Experience:0 Deadline Date:October 17, 2021 Date Posted: October 26, 2021 ✅JOB REQUIREMENT 👉Educational Qualification: BA Degree in Accounting, and Accounting & Finance or in related fields from a recognized University or College 👉 Experience: 0 years of relevant work experience. 👉Place of work: Addis Ababa ⚠️HOW TO APPLY 👉NB: Only short listed candidates will be communicated. Interested and qualified applicants may submit their application letter, curriculum vitae and other credentials in person or through the following addresses within 7 (seven) working days from the date of this announcement ✅Address: Berhan Insurance S.C. at Bole Wollo sefer Square Garad Building 7th floor, in front of TK building.PO Box 9266, Addis Ababa 👉Email: [email protected] (Email applicants must enclose their document with a single PDF format & write the position they are applying for, on the subject line @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
9 203
53
🪧ከአማራ ክልል መንግሥት የተሰጠ መግለጫ🪧 ✅የአማራ ሕዝብ ኅልውና ጸንቶ የሚኖረው በአሸባሪው ትሕነግ መቃብር ላይ ነው ሲል የአማራ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ። 👉የክልሉ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል። የአማራ ሕዝብ ህልውና ጸንቶ የሚኖረው በአሸባሪው ትህነግ መቃብር ላይ ነው። የጀመርነውን የህልውና ዘመቻ ሳንቋጭ ሀሳብና ተግባራችን ከዓላማና ግባችን መንቀል ከፍተኛ ዋጋ እንዳያስከፍለን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። የህልውና ዘመቻው ተገደን የገባንበት እንደህዝብ የመኖርና ያለመኖር መጻኢ እጣፋንታችን የምንወስንበት እንጂ የፓለቲካ ማሳለጫ አይደለም። ሊሆንም አይችልም። ፓለቲካም ይሁን ስልጣን ህዝብና አገር ከመኖራቸው በሗላ የሚታሰቡ እና የሚመጡ ናቸው። ያለህዝብና ያለአገር የሚኖር ፖለቲከኛም ሆነ ስልጣን አይኖርም። አይታሰብምም። በአማራ ህዝብ ላይ እያንዣበበ ያለው የህልውና አደጋ፤ አደጋ ብቻ አይደለም። ለክልሉ መንግስት ይሁን የአማራ ህዝብ "ከህልውና ዘመቻው" የሚቀድም አንዳች አጀንዳ አይኖረውም። በሴራና በተንኮል ጥርሱን ነቅሎ ያደገው አሸባሪው ቡድን የእድሜ ልክ ምኞቱና ፍላጎቱ በስውር የአማራን ህዝብ አንገት ማስደፋት እና ማህበራዊ እረፍት መንሳት ነበር። ይህ በሴራ ተጠንስሶ በሴራ ተወልዶ የኖረን ቡድን ከዘመናት ሴራና ተንኮሉ ባሻገር በግላጭ በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ ፈጽሟል። በክልሉ በግልጽ ወረራ በፈጸመባቸው በሰሜን ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ በከፊል ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ቁጥሩ በውል የማይታወቅ የአማራ ህዝብ በጅምላ ተጨፍጭጭፏል። ለዘመናት ለፍቶ ፣ ጥሮና ግሮ ያፈራው ሀብትና ንብረቱን በወራሪው ሀይል ተዘርፏል፤ ወድሟል። የመንግሥት እና የግል አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ዘርፏል። ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ የአማራ ህዝብ ከሞቀ ሀብትና ንብረቱ ተፈናቅሎ ለአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ተዳርጓል። ከሕጻን እስከ እርጅና የእድሜ ደረጃ የሚገኙ እህቶቻችን በዚህ አሸባሪ ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍረዋል። አሁንም የሚፈጽመው ወረራ፣ ዝርፊያና ጭካኔ የተሞላበት ጅምላ ጭፍጨፋው እንደቀጠለ ነው። ለዚህ አሸባሪና ወራሪ ቡድን ጊዜ በተሰጠው ቁጥር ችግሩና ጥፋቱ ከዚህም የከፋ ይሆናል። ከጦርነት ቀጣናው ባሻገር ባሉና አማራ በሚኖርባቸው በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በደቡብ ክልል ማንነትንና ቋንቋን መሠረት ያደረገ ግድያና መፈናቀል የሚመነጨው ከዚሁ አሸባሪ ቡድንና የእርሱ ተላላኪ ባንዳዎች መሆኑን መናገር ደግሞ ለቀባሪ ማርዳት ነው። ዛሬም ሆነ ትናንት በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ የሚፈጠሩ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጅምላ ግድያዎች እና ግጭቶች ተዋናይ፣ አጋፋሪውና መሪው ከዚህ የጥፋት ቡድን የሴራና ተንኮል መንገድ የሚመነጩ እና የተቀዱ ናቸው። አሸባሪው ትህነግና ግብረ አበሮቹ ከኢትዮጵያ ምድር እስከወዲያኛው እስካልተነቀሉ ድረስ የአማራ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ህልውና በጽኑ መሰረት ላይ አይቆምም። ከዚህ አኳያ የአማራ ህዝብ ህልውናም ሆነ የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚረጋገጠው ትህነግ መቃብር ላይ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለበትም። ስለሆነም በአሸባሪው ቡድን እኩይ ተግባር ምክንያት ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ በጋራ መረባረብ ይኖርብናል። የሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን ወሎና የዋግኽምራ ህዝብ ከወራሪው ቡድን ነጻ ለማውጣት በሚደረገው ትግል መሳሪያ ያለው በመሳሪያው፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ትርፍ ሀብትና ንብረት ያለው በገንዘቡ፣ ሐሳብ ያለው በሐሳቡ ከአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ከሚሊሺያና ፋኖ ጎን በመሰለፍ የአሸባሪውን ቡድን ግብአተ መሬት ማረጋገጥ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም የአማራ ህዝብ ህልውናም ሆነ የሀገራችን ሰላም የሚረጋገጠው በአሸባሪው ትህነግ መቃብር ላይ ነው! @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
