cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

(✍ GOSPEL TALK ✍)

ክርስትና ማለት ክርስቶስ ነው ክርስትያን ነኝ ካሉ መኖር ነው ክርስቶስ ለኛ ሲል ከሞተ እኛ ለሱ ስንል መኖር ነው ዘማሪ አቤል ግዛው ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየቶች ካሏቹ በ @abel_graphics አናግሩን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
2 032Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መንፈሳዊ ልብወለዶችን አታች ለተቸገራችሁ በሙሉ ለህይወታችሁ ጠቃሚ የሆኑ መንፈሳዊ ልብ ወለዶችን የምለቅ አንድ መንፈሳዊ ቻናል ላስተዋውቃችሁ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Hopeful_Tube @Hopeful_Tube @Hopeful_Tube
Show all...
Repost from ናዝራዊ Tube
መንፈሳዊ ልብወለዶችን አታች ለተቸገራችሁ በሙሉ ለህይወታችሁ ጠቃሚ የሆኑ መንፈሳዊ ልብ ወለዶችን የምለቅ አንድ መንፈሳዊ ቻናል ላስተዋውቃችሁ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Hopeful_Tube @Hopeful_Tube @Hopoful_Tube
Show all...
Repost from ናዝራዊ Tube
ስለ ዮሃንስ ወንጌል እግዚአብሔር ይመስገን የዮሃንስ ወንጌል ልክ እንደ ሌሎቹ ሦስት ወንጌሎች ኢየሱስን በአመዛኙ ከታሪክ ጋር አጋብቶ ብቻ ሳይሆን የሚነግረን “አሁን” በአማኝ ወይም በቤተክርስትያን ሕይወት ውስጥ ያለውን ፋይዳ በጥልቀት በማውሳትም ነው፡ በሌላ አባባል ታሪካዊ / historical ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን የሚያስተዋውቀን አሁናዊ / existential ክርስቶስንም ነው። ዮሃንስ በወንጌሉ ከሚገልጻቸው አሁናዊ እውነቶች መካከል አንደኛው አንድነት / unity ነው፡ ይህንን የአንድነት ክቡር እውነት በዋነኛነት በምእራፍ 17 ላይ አጽንኦት በመስጠት ያቀርብልናል። ክፍሉ የሚጀምረው፦ “ኢየሱስም . . . ወደ ሰማይ አይኖቹን አነሳና እንዲህ አለ” ብሎ ነው። ይሄም የሚያሳየን እውነት በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታችን የሚናገረው ነገር በሙሉ በአብ ፊት እንደ ጸሎት የቀረበ ምልጃ መሆኑን ነው። በዚህ የምልጃ ምእራፍ ውስጥ ነው እንግዲህ ጌታችን በሚገርምና እጅግ ደስ በሚል መልኩ በአብ፣ በወልድና፣ በአማኞች መካከል ያለውን አንድነት ጸሎታዊ በሆነ ቅርጽ ለአባቱ የሚያቀርበው። #አንድ የአማኞች የእርስ በርስ አንድነት ክርስቶስ በዚህ ምእራፍ ቁጥር አሥራ አንድ ላይ እንዲህ ብሎ ይጸልያል፦ “ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው” መቼም ይህን ቁጥር በጥድፊያ ካላነበብነው በስተቀር ወሳኝ የሆነውን አሳብ የምናልፈው አይመስለኝም፡ ክርስቶስ በዋነኛነት አማኞች እርስ በርስ በአንድ የሰመረ ሕብረት እንዲሆኑ ወይም ብዙዎች ቢሆኑም ነገር ግን አንድ እንዲሆኑ አባቱን ይለምንላቸዋል፡ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ አማኞች አንድ እንዲሆኑ ለማነጻጸሪያ የተጠቀመበት እውነት ነው፡ እንዲህ ይላል፦ “እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ” የአንድነቱ ንጽረት አባትና ልጅ ናቸው፡ ታዲያ ይሄ አይገርምም! በዚሁ ወንጌል ውስጥ ጌታችን “እኔና አብ አንድ ነን - We are in one accord” ብሎ እንደተናገረ እናነባለን፣ ይሄንኑ አንድነት ወይም የአሳብና የልብ ስምረት አማኞች እርስ በርሳቸው እንዲለማመዱት ይጸልይላቸዋል፡ እውነት ግን እስኪ አስቡት፣ አብና ወልድ አንድ እንደሆኑት እኛ አንድ እንድንሆን