cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢየሱስ ያድናል

ስሙን የምጠራ ሁሉ ይድናል

Show more
Ethiopia12 053The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
129
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🙏እንኳን ወደ Offical ፈረሰ ማይል ብር ✅ ቦት በደህና መጡ.ፈረሰ ማይል ብር ✅ ቦት ለዘመድ አዝማድ እና ለጓደኛዎ ሼር በማድረግ በCBE BIRR / ሞባይል ባንኪግ እና ሞባይል ካርድ ገንዘብ መስራት ይችላሉ! ♻️1 ሰው ሲጋብዙ 5.00Birr ያገኛሉ 🔻ፈረሰ ማይል ብር ✅ ይቀላቀሉ ➡️ https://t.me/FERES_BIRRBOT?start=r0952706745
Show all...
ያንዳንዳችን በተሰጠን ብርሃን መጓዝ ይኖርብናል፡፡ ቀዳሚዎቹ ተርጓሚዎች አንተ፣ መጽሐፍ ቅዱስና መንፈስ ቅዱስ ናችሁ፡፡ ይህንንም መልሰህ በተርጓሚው ላይ በሌላ አባባል እንዳትወስደው፡፡ እነዚህ የውይይት ጥያቄዎች የተሰጡት የዚህን መጽሐፍ ክፍል ዋና ዋና ጉዳዮች በሚገባ እንድታጤን እንዲረዳህ ነው። ይህም ማለት በተገቢው እንድታሰላስል ለማነሣሣት እንጂ በዚህ ብቻ እንድትወሰን አይደለም። 1. የዚህ የቆይታ ጊዜ ዓላማው ምንድነው? 2. እጅግ ብዙ ተርጓሚዎች ምዕራፍ 10 ላይ ያለውን መልአክ ለምን እንደ ክርስቶስ ለመውሰድ ሞከሩ? 3. ቁ. 10፡7 ላይ የተጠቀሰው የእግዚአብሔር ምሥጢር ምንድነው? 4. ዮሐንስ እንዲበላ የታዘዘው ትንሽ መጽሐፍ ምንድነው? 5. ሁለቱ ምስክሮች እነማን ናቸው? መልእክታቸው ምንድን ነበር? 6. 11፡9 የኢየሩሳሌምን ከተማ ነው የሚገልጸው ወይስ የእግዚአብሔር ተቃዋሚ የዓለም መንግሥታት? ለምን? 7. በዚህ የቆይታ ጊዜ ላይ ያሉትን የብሉይ ኪዳን ጠቃሾች ዘርዝር? - NIV - shared using Simple Bible
Show all...
--------------------------------------------------- “ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም” 10፡11 ላይ ያለውን ማስታወሻ ተመልከት።  “ሦስት ቀን ተኵል” የቁ. 9 ጊዜ ከቁ. 11 ጋር ሲደባለቅ ከቁጥር ሰባት ጋር እኩል ይሆናል፣ እሱም በራዕይ እጅግ ተደጋግሞ ጥቅም ላይ የዋለ። ይህ ሁነት የእግዚአብሔር ፍጹም ሰዓት ነው። Revelation(ራዕይ) (11:10) እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስለ ሣቀዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል በደስታም ይኖራሉ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ። ----------------------------------------------------- “ደስ ይላቸዋል በደስታም ይኖራሉ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ” አንዳንዶች ይሄን የሚመለከቱት እንደ ፑሪም (የአይሁድ በዓል ግብዣ) ነው (አስቴር 9፡19፣22)። እሱም እጅግ የሚመሳሰለው ከዮሐንስ 16፡20 ጋር ነው (“ዓለም ደስ ይለዋል”)። ይህ የማያምነው ዓለም ደስታ የሁለቱን ምስክሮች መልእክት ኃይል ያመለክታል፣ የማያምኑት ግን ንስሐ አይገቡም (ዝከ. 9:20-21; 16:9,11)። Revelation(ራዕይ) (11:11) ከሦስቱ ቀን ተኵልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ፥ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው። ----------------------------------------------------- “ሦስቱ ቀን ተኵልም” ይህ ከዳንኤል የተጠቀሰ ነው፣ እሱም የስደቱ ተምሳሌታዊ ጊዜ የሆነ። 11፡9 ላይ ያለውን ማስታወሻ ተመልከት።  “ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው” ይህ የሕዝቅኤል 37 ጠቃሽ ነው፣ የደረቁ አጥንቶች ሸለቆ። ይህም የዕብራይስጥ ቃል “ruach” ዓይነት ነው፣ ፍችውም መተንፈስ፣ ነፋስ፣ እና መንፈስ (እንደ የግሪኩ ቃል pneuma)። ============================== ልዩ ርዕስ፡ መንፈስ በመጽሐፍ ቅዱስ I. የግሪክ ቃላት ሀ. pneō፣ መንፋት ለ. pno‘፣ ነፋስ፣ ትንፋሽ ሐ. pneuma፣ መንፈስ፣ ነፋስ መ. pneumatikos፣ በመንፈስ መወሰድ ሠ. pneumatikōs፣ መንፈሳዊነት II. የግሪክ ፍልስፍናዊ ዳራ (pneuma) ሀ. አርስቶትል ቃሉን የተጠቀመበት እንደ የሕይወት ኃይል ነው፣ እሱም ከልደት ጀምሮ ራስን እስከመግዛት ድረስ እየዳበረ የሚሄድ ለ. ስቶይኮች ቃሉን የሚጠቀሙበት ከpsuch‘፣ (ነፍስ) ጋር በተመሳሳይ ነው፣ psuch‘፣ (አዕምሮ) ጭምር፣ ከአምስቱ የስሜት ሕዋሳት እና ከሰው አስተሳሰብ ጋር በተያያዘ። ሐ. የግሪክ አስተሳሰብ - ቃሉ ከመለኮታዊ ድርጊት ጋር አቻ ሆኗል (ማለትም፣ መናፍስት ጠሪነት፣ አስማት፣ መተት፣ ሟርት፣ ወዘተ…) III. ብሉይ ኪዳን (ruah) ሀ. የአሀዳዊው አምላክ ድርጊቶች (ማለትም፣ መንፈስ ቅዱስ፣ በብኪ 90 ጊዜ ያህል ጥቅም ላይ ውሏል) 1. በአዎንታዊ፣ ዘፍጥረት 1፡2 116 2. በአሉታዊ፣ 1ሳሙ. 16:14-16፣23፤ 1ነገሥ. 22:21-22፤ ኢሳ. 29:10 ለ. እግዚአብሔር የሰጠው ሕይወት በሰው ውስጥ የሚሠራው (ማለትም፣ የእግዚአብሔር እስትንፋስ፣ ዘፍ. 2፡7) ሐ. ሴፕቱዋጂንት ruahን በ pneuma ይተረጉመዋል (100 ጊዜ ያህል በLXX (ሰባው) ጥቅም ላይ ውሏል) መ. በኋለኞቹ ራቢያዊ ጽሑፎች፣ የፍጻሜ ትንቢት ጽሑፎችና የሙት ባሕር ጥቅሎች፣ እነሱም የዞሮአስትሪያኒዝም ተጽዕኖ ያለባቸው፣ pneuma ጥቅም ላይ የዋለው ለመላእክት እና ለአጋንንት ነው IV. አዲስ ኪዳን (pneuma) ሀ. የእግዚአብሔር ልዩ መገኘት፣ ኃይል፣ እና ሰጭነት ለ. መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የቤተ-ክርስቲያን ሥራ ጋር ይያያዛል 1. ትንቢት 2. ተአምራት 3. ወንጌልን በግልጽ ለማወጅ 4. ጥበብ (ማለትም፣ ወንጌል) 5. ደስታ 6. አዲሱን ዘመን የሚያመጣ 7. ዳግም ልደት (ማለትም፣ መቃተትና ማደር) 8. ክርስቶስን መምሰል 9. የአገልግሎት የተለያዩ ጸጋዎች 10. ለአማኞች መጸለይ መንፈስ ቅዱስ የሰው ልጆችን ፍላጎት ያነቃል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ላለው ኅብረት፣ ይኸውም እነሱ ለተፈጠሩበት። ይህ ኅብረት ይቻላል፣ ምክንያቱም ከኢየሱስ፣ ከእግዚአብሔር መሲሕ አካልና ሥራ የተነሣ። አዲሱ መንፈሳዊ ንቃት ክርስቶስን ወደ መሰለ ሕይወት፣ አገልግሎት፣ እና መታመን ይመራል። ሐ. የበለጠ የሚታወቀው እንደ መንፈሳዊ ቀጣይነት ባለው መንፈስ ቅዱስ በአንድ ዳርቻ በኩል፣ እና የሰው ልጅ እንደ ሥጋዊ የዚህ ዓለም ፍጡር፣ ግን ደግሞ በሌላው ዳርቻ የእግዚአብሔር አምሳል በሆነ መንፈሳዊ ፍጡር ነው። መ. ጳውሎስ የአዲስ ኪዳን ደራሲ ነው፣ እሱም የመንፈስ ቅዱስን/መንፈስን ሥነ-መለኮት ያዳበረ ነው። 1. ጳውሎስ መንፈስን ይጠቀማል ሥጋን ለመቃረን (ማለትም፣ የኃጢአት ተፈጥሮ) 2. ጳውሎስ መንፈስን ይጠቀማል ሥጋዊነትን ለመቃረን 3. ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስን/መንፈስን ይጠቀማል የሰዎችን አስተሳሰብ፣ እውቀት፣ እና ሕላዌ ለመቃረን ሠ. ከ1ቆሮንቶስ ጥቂት ምሳሌዎች 1. መንፈስ ቅዱስ፣ 12፡3 2. የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ የሚገለጸው በመንፈስ ቅዱስ በኩል ነው፣ 2፡4-5 3. የእግዚአብሔር ድርጊቶች በአማኝ ውስጥ ሀ. አዲስ አስተሳሰብ፣ 2:12፤ 14:14፣32 ለ. አዲስ ቤተ-መቅደስ፣ 3:16፤ 6:19-20 ሐ. አዲስ ሕይወት (ማለትም፣ ሞራላዊነት)፣ 6፡9-11 መ. አዲስ ሕይወት፣ በጥምቀት ተምሳሌታዊ የሆነ፣ 12፡13 ሠ. ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት (ማለትም፣ ዳግም ልደት)፣ 6፡17 ረ. የእግዚአብሔር ጥበብ፣ የዓለም ጥበብ ሳይሆን፣ 2:12-15፤ 14:14፣32፣37 ሰ. እያንዳንዱ አማኝ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ያለው መሆኑ፣ ለአገልግሎት፣ ምዕራፍ 12 እና 14 4. መንፈሳዊው በተቃርኖ ከሥጋዊው ጋር፣ 9:11፤ 10:3፤ 15:44 5. መንፈሳዊው ዓለም በተቃርኖ ሥጋዊው ዓለም፣ 2:11፤ 5:5፤ 7:34፤ 15:45፤ 16:18 6. ወደ ሰዎች መንፈሳዊ/ውስጣዊ ሕይወት የማመላከቻ መንገድ፣ ከአንዱ ሥጋዊ አካል ልዩነት እንዳለው፣ 7፡34 ረ. ሰዎች በተፈጥሮ በሁለት ዓለማት ነው የሚኖሩት (ማለትም፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ)። የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ከነበረው ወዳጅነት ወድቋል (ዘፍ. 3)። በክርስቶስ ሕይወት፣ ትምህርቶች፣ ሞት፣ ትንሣኤ፣ እና በመመለሱ ተስፋ በኩል፣ መንፈስ ቅዱስ የሰው ልጆችን ይማልዳል በወንጌል እምነትን እንዲለማመዱ፣ በዚሁም ነጥብ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ይኖራቸው ዘንድ የተመለሱ። መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አካል ሲሆን እሱም አዲሱን የጽድቅ ዘመን ባሕርይ ያደረገ ነው። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር አብ ወኪል እና የወልድ ተጠሪ ነው፣ በዚህ “ዘመን”። ችግር የሚኖርበት ምክንያት አዲሱ ዘመን በጊዜው በመምጣቱና፣ የአሮጌው ዘመን ዐመጻ ገና ባለበት ጊዜ መሆኑ ነው። መንፈስ ቅዱስ አሮጌውን ወደ አዲስ ይለውጠዋል፣ ሁለቱም አንድ ላይ ቢኖሩም። ============================== Revelation(ራዕይ) (11:12) በሰማይም፦ ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ። ----------------------------------------------------- “በሰማይም። ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤” አንዳንዶች የሚመለከቱት የቤተ ክርስቲያን ድንገተኛ መነጠቅ ነው፣ ቁ 4፡1 ላይ፣ ዮሐንስ ወደ ሰማይ የተወሰደበት፣ ሌሎች የሚመለከቱት በመከራው መካከል የሚሆን የቤተ-ክርስቲያን ም
Show all...