9 632
12
🪧በሰሜን ሸዋ ዞን የተቃጠለው የጤፍ ክምር🪧 ✅በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በተፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው እህል መውደሙ ተገለፀ፡፡ 👉በዞኑ ኤፍራታ ግድም ወረዳ በማጀቴ አካባቢ ነዋሪ በሆኑ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ከትናንት በስቲያ ሌሊት በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ነው ጉዳቱ የደረሰው፡፡ 👉የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለ#ኢፕድ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ከወቅታዊ የአገሪቷ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በዞኑ ስጋቶች ስለነበሩ እንደ ዞን አቅጣጫ ተሰጥቶ የተለያዩ የጸጥታና ደኅንነት ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይቷል፡፡ በዋናነትም ከአርሶ አደሩ አንፃር የተሰበሰቡ ሰብሎች ማሳ ላይ እንዳያድሩና ከአደሩም ስምሪት ተሰጥቶ እንዲጠበቁ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል። 👉ይሁን እንጂ ጥቅምት 3 ተረኛ የነበሩና የጥበቃ ስራን እንዲያከናውኑ ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት በስፍራው ባልተገኙበት ሁኔታ አደጋው መድረሱንም አሳውቀዋል፡፡ 👉ይህንን ክፍተት ተጠቅመው ማንነታቸው ያልታወቀ ጉዳት አድራሾች የአርሶ አደሮችን ሰብል አቃጥለዋል ነው ያሉት አስተዳዳሪው፤ ትክክለኛውን መረጃ ለማጣራት የአጎራባች ወረዳ አካላትና መርማሪ የፖሊስ አባላት የተቀናጀ የምርመራ ሥራ እያከናወኑ ነው ብለዋል፡፡ 👉የማጀቴ ከተማ መሪ ማዘጋጀ ህንፃ ሹም ኃላፊ ያለው አየለ በበኩላቸው በጥቃቱ የበርካታ አርሶ አደሮች የጤፍ ክምር ተቃጥሏል፤ ይህም በገንዘብ ሲተመን ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ይደርሳል ብለዋል። 👉እስካሁን ባለው መረጃ ከ95 ኩንታል በላይ ጤፍ እንደተቃጠለ የተነገረም ሲሆን በቀጣይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል፡፡ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 975
5
🪧ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ገበያ እንዲወጣ የተባለው የአፕል ጭማቂ🪧 ✅በደቡብ አፍሪካ የሚመረተው ሲረስ የተባለው ታሸገ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ከሰባት የአፍሪካ አገራት ገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉ ተዘግቧል። 👉የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በበኩሉ ሲረስ አፕል ጁስ የተሰኘው ጭማቂ "በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት" ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ አውጥቷል። 👉ባለስልጣኑ ስለተገኘው መርዛማ ንጥረ ነገር በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በኩል በሰጠው ማብራሪያ በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን ከሚባል ከሻጋታ የሚመነጭ መሆኑን አመልክቶ ኅብተሰቡ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም መክሯል። 👉በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመርቶ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚሰራጨው ሲረስ የአፕል ጭማቂ በመበስበስና በመሻገት የሚከሰተው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር ስለተገኘበት ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። 👉በጭማቂው ላይ በተደረገ ቤተ ሙከራ ፍተሻ እንደተረጋገጠው ሲረስ በተባለው የአፕል ምርት ላይ በአንድ ሊትር ውስጥ እንዲኖረው ከተፈቀደው 50 ማይክሮ ግራም ከፍ ያለ መጠን መገኘቱ ተገልጿል። 👉ይህ የማይኮቶክሲን ውጤት የሆነው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር በአፕል እና በአፕል ምርቶች ውስጥ በሚከሰቱ በተለያዩ ሻጋታዎች አማካይነት የሚፈጠረው። 👉በጭማቂው ውስጥ የተገኘው ንጥረ ነገር ፓቱሊን በተጠቃሚዎች ላይ ማቅለሽለሽና ማስታወክን በማስከተል ጤናን ሊያውክ ይችላል ተብሏል። 👉ይህ ሲረስ የተባለው የአፕል ጭማቂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አመልክቶ ኅብረተሰቡ እንዳይ ጠቀመውና በገበያ ላይ ከተገኘም ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል። 👉ምርቱ በተጨማሪም በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በዛምቢያ፣ ዚምብብዌ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሞሪሺየስ ገበያዎች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገን ተነግሯል። 👉የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና (ኮሜሳ) የንግድ ውድድር ኮሚሽን በአገራቱ ውስጥ ያሉ የምርቱ ተጠቃሚዎች ባለፈው ሰኔ ወር ተመርተው የተሰራጩ የሲረስአፕል ጭማቂ ምርቶችን ከገበያ አስወጥተው ለአምራቹ እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 844
16
6 778
3
