en
Feedback
HUHCSF ✞

HUHCSF ✞

Open in Telegram

Haramaya University, Harar Health Campus Christian Students Fellowship Worship Center: @ Me'erab Harar MKC Meet Leaders: @Gutewr

Show more
291
Subscribers
+124 hours
+17 days
+130 days
Posts Archive
ትንቢተ ሚልክያስ በአገልጋይ ገዛኽኝ ክፍል 2፡ ቃሉን መያዝ

ትንቢተ ሚልክያስ በአገልጋይ ገዛኽኝ ክፍል 1፡እግዚአብሄር በቃልኪዳኑ አይለወጥም። የሌዊ ቃልኪዳን

የቃል ጊዜ

የአምልኮ ጊዜ

ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ እንዲሆን ሞገስ ዘውዴ የአንገት . (1) . ሁሌ ቃላህ ነውና የእግሬ መብራት መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (2x) አቤቱ እንዳልበድልህ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን መንገድም እንዲነጻልኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን በትዕዛዝህ መንገድ እንድሮጥ ተንሸራትቼም እንዳልገባ ማጥ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ስንፍናን ተግቼ ኃጢአትን ሳላምጥ ሕይወቴ በድንገት እንዳያመልጥ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ስትተትን እንዳስተውላት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን እንድሰወር ከስውር ኃጢአት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ከጓደኞቼ ጋር በሳቅ ጨዋታ መስመር እንዳላልፍ እንዳልረሳ ጌታ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን የድፍረት ኃጢአት ጠፍሮ እንዳይዘኝ ቃልህ ፍርሃት ሁልጊዜ እንዲያዘኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (2x) መፅናናት ሲያስፈልገኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን መከራው ሲያሳድደኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ከጠላቴ ዛቻ ከምክሩ እንዳልፈራ ልቤ እንዲጠበቅ በምክር እንድመራ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን የኃጥአን ገመዶች ሲተበተቡብኝ አለቆች ተቀምጠው ሲያሙኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን በአመፀኞች እንዳልቀና ትዝታዬ ቃልህ ይሁን የግፍ እንጀራ እንዳልበላ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን . (2) . ኑሬ ቤቴን ለመሙላት በከንፈሬ . (3) . ትዝታዬ ቃልህ ይሁን እግሬ እንዲከለከል ከክፋት ጐዳና በፈተና ሁሉ እምነቴ እንዲፀና ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (2x) ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ እንዲሆን ሞገስ ዘውዴ የአንገት . (1) . ሁሌ ቃላህ ነውና የእግሬ መብራት መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (2x)

ፀሎት🧎‍♀‍➡️🧎‍➡️ 🙏 እግዚአብሔር አባታችን ሆይ ዛሬም ቸርነትህን አብዝተህልን አንተ ባለህበት እንድንገኝ ፈቃድህ ሆኗል እና ክብር ምስጋና ለክቡር ስምህ ይሁን 🙏ጌታ እግዚያብሄር ሆይ ዛሬም አሁን እንደተወደድን አየተሰማን እናመሰግንሃለን። ገና ደካሞች ሳለን፣ እሚፈለግ ነገር እኛ ዘንድ ባልነበረ ጊዜ ታላቁን ፍቅር አሳይተኸናል፣ ክብር ሁሉ ለስምህ ይሁን። ኤፌሶን 2:1-5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ 🙏 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ዛሬም አንድ ነገር እንለምንሃለን ቃልህ "እንደተወደዱ ልጆች እግዚያብሄርን የምትከተሉ ሁኑ" እንደሚል ያንተን ፍቅር በመረዳት ውስጥ የሚገኘውን የህይወት በረከት እንድናገኝ፣ ከመታወቅ የሚያልፈውን ፍቅርህን እንድትገልጥልን በልጅህ እየሱስ ክርስቶስ ስም እንለምንሃለን — ኤፌሶን 5፥1 🙏በቃልህ ውስጥ የሚነገረው በረከት ያግኘን ቀሪ ተርፈው ያሉትን እያንዳንዱ ጊዜያት ላንተ ሰጠን

#የበጎ_ስራ ጥሪ ከሮሆቦት ቲም            👇👇👇 ሰላም ሰላም  የተወደዳችሁ!    ሮሆቦት በተሰኘው በህብረታችን ያለ የበጎ አድራጎት ቲም አስተባባሪነት ነገ   #ቅዳሜ በከተማዋ የሚገኙትን የጎዳና ተዳዳሪ ልጆችን መጎብኘት አስበናል።ወቅቱ እንደምታውቁት  ክረምት እንደመሆኑ ልብሶች በዚህ ሰአት በጣም ያስፈልጋቸዋል፤ ስለዚህ የአልባሳት  ስጦታ እንሠጣችዋለን።    ለጊዜው ከዚህ በፊት የተሰበሰቡ ልብሶች በእጃችን ስላሉ በአካል በመምጣት ብቻ ለእነዚህ ምስኪን ልጆች ፍቅራችንን በተግባር(#Love_in_Action) እናሳይ ስንል በጌታ ፍቅር ጋብዘናችኃል። መገናኛ ሰአት እና ቦታ፦ @3Lt, MKC 📍በየዶርማችሁ የተሰበሰቡ ልብሶች ካሉም ለሌላም ጊዜ ስለሚሆን  ይዛችሁ ብትመጡ ደስተኞች ነን።       ••••••♥••••••   “ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።”   — መዝሙር 41፥1    •••••💎••••••     ለበረከት  ሁኑ🙌