Elohim, ፈጣሪ አምላክ እንደ ሰጪ እና ጠባቂ (ዘፍ. 1:1; መዝሙር 104) 3. El Shaddai (ዝከ. 1:8), ብርቱና ርኅሩኅ አምላክ፣ እሱም ለመለኮት የአባቶች ስም የነበረ (ዘጸ. 6:3) ልዩ ርዕስ፡ የመለኮት ስሞች 1፡8 ላይ ተመልከት።  አአመመቅ “ያለህና የነበርክ” አኪጀት “ያለው የነበረው የሚመጣውም” አየተመት “ያለና የነበረ” አእት “ያለና የነበረ” አኢመቅ “ያለ፣ የነበረ” ይህ የተለመደው የእግዚአብሔር ገለጻ የወደፊት ገጽታ (ከአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የግሪክ አናሳ ቅጥልጣይ ጽሑፎች በቀር) ተትቷል፣ እግዚአብሔር መንገሥ በመጀመሩ ምክንያት። የእነዚህ ቅደም ተከተላዊ ገጽታዎች፣ ከሦስቱ የመጨረሻው በራዕይ መጽሐፍ ፈጽሞ በድጋሚ አልተጠቀሱም። መንግሥቱ መጥቷል (ዝከ. 11፡15-16)! ይህም ለማኅተሞቹ፣ መለከቶቹ፣ እና ጽዋዎቹ ትይዩአዊ ግንኙነት ማጠቃለያ ንድፈ-ሐሳብ ማስረጃ ይሰጣል!  አአመመቅ “ትልቁን ኃይልህን ስለያዝክ ስለነገሥህም” አኪጀት “ትልቁን ኃይልህን ስለያዝክ ስለነገሥህም” አየተመት “ትልቁን ኃይልህን ስለያዝክ እና ስለነገሥህ” አእት “ትልቁን ኃይልህን ስለያዝክ እና ስለገዛህ” አኢመቅ “ትልቁን ኃይልህን ስለያዝክ እና ስለነገሥህ” ይህ የተጠናቀቀ የድርጊት አመላካች ነው፣ የድርጊት የአሁን አመላካች የተከተለው። ኃይሉ ሁልጊዜም የእርሱ ነው፣ ግን ንግሥናው አሁን ይጀምራል (የመግቢያ ድርጊት)። Revelation(ራዕይ) (11:18) አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ። ----------------------------------------------------- “አሕዛብም ተቆጡ” ይህ ጠቃሽ ነው የመዝ. 2; 46:6; እና ሕዝቅኤል 38-39 (በሴፕቱዋጂንት የአስቴር አፖካሎፕቲካዊ መግቢያ ሊሆን ይችላል)። ይህ የአሕዛብ ቁጣ በሁለት መንገዶች ሊታይ ይችላል። 1. የወደቀው የዓለም ሥርዓት እግዚአብሔርን እና ዕቅዱን እና አገዛዙን እና ሕዝቡን ይጠላል 2. በእግዚአብሔር ላይ የፍጻሜ ዘመን ዐመጻ ይኖራል፣ በውጊያ የሚገለጥ (አርማጌዶን፣ ራዕይ 20)  “ቁጣህም መጣ” ይህ የመዝ. 2 ወይም 110፡5-6 ጠቃሽ ይሆናል። ይህ የግሪክ ቃል orgē ነው። ሙሉውን ማስታወሻ 7፡14 ላይ ተመልከት። 119  “ጊዜው መጣ” የጌታ ቀን ለአንዳንዶች የፍርድ ቀን ሲሆን ለሌሎች ደግሞ የሽልማት ነው። ይህ መንታ ገጽታ ማቴ. 25:31-46 እና ራዕ. 20:11-15 ላይ ይታያል። ሰዎች ሁሉ (ትንሾችም ትልቆችም) በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ፣ ስለ ሕይወታቸውም ምላሽ ይሰጣሉ (ገላ. 6:7; II ቆሮ. 5:10)። “በሙታንም ላይ ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ” የፍጻሜው ዘመን የእግዚአብሔር ፍርድ ማቴዎስ 25 እና ራዕይ 20 ላይ ተብራርቷል። ይህ ሐረግ የሚያጸናው የራዕይን ትርጓሜ በሰባት ገቢሮች (ትዕይንቶች) ነው፣ የፍጻሜ ዘመኑ የሚከሰተው በእያንዳንዱ ምድብ የሆነበት (በተለይም በማኅተሞቹ፣ መለከቶቹ እና ጽዋዎቹ ላይ ግልጽ የሆነ)።  “ለባሪያዎችህም ለነቢያት” ይኸው ሐረግ 10፡7 ላይ ይከሰታል። ዮሐንስ ራሱን የሚገልጸው እንደ ነቢይ ነው፣ መጽሐፉንም እንደ ትንቢት፣ ስለዚህ፣ ይህ ቃል ዘወትር በራዕይ መጽሐፍ ጥቅም ላይ ይውላል። ማለት የሚቻለው ይህ ቃል “ሐዋርያ” የሚለውን መጠሪያ መተካቱን ነው (ዝከ. 10:7; 11:10,18; 16:6; 18:20,24; 22:6,9)። ልዩ ርዕስ፡ የአኪ ትንቢት 16፡6 ላይ ተመልከት።  “ቅዱሳን” “ቅዱሳን” የሚለው ቃል አማኞች በክርስቶስ የሚኖራቸውን አቋም የሚያመለክት እንጂ፣ ኃጢአት የለሽነታቸውን አይደለም። እሱም ደግሞ ቀጣይነት ያለውን ክርስቶስን መምሰላቸውን መግለጽ ይኖርበታል። ቃሉ ዘወትር የብዙ ነው፣ ፊሊ. 4፡21 ላይ ካልሆነ በቀር። ሆኖም፣ በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ እንኳ የተጠቃለለ ነው። ክርስቲያን መሆን የማኅበረሰቡ፣ የቤተሰቡ፣ የአካሉ አባል መሆን ነው። ልዩ ርዕስ፡ ቅዱሳን 5፡8 ላይ ተመልከት። ይህ መጠሪያ በርግጥ የሚወክለው የአኪ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነው፣ ቤተ ክርስቲያንን።  “ለታናናሾችና ለታላላቆችም” ይህ የሚመስለው በዚህ ቁጥር ሁለት ወገኖች ብቻ መጠቀሳቸውን ነው፣ ነቢያትና ቅዱሳን። “ትንንሾችና ትልልቆች” የሚለው ይህ ሐረግ ቁ. 19፡5 ላይ ይገኛል። እሱም በዮሐንስ ወንጌል የተወደደ አገላለጽ ነበር (ዝከ. 13:16; 19:5,18; 20:12; 19:5 የመዝ. 115፡13 ጠቃሽ የሆነ፣ ይኸውም ያሉትን ወገኖች ሁሉ የሚያካትት)።  “ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ” ይህ የወደቀው ሰው ባሕርይ ዘፍጥረት 3 እና ሮሜ. 8፡18-22ን ያመለክታል። ክፉ ሰዎች በስግብግብነት እና በግለኝነት በመጠቀም፣ አዛብተው በመጠቀም፣ አላግባብ የእግዚአብሔርን ሥጋዊ ፍጥረት ይጠቀማሉ። ይሄም ሊተረጎም የሚችለው፣ ክፉው የሰው ልጅ፣ እሱም እግዚአብሔር በምድር ላይ ፍርድ እንዲያመጣ እንደሚያስገድደው ነው (የጥፋት ውኃ፣ ዘፍጥረት 6-9፤ የግብፅ መቅሠፍቶች፣ ዘጸዓት 7-12፤ የኪዳን ርግማኖች፣ ዘዳግም 27-28፤ ወይም በእሳት የምትጠፋው ምድር፣ 2 ጴጥ. 3፡10)። ራዕይ ላይ፣ ማኅተሞቹ ¼፣ መለከቶቹ 1/3፣ እና ጽዋዎቹ አጠቃላይ ጥፋት በምድር ላይ ያደርሳሉ። Revelation(ራዕይ) (11:19) በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ። ----------------------------------------------------- “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ” ይህ ራዕይ የሚጀምረው በሰማይ በተከፈተ በር መሆኑን አስታውስ (ዝከ. 4፡1፤ 15፡5)። እንግዲህ፣ የእግዚአብሔር ሰማያዊ መቅደስ ውስጠኛው ክፍል ሊታይ ይችላል (ዕብ. 8:5; 9:23-28)። ኢየሱስ ሲሞት የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች መቀደዱ የሚያመለክተው አሁን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ለሁሉም መቻሉን ነው፣ በክርስቶስ በኩል (ማቴ. 27:51; ማርቆስ 15:38; ሉቃስ 23:45; ከ ዕብ. 9:8; 10:20 ጠቃሽ ሆነዋል)። ይኸው ተመሳሳይ ተምሳሌት እዚህ ተደግሟል። እግዚአብሔር ለሁሉም ይገኛል። የሰማይ ውስጣዊ መቅደስ አሁን ሙሉ ለሙሉ ተከፍቶ ይታያል።  “የኪዳኑም ታቦት” የኪዳኑ ታቦት በሆነ ጊዜ በባቢሎን ምርኮ ወቅት ጠፍቷል (ወይም ወደ ግብፅ ፈርዖን ሺሻክ፣ 1 ነገሥ. 14፡25)። እሱም ተምሳሌት የሚሆነው ለእግዚአብሔር መገኘት ነው፣ እስራኤል የዮርዳኖስን ወንዝ ከተሻገሩ በኋላ፣ ወደ ተስፋይቱ ምድር። እሱም ደግሞ ተምሳሌት የሚያደርገው የእግዚአብሔርን የኪዳን ቃሎች ነው፣ እሱም ምሥጢርን የሚያመለክት (ዝከ. 10፡7)፣ የእግዚአብሔር የመቤዠት ዓላማ ለሰው ልጆች ሁሉ (ሮሜ. 16:25-26)። በብኪ ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር ይሄንን ቅዱስ ዕቃ የሚቀርበው፣ በዓመት አንድ ጊዜ በመቀደስ ቀን (ሌዋውያን 16)። እንግዲህ፣ የእግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መገኘት መምጣት ይችላሉ።  “መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ” ይህ ከ8:5 እና 16:18-21, እሱም ዘጸ. 9:24 and 19:16- 19ን የሚያንጸባርቅ። የውይይት ጥያቄዎች ይህ የጥናት መመሪያ ትርጓሜ ሲሆን፣ ያም ማለት ግን መጽሐፍ ቅዱስን በግል ለምትተረጕመው ኃላፊነቱን ትወስዳለህ ማለት ነው፡፡ እ
Show all...