🪧 ረቡዕ ጥቅምት 3/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች🪧 ✅ የሰሜኑ ጦርነት ወደ አፋር ክልል ተዛምቶ ሐሮ እና ጭፍራ በተባሉ አካባቢዎች ውጊያ እየተደረገ መሆኑን የአማጺው ሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ ተናግረዋል። 👉በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ አቅራቢያም ውጊያ እንዳለ ጌታቸው ተናግረዋል። የኤርትራ ወታደሮች በአፋር ክልል በርሃሌ ከተማ አቅራቢያ በውጊያ እየተሳተፉ እንደሆነ የተናገሩት ደሞ የረድዔት ድርጅት ምንጮች ናቸው። 👉ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ስላገረሸው ውጊያ ያለው ነገር የለም። ✅ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ብሄር ተወላጆች የፌደራል መንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ባስቸኳይ ከጥቃት እንዲታደጓቸው መጠየቃቸውን የአማራ ክልል ብዙኀን መገናኛ ኮርፖሬሽን ዘግቧል። 👉 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በብሄሩ ተወላጆች ላይ ከመስከረም 30 ጀምሮ እስከዛሬው ዕለት ድረስ ግድያ እየፈጸሙ እንደሆነ ከጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። 👉የአካባቢው አስተዳደር ከጥቃቱ እንዲታደጋቸው ላቀረቡት አቤቱታ ምላሽ እንዳልሰጣቸው ነዋሪዎቹ ገልጠዋል። ✅ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ ማሞ ምኅረቱ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን ከአፍሪካ የቀረጥ ነጻ ንግድ ተጠቃሚነት እንዳታግድ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት ላይ በጻፉት መጣጥፍ ተማጽነዋል። 👉አሜሪካ በኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ላይ ቅሬታ ቢኖራትም፣ ኢትዮጵያን ከቀረጥ ነጻ ንግድ ተጠቃሚነቷ ማገድ ግን አጣብቂኝ ውስጥ ባለው የሀገሪቱ አምራች ዘርፍ ሕልውና ላይ ከባድ አደጋ ይደቅናል ብለዋል። 👉ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የትግራዩ ጦርነት ባስቸኳይ ካልቆመ፣ ኢትዮጵያን ከነጻ ንግዱ ተጠቃሚነት እንደሚያግዱ በቅርቡ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል። 👉ማሞ ግን እገዳው ከተጣለ ከትግራዩ ግጭት ጋር አንዳችም ግንኙነት በሌላቸው ተራ ኢትዮጵያዊያን ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ✅ በአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የተመራ ከፍተኛ ዓለማቀፍ መድረክ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ተፋላሚዎች ባስቸኳይ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ማሳሰቡን የብሊንከን ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። 👉በምክክሩ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አውሮፓ ኅብረት፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ጀፍሪ ፊልትማን፣ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ እና የኢጋድ ሊቀመንበር የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ ተሳትፈዋል። 👉ተወያዮቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ ግጭቱን በሰላም ለመፍታት እያሳዩት ያለውን ቅንጅት ያደነቁ ሲሆን፣ ግጭቱ ባስቸኳይ በድርድር ላይ ወደተመሠረተ ተኩስ አቁምና ሁሉን ዓቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት ማምራት እንዳለበት አሳስበዋል። ✅ የአማጺው ሕወሃት ጦር አዛዥ ጀኔራል ጻድቃን ገ/ኪዳን በሕወሃት እና መከላከያ ሠራዊት መካከል ሰሞኑን የተጀመረው ውጊያ በቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል ብለው እንደሚጠብቁ ለኒውዮርክ ታይምስ ተናግረዋል። 👉 ጦርነቱ ከፍተኛ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ አንድምታ ይኖረዋል- ብለዋል ጻድቃን። 👉ኤርትራ ትልቅ ወታደራዊ ስጋት እንደሆነችባቸው የጠቀሱት ጻድቃን፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ኤርትራን እንዲያስታግስላቸው ጠይቀዋል። 👉ኢትዮጵያ በቅርቡ ቱርክ፣ ኢራን እና ቻይና-ሰራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ታጥቃለች ሲሉ የተናገሩት ደሞ አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለሥልጣን ናቸው። ✅ በኢትዮጵያ የተመድ የስነ ሕዝብ ቢሮ ሃላፊ ደኒያ ጌል ከትግራዩ ግጭት ጋር በተያያዘ በሰጡት አስተያየት ሳቢያ ወደ ኒውዮርክ እንደተጠሩ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል። 👉 ሃላፊዋ የተጠሩት፣ ለአማጺው ሕወሃት ወገንተኛ የሆኑ ከኒውዮርክ የሄዱ የተመድ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ ያሉ የድርጅቱን ተወካዮች በትግራዩ ግጭትና ሰብዓዊ ቀውስ ዙሪያ ከውሳኔ አግልለዋል በማለት ለካናዳዊው ጋዜጠኛ ጀፍ ፒርስ የሰጡት ቃለ ምልልስ ድምጽ ቅጂ አፈትልኮ መውጣቱን ተከትሎ ነው። የድርጅቱ ቃል አቀባይ የሃላፊዋ አስተያየት የድርጅቱን አቋም አይወክልም በማለት ተናግረዋል። 👉በኢትዮጵያ የተመድ ፍልሰተኞች ድርጅት ለኢትዮጵያ ተወካዩ ለሞሪን አቼንግ በተመሳሳይ ምክንያት ሰኞ'ለት የግዳጅ እረፍት እንደሰጠ ይታወሳል። ✅ የአሜሪካ ዓለማቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና ሃላፊ ሳማንታ ፓዎር በሰሜን ኢትዮጵያው ሰብዓዊ ቀውስ ዙሪያ ከቡድን-7 ሀገራት ሚንስትሮች ጋር እንደተወያዩ ቢሯቸው ካሰራጨው መግለጫ ተመልክተናል። 👉 የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ላይ የተጋረጡ ችግሮችን ለመፍታት ሌሎች መንገዶችን ለመፈተሽ ተስማምተዋል። 