cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
3 130
Subscribers
+424 hours
+737 days
+24830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የመምህራን እና የት/ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ለሚመዝኑ መዛኞች፣ሱፐርቫይዘሮች እና የፀጥታ አካላት በምዘናው ዙሪያ ኦሬንቴሽን ተሰጠ፡፡ (ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በ2016 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው የመምህራን እና የት/ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ለሚመዝኑ መዛኞች፣ሱፐርቫዘሮች እና የፀጥታ አካላት በምዘናው ዙሪያ ኦሬንቴሽን መሰጠቱ ተጠቆመ፡፡ በኦሬንቴሽኑ መድረክ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ እንደተናገሩት የሙያ ፈቃድ ምዘና ሂደት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ዋና ተግባራችን ነው ብለዋል፡፡ስለሆነም በጉለሌ ክፍለከተማ አስተዳደር የሚገኙ የግልና የመንግስት ት/ቤት መምህራንና የት/ቤት አመራሮች ሁሉም በፈቃዳቸው የተመዘገቡ ከ2020 በላይ ተመዛኞች ከግንቦት 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚሠጠው የሙያ ብቃት ምዘና ተመዛኞች በሰዓቱ በዕለቱ እና በተመደቡበት ተቋም በመገኘት በሃላፊነት ስሜት መመዘን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ የቅ/ጽ/ቤቱ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ባለሙያ የሆኑት አቶ አሸናፊ መለሰ የውይይት ኦሬንቴሽን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩም የተሳተፉ ተሳታፊዎች ላነሱት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ፍቅሩ ጋቢሳ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Show all...
ተወዳዳሪ የሆነ፣በምዘና ስርዓት ያለፈ፣ ራሱን ሁልጊዜ የሚፈትሽና ብቁ የሆነ መምህር የት/ቤት አመራር ለከተማችን የትምህርት ጥራት መጠበቅ እና መረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡በተጨማሪም ተመዛኝ መምህራንና የት/ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ተመዝኜ እና ብቃቴን አረጋገጬ መስራት አለብኝ የሚል አስተሳሰብ መያዝ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤትን ለመደገፍና ለማስተባበር በጊዜአዊነት የተመደቡ የማዕከል የአሰራር ጥራት ቡድን ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ከበደ ጋሹ በኦሬንቴሽኑ መድረክ ባስተላለፉት መልክት በሙያ ብቃት ምዘና ማለፍ የግድ ሲሆን ብቃቱን ያረጋገጠ መምህርና አመራር በዘርፉ በርካታ ጥቅሞችን በቀጣዩ እንደሚያገኝ ታሳቢ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የክፍለ ከተማው የትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ከበደ ዲሪባ እንደተናገሩት የከተማችንን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ በጋራ እንደሚሰሩና የክፍለከተማው መምህራንና የት/ቤት አመራሮች ለመመዘንና ብቃታችሁን ለማረጋገጥ ፈቃደኛ በመሆናችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል፡፡ እንዲሁም የክፍለከተማው የመምህራን ማህበር ሰብሳቢ አቶ ኦርጌሳ ደጀኔ እንደተናገሩት ከሆነ ሁሉም የክፍለከተማችን መምህራንና የት/ቤት አመራሮች በግንቦት ወር በሚሰጠው የሙያ ብቃት ምዘና ስርዓት ለማለፍ ዝግጁ እንድትሆኑ በማለት ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የክፍለተማው የአፋን ኦሮሞ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሲሳይ ተሰማ በአፋን ኦሮሞ ለሚያስተምሩ መምህራንና አመራሮች፣እንዲሁም በአማርኛ ለሚስተምሩ ደግሞ ከክፍለከተማው ከትምህርት ጽ/ቤት የመምህራን ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ዘውዴ እና ከቅ/ጽ/ቤቱ ደግሞ ወ/ሮ ሄለን ሰለሞን የመምህራን ሙያ ብቃት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት በሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ስርዓት ዙሪያ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡በሁለቱም መድረኮች ውይይቱን በሁለቱ ተቋማት አመራሮች የተመራ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሁለቱም መድረኮች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ከአንድ ሺህ በላይ ተመዛኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በ2016 ዓ.ም በሙያ ብቃት ምዘና ዙሪያ ኦሬንቴሽን መሰጠቱ ተጠቆመ፡፡ (ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት፣ የክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት እና ከክፍለከተማው የመምህራን ማህበር ጋር በመተባበር በ2016 ዓ.ም ግንቦት ወር በሚካሄደው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በሙያ ብቃት ምዘና ዙሪያ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ አስተዳደር በሁለት መሰብሰቢያ አዳራሾች ከ1000 በላይ ለሚሆኑ መምህራንና የት/ት አመራሮች ኦሬንቴሽን በትላንትናው ዕለት መስጠቱ ተገለፀ፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ምትኩ በመድረኩ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ስርዓቱ ያለብንን ስብራት ለማስተካከል የትምህርትን ጥራት ማረጋገጥ ከፍተኛ ተግባራችንና ትኩረታችን ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ የተገኘ እውቀት በራሱ በቂ አይደለም ዘመኑን የዋጀ ብቃት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
Show all...