ሥጢራዊ መነጠቅ ነው፣ እነዚህ ሁለት ምስክሮች ወደ ሰማይ የተጠሩበት፣ በዚህ ቁጥር ላይ። እዚህም ደግሞ የእኛ ቅድመ-ግምቶች እና ሥነ-መለኮታዊ አቋሞች፣ የተምሳሌታውያኑን፣ አሻሚዎቹን ጽሑፎች ትርጉሞች ያወጣሉ! 117  “ከዚያም እነርሱ ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።” ይህ መለኮታዊ መጓጓዣ ነው። መሲሑ በሰማይ ደመና ይጓጓዛል፣ ዳን. 7፡13 ላይ። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ያረገው በደመና ነው (ሐዋ. 1፡9)። ኢየሱስ በሰማይ ደመና ይመለሳል ማቴ. 24:30; 26:64; ማርቆስ 13:26; I ተሰ. 4:17; ራዕ. 1:7; 14:14)። Revelation(ራዕይ) (11:13) በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፥ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፥ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፥ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፥ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ። ----------------------------------------------------- “በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፥ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ” የመሬት መንቀጥቀጥን በተመለከተ ራዕይ ላይ ሰባት ማጣቀሻዎች አሉ (ዝከ. 6:12; 8:5; 11:13,19; 16:18)። ይህ የሚያሳየው በመከናወን ላይ ያለውን፣ ቀጣዩን፣ የተወሰነውን የእግዚአብሔርን ፍርድ ነው፣ በማያምኑት ላይ። ይህም የሕዝ. 38፡17-23 ጠቃሽ ይሆናል።  “የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፥ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።” በርካታ ውይይቶች “የተቀሩት” በሚለው ቃል ላይ ተካሂደዋል። እሱም ሊያመለክት የሚችለው 1. በጥሬው የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች (ዘካ. 12፡10) ወይም ሮም 2. በመከራው ሰዓት የዳኑት፣ ማለትም፣ በእውነት ንስሐ የገቡ 3. አማኝ አይሁድ፣ ከሮሜ 11 4. ሰዎች፣ እንደ ናቡከደነፆር እና ሲረስ የመሳሰሉት፣ በእግዚአብሔር ድርጊት የደነገጡት፣ ነገር ግን በእውነት ያልተለወጡት። በ9:20-21; 14:7-8 እና 16:10 ምክንያት፣ ቁ. 4 የተሻለ አማራጭ ነው። ሆኖም፣ 16፡9 ላይ ክብር መስጠት ከንስሐ ጋር ይያያዛል። እሱም በርግጥ የሚቻለው እነዚህ (አይሁድ ወይም ጣዖት አምላኪዎች) አምነዋል! ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ ዓይነተኛ ዓላማ ነው (ዝከ. 9:20-21; 16:9,11) Revelation(ራዕይ) (11:14) ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል። ----------------------------------------------------- ይህ የመሸጋገሪያ አገባብ (9፡12፤ 12፡12)። Revelation(ራዕይ) (11:15) ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። ----------------------------------------------------- “የዓለም መንግሥት” ኪጀት እና አኪጀት “የዚህ ዓለም መንግሥታት” የሚል አላቸው። የብዙ ቁጥሩ በማናቸውም በጥንታዊ የግሪክ ጽሑፎች ላይ የለም።  “ሆነች” ይህ የድርጊት መካከለኛ (አረጋጋጭ) አመላካች ነው። ይህ የወደቀው የሰው ልጅ መንግሥታት አገዛዝ ፍጻሜና የአምላካችን አገዛዝ መጀመሪያ ነው (ዝከ. 12፡10)። አዲሱ የመንፈስ ዘመን በሙላት መጥቷል። ይህ የሚያረጋግጠውም የማጠቃለያው ንድፈ-ሐሳብ፣ እሱም፣ ዳግም ምጽአቱ የሚሆነው ከእያንዳንዱ ከሦስቱ የፍርድ ዑደቶች ፍጻሜ በኋላ ነው፡ ማኅተሞቹ (ዝከ. 6፡12- 17)፣ መለከቶቹ (ዝከ. 11፡15-18)፣ እና ጽዋዎቹ (ዝከ. 19)። ራዕይ ዜና መዋዕላዊ፣ ቅደም ተከተላዊ ተራ ያለው አይደለም፣ ነገር ግን በሰባት ዑደቶች ድራማዊ አቅርቦት ነው፣ እያንዳንዱም ተመሳሳይ ጊዜን የሚመለከት፣ ነገር ግን ማኅተሞቹ፣ መለከቶቹ፣ እና ጽዋዎቹ በተከታታይ እና በተጠናከረ ደረጃ የሆኑ ፍርዶች ናቸው (1/4፣ 1/3፣ ሙሉ)።  “ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ” አብና ወልድ እንዴት በቅርብ እንደተያያዙ ተገንዘብ (መዝሙር 2)። ደግሞም፣ የI ቆሮ. 15:24-28 እና ኤፌ. 5:5 አጽንዖት አሁን መፈጸሙን ተገንዘብ። አንዳንዶች ከዘካ. 14፡9 ጠቃሽ ይመለከታሉ፣ እሱም ሊሆን የሚችል፣ ምክንያቱም የዮሐንስ ተመራጭ የአፖካሊፕቲካዊ ምስያ ምንጭ ዳንኤል፣ ሕዝቅኤል፣ እና ዘካርያስ በመሆኑ።  “ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል” ይህ የሚያመለክተው የአምላካችንን ዘላለማዊ ንግሥና ነው (ዘጸ. 15:18; መዝ. 10:16; 29:10; ኢሳ. 9:6-7; ዳን. 2:44; 4:34; 7:14,27; ዘካ. 14:9; ሉቃስ 1:33; I ተሰ. 4:17; II ጴጥ. 1:11), የሚሊኒየማዊ ንግሥና አይደለም (ራዕይ 20) የክርስቶስ። ይህ በርግጥ የማቴ. 6፡10 የኢየሱስ ጸሎት ፍጻሜ ነው፣ ይኸውም የእግዚአብሔር ፍቃድ በምድር ላይ ይሆናል፣ በሰማይ እንደሆነ ሁሉ። የእግዚአብሔር መንግሥት ዋነኛ ጭብጥ ነው በወንጌላትና በራዕይ ላይ። ተለዋዋጭነትና ተቃርኖ አለው፣ በወቅቱ እውነታ (ድኅረ-ሚሊኒየማዊ እና በሚሊኒየማዊ) መካካል እና በወደፊቱ ቅድጅት (ታሪካዊ ቅድመ-ሚሊኒየማዊ እና ከፊል ቅድመ- ሚሊኒየማዊ)። ይኸው ተመሳሳይ ተለዋዋጭነት ደግሞ በምድራዊ ገጽታ (ሚሊኒየማዊ) እና በእርሱ ዘላለማዊ ገጽታ መካከል አለ። አንዳንድ አታቾች፣ አስተምህሮዎች፣ እና መሠረተ እምነቶች በተለዋዋጩ በአንደኛው ገጽታ ይኖራሉ፣ ነገር ግን ቀሪዎቹን ችላ ይሏቸዋል ወይም ይጠመዝዟቸዋል፣ ከራሳቸው ቅድመ-ግምት እና ሥነ-መለኮታዊ ሥርዓት ጋር እንዲሰማሙ ለማድረግ። 118 ለምዕራባውያን ሰዎች እጅግ ጠጠር ይላል፣ የምስራቃዊ ሥነ-ጽሑፍን ተለዋዋጭነት፣ ዘይቤአዊነት፣ እና ተቃርኖ ለማጣጣም፣ በተለይም አፖካሊፕቲካዊ ዘውጉን። ጌታችንና የእርሱም ክርስቶስ ነግሠዋል፣ በንግሥና ላይ ናቸው፣ ይነግሣሉም፤ ዝርዝሩ እጅግም አስፈላጊ አይደለም! መሲሐዊ ንግሥና ለተወሰነ ጊዜ ሊኖር ይችላል (I ቆሮ. 15:23-28); ብሔረ እስራኤል ጥቂት ክፍል ሊኖረው ይችላል (ሮሜ 11)። ሆኖም፣ የራዕይ ዘይቤዎችና ተምሳሌቶች ሁለንተናዊዋን ቤተ ክርስቲያንን እንጂ እስራኤልን አይመለከቱም (ዳን. 2:34-35,44)። እኔ በግሌ ክፍት ነው የምተወው፣ እስራኤል በፍጻሜ ዘመን ሁነቶች ላይ ድርሻ እንደሚኖረው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም ዝርዮች ቃል ስለ ገባ (ኢሳ. 9:6-7; ዘካ. 12:10) በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ በመመሥረት (ሕዝ. 36:22- 38)። Revelation(ራዕይ) (11:16) በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ ----------------------------------------------------- “ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች” ልዩ ርዕስ 4፡4 ተመልከት። Revelation(ራዕይ) (11:17) እንዲህ አሉ፦ ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤ ----------------------------------------------------- 17-18 ይህ የምስጋና ጸሎት በአኪጀት፣ አየተመት፣ እና አእት በቅኔ መልክ ነው የተጻፈው፣ በአአመመቅ እና አኢመቅ ደግሞ በስድ- ንባብ። እነዚህ ፈንቅለው የወጡ ጸሎትና ምስጋና የቀጣዩ መገለጥ የተሻሉ ተርጓሚዎች ናቸው (ከዝማሬዎች እና መልአካዊ ትርጓሜዎች ጋር)። 11፡17 “ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥” ይህ የሚያመለክተው ሦስቱን ዋነኛ የብኪ የእግዚአብሔር መጠሪያዎችን ነው። 1. ያህዌ፣ የኪዳን አምላክ አንደ አዳኝ (ዘጸ. 3:14; መዝሙር 103) 2.