👉አሜሪካ ለአማራ እና አፋር ክልሎች የጦርነቱ ተጎጅዎች 26 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለግሳለች። 👉የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ዛሬ በቪዲዮ ባደረጉት ንግግር ደሞ፣ መንግሥት በትግራይ ላይ የጣለው ሁለንተናዊ እገዳ የዕርዳታ አቅርቦትን አስቸጋሪ አድርጎብናል በማለት ተናግረዋል። ✅ የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 39ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ እና ዐርብ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። 👉ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ የኒጀር፣ ቡሩንዲ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ አልጀሪያ፣ ኮንጎ፣ ኮትዲቯር እና ጋቦን ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እንደገቡ ሚንስቴሩ ገልጧል። ✅ ዓለማቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በኬንያ እና ሱማሊያ የባሕር ግዛት አከላለል ውዝግብ ላይ ትናንት የሰጠውን ብይን ሱማሊያ ተቀብለዋለች። 👉ፍርድ ቤቱ አብዛኛውን የሱማሊያን የባሕር ግዛት ጥያቄ ተቀብሏል። 👉የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ግን፣ ብይኑ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ የሚያሻክር ነው በማለት ውድቅ እንዳደረጉት ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። 👉 ሀገራቸው ውዝግቡን በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ለመፍታት ጥረት እንደምታደርግ ኬንያታ ጠቁመዋል። 👉የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ በበኩላቸው ኬንያ ብይኑን እንድትቀበል ጠይቀዋል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
8 220
25
🪧ስራ ንግድ ባንክ 10ኛ ክፍል 🪧 የገንዘብ ቤት ተላላኪ (CASዘ OFFICESER VICEATTENDANT) ✅JOB OVERVIEW Salary Offer:As per Company Scale Experience Level: Junior Total Years Experience:1 year Date Posted:October 13, 2021 Deadline Date: October 26, 2021 ✅JOB REQUIREMENT 👉 የትምህርት ደረጃ:10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች 👉 የስራ ልምድ: ኣንድ ኣመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት 👉የስራ ቦታ: በባንኩ ሥር ላሉ ዲስትሪክቶች እና ቅርን ጫፎች ✅HOW TO APPLY 👉መሰፈርቱን የምታሟሉት እና ፍላጎት ያላችሁ እመፅካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በባንኩ የሰራ ማመልከቻ ድህረ ገፅ https://vacancy-cbe.com.et በመግባት እንድታመለክቱ እና የተጠየቀውን የትምህርትማስረጃ፡ የስምንተኛ ክፍል ሰርተፊኬት እና የስራ ልምድ እንድታያይዙ እንገልፃለን። ሆኖም ግን ባንኩ ስራውን የመሰረዝ ወይም ሌላ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው። ⚠️ስካን አድርጋችሁ የምታያይዟቸውን መስረጃዎች pdf ወይም በdocx ሆኖ የአንዱ ማስረጃ ከ2 MB መብለጥ የለበትም። 👉 በተጨማሪም ሰኔ 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በወጣዉ የሰራ ማሰታወቂያ ላይ ያመለከታችሁ አሁን በወጣዉ የስራ ማስታወቂያ ላይ ደግሞ ማመልከት አይጠበቅባቹም። ✅ስለሆነም እኛ የእውነት ሚድያ አባላት እደዚህ ቀደሙ 👉 አቅራቢያችሁ internet cafe ለማታገኙ 👉ለመመዝገብ ወረፋ ለሆነባችሁ 👉online apply ለማረግ ለተቸገራችሁ ✅ለመመዝገብ ዝግጁ ነን ስለዚህ በስልካችን (094) 609-4710 ደውላችሁ ማናገር ትችላላችሁ። መልካም ዕድል @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 964
50
🪧ማክሰኞ ጥቅምት 2/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች🪧 ✅ የአማጺው ሕወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል በወረራ በያዟቸው የሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ዞኖች የአርሶ አደሮችን የኢከኖሚ መሠረት በማውደም ዘመቻ ላይ ተሠማርተዋል ሲል ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከሷል። 👉አማጺያኑ የአርሶ አደሮችን የደረሱ ሰብሎች እያጋዙ እና ከፍጆታቸው የተረፈውን የአርሶ አደር ጥሪት እያወደሙ እንደሆነ የገለጠው ሚንስቴሩ፣ ዓለማቀፍ ኅብረተሰብ በሕወሃት ወረራ ስር ላለው ዕርዳታ ፈላጊ ሕዝብ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል። 👉 አማጺዎቹ የአርሶ አደሮችን እንስሳትን በጅምላ እየገደሉ፣ ዕርዳታ እየዘረፉ፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ባንኮችንና የሕክምና ተቋማትን እያወደሙና በግንባታ ላይ ባለው የአዋሽ-ወልድያ-ሐራ ገበያ ባቡር ሐዲድ ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሆነ ሚንስቴሩ ጠቁሟል። 👉 ሕወሃትን ይህን የሚያደርገው፣ "የፖለቲካ ተዋናይ ሆኖ ለመቀጠል" እና በትግራይና አማራ ሕዝቦች መካከል ጥላቻ ለመፍጠር ነው- ብሏል ሚንስቴሩ። ✅ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑን ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። 