cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hikmas poem

leave ከማለትዎ በፊት አስተያየቶን ያድርሱን። @Otommanbot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
173
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አስተማሪ ቂሷ አንድ ትንሽዬ ልጅ ለወላጆቹ፦"3 ጥያቄዎቼን የሚመልስልኝ ጠንካራ ዑለማ አምጡልኝ" አላቸው። ወላጆቹም በአከባቢያቸው ያለ አንድ ኡስታዝ አመጡለትና አገናኙት። ልጁ፦"ማን ነህ አንተ? እኔ ስለምጠይቀውስ ጥያቄ መልስ እንዳለህ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ?" ኡስታዙ፦"ስሜ ዐብዱላህ ይባላል ከአላህ ባሪያዎችም አንዱ ነኝ።ለምትጠይቀኝ ጥያቄዎችም በአላህ ፍቃድ መልስ እሰጥሀለሁ።" ልጁ፦"አንተ ግን ብዙ ዑለማኦች ሊያብራሩልኝ ያልቻሉትን ጥያቄዬን እንደምትመልስልኝ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነህ? ኡስታዙ፦"ልመልስልህ እሞክራለሁ በአላህ እገዛ።" ልጁ፦" 3 ጥያቄዎች አሉኝ። 1=>እውነት ፈጣሪ አለ? አዎ አለ የምትል ከሆነ አሳየኝ የት ነው ያለው? 2 => ቀዷ እና ቀደር ምንድነው? 3 =>እውነት ሸይጣን ከእሳት የተፈጠረ ከሆነ እንዴት በእሳት ይቀጣል? ከእሳት ተፈጥሮ እሳት አያቃጥለውም። "ይሄን ግዜ ኡስታዙ እሳት በሆነች ጥፊ ልጁን አጮለው። ልጁ፦"እንዴ!!! ለምን ትመታኛለህ? ምን ሚያስመታ ነገር ተናገርኩ? ኡስታዙ፦"አረ!!! እኔ አልተቆጣሁም ግን ያሁኗ ጥፊ ለሶስቱም ጥያቄዎችህ መልስ ናት። ልጁ፦"እንዴት? አልገባኝም... ኡስታዙ፦"በጥፊ ስመታህ ምን ተሰማህ? ልጁ፦"በጣም ህመም ተሰማኝ። ኡስታዙ፦"ህመም እንዳለ ታምናለህ?" ልጁ፦"አዎ አምናለሁ።" ኡስታዙ፦"አሳየኝ የት ነው ያለው?" ልጁ፦"አይ አለ ግን ማየት እንኳን አይቻልማ" ኡስታዙ፦"ይህ ለመጀመሪያ ጥያቄህ መልስ ነው።ሁላችንም አላህ እንዳለ እናምናለን ነገር ግን ማየት አንችልም። እሺ ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ ገምተህ ነበር?" ልጁ፦"አልገመትኩም።" ኡስታዙ፦"እሺ እኔስ አንተን ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ አስቤ ነበር? ልጁ፦"አላሰብክም።" ኡስታዙ፦"ለ2ኛ ጥያቄህ መልስ ይህ ነው ቀዷ ቀደር የሚባለው። እሺ እኔ አንተን የመታሁበት እጄ ከምንድነው የተፈጠረው?" ልጁ፦"ከአፈር" ኡስታዙ፦"እሺ በእጄ የመታሁት ያንተ ፊትስ ከምንድነው የተፈጠረው?" ልጁ፦"ከአፈር" ኡስታዙ፦"ስመታህ ምን ተሰማህ?" ልጁ፦"አመመኝ" ኡስታዙ፦"ከአፈር የተሰራ አፈርን ሲመታው እንደሚያሳምመው ሁላ ከእሳት የተሰራውም ሸይጣን በእሳት ሲቀጣ በጣም ያመዋል።" ክብር በየሀገሩ ላሉ ዑለማኦች ይገባቸዋል ምንጭ፦" ﻋﺠﺎﺋﺐ ﻭﻏﺮﺍﺋﺐ ﻭﻃﺮﺍﺋﻒ ﺣﻮﻝ ﺍﻟﻌﺎﻟﻢ ከተሰኘው የዐረብኛ ፔጅ @endallahyetale @endallahyetale
Show all...
ፍትህን አፋልጉኝ አለም ደበቀብኝ እውነትን አዳፍነው ዉሸት ነገሰብኝ እኔ የአለም ሙስሊም ፍትህ ፈላጊ ነኝ ሙስሊም በመሆኔ በየሀገራቱ እጨቆናለሁኝ የሙስሊሙን ፍትህ አለም ላይ ለማስፈን እኛ ነን ያለነው ለኛው ለራሳችን የአለማት ሙስሊም በአንድነት በብርታት ሁላችን ተነስተን እናግኝ ፍትህን። ✍ሂክማ አክመል @hikmaspoem @hikmaspoem @hikmaspoem
Show all...
🌼 ዛሬ እኛ የምንጋደልባት ዱንያ ትላንት የነቢዩላህ አደም (ዐ.ሰ) ቅጣት ነበረች!🌼 @hikmaspoem
Show all...