Show all...
Revelation(ራዕይ) (11:1) በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ፦ ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ። ----------------------------------------------------- “በትር የሚመስል መለኪያ” ባለፉት ክፍሎች ዮሐንስ የተመለከተው መላእክት የሚሠሩትን ተግባራት ነበር። ነገር ግን ሰባተኛው መለከት ላይ ዮሐንስ በድርጊቱ ውስጥ ይገባል። 113 “የመለኪያ በትር” የሚለው ቃል (kalamos፣ በዚህ መልኩ ጥቅም ላይ የዋለው እዚህ ብቻ ነው) ሊያመለክት የሚችለውም የብኪን የወንዝ ዳር ሸንበቆ ነው፣ የቁመት መለኪያ መሣሪያ የነበረውን (ልዩ ርዕስ፡ ጽድቅ 19፡11 ላይ ተመልከት)። እነርሱም ከስምንት እና ሃያ ጫማ መካካል ቁመት ነበራቸው (ሕዝ. 40:5-42:20)።  “ተነሥተህ ለካ” መለካት ምልክት የነበረው (1) የተስፋ እድገትና ጥበቃ (ኤር. 31:38-40፤ ራዕ. 21:15)። ይህም የሕዝቅኤልን የፍጻሜ ሰዓት መቅደስ የሚያመለክት ይሆናል (ዝከ. 40-48) ወይም የዘካርያስን አዲሲቷን ኢየሩሳሌም (ዝከ. 1:16፤ 2:1-13)፤ ወይም (2) ፍርድ (II ሳሙ. 8:2፤ II ነገሥ. 21:13፤ ኢሳ. 28:17፤ ሰቆ. 2:8)። እዚህ፣ ምዕራፍ 7 ላይ እንዳለው ማኅተም፣ እግዚአብሔር ለአማኞች ያለውን ጥበቃ ምልክት ነው። ይህ የቆይታ ጊዜ ከምዕራፍ 7 ጋር ትይዩ ከሆነ እንግዲያውስ መቅደሱ ሞላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው (አማኝ አይሁድ እና አማኝ አሕዛብ)። እንግዲያውስ ይህ ከምዕራፍ 12 ጋር ትይዩ ነው።  “የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን” የመቅደሱ ማንነት የሚወሰነው አንዱ ባለው የትርጓሜ ቅድመ- ግምት ነው። 1. የዮሐንስ ምስያ ከሕዝቅኤል 40-48 ተወስዷል ብለን ብንገምት፣ እንግዲያውስ ይህ ጥሬአዊ የፍጻሜ ዘመን ቤተ-መቅደስ ነው፣ በኢየሩሳሌም ያለ (2 ተሰ. 2፡4)። 2. ሆኖም፣ ዘካርያስ 2 ነው ብለን ጠቃሹን ብናስብ፣ እንግዲያውስ ምስያው የእግዚአብሔር ከተማ ነች፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም። 3. ሰማያዊውን ቤተ መቅደስ ብናስብ (ዝከ. 7:15፤ 11:19፤ 15:58፤ ዕብ. 9:23) እንግዲያውስ የ7፡9 ብዛት ያለው ሕዝብ (ቤተ ክርስቲያን፣ እና ምዕራፍ 12 ላይ ያለችው ሴት) ትኩረት ሊሆኑ ይችላሉ (21፡15-16)። ዮሐንስ እዛ የሚያመልኩትን ሰዎች እንዲለካ መነገሩን መገንዘብ አስደናቂ ነው። ይህ ያልተለመደ ቃል ነው። ይህ ምስያ ከሕንፃ ላቅ ያለ ነገርን ያመለክታል። ይህ ምስያ ነው የእምነትን ሰዎች ከማያምኑት መለያ ምልክት የሚሆነው፣ የእግዚአብሔርን ቁጣ በመቀበል። ስለዚህ፣ እሱ በአማኞች ግንባር ላይ ከሚሆነው ከእግዚአብሔር ምልክት ትይዩ ነው (ዝከ. 7፡3-4)። Revelation(ራዕይ) (11:2) በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል። ----------------------------------------------------- “በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ” ይህ ከውጭ ያለ እድሞ ጽንሰ-ሐሳብ የሚያመለክተው ከታሪክ አኳያ የአሕዛብ ስፍራ ነው፣ በሔሮድስ ቤተ-መቅደስ። በርካታ የብኪ ጠቃሾች አሉ፣ ስለ ኢየሩሳሌም ሐሳብና በአሕዛብ ስለሚረገጠው ቤተ መቅደስ (መዝ. 79:1- 7፤ ኢሳ. 63:18፤ ዳን. 8:13፤ ዘካ. 12:3 በሴፕቱዋጂንት)። ኢየሱስ ቀጥተኛ ጥቅሻ ያደረገ ይመስላል ዳን. 8፡13ን ሉቃስ 21፡24 ላይ።  “አሕዛብ” 2፡26 እና 10፡11 ላይ ያለውን ማስታወሻ ተመልከት።  “አርባ ሁለት ወራት” ከታች ያለውን ልዩ ርዕስ ተመልከት። ===================================== ልዩ ርዕስ፡ አርባ ሁለት ወራት አርባ ሁለት ወራት የሚለው ቁጥር ከትንቢት አኳያ ባሕርይ የሚሆነው የስደቱን ጊዜ ነው። እውጭ ያለው ስፍራ መረገጥ፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በታሪክ የተለያዩ ጊዜያት በማያምኑት ሥር መሆኑን ምሳሌ ነው— አንቲከስ አፒፋነስ፣ ሮማውያን በ70 ዓ.ም፣ እና የፍጻሜው ዘመን የክርስቶስ ተቃዋሚ። አርባ ሁለት ወራት፣ ወይም የእሱ አቻ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። መነሻው የዳንኤል መጽሐፍ ይመስላል። 1. ዳንኤል 7፡25፤ 12፡7 “ዘመን፣ ዘመናት፣ የዘመናት እኩሌታ” ወይም 1277 ቀናት (“ጊዜ” ከዓመት አኩል አድርጎ በመገመት) ተጠቅሷል 2. ዳንኤል 8፡14 2300 ማታ እና ጠዋት ተጠቅሷል 3. ዳንኤል 12፡11 1290 ቀናት ተጠቅሷል 4. ዳንኤል 12፡12 1335 ቀናት ተጠቅሷል። ተመሳሳይ ሐረግ ራዕ. 12:6 (1260 ቀናት) እና 13:5 (42 ወራት) ተጠቅሷል። እነዚህ ሁሉ ሁነቶች ግምት ውስጥ ሲገቡ፣ የእነርሱ ልዩነት ሊል የሚሻው የቁጥሮቹን ተምሳሌታዊ ተፈጥሮ ነው፣ የእነርሱ ለአርባ ሁለት ወራት ተቀራራቢነት ሊያሳይ የሚሻው ለስደቱ ጊዜ ተምሳሌታዊ ቁጥር ነው። ሦስት ከግማሽ የሰባት እኩሌታ እስከሆነ ድረስ፣ እሱ የሚመስለው የተጠናቀቀው የመከራ ጊዜ አመላካች ነው፣ እንዲያጥር የተደረገው (ማቴ. 24:22፤ ማርቆስ 13:20፤ ሉቃስ 21:24)። መከራ በእግዚአብሔር ፍቅር የተወሰነ ነው፣ ፍርዱ እንደሆነ ሁሉ። =====================================  “ቅድስቲቱ ከተማ” ይህ ሊያመለክት የሚችለው ኢየሩሳሌምን ነው (ኢሳ. 52:1፤ ማቴ. 27:53)። ሆኖም፣ ራዕ. 3፡12 ላይ ያለውን መቅደስ ትርጓሜ ተከትሎ፣ የአኪ አማኞችን እንደሚጠቅስ፣ ተመሳሳይ ዘዴ ይህን ሐረግ መከተል ይኖርበታል። በራዕይ ኋለኞቹ ምዕራፎች እሱ የሚያመለክተው የአኪን የእግዚአብሔር ሕዝቦችን ነው (ዝከ. 20:9፤ 21:2፣10፤ 22:19)። ዮሐንስ ዘይቤዎችን ከብኪ አምጥቶ ለአኪ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ጥቅም ላይ አውሏቸዋል። ቤተ ክርስቲያን የተሠራችሁ ባመኑ አይሁድና አሕዛብ ነው። ራዕይ ላይ በአይሁድ ዘርም ሆነ በአሕዛብ ላይ ምንም ዓይነት አጽንዖት የለም። ከእንግዲህ ወዲያ አይሁድም ግሪክም የለም (1 ቆሮ. 12:13፤ ገላ. 3:28፤ ቆላ. 3:11)። Revelation(ራዕይ) (11:3) ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ። ----------------------------------------------------- “ለሁለቱ ምስክሮቼ ሥልጣን እሰጣለሁ” ይህ የሚያመለክት የሚመስለው የእግዚአብሔር አብን ንግግር ነው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ቁ. 8 ላይ ስለተጠቀሰ (ምንም እንኳ የግሪክ እጅ ጽሑፍ ችግር እዚህ ተውላጠ ስም ላይ ቢኖርም፣ እሱም ፒ47 እና  ላይ ስለተገደፈ)።  “ሁለቱ ምስክሮቼ” ስለ እነዚህ ብርቱ ሰባክያን ማንነት በርካታ ንድፈ-ሐሳቦች አሉ፡ 114 1. ጠቃሹ (ዝከ. ቁ. 4) ከዘካ. 4:3፣11፣14። ይህ በዋነኝነት የሚያመለክተው የዳዊትን ዘር መመለስ ነው፣ ዘሩባቤል፣ እና የታላቁ ካህን ዘር መመለስ ነው፣ ኢያሱ፣ እነርሱም ሁለቱ መንፈስ-መር መሪዎች ነበሩ (ሁለቱ የወይራ ዛፎች) ከባቢሎን ግዞት መመለስን የመሩ (ማለትም፣ የተመለሰ የእግዚአብሔር ሕዝብ)። 2. ሁለቱ መቅረዞች (ዝከ. 1፡20) የሚያመለክቱትም ሁለቱን ታማኝ ቤተ ክርስቲያኖችን ነው፣ ሰምርኔስ፣ 2፡8-11 እና ፊልድልፍያ፣ 3፡7-13። 3. ሁለቱ ምስክሮች የሚያመለክቱት በፍርድ ቤት የሚደረግን ምስክርነት ነው (ዘኍ. 35:30፤ ዘዳ. 17:6፤ 19:15)። 4. የእነዚህ ሁለት ምስክሮች ገለጻ የሚያመለክተው ኤልያስን (ሰማይን የዘጋ ከቁ. ቁ. 6፣ I ነገሥ. 17:
Show all...