👉 ታጣቂዎች ንጹሃን የአማራ ብሄር ተወላጅ ነዋሪዎችን እየገደሉ እና እያሳደዱ ያሉት፣ በኪራሙ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች እንዲሁም በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ እና ሆሮ በተባሉ ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ነው:: ✅ ኢዜማ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች በተደጋጋሚ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት የክልሉ ፖሊስ እና ፌደራል ፖሊስ ለምን ማስቆም እንዳልቻሉ ማብራሪያ እንዲሰጡ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። 👉የንጹሃን ግድያ ዛሬም መቀጠሉ መንግሥት ለችግሩ በቂ ትኩረት እንዳልሰጠውና ችግሩን ለመቅረፍ አስተዳደራዊና ሕጋዊ ርምጃዎችን እንዳልወሰደ ያሳያል- ብሏል ኢዜማ። 👉ታጣቂዎች ወደ አጎራባች ወረዳዎች የሚያስወጡ ሁሉንም መንገዶች በመዝጋታቸው፣ በርካታ መውጫ ያጡ ነዋሪዎች በመድሃኒት እና ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑን ገልጧል። ✅ በኢትዮጵያ የተመድ ዓለማቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ሃላፊ ማውሪን አቼንግ ከትግራዩ ግጭት ጋር በተያያዘ በሰጡት አስተያየት ለጊዜው የግዳጅ ሥራ ፍቃድ እንዲወስዱ መደረጋቸውን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል። 👉 ሃላፊዋ የግዳጅ ፍቃድ የተሰጣቸው፣ "ለሕወሃት የወገኑ" ያሏቸው በኒውዮርክ የተመድ ከፍተኛ ሃላፊዎች እርሳቸውን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተመድ ሃላፊዎችን በትግራዩ ግጭት ዙሪያ ከውሳኔ ሰጭነት እና መረጃ ልውውጥ እንዳገለሏቸው ጠቅሰው፣ ለካናዳዊው ጋዜጠኛ ጄፍ ፒርሰ የሰጡት ቃለ ምልልስ የድምጽ ቅጂ ሾልኮ ከወጣ በኋላ ነው። 👉ሃላፊዋ በቃለ ምልልሳቸው ሕወሃት ከሳዑዲ ዐረቢያ የተባረሩ የትግራይ ተወላጅ ፍልሰተኞችን ሩዋንዳ ለማስፈር አሲሮ እንደነበር ጠቅሰዋል። 👉የዓለማቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ሃላፊ አንቶኒዮ ቪቶሪኖ የሃላፊዋ አስተያየት ድርጅቱን እንደማይወክል የሚገልጽ ደብዳቤ አሰራጭተዋል። ✅ መስከረም 20 ምርጫ በተደረገባቸው ሱማሌ፣ ሐረሬ እና የተወሰኑ የደቡብ ክልል ምርጫ ክልሎች አብዛኛውን መቀመጫ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ እንዳሸነፈ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው ውጤት አስታውቋል። 👉ከሦስቱ ክልሎች አንድ የሱማሌ ክልል የግል እጩ ብቻ ለክልሉ ምክር ቤት አሸንፈዋል። በደቡብ ክልል 3 የክልል እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች እንዲሁም በሱማሌ ክልል 2 የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች ላይ ግን የቅሬታዎች ምርመራ ገና ባለመጠናቀቁ፣ በዛሬው የተረጋገጠ ውጤት አልተካተቱም። 👉በሦስቱ ክልሎች ምርጫ የተካሄደው ለ47 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለ106 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ነው። ✅ ምርጫ ቦርድ ትናንት ባጸደቀው ሕዝበ ውሳኔ መሠረት አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጥቅምት 29 እንደሚመሠረት የክልሉ ምስረታ ጊዜያዊ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤቱ መግለጹን የሀገር ውስጥ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። 👉 በሕገ መንግሥቱ መሠረት የአዲሱ ክልል ምሥረታ እውን የሚሆነው፣ ከደቡብ ክልል ጋር የሥልጣን ርክክብ ሲያደርግ ነው። 👉አስተባባሪ ጽሕፈት ቤቱ ለአዲሱ ክልል ያዘጋጀውን ረቂቅ ሕገመንግሥት ወደ ሕዝቡ እንዳወረደ ገልጧል። የአዲሱ ክልል መስራቾች ካፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና ኮንታ ልዩ ወረዳ ናቸው። ✅ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ለ5 ዓመታት ተዘግቶ የነበረው የአህያ ማረጃ ቄራ እንደገና ሥራ እንደጀመረ ፎርቹን ዘግቧል። 👉በ60 ሚሊዮን ብር ባንድ የቻይና ኩባንያ የተቋቋመው ቄራ፣ ባለፈው ወር 80 ሺህ ዶላር የአህያ ስጋ ለምሥራቅ እስያ ገበያ እንዳቀረበ ዘገባው ጠቅሷል። 👉ቄራው ከ5 ዓመት በፊት የተዘጋው ከኅብረተሰቡ ባሕል እና እምነት ጋር ይጋጫል በሚል ሲሆን፣ አሁን ግን ከከተማዋ አስተዳደር፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሐይማኖት አባቶች ጋር በተደረሰ መግባባት እንደገና የአህያ ስጋ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምሯል። ✅ ኬንያ እና ሱማሊያ ከፍተኛ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ባለበት የሕንድ ውቅያኖስ ግዛት ላይ ያነሱትን የይገባኛል ውዝግብ ሲመለከት የቆየው ዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ኬንያ ያቀረበችውን የባሕር ድንበር አከላለል ውድቅ ማድረጉን የሀገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። 👉 ኬንያ በአወዛጋቢው ባሕር ላይ የጋዝ ቁፋሮ በማድረግ ሉዓላዊነቴን ጥሳለች በማለት ሱማሊያ ያቀረበችውን ክስ ችሎቱ አልተቀበለውም። ኬንያ ፍርድ ቤቱ ለውዝግቡ ብይን ለመስጠት አለኝ ለሚለው ሕጋዊ መሠረት እውቅና ነፍጌያለሁ በማለት ብይኑን እንደማትቀበል ባለፈው ሳምንት ማስታወቋ ይታወሳል። ✅ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በኒውዮርክ ተገናኝተው ስለ ትግራይ ግጭት እና ሰብዓዊ ቀውሱ እንደተወያዩ ጽሕፈት ቤታቸው ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። 👉ኬንያታ እና ጉተሬዝ ለትግራዩ ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማፈላለግ ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከሌሎች የግጭቱ ተዋናዮች ጋር ውይይት ማድረጋታቸውን እንደሚገፉበት ገልጠዋል። ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ጸጥታው ምክር ቤት በብዝሃነት፣ ሀገር ግንባታ እና ጸጥታ ላይ የሚያደርገውን ስብሰባ በሊቀመንበርነት ይመራሉ። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 442