+1
የካታኮምቡ ሰማዕታት ትረካ ክፍል 13

የዛሬው የህብረት ጊዜያችን ይሄን ይመስል ነበር። በኛ መካከል የተገኘው መንፈስ ቅዱስ ይባረክ🙏 ቀጣይ ሳምንት በዚህ መልክ እስኪያገናኘን ጌታ ከናንተ ጋር ይሁን🙌

ቡራኬ🙌        📖 ዮሐንስ 15፥13  📖      በጌታ በኢየሱስ ስም ለጌታ ወዳጅ የሆናችሁበትን ነፍስ የተከፈለበትን ፍቅር እግዚአብሔር ያብራራላችሁ ! የተቀበላችሁትን ጥግ ከሆነው የእግዚአብሔርን ፍቅር ይልቅ የሚበልጥ ሌላ አይኑርላችሁ! የወደዳችሁን ጌታ በመወደዳችሁ መጠን የምትወዱበትን ፀጋ ይብዛላችሁ! እግዚአብሔር ወዳጅ ብሎ ባቀረባችሁ ልክ በመገኘቱ ውስጥ መኖር ይሁንላችሁ ! በ   ሮሜ 8፥35 ተብሎ እንደተፃፈ መወደዳችሁን ያላችሁበት ሁኔታ አይከልልባችሁ! ከክርስቶስ ፍቅር አልፎ ልባችሁን የሚያሸንፍ አንድ ነገር ከናንተ ዘንድ አይገኝ ! ከሚታየው የመሳካት ወይም ያለመሳካት ትዕይንት ይልቅ በልባችሁ የፈሰሰው ፍቅር ይዳሰስላችሁ! አይደለም ያጣችሁት እጃችሁ የገባው የእግዚአብሔርን ፍቅር ሊተርክላችሁ አይቻለው! የሚጠቀስ ፣ስም ያለው ከክርስቶስ ውጪ የሆነ የፍቅር ተራኪ በህይወታችሁ ድርሻ ይታጣለት !  በ  ኤፌሶን 3:16-19 ተብሎ እንደተፃፈ መፅኛና መሰረታችሁ የጌታ ፍቅር ይሁንላችሁ ! ከመታወቅ የሚያልፈውን የክርስቶስ ፍቅር እንድታውቁ ጌታ ያበርታችሁ! ወደ ላይ ብትወጡ ወደ ጥልቅም ብትወርዱ የማታመልጡበትን የፍቅሩን ዳርቻ ራሱ ያብራራላችሁ!  በ  1ኛ ዮሐንስ 4፥16 ተብሎ እንደተፃፈ አለን ብላችሁ የምትይዙት እውቀት ቢሆን እምነት እግዘብሔር ለእናንተ ያለው ፍቅር ይሁንላችሁ ! በፍቅሩ በመኖር ውስጥ እግዚአብሔር ራሱ ጋር ያሰንብታችሁ! እግዚአብሔርን እናንተ ጋር የሚያኖር የራሱን ፍቅር ያችራችሁ ! እግዚአብሔር ይባርካችሁ፥ ይጠብቃችሁ፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራላችሁ፥ ይራራላችሁም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ እናንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጣችሁ! ተባረኩ!            🙌 አሜን 🙌

ትንቢተ ሚልክያስ በአገልጋይ ገዛኽኝ ክፍል 5፡ፀሎት

ትንቢተ ሚልክያስ በአገልጋይ ገዛኽኝ ክፍል 4፡ የእግዚአብሄር ስም

ትንቢተ ሚልክያስ በአገልጋይ ገዛኽኝ ክፍል 3፡ እግዚአብሄር በክብሩ አይለወጥም።

ትንቢተ ሚልክያስ በአገልጋይ ገዛኽኝ ክፍል 2፡ የእግዚአብሄር ፍቅር

የቃል ጊዜ

ትንቢተ ሚልክያስ በአገልጋይ ገዛኽኝ ክፍል 1፡ እግዚአብሄር በፍቅሩ አይለወጥም።

የአምልኮ ጊዜ

ቸር ነህና.m4a7.78 MB

ፀሎት እግዚያብሄር አምላክ ሆይ በፊትህ እንሆን ዘንድ ይህን እድል ስለ ስጠህን እጅግ አድርገን እናመስግንሀለን:: ጌታ ሆይ በዘመናችን ሁሉ በፊትህ መሆን እንድንችል እርዳን የሚመጣው ጊዜያዊ ነገር ስፍራችንን እንዳንለቅ እርዳን። ሩት ፩:፩ አምላክ ሆይ በተወደድንበት በዛ ፍቅር መኖር ይሆንልን ዘንድ እርዳን ። የምናየው ሌላ ነገር ሀሳባችንን ከአንተ አይውስድብን። አባት ሆይ ገና በመሀፅን ሳለን ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለመረጥከን ለአንተ የምንኖር ልጆች አድርገን። ጌታ ሆይ በዘመናችን ሁሉ ስለ ተቀበልነው ህይወት ዋጋ ስቶ መኖር ይብዛልን። ፍቅርህ ጌታ ሆይ ለመቆማችን ዛሬም በቤትህ ለመኖራችን ብቸኛው ምክንያት ነው ስለዚህ ታላቅ ፍቅር እናመስግናለን። ቀርቶ ባለው ጊዜ የልብህን ሀሳብ አስተምረን። አሜን🙏

የካታኮምቡ ሰማዕታት ትረካ ክፍል 12