1፤ 18:1፤ ሉቃስ 4:25፤ ያዕቆብ 5:17 እና እሳትን ማውረድ፣ ዝከ. I ነገሥ. 18:24፣38፤ II ነገሥ. 1:10፣12) እና ሙሴ (ውኃውን ወደ ደም የቀየረ ከቁ. 6፣ ዘጸ. 7:17-19)። እነዚህ ሁለቱ በመለወጥ ተራራ ላይ ከኢየሱስ ጋር ታይተዋል (ማቴ. 17፡4)። 5. በይነ ኪዳናዊው አፖካሊፕቲካዊ መጽሐፍ 1 ሔኖክ 90፡31 እና ሁለቱ የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ተርቱሊያን እና ሂፖሊተስ እንደሚያስረግጡት እነርሱ ከብኪ ሁለቱ ሰዎች ናቸው፣ ተፈጥሯዊ ሞትን ያልሞቱት፣ ሔኖክ (ዘፍ. 5:21-24) ኤልያስ (II ነገሥ. 2:11)። 6. የአኢመቅ የግርጌ ማስታወሻ የሚያስረግጠው፣ እሱ የሚጠቅሰው ጴጥሮስንና ጳውሎስን ነው፣ ሁለቱም በሮም ሰማዕት ሆነዋል፣ በኔሮ አገዛዝ (ገጽ 435)። እኔ በግሌ የምመለከታቸው እንደ መላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ምስክርነት ተምሳሌት ነው፣ በሰባቱ ማኅተሞች ትይዩአዊ አወቃቀር የተነሣ እና በቆይታ ጊዜው እና ከሰባቱ መለከቶችና ከቆይታ ጊዜው የተነሣ። ስለዚህ፣ ሁለቱም 144,000 (አማኝ አይሁድ) እና ሊቆጠሩ የማይችሉ ወገኖች (አማኝ አሕዛብ)፣ እንዲሁም ሁለቱ ምስክሮች፣ ቤተ ክርስቲያንን ያመለክታሉ።  “ማቅ ለብሰው” ይህ ሊሆን የሚችለው አንድም (1) የኀዘንና የንስሐ ምልክት ነው (ዘፍ. 37:34፤ II ሳሙ. 3:31) ወይም (2) የነቢይ የተለመደው ልብስ (II ነገሥ. 1:8፤ ኢሳ. 20:2፤ ዘካ. 13:4)።  “ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ” እያንዳንዱ ሠላሳ ቀናት ያለው አርባ ሁለት ወር ከሺህ ሁለት መቶ ስድሳ ቀናት ጋር እኩል ነው። ወንጌል በማያምኑት አሕዛብ በሚደረገው ስደት ጊዜ ይሰበካል (ማቴ. 24:8-14፣ 21-22)። ተምሳሌታዊ ቁጥሩ የሚመጣው ከዳን. 7:25፤ 12:7 ሲሆን በራዕይ (ዝከ. 12:6፤ 13:5) ተዘውትሮ ጥቅም ላይ ይውላል። Revelation(ራዕይ) (11:4) እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው። ----------------------------------------------------- “ሁለቱ የወይራ ዛፎች” ይህ ጠቃሽነቱ ለዘሩባቤል ነው፣ ከግዞት የተመለሰው የዳዊት ዘር እና ኢያሱ፣ ከግዞት የተመለሰው የአሮን ዘር (ዘካ. 4:3፣11፣14)። ይህ ምናልባት የሚያመለክተው ወንጌል የሚመሰክረው የፍጻሜ ዘመን የሚወክለው ንጉሣዊ መሲሐዊ እና ካህናዊ መሲሐዊ አጽንዖት ነው (ኢየሱስ እንደ ንጉሥና ካህን፣ መዝሙር 110፤ ዕብ. 1፡3)። እነዚህ ተመስጧዊ የንስሐ ሰባክያን የእግዚአብሔርን ብርሃን ያመጣሉ (ዘካርያስ 4) ለዐመጸኛው ዓለም (ዐመጸኛው እስራኤል አሁን ዐመጸኛው የሰው ዘር ሆኗል፣ ኢሳ. 6:9-11፤ 43:8-13፤ ኤር. 5:21-29፤ ሕዝ. 12:2)። Revelation(ራዕይ) (11:5) ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል። ----------------------------------------------------- “ማንምም ሊጎዳቸው ቢወድ… ማንም ሊጎዳቸው ቢወድም” እነዚህ ሁለቱም አንደኛ መደብ ሁኔታዊ ዓረፍተ ነገሮች ናቸው፣ የሚታሰበውም ሊጎዷቸው የሚፈልጉ እንዳሉ ነው፣ ነገር ግን እነርሱ በመለኮታዊ ይጠበቃሉ፣ ተልእኳቸው እስከሚፈጸም ድረስ።  “እሳትም ከአፋቸው ይወጣል ጠላቶቻቸውንም ይበላል” የአፋቸው ኃይል እሱም የሚያውጁት መልእክት ኃይል እንደሆነ አስተውል። በራዕይ አፍ መሣርያ ነው፣ ምላስም ሰይፍ (ዝከ. 9:17፤ 19:15፤ ዕብ. 4:12)። Revelation(ራዕይ) (11:6) እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው። ----------------------------------------------------- እነዚህ የብኪ ድርጊቶች የኤልያስን (I ነገሥ. 17:1) እና የሙሴን (ዘጸ. 7:17-19) ድርጊት ያስታውሳሉ። Revelation(ራዕይ) (11:7) ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል ያሸንፋቸውማል ይገድላቸውማል። ----------------------------------------------------- “ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ” ይህ የዳንኤል 7 ጠቃሽ ከሆነ፣ እንግዲያውስ አውሬው ዳንኤል ሰባት ላይ የተጠቀሱት አራት አውሬዎች ድብልቅ ዘይቤ ነው፣ የሚቆመውም ለመዳረሻው የፍጻሜ ዘመን የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው (2 ተሰ. 2፡3)። “ጥልቁ” የሰይጣናዊ ቤት ነው (ዝከ. 9፡1፤ 20፡1)። ይህ የአውሬው ጽንሰ-ሐሳብ ምዕራፍ 13 እና 17 ላይ ዳብሯል።  “ከእነርሱ ጋር ውጊያ ያደርጋል፣ ያሸንፋቸውማል፣ ይገድላቸውማል” ይህ የዳን. 7፡21 ጠቃሽ ነው፣ እሱም እጅግ በሙላት ራዕይ 13 ላይ ተብራርቷል። እዚህ፣ ሐረጉ የሚያመለክተው ሁለቱ ምስክሮች ብዙ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተምሳሌታዊ መሆናቸውን ነው (ዝከ. 13፡7 ማለትም፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ)። እነርሱ ከመከራና ከሞት አይጠበቁም። Revelation(ራዕይ) (11:8) በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት። ----------------------------------------------------- “በድናቸውም አደባባይ ላይ ይተኛል” ይህ የሞቱ አካላት ውርደት የሚያሳየው ንቀትን ማመላከቻ መንገድ ነው (ዝከ. ቁ. 9; ዘዳ. 28:26; መዝ. 79:2; ኤር. 7:33; 8:2; 16:4; 19:7; 34:20)። ሆኖም፣ እግዚአብሔር የእነርሱን የሚታይ አካላት በኃይለኛ ትንሣኤ ተጠቅሞበታል፣ ለኃይሉ መገለጫና ለመልእክታቸው ማረጋገጫ። 115  “ታላቂቱ ከተማ” ይህ የኢየሩሳሌም ገለጻ ይመስላል፤ ሆኖም፣ ዘይቤአዊ ቋንቋው የሚያመለክተው በምድራዊ መንግሥት እና በሰማያዊ መንግሥት መካከል ያለውን መንፈሳዊ ውጊያ ነው። የእኔ ምክንያቶች እነሆ፡ 1. “ታላቂቱ ከተማ” የሚለው ሐረግ ጥቅም ላይ የዋለው ለባቢሎን ወይም ለሮም ነው (ዝከ. 16:19; 17:18; 18:10,16,18,19,21)። 2. ምንም እንኳ ኢየሩሳሌም ሕዝ. 16:46-49 እና ኢሳ. 1:9-10, ላይ ሰዶም ተብላ ብትጠራም፣ ግብፅ ተብላ ፈጽሞ አልተጠራችም፤ ሰዶምና ግብፅ የኃጢአትና የባርነት ዘይቤዎች ናቸው። 3. “እዚያም ጌታ የተሰቀለበት” ኢየሩሳሌምን የሚያመለክት ይመስላል፣ ነገር ግን የአምላክ ተቃዋሚ የሆኑት የዚህን ዓለም መንግሥታት የመግለጫ መንገድ ሊሆን ይችላል። 4. “ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም” ቁ. 9 ላይ የሚያመለክተው ሀ. መላው ዓለም የሚገኝባት ቦታ፣ እሱም ከኢየሩሳሌም ይልቅ ለሮም የሚሰማማ ለ. “ከተማ” ለዐመጸኛው የሰው ልጅ ጥቅም ላይ የዋለ ዘይቤ ነው (ዘፍ. 4:17; 10:8-10) 5. “በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል በደስታም ይኖራሉ” ቁ. 10 የሚያመለክተው የእነዚህ ሁለት ምስክሮች መልእክት ለአይሁድ ብቻ አይደለም፣ በመላው ዓለም ላሉ ለማያምኑት ሁሉ እንጂ። ይህም የሚገልጸው በዚህ ዓለም መንግሥት እና በመሲሐዊው መንግሥት መካከል ቀጣይነት ያለውን ውጊያ ነው (ዝከ. 11፡ 15)፣ በተለይም አንደ ዳንኤል 2 እና መዝሙር 2። Revelation(ራዕይ) (11:9) ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፥ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም። --
Show all...