ቅ/ጽ/ቤቱ እውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው አጫጫር ስልጠና እየሰጡ የነበሩ ተቋትን የማሸግ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡ (ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም) በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የቦሌ ቅ/ጽ/ቤት እውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው አጫጭር ስልጠና እየሰጡ ያሉ 10 ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል። እነዚህም እርምጃ የተወሰደባቸው ተቋማት የሚከተሉት ሲሆኑ በቀጣይም እርምጃው በሌሎች ህገወጥ ማሰልጠኛ ተቋማትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቅ/ጽ/ቤቱ አሳውቋ። 1. ሀኒ የውበትና ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ 2. ያሬድ የውበትና ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ 3. መሲ የውበት ማሰልጠኛ 4. ሪች ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ 5. ለትሽ የውበት ማሰልጠኛ 6. ሜሎዲ የሙዚቃ ማሰልጠኛ 7. ሄመን ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ 8. አልሚ የጸጉር ውበትና ሜካፕ ማሰልጠኛ 9. ፓሪስ የውበት ማሰልጠኛ 10. ጆ የውበት ማሰልጠኛ ናቸው። #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Show all...
በኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሳውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ስራን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እና ሌሎች የሀይማኖቱ አባቶች በተገኙበት ዛሬ አስጀምረናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የከተማ ኘላን እና ልማት እንዲጠበቅ፣ ከተማችን እንድትለማ፣ እንድትዘምን እና የተሻለ ዲዛይን እንዲተገበር በርካታ ትብብር በማድረግ ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህ ዛሬ መልሶ ግንባታ ስራውን ያስጀመርነው ህንጻ የዚህ አንዱ ማሳያ ነው። ይህ ህንጻ ባለ 4 ወለል የነበረ ሲሆን አዲሱ ግንባታ ለፓርኪንግ ግልጋሎት የሚውል አንድ ቤዝመንት የሚጨምር ዘመናዊ ባለ አራት ወለል ህንጻ ሆኖ ከአካባቢው ልማት፣ፕላን፣ በዙሪያው ካሉ ሌሎች ቅርሶች እንዲሁም ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር የሚናበብ ነው። ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀን ለቤተክርሰቲያኗ የምናስረክብ ይሆናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የልማት ኮሪደር ስራውን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Show all...
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሠራተኞች የማነቃቂያ እና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡ (ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም) በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የን/ስ/ላ/ቅ/ጽ/ቤት በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሰኞ ማለዳ የሚቀርበው የማነቃቂያና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር የተቋም ባህል ግንባታ ምን መምሰል አለበት በሚል ርዕስ በዛሬው እለት የቅርንጫፉ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ የመወያያ ሃሳቡን ያቀረቡት የቅርንጫፉ የእውቅና ፈቃድ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ጌቱ ቱፋ ሲሆኑ በተቋም ባህል ግንባታ ምንነትና አስፈላጊነት ላይ ሃሳብ ቀርቦ ውይይት ተከናውኗል፡፡ በዚህም የተቋም ባህል የሚገነባው በእውነትና በመርህ ላይ ሊሆን እንደሚገባ እውነትና መርህ ደግሞ ለምንሰራው ስራ ለምንሰጠው አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል። #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Show all...
