en
Feedback
📚 የኛ_ግጥም 📚

📚 የኛ_ግጥም 📚

Open in Telegram

Show more
Ethiopia4 030The category is not specified
6 604
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#አትሟት © ሲራክ ወንድሙ . መሬት የሚጠርገው የቀሚሷ ጫፉ፣ በወንጌል ቢታሰር የሚቀድስ አፉ ፣ ምናልባት እዚህ ቤት... ፀሀይ ፈገግታዋን የተሻማ ሁሉ ፣ ከፈገግታ ጀርባ መከልከል እንዳለ የነገራት ውሉ ፣ ባይገባው ነው እንጂ... እስኪ አትሟት ይህቺን... ለቆረባት ሁሉ እህትነት ይዟት ከመጣው ብትቆርብም ፣ እሷ ቀሚሷን ነው ሳቋን አትሰስትም። ................... //////.................... ሲራክ @siraaq < የብርሃን መንገድ >

ንቅለ ጉልቻ ያልባረከው ትዳር ... ሲጋፈጥ መዘዙ አወይ እባብ ...ጣሙ ካልተገዳደሩ መች ይወጋል መርዙ... ይመስገን አደቤ አንችን አየው ከይሲ ፥ ታዘብኩሽ በብዙ ። ካዝማዴ ተጣላሁ ፥ ተፋታሁ ከስጋ ነብስ አባቴ ሳይቀር ፥ በእጁ ጆሮ ዘጋ ጩኸቴን ቀምተሽ ፥ አነባሽ በነጋ እራሱ ገረፈ ... እራሱ ተናጋ በሚል አጭር ስንኝ እውነቴ ተለጋ ። አበምኔት ያረገሽ ፥ ወዳጅ ግትልትሉ የጠላሽ ይጠላ ፥ የረገምሽው ይሙት ፥ ሲሉ ተከተሉ ባልሽ አፈር ይብላ ድንጋይ ይንተራሰው ብላችሁ ፀልዩ ፥ ስትይ የሰማሰው ሲሞት እንዳይገድሽ... አገር ምድሩን ማሰው የኔ ያልኩት ሁሉ ፥ መደፋት ሲደርሰው ወዝና ስጋዬ እየተሞዠቀ ፥ ጅማት ሰጠሁ ለሰው ከደም ጠፈጠፌ ፥ አገሬው ደረሰው እንዲህም ሆኖ ግን ... ለምነው ማትሞተው ... ይለኛል አላፊ እላለሁ መልሼ ፥ ለዚህ ተላላፊ ቀኑ ያልደረሰ ሰው ለሞት አይወድቅም ፥ እንኳንስ ለጥፊ ታሪክ ለድምቀቱ... ማሰለፍ ይወዳል ፥ አጥፊውን ከጠፊ ። ከለታት ባንዱ ቀን እገሌ ከገሊት ፥ ተጋብተው ነበረ ሲኖሩ ሲኖሩ ፥ እሷ ስትወደው ፥ ይገፋት ነበረ ትላንት የነበረ ፥ ዛሬ በቀን ሻረ ፥ በለት ተቀየረ እንዲህ ሆነች እሷ ፥ እሱም እንዲህ ቀረ ያባብላል ወራት የገንፎ ላይ ስንጥር ፥ የጎን ላይ ውጋት ሁነሽኛል መቼም ለግፍሽ እርግጫ ፥ ለበቀልሽ ቼቼ አልጥልሽም ከቶ ፥ ባንቺ ቀን ታግዬ ፥ በሸንጎሽ ሞግቼ ድሌን እሽታለው ... እሳት ላይ ተኝቼ ምሳሩ ቢበዛ ፥ እውነቴን ላይበጥስ ፥ አምናለሁ በርትቼ እስከቀኔ አልፋለው ፥ ቀኜ ሲዝልብሽ ፥ ግራዬን ሰጥቼ ። ይሄም ሆኖ ግና... አይንሽ ደም ለውሶ ፥ አንዴ ሰክረሽ ለኔ ጎንጉነሽ ጎንጉነሽ ፥ ግፍና ኩነኔ ያዘዘልሽ አልቆ ፥ ያዘዘው እስኪደርስ እንባና ለቅሶዬ ... ገደል ልብሽ ላይደርስ ሸለል በይ ካብ ለካብ ተሳቢ ... በዲቡ እስኪጥልሽ እጄ ... እስኪክሰኝ ፀቡ ። አብርሃም ተክሉ @Getamiyan @getamiyan