ብጥ፣ በታሪክ ቅደም ተከተል፣ ወይም በሌሎቹ የቅርብ ምስራቅ የሥነ-ጽሑፍ ፈርጆች ነበር፣ አሁን ግን አናገኘውም። እሱ ሥነ-ቃል ስለሆነ፣ እንደ ስድ ንባብ ጽሑፍ ያለ መዋቅር የለውም። ይህም መጻሕፍቱን በቀጥታ ለማንበብ አዳጋች ያደርገዋል፣ እንዲሁም ያለ ልዩ ታሪካዊ መቼት ለመረዳት አስቸጋሪ ያደርገዋል። ሠ. ነቢያት መልእክቶቻቸውን ለማስተላለፍ የተለያዩ ፈርጆችን ይጠቀማሉ። 1. የፍርድ ቤት ትዕይንት - እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ ወደ ፍርድ ቤት ይወስዳል፣ ብዙ ጊዜ የፍቺ ጉዳይ፣ እሱም ያህዌ ሚስቱን አልቀበልም ሲል (እስራኤል) ታማኝ ሆና ስላልተገኘች (ሆሴዕ 4፤ ሚክያስ 6)። 2. የልቅሶ ሙሾ - ልዩ የሆነው የዚህ ዓይነት መልዕክት መለኪያና ባሕርዩ “ወዮ” ልዩ መልክ ይሰጠዋል (ኢሳይያስ 5፤ ዕንባቆም 2)። 3. የኪዳናዊ ባርኮት መግለጫ - የኪዳኑ ሁኔታዊ ተፈጥሮ አጽንዖት ተሰጥቶታል እንዲሁም የሚያስከትለው ውጤት፣ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ፣ ለቀጣዩ ጊዜ ይወጣል (ዘዳግም 27-28)። V. ትንቢትን ለመተርጎም ረጂ መመሪያዎች ሀ. የዋነኛውን ነቢይ (አዘጋጅ) ሐሳብ ፈልግ የእያንዳንዱን ትንቢት ጽሑፋዊ ይዘት ታሪካዊ መቼት በመመዝገብ። እሱም ዘወትር የሚያካትተው እስራኤል ሙሴያዊውን ኪዳን በዚህ መንገድ መስበሩን ነው። ለ. ሁሉንም ትንቢት አንብበህ ተርጉም፣ ክፋዩን ብቻ አይደለም፤ እሱን እንደ ይዘት መድብ። እሱም ከአካባቢዎች ትንቢት ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ተመልከት። የሞላውን መጽሐፍ ማውጫ ለማውጣት ሞክሩ። ሐ. የአንቀጹን ጥሬ ትርጉም እየተመለከትክ ሂድ፣ ከራሱ ከጽሑፉ ውስጥ ተምሳሌታዊ አጠቃቀም እስከሚያሳይህ ድረስ፤ ከዚያም ተምሳሌታዊ ቋንቋውን በጽሑፍ አስፍረው። መ. በታሪካዊ መቼት እና በትይዩአዊ አንቀጾች አመላካችነት ተምሳሌታዊ ድርጊቶችን ተንትን። እነዚህ ጥንታዊ የቅርብ ምስራቅ ሥነ ጽሑፎች ዘመናዊ የምዕራባውያን ሥነ-ጽሑፍ እንዳልሆኑ ግን አስታውስ። ሠ. ትንቢቶችን በጥንቃቄ አስፍር 1. እነሱ የደራሲውን ጊዜ ብቻ በተናጠል የሚያዩ ናቸውን? 2. እነሱ በእስራኤል ታሪክ ኋላ ላይ ተፈጻሚ ሆነዋልን? 3. እነሱ የቀጣይ ሁነት ናቸውን? 4. እነሱ ተጓዳኝ የሆነ ፍጻሜ እና የወደፊት ፍጻሜ ይኖራቸዋልን? 5. ለጥያቄዎችህ ምሪት ይሆን ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን ተከተል፣ ዘመናዊዎቹን ጸሐፊዎች ትተህ። ረ. ልዩ ትኩረቶች 1. ትንበያው ሁኔታዊ ምላሽ የሚያስፈልገው ነውን? 2. ትንቢቱ ለማን እንደሆነ በእርግጠኝነት ታውቋልን (ለምን)? 3. በሁለቱም በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እና/ወይም በታሪካዊነት አኳያ ድርብ ፍጻሜ የመኖር አጋጣሚ አለውን? 4. የአዲስ ኪዳን ጸሐፍት በተመስጦ ሆነው መሲሑን በብኪ በብዙ ስፍራ ለማየት ችለዋል፣ እሱም ለእኛ ግልጽ ያልሆነልን። እነሱም ምድቦችን ወይም የቃላት አግባቦችን የተጠቀሙ ይመስላል። እኛ ተመስጧዊ እስካልሆንን ድረስ ይሄንን አግባብ ለእነሱ ብንተወው የተሻለ ነው። 112 VI. ረጂ መጻሕፍት ሀ. ለመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት መመሪያ በካርል ኢ. አሜንዲንግ እና ደብሊዩ. ዋርድ ባስኩ ለ. መጽሐፍ ቅዱስ ከነሙሉ ጠቀሜታው እንዴት እንደሚነበብ በጎርዶን ፊ እና ዳግላስ ስቱዋርት ሐ. ነቢያት የእኔ አገልጋዮች በኤድዋርድ ጄ. ያንግ መ. ፕላውሼርስ እና ፕሩኒንግሁክስ፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት ቋንቋ እና የፍጻሜን (አፖካሊፕቲክ) ዳግመኛ መመርመር በዲ. ብሬንት ሳንዲ ሠ. አዲሱ ዓለም አቀፍ የብሉይ ኪዳን ሥነ-መለኮትና ትርጓሜ መዝገበ ቃላት፣ ቅጽ 4 ገጽ 1067-1078 ============================== Revelation(ራዕይ) (10:8) ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና ሲናገረኝና፦ ሂድና በባሕርና በምድር ላይ ከሚቆመው መልአክ በእጁ ያለችውን የተከፈተችውን መጽሐፍ ውሰድ ሲል ሰማሁ። -------------------------------------------------------- “ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደገና ሲናገረኝ ሰማሁ” በርካታ ግምቶች አሉ፣ ስለ ተናጋሪው ማንነት። አንዳንዶች የሚያስረግጡት እግዚአብሔር፣ ወይም ክርስቶስ፣ ወይም መንፈስ ቅዱስ፣ ወይም ከብርቱዎቹ መላእክት አንዱ እንደሆነ ነው። ቁ. 11 ላይ ድምፁ የብዙ ነው፣ የሚያመለክተውም በሦስትነቱ አንድ የሆነውን አምላክ ይሆናል። የብዙ ቁጥሮች በብኪ ለመለኮት ነው ጥቅም ላይ የሚውሉት (Elohim የሚለው ስምና “እኛ” የሚለው ዘፍ. 1:26፤ 3:22፤ 7:11፤ ኢሳ. 6:8) ላይ ያለው በበርካታ መንገዶች ተብራርቷል። 1. ሰዋሰዋዊ መልክ “የግርማዊነቱ ብዙነት” ይባላል፣ ይህም ብዙነት ጽንሰ-ሐሳቡን ወይም ቃሉን ያጠናክራል 2. ያህዌ በጥቅሉ ነው የሚናገረው ለመላእክት ጉባኤ (I ነገሥ. 22:19፤ ኢዮብ 1:6፤ 2:1፤ ኤር. 23:18፤ ዳን. 7:10) 3. በሦስትነቱ አንድ የሆነው አምላክ ወይም የሥላሴ ጽንሰ-ሐሳብ መነሻ መልክ (መዝ. 110:1፤ ዘካ. 2:8፤ 17:10) ልዩ ርዕስ፡ የመለኮት ስሞች 1፡8 ላይ ተመልከት። Revelation(ራዕይ) (10:9) ወደ መልአኩም ሄጄ፦ ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ አልሁት። እርሱም፦ ውሰድና ብላት፥ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች አለኝ። -------------------------------------------------------- “‘ውሰድና ብላት’” ይህ የሕዝ. 2:8-3:14 ወይም ኤር. 15:16-17 ጠቃሽ ነው። ይህ ተምሳሌታዊ አድርጎ የእግዚአብሔርን መልእክት የመናገር ተልዕኮ ነው። ትንሿ መጽሐፍ ተምሳሌትነቷ የእግዚአብሔር መልእክት እሱም ለአማኞች ዋስትናን የያዘ ነው (ማር፣ መዝ. 19:10-11፤ 119:103) እንዲሁም ለማያምኑትም ፍርድን (መራራ)። ይህ ጥቅል ኢየሱስ ምዕራፍ 6 ላይ እንደከፈተው ዓይነት አይደለም። ይህ የሚያመለክተው ከብርቱው መልአክ የሆነውን መልእክት ነው (ዝከ. ቁ. 7-11)። Revelation(ራዕይ) (10:10) ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ። Revelation(ራዕይ) (10:11) በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል ተባለልኝ። - NIV - shared using Simple Bible
Show all...