እኮ ነው የሚጸልየው፡ በምድር ላይ የአማኞችን አንድነት ለማነጻጸር የሚመጥን አንድ እውነት ያለው በአብና በኢየሱስ መካከል ያለው አንድነት ብቻ ነው፡ ይሄ አንድነት ደግሞ እኛ #የምንጀምረው ሳይሆን #የምንገባበት ነው፣ ምክንያቱም አስቀድሞ በአባትና በኢየሱስ መካከል የተመሰረተ ነው። አንድነታችን የዘር፣ የቋንቋ፣ የአጥቢያ ቤተክርስትያን፣ የጓደኝነት፣ ወይም የቲፎዞ ሳይሆን የእግዚአብሔርና የኢየሱስ ነው፡ ከዚህ ያነሰ አንድነት በሰው፣ ከሰውና፣ ለሰው የሆነ ነው። #ሁለት የአብ፣ የወልድና፣ የአማኞች አንድነት አማኞች እርስ በርስ ሊኖራቸው ከሚገባቸው አንድነት ወይም ሕብረት በዘለለ መልኩ ጌታችን፣ እርሱ፣ አብና፣ አማኞች ደግሞ በአንድ አንድ እንዲሆኑ ሲጸልይ እናነባለን ቁጥር 21 - 22 “አባት ሆይ በእኔ እንዳለህ፣ እኔም በአንተ፣ እነርሱም ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ . . . እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ . . . “ ደቀመዛሙርት በአብና በወልድ መካከል ባለ አንድነት እርስ በርሳቸው አንድ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን የተጸለየላቸው፣ እነርሱ ራሳቸው ከአብና ከወልድ ጋር በአንድ እንዲሰመሩም ጭምር ነው፡ አብ በወልድ ውስጥ፣ ወልድ ደግሞ በአብ ውስጥ፣ አማኞች ደግሞ በአብም በወልድም ውስጥ ሆነው በአንድ እንዲሆኑ፡ እውነት ከዚህ የሚበልጥ ጸሎት አለ? እውነት ከዚህ የሚበልጥ ክብር ወይም ሕይወት አለ? ከአብና ከወልድ ጋር አንድ መሆን!! #ማሳረጊያ የእርስ በርስ አንድነታችን ወይም ሕብረታችን በአብና በወልድ መካከል ባለው ሕብረት መቃኘቱ ሲገባን፣ እንዲሁም አንድነታችን የእርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ከአብና ከወልድም ጋር በአንድ መሆኑ ሲገባን፣ ለዚህ ክቡር እውነት ስንል የማንጥለው ነገር አይኖርም፡ ለዚህ ሕብረት ብለን የምንጥለው ነገር ሕብረቱ የገባንን ያህል ነው። በዚህ አንድነት ውስጥ ያልተሰመረ ሁሉ፣ ፓስተር ይሁን ሐዋርያ፣ ወንጌላዊ ይሁን ነብይ፣ የሥነ-መለኮት ምሁር ይሁን ዓቃቤ-እምነት፣ ፈጽሞ የመለኮትን ሕይወት አይቋደስም - የመለኮት ሕይወት ከአብና ከወልድ ጋር እንዲሁም እርስ በርስ አንድ በመሆን ብቻ የሚገለጥ ነው። ምን አይነት ክብር ነው! ከአብም ከወልድም ጋር በአንድ መሰመር! “ኅብረታችንም ከአባት ጋር ክልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው” ✍🏾Yilu danu @nazrawi_tube @nazrawi_tube
Show all...
የተሠጠክ ምን ያክል #ትልቅ እንደሆነ ብታውቅ የጠየከው #ቀሊል እንደሆነ ይገባካል 💯 ✅በነፃ የተሠጠህ #ክርስቶስ_ታላቅ ነው 💯 አንዳች ነገር አስፈልጎክ ወደ #ፀጋው_ዙፋን_ፊት ቀርበህ ስትጠይቅ፣ #በእምነት አድርገው እንጂ ላንተ ሠማይ የደመደልክ የጠየከው ያንተ እንዲሆን ያረጋገጠልክ #የኪዳን_ቋንቋ #እንዲያው✅ የሚል ነው ‼️ "ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ #ሁሉን ነገር #እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?" ሮሜ 8:32           ‼️ስለዚህ የሠማይ አባትክን #አምነክ ቅረበው፣በነፃ የሠጠክ #ልጁ ታላቅ #ከልኬትም_በላይ  በመሆኑ ሌላውን #ልጄ_ሆይ በነፃ ውሠድ ይልካል ✅ ‼️ጌታን ከምጠይቀው ይልቅ እርሡ አስቦልኝ በነፃ የሠጠኝ ታላቅ ነውና ሌላውን ነገር #እንዲያው ይሠጠኛል የሚል ብቻ #አሜን ሲል መልክቱን ይቀበላል ✅ Share ✅share Join ✅join @gospel_talk
Show all...
የትኛውን እንጀምር በቅርቡ -Relation ship ❤ -sexual purity🙄 -leader ship 👍 -ወጣትነት እና ተግዳሮቱ 👏
Show all...