አጭሬ ፭ የአጫጭር ግጥሞች ስብስብ . የገጣሚ :- በዕውቀቱ ስዩም የገጣሚ :- በረከት በላይነህ የገጣሚ :- ዲበኩሉ ጌታ የገጣሚ :- ኤፍሬም ስዩም .......... #እና የገጣሚ :- መዘክር ግርማ ግጥሞች ተካተውበታል አንባቢ ሲራክ @siraaq @Getamiyan @getamiyan

#የለም ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሳ አንባቢ #ሲራክ @siraaq @Getamiyan @getamiyan

ተጋበዙልኝማ ይሄን ❤️ የወዳጄን ❤️ በኩር ልጅ #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት ( ዳግም ሄራን ) በተገኘበት ይነበብ !!! @getamiyan
ተጋበዙልኝማ ይሄን ❤️ የወዳጄን ❤️ በኩር ልጅ #ሰው_ፍቅር_ናፍቆት ( ዳግም ሄራን ) በተገኘበት ይነበብ !!! @getamiyan

🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋 🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋 ........... ©ሲራክ ...... በእለተ ከተራ ፥ በበዓል ዋዜማ፣ አደባባይ ሳይሽ ፥ ደምቀሽ በሃገር ሸማ ፣ ወርውር ወርውር አለኝ ፥ ሎሚውን ግዛና፣ ሎሚ ሻጭ ፈለግኩኝ...... ጎዳናውን ሙሉ ፥ ስዞር አመሸሁኝ። በጥምቀተ ባህር ፥ ህዝብ ሁሉ በሆታ ፣ እያጨበጨበ ፥ ታቦቱን አጅቦ ሲገባ በእልልታ፣ ማጨብጨብ ተስኖኝ ... እልልታ ጠፍቶብኝ... ሎሚ ፈልጋለሁ ፥ ከአይኔ ሳትጠፊብኝ። ይኸውልሽ ውዴ .... አትታደል ሲለኝ ፥ ቢጠፋ ነው እንጂ .. እድሌ ባይቀና ፥ ብኩን ብሆን እንጂ.. ከአስራ አምስት ቀን በፊት ፥ ለጨዋታ ብዬ ፣ ለገና ጨዋታ ፥ ለአሲና ገናዬ ፣ ዱላ እየፈለግኩኝ ፥ ከጫካ ገብቼ ፥ ሎሚ ጨፍጭፌያለሁ ፥ ዛፉን ተመኝቼ ። እድል እንደዚህ ናት ፥ የዋርካ ስር ጤዛ ፣ ይኸው እኔ ዛሬ ፥ በዋዛ ፈዛዛ፣ እልፍ የሎሚ ዛፍ ፥ ጨፍጭፌ ሳበቃ፣ አንድ ሎሚ አጣው ፥ ለአንቺ የሚበቃ ። አዬ እድል እያልኩኝ ፥ ከወደ አመሻሽ ፥ ከቤቴ ገብቼ ፣ ሎሚ ዛፍ ተከልኩኝ ፥ ለዓመቱ አስልቼ ። እስከዛ ግን አንቺ ..... ሎሚ ወርዋሪዎች ፥ በሌሉበት መንገድ ሂጂልኝ ግድ የለም፣ ዘንድሮን ያለፍኩት ፥ ሎሚ ቢጠፋ እንጂ... ፈርቼስ አይደለም። ወርውር ያለኝ ልቤ ..... ተግቶ ተሰናድቶ ፥ ዓመቱን ጠብቆ፥ በእለተ ከተራ ፣ እመጣለሁ ብሏል ፥ ከአስር ሎሚ ጋራ። 🍋🍋🍋🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋🍋🍋 --------- ሲራክ ወንድሙ @siraaq @getamiyan @getamiyan