ው ቃል ከ“ማየት” 110 ነው። የቦዝ አንቀጽ ዓይነቱ ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው ነቢያትን ለማመላከት ነው (ማለትም፣ “ተመልከቱ”)። 3. ናቢ = “ነቢይ፣” ከአካድያን ግሥ ከናቡ ጋር ይያያዛል = “መጥራት” እና ዓረባዊ ናባ = “ማወጅ።” ይህ በብሉይ ኪዳን ነቢይን ለመግለጽ በእጅጉን የተለመደ ቃል ነው። እሱም ከ300 ጊዜ በላይ ጥቅም ላይ ውሏል። ትክክለኛው ሥርወ - ቃል አይወቅም፣ ግን “መጥራት” በአሁኑ ጊዜ የተሻለው አማራጭ ይሆናል። የተሻለው መረዳት ሊመጣ የሚችለው ያህዌ፣ ሙሴ ከፈርዖን ጋር ያለው ግንኙነት በአሮን በኩል ማድረጉን የገለጸበት ነው (ዘጸ. 4፡10-16፤ 7፡1፤ ዘዳ. 5፡5። ነቢይ ማለት ከእግዚአብሔር አኳያ ለሕዝቡ የሚናገር ነው (አሞጽ 3:8፤ ኤር. 1:7፣17፤ ሕዝ. 3:4።) 4. ሦስቱም ቃላቶች ሁሉ በነቢያት ምድብ ጥቅም ላይ የዋሉት በ1ኛ ዜና. 29፡29፤ ሳሙኤል - ሮህ፤ ናታን - ናቢ እና ጋድ - ሆዜህ ላይ ነው። 5. ሐረጉ፣ ኢሻ - ኤሎሂም፣ “የእግዚአብሔር ሰው፣” ደግሞ ሰፋ ያለ መለያ ነው፣ ለእግዚአብሔር ለሚናገር። እሱም 76 ጊዜ ያህል በብኪ ጥቅም ላይ ውሏል፣ “ነቢይ” በሚል ስሜት። 6. “ነቢይ” የሚለው ቃል መነሻው ግሪክ ነው። እሱም የመጣው ከ፡ (1) ቅድመ = “በፊት” ወይም “ለ” እና (2) ፌሚ = “መናገር” ነው። II. የትንቢት መግለጫ ሀ. “ትንቢት” የሚለው ቃል ሰፋ ያለ የዕብራይስጥ የፍቺ መስክ አለው፣ ከእንግሊዝኛ ይልቅ። ከኢያሱ እስከ መጽሐፈ ነገሥት (ሩትን) ሳይጨምር ያሉት የታሪክ መጻሕፍት፣ በአይሁድ የሚለዩት እንደ “ቀደምት ነቢያት” ነው። ሁለቱም፣ አብርሃም (ዘፍ. 20፡7፤ መዝ. 105፡5) እና ሙሴ (ዘዳ. 18፡18) እንደ ነቢያት ይቆጠራሉ (ማርያም ጭምር፣ ዘጸ. 15፡20)። ስለዚህ፣ ግምታዊ ከሆነ የእንግሊዝኛ መግለጫ ተጠበቁ! ለ. “ትንቢታዊነት በሕጋዊ መንገድ ሊገለጥ የሚቻለው እንደ ታሪክን መረዳት ነው፣ እሱም ትርጉምን ከመለኮታዊ አግባብ፣ መለኮታዊ ዓላማ፣ መለኮታዊ ተሳትፎ አኳያ ከሚቀበለው፣” የተርጓሚዎች የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ቅጽ 3፣ 896። ሐ. “ነቢይ፣ ፈላስፋም ሆነ ስልታዊ የሥነ-መለኮት ሰው አይደለም፣ ነገር ግን በኪዳን መሐል ሆኖ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ሕዝቡ የሚያመጣ ሲሆን፣ መጪአቸውን መልክ በማስያስ አሁን ያሉበትን ለማደስ፣ “ነቢያትና ትንቢት፣” ኢንሳይክሎፔዲያ ጁዳይካ ቅጽ 13 ገጽ 1152። III. የትንቢት ዓላማ ሀ. ትንቢት፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚናገርበት መንገድ ነው፣ አሁን ላሉበት መቼት ምሪት የሚሰጥበት ነው፣ እንዲሁም ሕይወታቸውና የዓለም ሁነቶች በእሱ ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ተስፋ እንዲያደርጉ። የእነሱ መልዕክቶች በመሠረቱ የተደራጁ ናቸው። ማለትም፣ ለመገሠጽ፣ ለማበረታታት፣ እምነትን ለመፍጠር እና ለንስሐ፣ እናም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ያስገነዝባል፣ ስለ ራሱም ሆነ ስለ እቅዱ። እነሱም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይይዛሉ፣ ወደ እግዚአብሔር ኪዳናት ጽኑ ዕምነት። እዚሀ ላይ የግድ መጨመር የሚኖርበት፣ እሱ ዘወትር ጥቅም ላይ የሚውለው የእግዚአብሔርን የቃል አቀባይ ምርጫ ለመግለጽ ነው (ዘዳ.13:1-3፤ 18:20-22)። ይህ፣ በድምዳሜ የሚወሰደው፣ መሲሑን ለማመላከት ነው። ለ. ዘወትር፣ ነቢይ የሱን ዘመን ታሪካዊ ወይም ሥነመለኮታዊ ኪሳራዎችን ይወስዳል፣ እናም ይሄንን ወደ ፍጻሜያዊ የሆነ መቼት ይቀይሰዋል። ይህ የታሪክ የመጨረሻው ሰዓት የሆነ እይታ በእስራኤል የተለየ ነው፣ እናም የእሱ የመለኮታዊ ምርጫ እና የኪዳን ተስፋዎች እሳቤ የተለዩ ናቸው። ሐ. የነቢያት ሹመት ለማመዛዘን የፈለገ የሚመስለው (ኤር. 18፡18) እና የሊቀ ካህናቱን ሹመት ሥልጣን መያዝ የእግዚአብሔርን ፍቃድ እንደማወቂያ መንገድ አድርጎ መውሰድን ነው። ኡሪምና ቱሚም ከእግዚአብሔር ቃል አቀባይ የመጣውን ወደ ቃል መልዕክት ያደገ ነው። የነቢያት ሹመት ከሚልክያስ በኋላ በእስራኤል ያከተመለከት ይመስላል። እሱም ከ400 ዓመት ቆይታ በኋላ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ አልተከሰተም። የአዲስ ኪዳን “የትንቢት” ስጦታ ከብሉይ ኪዳን ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ርግጠኝነት የለውም። የአዲስ ኪዳን ነቢያት (ሐዋ.11:27-28፤ 13:1፤ 14:29፣32፣37፤ 15:32፤ I ቆሮ. 12:10፣28- 29፤ ኤፌ. 4:11) አዲስ ራዕይ ወይም ቃል ገላጮች አይደሉም፣ ነገር ግን በኪዳኑ ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን ፍቃድ የሚነግሩ የሚተነብዩ ናቸው። መ. ትንቢት በባሕርዩ ያልተጠቃለለ ወይም ቀደም ብሎ የሚታወቅ አይደለም። ትንበያ የእሱን ሹመት እና መልእክት የማረጋገጫ መንገድ ነው፣ ነገር ግን እሱ የግድ መመዝገብ ያለበት “የመሲሓዊ ትንቢት 2% ያነሰ ነው። ከ5% በታች በተለይ የሚገልጸው የአዲሱን ኪዳን ዘመን ነው። ከ1% ያነሰ ወደፊት የሚመጡትን ሁነቶች በተመለከተ ነው።” (ፊ እና ስቱዋርት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከነሙሉ ጠቀሜታው እንዴት እንደሚነበብ፣ ገጽ 166)። ሠ. ነቢያት እግዚአብሔርን ለሕዝቡ ሲወክሉ፣ ካህናት ደግሞ ሕዝቡን በእግዚአብሔር ፊት ይወክላሉ። ይህ አጠቃላይ መግለጫ ነው። የተለየነት ያላቸው ይኖራሉ፣ እንደ ዕንባቆም፣ ጥያቄውን ለእግዚአብሔር እንደሚያቀርበው ዓይነት። ረ. ነቢያትን ያለመረዳት አንደኛው ምክንያት፣ መጽሐፎቻቸው እንዴት እንደተዋቀሩ አለማወቃችን ነው። ታሪክ ቅደም ተከተላዊ አይደሉም። ጭብጣዊ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ዘወትር ማንም በሚጠብቀው መንገድ አይደለም። ዘወትር ግልጽ የሆነ ታሪካዊ መቼት፣ የጊዜ ቅንብብ ወይም ከመናፍስተኞች ጋር ግልጽ የሆነ ምድብ የለውም። እነዚህ መጻሕፍት አስቸጋሪዎች ናቸው (1) በአንድ ጊዜ ቅምጥ ለማንበብ፤ (2) በየርዕሱ ለመፈረጅ፤ እና (3) በእያንዳንዱ ትንበያ ላይ ማዕከላዊውን እውነት ወይም ሥልጣናዊ ሐሳብ ለማስረገጥ። 111 IV. የትንቢት ባሕርያት ሀ. በብሉይ ኪዳን የ “ነቢይ” እና “ትንቢት” ጽንሰ-ሐሳብ እያደገ የመጣ ይመስላል። በጥንታዊ እስራኤል የነቢያት ኅብረት እየተጠናከረ መጥቶ ነበር፣ እሱም ይመራ ይነበረው እንደ ኤልያስና ኤልሳ በመሳሰሉ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ መሪዎች ነበር። አንዳንድ ጊዜ፣ “የነቢያት ልጆች” የሚለው ሐረግ ጥቅም ላይ ይውል ነበር ይሄንን ቡድን ለመለየት (2ኛ ነገሥት 2)። ነቢያት ባሕርያቸው ይመደቡበት የነበረው መልክ ተመስጧዊነት ነው (1ኛ ሳሙ. 10:10-13፤ 19:18-24)። ለ. ሆኖም፣ ይህ ጊዜ በፍጥነት ወደ ግለሰብ ነቢያት ተሸጋገሩ። እነዚያ የነበሩት ነቢያት (እውነተኞችም ሆነ ሐሰተኞች) በንጉሥ የሚታወቁት፣ እናም በቤተ-መንግሥት ይኖሩ ነበር (ጋድ፣ ናታን)። ደግሞም ነጻ የሆኑም ነበሩ፣ አንዳንድ ጊዜም ከእስራኤል ማኅበረሰብ አቋም ጋር ጨርሶ የማይገናኙ ነበሩ (አሞጽ)። እነሱም ወንድና ሴት ነበሩ (2ኛ ነገሥ. 22፡14።) ሐ. ነቢይ ዘወትር መጻዒውን የሚተነብይ ነው፣ በሰዎች ፈጣን ምላሽ ላይ የተንተራሰ። የነቢያት ተግባር ዘወትር የነበረው እግዚአብሔር ለፍጡሩ ያለው የማይታጠፍ ሁለንተናዊ እቅድ ሲሆን፣ ፣ እሱም በሰዎች ምላሽ አይስተጓጎልም። ይህ ሁለንተናዊ ፍጻሜ-ተኮር እቅድ በጥንታዊ ቅርብ ምስራቅ ነቢያት ዘንድ የተለየ ነበር። ትንበያና የኪዳን ትክክለኛነት ምንታዌ አትኩሮቶች ነበሩ፣ የትንቢታዊ መልዕክቱ (ዝከ. ፊ እና ስቱዋርት፣ ገጽ 150)። ይህ የሚያመለክተው ነቢያት በቅድሚያ ኅብረታዊ ላይ ነው የሚያተኩሩት። እነሱ ዘወትር፣ በአጠቃሎሽ ሳይሆን፣ ሕዝቡን የሚመለከቱ ናቸው። መ. አብዛኛው ትንቢታዊ ነገር በቃል የሚቀርብ ነው። ኋላ ላይ ነው የተጠናቀረው፣ በጭ
Show all...