14
🥷የአሸባሪው ህወሓት የድረሱልኝ ጥሪ🥷 ✅አሸበሪው ህወሓት በሰጠው አሁናዊ መግለጫ የድረሱልኝ ጥሪውን አሰምቷል፡፡ 👉የሽብር ቡድኑ እያሰማ ያለውን የድረሱልኝ ጥሪ በተመለከተ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የመግለጫው ሙሉ ቃልም እንደሚከተለው ቀርቧል፡- 👉አሸባሪው ህወሃት በሰጠው አሁናዊ መግለጫው "...የኢትዮጵያ ሰራዊት በአነስተኛ ወይም ትናንሽ ማጥቃት ሲፈፅም የቆየውን አሁን ላይ በከባድ መሳሪያ፣ በአየር ኃይል ታግዞና ሁሉንም የፀጥታ ኃይሎች አቀናጅቶ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየፈፀመ ነው።..." ይላል። 👉የጦርነቱን አላማ ሲገልፅም "...በትግራይ ህዝብ ላይ ዳግም ወረራ ለመፈፀም፤ ሰቆቃውን ለማብዛትና ለማጥፋት እንዲሁም ውጊያውን በትግራይ መሬት በማድረግ ሊጨርሰን ነው " ይላል። 👉ይህንን ባለበት አንደበቱ "...የትግራይ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሰራዊት ባለበት ተኮማትሮ እንዲቀመጥ አድርገነዋል..." ይላል። 👉"ተጠቃሁ" ከሆነ ወደፊትና ወደ ጎን እንቅስቃሴ አለ ማለት ሲሆን፣ "አኮማትሬያለሁ" ግን ተዘርግቶም ሆነ ወደፊት መንቀሳቀስ የማይችል አድርጌዋለሁ ማለት ነው። 👉ሽብርተኛው ሁልጊዜ ውሸት ቀለቡ ነው፤ አንድ ነገር ሲፈልግ መጀመሪያ የሚያቅደው እንዴት ልዋሽ ብሎ ነው፡፡ ቅጥፈቱ ደግሞ እልም ያለ ከመሆኑ የተነሳ "ይታወቅብኝ ይሆን ? " የሚል ጭንቀት የለበትም፡፡ 👉የዛሬው ፈሊጥ ደግሞ አይናችሁን ያዙ ላሞኛችሁ ዓይነት ሆኗል፡፡ ለጋላቢዎቹ "መጠነ ሰፊ ጥቃት" ተሰነዘረብኝ እባካችሁ አድኑኝ እያለ ሲማጸን፤ ለሚጋልባቸው ደግሞ "አኮማትሬያለሁ" እያለ መዘላበድ ሆኗል፡፡ 👉ይህ መንታ ምላስ እራሱ ወሮና አጥቅቶ ህዝብ ያጎሳቆለው ሳያንስ እና ኢትዮጵያን የማፍረስ ህልሙን በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እና በመላው የፀጥታ ኃይላችን አልሳካ ሲለው፤ በተለመደ ውሸቱ ዓለምን ለማደናገር የድረሱልኝ ጥሪውን ያቀርባል። 👉"እንጦጦ እንደርሳለን" ያለ ኃይል፣ ተገልብጦ "ድረሱልን...!"፡፡ ወሮ "ተወረርን...!" አጥቅቶ "ተጠቃን...!" እያለ ውሸት የማያልቅበት ኃይል ነው። 👉የመከላከያ ሰራዊታችን በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ ግን "ተጠቃሁ" ብሎ ለመናገር እንኳ ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት። 👉የዚህ አሸባሪ የጁንታ ቡድን ውሸትና ማደናገሪያ እድሜው የመሸበት የቁራ ጩኸት ነው። 👉በመሆኑም ህዝባችን በወሬ ሳይደናገር የቁርጥ ቀን ልጆቹ በመንግስታቸው ትዕዛዝ አይቀሬውን ድል እስኪያበስሩ የተለመደው ድጋፍ እንዳይለየን እንላለን። 👉የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 609
15
🪧ስራ ደቡብ ግሎባል ባንክ🪧 ✅ADMINISTRATIVE ASSISTANT ✅JOB OVERVIEW 👉Salary Offer : As per Company Scale 👉Experience Level:Junior 👉Total Years Experience :0-2 👉Date Posted:October 15, 2021 👉Deadline Date: October 10, 2021 ✅JOB REQUIREMENT 👉 Education (Minimum): BA/College Diploma in Secretarial Science and Office Management, Management or related field 👉 Experience: 0 or 2 years of experience in secretarial jobs Place of work: Addis Ababa ⚠️HOW TO APPLY ✅Application Dead line: 5 working days (October 11-15, 2021) starting from the date of announcement on the newspaper Interested applicants should submit their non-returnable applications along with CV and photocopies of other relevant documents through post office only. Debub Global Bank S.C Human Resources Management Dep't P.O. Box 100743 Addis Ababa @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 465
18
🪧በወራቤ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ🪧 ✅በወራቤ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ዱና ስታዲየም ፊት ለፊት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ ድንገት በተነሳ የእሳት አደጋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት ሲደርስ አራት ቤቶች ተቃጥለዋል። 👉የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን አብዱረሂም ሁሴን እንደገለጹት በእሳት አደጋው በአንድ ሰው ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን÷ የአደጋው ተጎጂ በህክምና ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። 👉በከተማው የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስዔ በመጣራት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። 👉እንደ ዋና ሳጅን ሁሴን ገለጻ ህብረተሰቡ እንደ ቤንዚን እና ተቀጣጣይ ነገሮችን በመኖሪያ አካባቢ ማኖር የለበትም ሲሉም አስገንዝበዋል። 👉የእሳት ቃጠሎው በከተማው የእሳት አደጋ ተሽከርካሪ እና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን÷ የደረሰው የአደጋ መጠን በመጣራት ላይ መሆኑን ማስረዳታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 058
5