🙄
👍
👏
#የዋዜማ መልዕክት በህይወቴ በጣም ከምገረምበት ነገር አንዱ በአል ሲመጣ በአል ነው ብለን ያመንበትን ምክንያት ከማሰብ ይልቅ ስለምንበላው ፣ ስለምንጠጣው ፣ ስለ ልብሳችን መጨነቃችን ነው ። 👉 አዲስ አመት መጣ አዲስ ልብስ ልግዛ ፣ 👉 ገና ነውና ስጦታ ካልተሰጠኝ ፣ 👉ፋሲካ ነው ዛሬ በጉን ዶሮውን ልግዛ ሆኖል የኛ ህይወት መብላቱ መጠጣቱ ክፋት ሆኖ ሳይሆን ከርሱ በላይ እግዚአብሔርን እንድናስበው ስለምፈልግ ነው እንደሚታወቀው ነገ ፋሲካ ነው ዛሬ ዋዜማው ላይ ቆመናል ብዙዎቻችንን ያስጨነቀን ነገር ግን የሽንኩርት ፣ የዘይት ፣ የዶሮ መወደድ ነው እስቲ ስንቶቻችን ነን ከበአሉ ሽር ጉድ ውጪ በፅሞና ስለተደረገልን ስለተከፈለልን ዋጋ የምናስበው ? 📌 ከምንበላው በግ በላይ የናዝሬቱ ኢየሱስ ለኛ እንደ በግ ታርዶልናል እሱ ነው ሊያሳስበን የሚገባው !!! 📌የተከፈለልኝ ዋጋ ዋጋቢስ አድርጌዋለሁ ወይስ ገብቶኛል ብሎመፈተሹ ተገቢ ነው ።በአል ወር ሲቀረው ጀምረን በወጪ ከምንጨናነቀው በላይ ስለነፍሳችን ፣ ስለመዳናችን እንጨነቅ ። 🌹እንደ ፅጌረዳ ፈክተን ተሽሞንሙነን እየበላን እየጠጣን ብቻ ከምናሳልፈው ይልቅ ምንም ሳይኖረን የተደረገልንን እያሰብን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አድርገን ብናሳልፈው እሱ ለእግዚአብሔር ታላቅ ዋጋ አለው ። ይህን ስል መብላቱ መጠጣቱ አያስፈልግም ማለቴ ሳይሆን በምቾታችን ተታለን ቅድሚያ መሰጠት ያለበትን ነገር እየረሳነው ይመስለኛል ። ከጎረቤት አላንስም ፣ ያስለመድኩት አይቀርም እያልን አጉል መጨናነቅ ውስጥ ከመግባት ባለን ተደስተን ከቻልን አካፍለን እግዚአብሔር እያመሠገንን ባዕሉን ማሳለፍ ነው ። ቅድሚያ ትኩረታችን #ኢየሱስ ላይ ይሁን ሌላው ትርፍ ነው ። በሰበብ ባስባቡ አመት ባል በመጣ ቁጥር ልዝናና ፣ ልጨፍር ፣ ልብላ ከማለት ይልቅ ልክ እንደ ወርቃማ እድል ቆጥረነው የምንችል ቤተክርስቲያን ያልቻልን ቤታችን ወይም ባለንበት ቦታ እግዚአብሔርን ፣ የተደረገልንን ነገር እያሰብን እናክብረው ማሰብ ብቻ ሳይሆን በቀረም ዘመናችን የመስቀሉን ስራ እያሰብን በዋጋ ተገዝተናልና ስለዛ እንኑር ። 🙏🙏 መልካም የፋሲካ በአል እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ተመኘሁ 😊 ✍በያኔት ማስረሻ #share @yanet_literatures
Show all...
በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው "አሁን ሰላም ነው" የተሰኘው የዘማሪ ሙሴ አለሙ መዝሙር ተለቋል በዩቱብ እየገባች አድምጣችሁ ተባረኩበት። https://youtu.be/MClQY-b0ctQ
Show all...
አሁን ሰላም ነው ዘማሪ ሙሴ አለሙ AHUN SELAM NEW MUSE ALEMU NEW PROTESTANT AMHARIC WORSHIP SONG

ሰላም ቅዱሳን! የኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ከበደል ከኃጢያት፣ ከዘላለም ሞት አድኖናል። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ኤፌ 2፡17ስለዚህ ሰላም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን...

የማንን መዝሙር ይፈልጋሉ? ከታች ያሉትን የዘማሪዎችን ሰም በመንካት ዝማሬውን ያገኙ 👇👇👇👇👇👇👇
Show all...
🎵 ይትባረክ ታምሩ 🎵
🎵 ይትባረክ አለሙ 🎵
🎵 ሀና ተክሌ 🎵
🎵 ይሳኮር ንጉሴ 🎵
🎵 ቃልኪዳን ጥላሁን 🎵
🎵 እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ 🎵
🎵 ቤቲ ወልዴ 🎵
🎵 አይዳ አብርሀም
🎵 ይስሀቅ ሰዲቅ 🎵
🎵 ታምራት ሀይሌ 🎵
🎵 ሳሙኤል ንጉሴ 🎵
🎵 ሳሙኤል ተ/ሚካኤል 🎵