11:18፤12:12፣14). 2. በርካታ ፈሊጦች ጥቅም ላይ ውለዋል: ሀ. “በቅርቡ የግድ የሚሆኑ ነገሮች” (ዝከ. 1:1፤ 22:6) ለ. “ጊዜው ቅርብ ነው” (ዝከ. 1:3፤ 3:11፤ 22:10) ሐ. “ፈጥኜ እመጣለሁ” (ዝከ. 2:5፣16፤ 22:7፣12፣20) መ. “እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ” (ዝከ. 3:3፤ 16:15) እነዚህ ሁሉ የሚናገሩት ስለ ድንገተኝነቱ ነው (ልዩ ርዕስ 1፡3 ላይ ተመልከት)። ሆኖም፣ አንዳንድ ምንባቦች ስለ መዘግየቱ ይናገራሉ (ዝከ. 6:11፤ 10:6፤ 14:13)። ሌለኛው ፈሊጥ፣ የፍርድና የሽልማት ቀን መድረሱ ነው፣ “ሆኗል” (ዝከ. 16:17፤ 21:6) ወይም “ሰዓቱ ደርሷል” (ዝከ. 11:18፤ 20:12)። ይህ ተለዋዋጭነት የትርጓሜ ስልቶችን በመለየት ጥቅም ላይ ውሏል፣ የተወሰነ የጊዜ ገጽታን አጽንዖት በመስጠት (አንደኛ ክፍለ-ዘመን፣ ዘመናቱን ሁሉ፣ ወይም የመጨረሻውን ትውልድ)። የመልአኩ የምር መሐላ፣ የፍጻሜ ሰዓት ሁነቶች አሁን እንደሚጀምሩ ነው። የሰማዕታት ጸሎት ተሰምቷል! ራዕይ የግድ መተርጎም የሚኖርበት በመጀመሪያዎቹ አንባቢዎች ብርሃን ነው (የጆን ብሬይን፣ የማቴዎስ 24 ፍጻሜን ተመልከት)። Revelation(ራዕይ) (10:7) ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ። -------------------------------------------------------- አአመመቅ “የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል” አኪጀት “የእግዚአብሔር ምሥጢር ተፈጻሚ ይሆናል” አየተመት “የእግዚአብሔር ምሥጢር ተፈጻሚ ይሆናል” አእት “እግዚአብሔር የምሥጢር ዕቅዱን ይፈጽማል” አኢመቅ “የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል” ቃሉ በርካታ ፍችዎች አሉት። 1. ጳውሎስ እሱን ዘወትር የሚጠቀምበት የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ የመዋጀት ዕቅድ ለማመልከት ነው፣ አይሁድንም ሆነ አሕዛብን በክርስቶስ ባለ እምነት (ኤፌ. 2:11-3:13፣ ልዩ ርዕስ 4፡1 ላይ ተመልከት)። 2. ራዕይ ዘወትር የሚያመለክተው ምሥጢርን ነው፣ ስለ ራዕዩ ክፋይ (ዝከ. 1:20፤ 17:5፣7)። 3. 10፡7 ላይ እሱ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ የመቤዝት ዕቅድ ነው፣ ጳውሎስ ሮሜ 16:25-26 እና ኤፌ. 2:11-3:13 ላይ እንዳደረገው። ማለት የሚቻለው ዮሐንስ ይሄን ቃል ከዳንኤል እንደወሰደው ነው፣ በተለይም ምዕራፍ 2 (ዝከ. 2:18፣19፣27፣28፣29፣30፣ 47)። እንደዚያ ከሆነ፣ እሱ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ችሎታ ነው፣ ድርጊቶቹን ለመግለጥ። እግዚአብሔር የሚያውቅና ሁሉንም ታሪክ የሚቆጣጠር ነው። ============================== ልዩ ርዕስ፡ ምሥጢር በወንጌላት ውስጥ ሀ. ምሥጢር የሚለውን ቃል በሦስቱ ስኖፐፕቲክ ወንጌላት ውስጥ የኢየሱስ ምሳለዎችን መንፈሳዊ መረዳት ለማሳየት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ 1. ማርቆስ 4፡11 2. ማቴ 13፡11 3. ሉቃስ 8፡10 ለ. ጳውሎስ “ምሥጢር” የሚለውን ቃል ተጠቅሟል፣ ይህንን አጠቃላይ የመቤዠት ዕቅድ ለመግለጽ (1ቆሮ. 4:1፤ ኤፌ. 6:19፤ ቆላ. 4:3፤ 1ጢሞ. 1:9)። ሆኖም፣ በተለያዩ በርካታ አግባቦች ተጠቅሞበታል፡ 1. የእስራኤል ከፊል ልበ-ደንዳና መሆን፣ አሕዛብ ይጨመሩ ዘንድ ለመፍቀድ። ይህ የአሕዛብ መጉረፍ አይሁድ ኢየሱስን 2. በትንቢቱ መሠረት እንደ ክርስቶስ ይቀበሉ ዘንድ እንደ ብልሃት ሆኖ አገልግሏል። (ሮሜ 11:25-32)። 3. ወንጌሉ ለሕዝቦች ሁሉ እንዲታወቅ ተደርጓል፣ እነሱ ሁሉም በክርስቶስ እና በክርስቶስ በኩል የተካተቱት ናቸው (ሮሜ 16:25-27፤ ቆላ. 2:2)። 4. የአማኞች አዲስ አካላት በዳግም ምጽዓቱ (1ቆሮ. 15:5-57፤ 1ተሰ. 4:13-18)። 5. የሁሉም ነገር በክርስቶስ መጠቅለል (ኤፌ. 1:8-11)። 6. አሕዛብና አይሁድ አብረው ወራሾች ናቸው (ኤፌ. 2:11-3:13)። 109 7. የክርስቶስና የቤተ-ክርስቲያን ወዳጃዊ ቅርበት በጋብቻ ቃላት ተገልጿል (ኤፌ. 5:22-33)። 8. አሕዛብ ከኪዳኑ ሕዝቦች ጋር ተካተዋል፣ እናም የክርስቶስ መንፈስ ያድርባቸው ዘንድ፣ ይህም ክርስቶስን የመምሰል ብስለት እንዲያፈሩ፣ ይህም የወደቀውን ሰው የእግዚአብሔርን መልክ ለመመለስ (ዘፍ. 6:5፣11-13፤ 8:21) እግዚአብሔርን በሰው ውስጥ (ዘፍ. 1:26-27፤ 5:1፤ 9:6፤ ቆላ. 1:26-28)። 9. የፍጻሜው ዘመን የክርስቶስ ተቃዋሚ (2ተሰ. 2:1-11)። 10. የጥንታዊቷ ቤተ-ክርስቲያን የምሥጢር ማጠቃለያ በ1ጢሞ 3፡16 ላይ ይገኛል። ሐ. በዮሃንስ ራዕይ ውስት ዮሐንስ ያያቸውን ራዕይ ምልክቶችን ትርጉም ለማሳየት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ 1. 1:20 2. 10:7 3. 17:5,6 መ. እነዚህ ሰዎች ሊረዱት የማይቻላቸው መገለጦች ናቸው፤ እግዚአብሔር ሊገልጥልን ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ መገለጦች የእግዚአብሔር ለሰው ልጆች ደህነነት ያለውን ዘላለማዊውን እቅድ ለመረዳት በጣም ወሳኞች ናቸው(ዘፍ. 3:15). ==============================  “ነቢያት” ============================== ልዩ ርዕስ፡ መተንበይ I. መግቢያ ሀ. የመክፈቻ መግለጫዎች 1. አማኙ ማኅበረሰብ እንዴት አድርጎ ትንቢትን እንደሚተረጉም ስምምነት የለውም። ሌሎቹ ሐቆች ቀጥተኛ በሆነ አቋም ላይ ለዘመናት ሁሉ የተመሠረቱ ሲሆኑ፣ ይሄኛው ግን አይደለም። 2. በርካታ በሚገባ የተገለጹ የብኪ ትንቢት ደረጃዎች አሉ ሀ. ቅድመ- ዘውዳዊ (ሞናርኪያዊ) (1) ነቢያት ተብለው የሚጠሩ ግለሰቦች (ሀ) አብርሃም — ዘፍ. 20፡7 (ለ) ሙሴ — ዘኍ. 12:6-8፤ ዘዳ. 18:15፤ 34:10 (ሐ) አሮን - ዘጸ. 7:1 (የሙሴ ቃል አቀባይ) (መ) ማርያም - ዘጸ. 15:20 (ሠ) ሜዳድና ኤልዳድ - ዘኍ. 11:24-30 (ረ) ዲቦራ - መሳ. 4:4 (ሰ) ስሙ ያልተጠቀሰ - መሳ. 6:7-10 (ሸ) ሳሙኤል - I ሳሙ. 3:20 (2) ለነቢያት እንደ ምድብ ማጣቀሻ - ዘዳ. 13:1-5፤ 18:20-22 (3) ትንቢታዊ ምድብ ወይም ተጓዳኞች - I ሳሙ. 10:5-13፤ 19:20፤ I ነገሥ. 20:35፣41፤ 22:6፣10-13፤ II ነገሥ. 2:3፣7፤ 4:1፣38፤ 5:22፤ 6:1፣ ወዘተ. (4) መሲሕ ነቢይ ይባላል - ዘዳ. 18:15-18 ለ. ያልተጻፈ ዘውዳዊ (ሞናርኪያዊ) (እነሱም ንጉሥን ያመለክታሉ) (1) ጋድ — 1ኛ ሳሙ. 22:5; II Sam. 24:11; I Chr. 29:29 (2) ናታን - II ሳሙ. 7:2፤ 12:25፤ I ነገሥ. 1:22 (3) አሂጃ - I ነገሥ. 11:29 (4) ጄሁ - I ነገሥ. 16:1፣7፣12 (5) ስሙ ያልተጠቀሰ - I ነገሥ. 18:4፣13፤ 20:13፣22 (6) ኤልያስ - I ነገሥ. 18-II ነገሥ. 2 (7) ሚልክያስ - I ነገሥ. 22 (8) ኤልሳ - II ነገሥ. 2:8፣13 ሐ. የጥንታዊ ጽሑፍ ነቢያት (እነሱም ሕዝቡን እንዲሁም ንጉሡን ያመለክታሉ)፡ ከኢሳይያስ እስከ ሚልኪያስ (ከዳንኤል በቀር) ለ. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት 1. ሮህ = “ነቢይ፣” 1ኛ ሳሙ. 9፡9። ይህ ማጣቀሻ ራሱ የሚያሳየው ናቢ የሚለውነ ቃል ትርጉም ነው። ሮህ ከአጠቃላይ ቃል “ማየት” ከሚለው ነው። ይህ ሰው የእግዚአብሔርን መንገዶችና ዕቅዶች የተረዳ ሲሆን፣ በአንድ ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለማወቅ የሚያማክሩት ነው። 2. ሆዚህ = “ነቢይ፣” 2ኛ ሳሙ. 24፡11። እሱም በመሠረቱ ከሮህ ጋር ተመሳሳይ ነው። እሱ ከማይዘወተረ
Show all...