🪧ስራ Cooperative Bank Of Oromia🪧 ✅ከቀናት በፊት በቴክኒክ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የግራጁዬት ትሬይኒ ምዝገባ አሁን ጀምሯል። ⚠ ከአንድ በላይ ድስትሪክት ላይ ለመመዝገብ የሚያደርጉት ሁሉንም ምዝገባዎን ያሰርዛል። ✅ ከቀናት በፊት ስማችሁ የተዘረዘረ አመልካቾች በድጋሚ መመዝገብ አይጠበቅባችሁም። _____ Position - Graduate Trainee _____ Requirements to Apply *BA Degree in Cooperatives, Accounting, Agricultural Economics, International Trade and Investment Management, Agri-Business and Value-chain Management, Agro-Business Management, Economics, Management, Business Administration, Business Management, Banking and Finance, Banking and Insurance, Public Administration and Development Management, Accounting and Auditing, Accounting and Finance, or any other related field with CGPA of 2.5 and above. *Age of the applicant shall not exceed 27 years (inclusive). *Only graduate of 2019/20 and 2020/21 G.C. _____ Work Experience: 0 Year _____ Employment Center 1. Branches under Dire Dawa District|Dire Dawa, East Hararge, West Hararge, Harari Region, Somali Region 2. Branches under Chiro District|West Hararge, East Hararge 3. Branches under Nekemte District|East Wollega, West Wollega, Qellem Wollega,Horro Guduru Wollega Zones and Benishangul Gumuz Region 4. Branches under Jimma District|Jimma Zone, Ilu Abba Bora Zone, Bunno Bedelle Zone, Bench Maji Zone and Gambella Region 5.Branches under Shashemene District|Bale and West Arsi Zone 6. Branches under Hawassa District|Sidama Region, SNNP Region, East Guji Zone, West Guji Zone, Borena Zone 7. Branches under Bahir Dar Relationship Office|Bahir Dar, Debre Markos, Bure, Gondar, Metema, Gendawuha, Dessie, Kombolcha, Kamise, Bati areas and Afar Region Logia. ______ Registration Deadline: October 13, 2021 ______ How to Apply Interested applicants should register to our job portal by following one of the links below and submit their CVs along with required credentials. ⚠ Any attempt to apply at more than one district will lead to automatic disqualification. *All those whose names have listed last time and do not need to reapply. 1. For branches under Nekemte District, Jimma District and Bahir Dar Area Relationship Office, please follow http://jobs.cbo.com.et:9510/ 2. For branches under Dire Dawa District, Chiro District, Hawassa District and Shashemene District, please follow http://jobs.cbo.com.et:9512/ ⬆️ Tip ለ እውነት ሚድያ ቤተሰቦች online apply ስታደርጉ ካስቸገራችሁ በስልካችን (094) 609-4710 ደውላችሁ እርዳታ ማግኘት ትችላላችሁ መልካም ዕድል @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 469
43
🪧የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት🪧 1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል ነጭ ሽንኩርት መብላት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ 2. ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡ 3. በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡ 4. ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡ 5. ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ መልሶ ይጠነክራል፡፡ 6. ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡ 7. ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡ 8. በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት varicose የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡ 9. ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማትን ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡ ሰላም እና ጤና ከእናተ ጋር ይሁን @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
8 649
160