በእሾህ መንገድ መሀል (በእውቀቱ ስዩም) ያገሩ አየር ጠባይ ቆላ- ወይን- አደጋ ከላይ የሚያስፈራ፥ ከታች የሚያሰጋ አጉል ነው መንገዱ ቅፅሩም ሲገዝፍ ያድራል በቁመት በወርዱ እና ምን ይጠበስ? የማይቆም ጅረት ነኝ፤ የማይቀለበስ ቢገፏት ቢያዳፏት ከቅርንጫፏ ጋር የማትነጣጠል በወጀብ መሀከል ፥የምትደንስ ቅጠል እንደዚህ ነኝ እኔ፤ ምቾትስ ለምኔ ቀይ ምንጣፍ አያምረኝ ይመስገን ዘመኔ በእሾህ መንገድ መሀል፤ መጉዋዝ ላስተማረኝ @getamiyan @getamiyan

#ላለፈ_ክረምት ገጣሚ:- ጋሽ አበራ ለማ አንባቢ:- ሲራክ ወንድሙ @siraaq ....... ብቻ እንዲያው ብቻ እንዲያው ድፍን ቅል ሰበራ፣ ውኃ ማንቀዳበት ጥሬ ማንሰፍርበት የልጅ ቢጤ ስራ መውደድም አንዴ ነው መጥላትም አንዴ ነው ሲያስለን የሚኖር ትዝብቱ ብቻ ነው። ..... @Getamiyan @getamiyan

🙏🙏🙏 የገና መዋያ 🙏🙏🙏 @Abrham_teklu

_ ይኸው ነው _ © ሲራክ ወንድሙ . ያ ክፉ አመሏ ከሰው .... ከባህል ልማዷ ባራራቃት ማግስት፣ እሷ እሷን ሳትሸት በሚወስዳት ወሃ ልጫወት ያለች 'ለት፣ ኒሻን የመሰላት ትንፋሽ ቆራጭ ቀላድ ወዲያ ሲሸመቀቅ፣ እውር እድል አምና ገባች ከመቀመቅ። ////////________////////// © ሲራክ @siraaq @Getamiyan

#መሸ_ደሞ_አምባ_ልውጣ ግጥም :- ከብላቴን ጌታ አብዬ ፀጋዬ ገ/መድህን አንባቢ :- ሲራክ ወንድሙ @siraaq @getamiyan

ትርጉም ! (በረከት በላይነህ) .. "አስቀያሚ፣ አሰጠሊታ ፣ መልከ ጥፉ፤ እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ! የማትባል እዚህ ግባ ፣ የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ! ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር! የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር ባትታይም የማታምር! !!" እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣ ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤ አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ! ለምን ብትይ? መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤ ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ @getamiyan @getamiyan

Mele: https://t.me/joinchat/S_t0VGFGmP4WwZhC (አዲስ የቴሌግራም ቻናሌ ነው እስቲ ግቡበት አትከፍሉበት🙄😂❤️)

Watch "የመንገድ ዳር ጥሩንባ - አብርሃም ተክሉ- - ጦቢያ ግጥምን በጃዝ #106-13" on YouTube https://youtu.be/L3ifEpFES7s

......... ስሪት አንቺዬ ያዘዘለት ስጋሽ ፥ ጥፍሩ ይጠበቃል ያዘዘበት እኔሽ ጣትሽን እያየ ፥ በጣት መሄድ ያልቃል አሁን ለዚህ ውበት ...የቱ ቃል ይበቃል ? ✍ አብርሀም_ተክሉ @Abrham_te
......... ስሪት አንቺዬ ያዘዘለት ስጋሽ ፥ ጥፍሩ ይጠበቃል ያዘዘበት እኔሽ ጣትሽን እያየ ፥ በጣት መሄድ ያልቃል አሁን ለዚህ ውበት ...የቱ ቃል ይበቃል ? ✍ አብርሀም_ተክሉ @Abrham_teklu

#ውዝግብ_2 አራሚም ታራሚሚ ባልተበየነለት እንደልቡ ዘመን ወላድ በሬው በዝቶ... እንዳገር ተዛመን ስልቻ ባነሰው ፥ የሀተታ ስብስብ በቢላዋ ምላስ እየተመተረ...... ነጭ የወሬ ስብ ግንባር ስጋ ያሉት ቁልፍልፉ ወጥቶ ..... ከማደናገሩ በጠየቁ ቁጥር.........ብዙ በቆፈሩ ጥያቄ ያጭራል ፥ የመልስ ዳር ዳሩ ። አብርሀም_ተክሉ @Abrham_teklu @Abrham_teklu