cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ @bewketuseyoum19 Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19 For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot Thank you!

Show more
Advertising posts
129 065Subscribers
-15324 hours
-9207 days
-4 48030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰባት ሆነን ነበር ትምርት ቤት የምንሄደው አንለያይም። እናጠናለን አቅማችን ፥ ኑሯችን ፥ ጥረታችን ተመሳሳይ ነበር። ማትሪክ ደረሰ ፤ አጠናን ተፈተንን ፤ ፕሪፕ ስንገባ ምን እንደምንመርጥ እቅዳችን አውጠነጠንን ፤ ውጤት ከብዙ ጥበቃ በሆላ ወጣ ተባለ ፤ ልንቀበል ሄድን... ሁሉም አለፉ ከኔ በቀር። ከውጤት መልስ አብርያቸው ነበርኩ እንደልባቸው ድላቸውን እንዳያጣጥሙ አደረኳቸው። ጓደኞቼ ፣የሰፈሩ ሰዎች፣ የጓደኞቼ ቤተሰቦቾ አይዞህ አሉኝ አዘኑልኝ። ውጤቴን ለቤተሰቦቼ አሳየኋቸው እቤት እከሌስ እከሌስ እንዴት ሆነ ሲሉኝ ከኔ በቀር ሁሉም አልፈዋል አልኳቸው። ለመጀመርያ ግዜ ከቤት መውጣት ደበረኝ። አለመርባት ስሜት ተሰማኝ.. እድል የለኝም አልኩ.. ምን አለ ሞቼ ብሆን አልኩ.. ድብርት አከሳኝ። አብሮ አደጎቼ ጋ መሆን አልፈለኩም ነበር። ኋላ የምቀር መሰለኝ ....የሆንኩትን የገጠመኝን ቀላል እንደሆነ የሚያሳምነኝ አንድም አላገኘሁም። መውደቅን ፥ ማነስን ፥ ብቻዬን ተጋፈጥኩት። እናቴ ብቻ ናት የራሱ ጉዳይ አንተ ብቻ ደና ሁንልኝ ያለቺኝ ዋናው ጤና ነው የሚቀጥለው ታሻሽላለህ አለቺኝ። ደግሜ መፈተን እንደማልችል አልገባትም ነበር። . . . አጎቴ ገራዥ ነበረው እሱ ጋ መዋል ጀመርኩ። የማታ Auto mechanic መማር ጀመርኩ። ጎበዝ ባለሙያ ሆንኩኝ። practically እወቀቱን ሳየው ስለምውል theory ቀለለኝ። ከክፍሉ አንደኛ እየወጣሁ ስራ ቦታም ጎበዝ መካንኪ ሆንኩኝ። ብቻ መቆም ለመድኩኝ ብቻ መውደቅ ምን ምን እንደሚል ጌታዬ አስተማረኝ የወደቀ ሰው እንዴት እንደሚፅናና ተማርኩኝ መውደቅ ሁሉ መውደቅ እንዳይደለ ተማርኩ ዛሬ ሃብታም ነኝ። የመኪና 'spare part' አስመጪ እና ላኪ ሆኛለሁ። ጌታ ኋላ የቀረን ግምባር ቀደም ማድረግ እንደሚችል ፤ በሁሉም ሰው የታዘነለትን ፥ በሁሉም ዘንድ የሚያኮራበት ሰው ማድረግ እንደሚችል አይቻለሁ። ያኔ ብቻዬን ስሆን የተሰማኝ ውድቀት የወለደልኝ ጥንካሬ እና ብስለት ዛሬ ድረስ ስንቴ አሻግሮኛል...! አንዳንዴ ተለይቶ የመውደቅ መጨረሻ ድልም ሊሆን ይቻላል!! © Adhanom Mitiku 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
👍 40 13👏 2