✍ድንቅ ምክር... ነብዩላህ ዩሱፍ ﷺ ለወንድሙ እንዲህ አለው፦ " لا تبتئس" .. ተስፋ አትቁረጥ ነብዩሏህ ሹዐይብ ለነብዩሏህ ሙሳ ﷺ " لا تخف" .. "አትፍራ" አሉት ነብዩሏህ ሙሃመድ ለጓደኛቸው፦ " لا تحزن" .. "አትዘን" አሉት እኔም ለውድ ለጉሩፔ ቤተ ሰቦች የሃቢቢን ﷺ ቃል ልበላችሁ " لا تحزن" .. "አትዘን" በማንኛውም በዚህች አለም ላይ በምያጋጥማችሁ ነገር አትዘኑ አትፍሩም ተስፋም አትቁረጡ !! ምክንያቱም የዱንያ ባህሪዋ ይህም ስለሆነ !! ነገር ግን አንድ ቀን እንዘን ፦ የዛኔ ሁሉም በሚቀሰቀስበት ቀን የመልካም ስራ ሚዛናችን አንሶ የመጥፎ ስራችን የበዛ እለት ... እንፍራ እንዘን..
Show all...
አንዳንድ ሰዎች የለበሱት ልብስ ከራሳቸው በላይ ውድ ነው። @hikmaspoem
Show all...
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ አላህን ፍሩ አላህን ፍሩ ኢተቂላህ ሙሉውን ካላነበቡ አይጀምሩት❗️❗️ አንድ ቀን ጂብሪል(ዐ.ሰ) ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁበት ሰዐት አላህ(ሱ.ወ) የጀሀነም አቀጣጣዮችን እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም" ብሎ መለሰላቸው። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት። ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም። ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.... የመርፌ ቀዳዳ ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....ከጀሀነም ሰዎች ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር። ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ....አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይቀልጣል። ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ....በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው። 7 በሮች አሏት።ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ መለሰላቸው። ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ)፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?" ብለው ...ሲጠይቁት ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት ያስኬዳል። እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል።የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል። ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ ይታሰራል። እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል።ከዚያምሕ በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ ይመቷቸዋል።ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ መለሰላቸው። ነቢያችንም(ሰ.ዐ.ወ)፦"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?"ብለው ጠየቁት። ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦ "በታችኛው በር የሚገቡት 1፦ሙናፊቆች 2፦በዒሳ ዐሰ ማዕድ የካዱት 3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ የ አንደኛው በሩ ስም ሀዊያ ይባለል። ሁለተኛው በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው። ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል። በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም ለዟ ይባላል። አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል። ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት ያዘው። ነቢያችንም(ሰ.ዐ.ወ)፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው ሲጠይቁት ጂብሪልም(ዐ.ሰ)፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ ሲመልስላቸው ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ)ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ። 😭😭😭😭/ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/😭😭😭😭 ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ። ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ? እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭 ያ አሏህ ያ ረህማን ሙስሊሞች አድርገህ እንደፈጠርከን ሙስሊሞች አድርገህ ውሰደን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ይህን ሀዲስ አንተ ጋር ወይም አንቺ ጋር እንዲቀር አታድርጉ ቢያንስ ለ 10 ሰው እንላከው ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያዳርሱ በማይቋረጠው አጅር ተካፋይ ይሁኑ
Show all...
ብረት ከሚገፉ ሰዎች ይልቅ #ትእግስተኛ ሰዎች ጠንካራ ናቸው join @hikmaspoem👈
Show all...
(ጌታዬ ሆይ) እጄን አንስቼ 🙏የምነግርህ ትልቅ ጉዳይ አለ ከኔ በላይ ያሉ ሰዎች ከነሱ በላይ አንተ እንዳለህ ዘንግተው አንተ የፈጠርከኝ ሳይሆን እነሱ የፈጠሩኝ እየመሰላቸው ነው ። join 🌱 @hikmaspoem
Show all...
💗#ነ___ብ____ዩ (ሰ.ዓ.ወ) 💗 ''ከሶሃቦቻቸው ጋር በጉዞ ላይ ሳሉ ፍየል እንዲታረድ አዘዙ::'' ➺ከእነሱም አንዱ ሶሃባ ማረዱ የኔ ፋንታ ነው አለ:: ➺ሁለተኛው ደግሞ ቆዳውን መግፈፍ የኔ ፋንታ ነው አለ:: ➺ሦስተኛው ደግሞ መቀቀሉ (ስጋ ማብሰሉ) የኔ ፋንታ ነው አለ:: ነብዩ (ሶ.ዓ.ወ) በበኩላቸው "ለማገዶ የሚሆን እንጨት መልቀሙ የኔ ፋንታ ነው" ሲሉ ሶሃባዎቹ እኛ እንበቃለን ያ ረሱሉላህ ሲሏቸው "እንደምትበቁ አውቃለሁ ነገር ግን ከእናንተ የተለየ ክብር እንዲኖረኝ እጠላለሁ ብለው!!!!'' [እንጨት መልቀም ጀመሩ።] ❤️ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለሏ❤️ @hikmaspoem🔸✨
Show all...
#የሂጃብ_ቀን ከህይወት ጅማሮ እስከ ህይወት ፍፃሜ የሚተገበር የአላህ ድንጋጌ እንጂ ለአንድ ቀን የሚተገበር የፎቶ ክብረ በአል አደለም !! @Abd_Islam 👈join @Abd_Islam 👈share
Show all...