🪧ስራ አቢሲኒያ ባንክ🪧 ✅Jimma District Bank Trainee ✅Job Details 📍Jimma District, Ethiopia ✅ Job Identification:933 Job Category:Banking Operation Locations:Jimma, Jimma, Oromia, ET Posting Date:10/07/2021, 03:31 PM Degree Level:BA Degree Job Schedule:Full time CGPA:≥3.00 Year of Graduation:2020-21 Required Work Experience:0 Required Job Family:Banking Operation Major Category:Business Related Maximum Age: 25Job Description 1. Job Title :Bank Trainee 2. Education : BA Degree in Business Administration, Management, Marketing,  Accounting and Finance, Economics or related fields   ✅Experience: Zero year of Experience Job Grade:IV Cumulative GPA: 3.00 and above Year of Graduation2020 and 202Age: 25 and below  Place of work: Branches under Jimma District ⚠️HOW TO APPLY ✅Read the vacancy announcement very carefully. Check the requirement of the vacancy from the details with eligibility. ✅Applicants should attach the following documents:- 👉8th Grade Certificate and Kebele ID, 👉Degree with CGPA (Student Copy) 👉Cost Sharing Documents, 👉All documents should be scanned only in pdf format, 👉Applicants should apply only on one job Position, 👉After checking the eligibility criteria and prepared all the necessary documents, qualified and eligible applicants apply online through BoA career website :  Click the link below to apply for a job on Oracle system: https://fa-enhf-saasfaprod1.fa.ocs.oraclecloud.com/hcmUI/CandidateExperience/en/sites/CX/requisitions ✅Applicants should apply before the closing date. ✅Note 👉In person or postal application is not acceptable, 👉Ineligible/Unqualified applicants will be automatically rejected, 👉Applicants who have applied on more than one position will be automatically disqualified from the process. 👉Any updates will be communicated only through email. ⬆️ Tip ለ እውነት ሚድያ ቤተሰቦች online apply ስታደርጉ ካስቸገራችሁ በስልካችን (094) 609-4710 ደውላችሁ እርዳታ ማግኘት ትችላላችሁ መልካም ዕድል @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 363
22
🪧የወላይታ ሶዶ ደ/መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ከፍተኛ የእሳት አደጋ ደረሰበት🪧 ✅ንዋያተ ቅዱሳትም ወድመዋል 👉በወላይታ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የወላይታ ሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ንዋያተ ቅዱሳት ማስቀመጫ ግምጃ ቤት በእሳት አደጋ በከፍተኛ ደረጃ መውደሙ ተሰማ። 👉በእሳት አደጋው ገዳሙ በቤተ መዘክሩ ያከማቻቸው ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ፥ ነገሥታት ለገዳሙ የሰጡት እጀ መንሻ የሆኑ ንዋያተ ቅዱሳት ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ወድመዋል። 👉የእሳት አደጋው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፫ኛ ቅዱስ ፓትርያሪክ የሆኑት የብጽጱ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የጸሎት በዓት በተጨማሪ አውድሟል። 👉የእሳት አደጋው መንሴው ምን እንደሆነ እሰከ አሁን ያልታወቀ ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት የተረባረቡ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች እና ከሌ ቤተ እምነት ለመጡ አካላት ቤተክርስቲያን ምስጋና አቅርባለች። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
6 228
4
🪧ዲቪ ሎተሪ🪧 ✅ዲቪ ሎተሪ 2023 ከዛሬ መስከረም 26 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ማመልከት ይቻላል። 👉ማመልከት የሚቻለው በኢንተርኔት ብቻ ሲሆን ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣ 👉ከስድስት ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ መጠቀም ያስፈልጋል፣ ዝርዝር መረጃው እነሆ:- ✅Diversity Visa Program 2023 is open! ✅Entries for #DV2023 begin on October 6, 2021 at 7 p.m. (local time) and ends on November 9, 2021 at 7 p.m. (local time). • All entries must be submitted online. • Registration is free. • Only enter the DV program once. • Use a recent photo from the last six months. Go here to enter your application: dvprogram.state.gov. @EthioEwuneta @EthioEwuneta
Show more ...
7 041
108
🪧ሥራ ጀምራለች🪧 ✅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ የተጀመረው በቀን 1 ጊዜ መመገብ ያልቻሉ ዜጎች የዕለት ጉርስ እንዲያገኙ በተከፈተው የተስፋ ብርሐን የምገባ ማዕከል 6ኛ ቅርንጫፍ ውስጥ ስራ ጀምራለች። @EthioEwuneta @EthioEwuneta
5 882
1
6 104
9
5 258
14
Last updated: 27.11.21
Privacy Policy