ናፍቀሽኛል ጊዜ ይሮጣል አሉ ጊዜ ይበራል አሉ አንደዚ በማለት ሚያወራ ሰው ሁሉ ምናለ ቢያስረዱኝ ይህንን ከቻሉ : : ለኔ ጊዜው አይሮጥም በፍፁም አይበርም እንደው ይባስ ብሎ መቁጠሩንም ትቷል ካንቺ ከራቅኩ ወዲህ ቀኑ አመት ሆኗል እናም ርዝማኔው አሁንስ ከብዶኛል የውነቴን ነው ምልሽ በጣም ናፍቀሽኛል : : ሀልጊዜም ቢሆን አንቺን ነው ማስብሽ ከራሴ በላይ ነው እኔ የምወድሽ በደስታ ቆዪልኝ በአካል እስካገኝሽ:: 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
👍 12🥰 2👏 1
...........ሳቅሽ....... ሳቅሽ  ለመተብተብ ብቻ ሚቃጣው የሸረሪት ድር ነው  ሸማ የማይወጣው ሳቅሽ የተንኮል ፈገግታ  የተንኮል ወትብትብ የዘመን ማዘሎ  ማይቆረጥ ማተብ ሳቅሽ የማያልቅ ፈትል  የማይጠፋ እሳት የሳቅሽ ሚስጥር ነው እሳትን ማስነሳት       By kerim 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
10👍 7🥰 1👏 1
❤️❤️‍🔥💔የልቤን ብታዪ❤️❤️‍🔥💔 አይኔ እንደ ቆራጥ አንቺን ባያይሽም      ሞልቶት ትንሽ ኩራት አፌም ጀነን ብሎ አሻፈረኝ ቢልም       ስምሽን ለመጥራት ጆሮዬም ቢያስመስል ከቶ እንደማይሰማ       አንቺን የሚል ወሬ በሄድሽበት መሄድ ሁሌ መከተሉን        ባይሞክረው እግሬ           በይ ልንገርሽ ዛሬ ሞኝ ልብ እንዳለኝ ማያውቅ ማስመሰል ጠዋትና ማታ ስራው አድርጎታል          አንቺን ማሰላሰል። 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
11👍 5🥰 4
🔴Dot Coin ማይን በማድረግ ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ ያውቃሉ? 💸💵Dot Coin active ሆነው ማይን ለሚያደርጉ ሰዎች 0.5 ton = $3.5 እየሰጠ ይገኛል። 🤑🤑🤑🤑🤑 ታዲያ ምን እየጠበቃቹ ነው ጊዜው ሳያልቅ አሁኑኑ ተቀላቀሉ። Click here ሚለውን በመጫን መቀላቀል ትችላላችሁ ይመቻችሁ። ✌️ 👇👇👇👇 Dot Coin click here
Show all...
ቀጣዩ ‘ስቴፕ” (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ቀነኒሳ አይነት ልእለ-ሰብ ሰዎችን ስታይ የእድሜ መገስገስ አያስፈራህም፤ እድሜ ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ብለህ ትፎክራለህ ፤ “ ቀነኒሳ አንበሳ “ ይላል ጀግና አሞጋሹ ጀግና ቴዲ አፍሮ፤ አንበሳ በምን እድሉ ነው ቀነኒሳን የሚስተካከለው ? አንድን አንበሳ በሀያ አመቱ በአጸደ ስጋ አታገኘውም፤ ካገኘኸው ጭርጭስ ብሎ፥ ጎብጦ ቁርበቱን እየላሰ ተኝቷል፤ ቀነኒሳ ግን በአርባ ሁለት አመቱ ማራቶን ያሸንፋል፤ ዋናው ጥያቄ- ለእድሜ ትገብራለህ ወይስ እድሜን ታስገብራለህ?” የሚል ነው፤ ርግጥ ነው እኔ በዚህ እድሜየ እንኳን ማራቶን ልሮጥ ውድድሩን በቲቪ ጨርሶ ለማየት ራሱ አቅምና ትግስት የለኝም፤ አንዳንድ ቀን፥ ከባለንጀሮቼ ጋር ኳስ ለማየት እቀመጣለሁ፤ በተቀመጥኩበት ሶፋ ላይ አራት ዙር ግልገል እንቅልፍ (ናፕ ) እተኛለሁ፤ በቀደም ከስንት ጊዜ በሁዋላ ጂም ሄድኩ፤ አሰልጣኙ ተቀብሎ ገና የስነልቦና ምክር እንኳ ሳይሰጠኝ “ ሀያ ጊዜ ቁጭ ብድግ ስራ “ አለኝ ፤” ቁጭ ማለቱ ላይ ችግር