እኔ የአንድ ወር ደሞዜን አስተዋፅኦ በማድረግ "ፅዱ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴሌቶን ላይ ተሳትፌያለሁ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችም የ"ፅዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና" ንቅናቄ በፍጥነት ጥሪውን ስለተቀላቀላችሁ በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ ያልተቀላቀላችሁ አመራሮችም ካምፔኑን እንድትቀላቀሉ ጥሪ አስተላልፋለሁ፡፡ ለአላማው መሳካት ሁሉም ሰው ያገባኛል በሚል በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የ"ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና" ናቅናቄን እንዲቀላቀል ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Show all...
ባለስልጣኑ ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚካሄደውን የሠራተኞች የማነቃቂያ እና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር አከናውኗል፡፡ (ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም) በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሰኞ ማለዳ የሚቀርበው የማነቃቂያና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር ደንበኞች እና መልካም አገልግሎት በሚል ርዕስ በዛሬው እለትም የባለስልጣኑ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ የመወያያ ሃሳቡን ያቀረቡት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ሲሆኑ ስኬታማ ህይወት ሚዛናዊ ነው ፡፡ሚዛናዊነታችንን ደግሞ የምናረጋግጠው በአገልግሎት ነው ስራ እና አገልግሎት ህይወት እንጂ የጊዜ ማሳለፊያ አይደለም አገልግሎት ለመኖር፣ለመስራት፣ለመበልፀግ ህልውና ነው ፤ስለዚህ ሁላችንም ለደንበኞቻችን ቅን አገልጋዮች እንሁን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Show all...
ምዘናው በየትምህርት ቤቶች ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት በጥራት ለማከናወን እና መምህራን ራሳቸውን በማየት አቅማቸውን ለማጎልበት የሚያግዝ እንዲሁም ጥራቱ የተጠበቀ ትምህርት በሀገሪቱ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ በተጨማሪም ከምዘናው የሚገኘው ግብረ መልስ ክፍተቶችን በመለየት የራሱ የሆነ ትንታኔ በማስቀመጥ ለፖሊስ አውጭዎች እንደ ግብአት የሚያገለግል መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ በምዘና ሂደት በቅቶ ማስተማር እና ሳይመዘኑ ማስተማር በራሱ ልዩነት ስላለው በትኩረት ምዘናውን ማካሄድ እንደሚገባ ጠቁመው በምዘና ወቅትም የምዘና ስርዓቶችን በተገቢው ሁኔታ በመተግበር ምዘናውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ አስገንዝበዋል ፡፡ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት የእውቅና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታነህ ባይሌ በበኩላቸው ምዘናውን አስመልክቶ እንደገለፁት ምዘናው ለ1507 መምህራን ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጥ እና ምዘናውም በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በሁለት የምዘና ጣቢዎች የሚካሄድ ሲሆን አይነ ስውራን መምህራንም በምዘናው ተሳታፊ እንደሚሆኑ አሳውቀዋል፡፡ ምዘናው ከመንግስት ት/ቤቶች 73.2% ከግል 26.8% የሚሸፍን መሆኑን ጨምረው አመላክተዋል፡፡ በዕለቱ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት የእውቅና ፍቃድ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ የትዋለ አታለለ ለምዘና የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል በሰነዱ ላይም የምዘናው አስፈላጊነት፣ የሙያ ፈቃድ መመሪያ ይዘቶች ፣የተመዛኞች መብትና ግዴታዎች እንዲሁም የምዘናው ሂደት እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዩች ቀርቧል፡፡ የቀረበውን ሰነድ መሰረት በማድረግ ጥያቄና አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎቸም በዕለቱ በተገኙ የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

በአገራችን ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት ውጤታማ እንዲሆን የመምህራን ብቃት በምዘና ማረጋገጥ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ (ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የቦሌ ቅ/ጽ/ቤት የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ሥርዓት በተመለከተ ዛሬ ውይይት ተደርጓል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አማካሪ እና የቦሌ ቅ/ጽ/ቤት ተወካይ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሠለሞን አለማየሁ ባስተላለፉት መልዕክት የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ምዘና ለማካሄድ ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የገለፁ ሲሆን
Show all...
Go to the archive of posts