የለብኝም ብሮ ! ብድግ ማለቱ ላይ ግን እገዛህን እሻለሁ “ ብየው ፥ ትንሽ ወልመጥ ወልመጥ አልሁ ፤ ቀጠለና አስር ፑሽ አፕ አዘዘልኝ፤ አምስቱን ወገቡን እንደተመታ እባብ እየተቅመደምድሁ ሰራሁ፤ በተረፈች፥ ጉልበቴ ምንጣፉን እየሳምኩ ተነሳሁ፤ በመጨረሻ ሳልፈልግ ፥በርከክ ብየ ለወጫጫ ተራራ ሰገድሁ፤ ማጠቃለያው ላይ፥ አምስት ኪሎ ድምቤል አሸከመኝ፤ ከዚያ መስታውት ፊት ቆሜ ፥ ከክርኔ በላይ ያለውን ክንዴን ክፍል እየዳበስኩ ገመገምኩት፤ ብዙም ሳይቆይ አሰልጣኙ ከተፍ አለና፥ “አሁን አሟሙቀሀል፤ ቀጣዩ ስቴፕ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ” ሲል ጠየቀኝ፥ “ ቀጣዩ “ ስቴፕ”ማ ንቅሳት እሚሰሩ ሰዎችን ማፈላለግ ነው ዠለስ“ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
👍 21🤩 12
🔴Range for sell Grade 60/70 Year. 2023 Origin. Iran Quantity 5000 Barrel Test. Tested Location legally Imported Price 21,000 / barrel 📲0913295326
Show all...
👍 7
/ ለምን ጠላሻለሁ/ መቼ ተለወጥኩኝ እንደዛው ነኝ እኔ ተለዉጧል እርሱ አይደለም እንደ ያኔ፤ እያልሽ የሌለኝን ማንነት አትስጪኝ ከመሬት አንስተሽ ከሰው አፍ አታውጪኝ፤ ደሞስ መች ሊጨክን ልቤስ ሊደነድን በሕይወት ሳለሁኝ ከቶ ሳልሆን በድን፤ የኔ የዋነቴን የልቤንም አይተሽ ዛሬ ምን ሲል ታየሽ ያኔ የሄድሽው ትተሽ፤ እርግጥ ሰው ባጠፋው ፀፀቱ ባይቀርም ወደሽኝ ቢሆን ኖሮ በኔና አንቺ አይከርም፤ ታዲያ መች እንደዛ ሆኖ ያንቺ ቀረቤታ ፌዝ አዘል ነበረ የጥርስሽ ፈገግታ፤ ያኔ ማፍቀርን ጠግቤው መፈቀር ቢርበኝ ያንቺ ልብ በፍቅር መች አምኖ ቀረበኝ፤ አሁን ላይ ጥያቄሽ ለይቅር ከሆነ ጥፋት እንዳጠፋሽ ልብሽ ይህን ካመነ፤ በሰው ቂም አሊዝም ይቅር ብዬሻለሁ ዳግም ባልወድሽም ለምን ጠላሻለሁ; #መሳይ ግርማ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
👍 12👏 5 2
ዘርተሽብኝ ሄደሽ አምነትና ተስፋ በረሃው ነቃ አለ በማግስቱ አካ`ፋ! ጠረንሽ ሲያልፍበት መዐዛሽ ሲያልፍበት እንኳንስ ዘንቦበት በረሃው ይድናል ተስፋ ካካፋበት። ሲያሳሳኝ የነበር በሰው መደነቄ በሰዎች መናቄ ዛሬ ገና ገባኝ በረሃ እንደነበርኩ ከቶ አለማወቄ። ይህ ከንቱ ድንበሬ በተስፋሽ ተለካ እራስን ማወቅ ነው ሌላን ማፍቀር ለካ። By Yadel Tizazu 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
👍 25 3👏 2
💗❤️ወድሻለው💗❤️ - ወደኔ ተራምደሽ ቆመሽ ካጠገቤ - ድንገት አይኔ አይቶሽ ሲደነግጥ ልቤ - ሻል እንዳለኝ ወዲያው ከጎንሽ እንዳለው - ለመናገር ሀቁን አይንሽን እያየው - ውስጤን አሳወኩሽ ብዬ ወድሻለው።          :          : 🎈 ወንዶች ለምትወዷት ሴት ላኩላት   📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Show all...
🥰 12👍 8