cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

++ግሽ አባይ ግቢ ጉባኤ ++ @gesheabaygebigubae

ጸሎተ ሐይማኖት ዘሰለስቱ ምኢት አሠርቱ ወሠመንቱ (318)

Show more
Advertising posts
347
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ውድ ተመራቂ እህቶች እና ወንድሞች እንኳን ደስ አላችሁ!!! እንኳን አደረሳችሁ!!!በቸርነቱ ለዚህች ሰዓት ያደረሰን አምላክ ይክበር ይመስገን። ነገ ሐሙስ ማለትም በ13/11/2015ዓ,ም ግቢ ጉባኤያችን ለተመራቂ ተማሪዎች የwell go እንዲሁም የአጋፔ (የፍቅር ማዕድ) መርሀ ግብር ስላዘጋጀ በሰዓቱ ትገኝተን የመርሀ ግብሩ ተካፋይ እንድንሆን። ቦታ ቅ/አርሴማ ከአዳራሹ ሰዓት ከቀኑ5:00-7:00 ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
Show all...
ስትመጡ ሁላችሁም ጋዎን ለብሳችሁ እንድትመጡ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባችሗለን
Show all...
"ስለታሙ የሐሜት ጥርስህ የሚያርፈው በወንድምህ ሥጋ ላይ ሳይሆን ነፍስ ላይ ነው፡፡.በዚህም ጥርስህ ወንድምህን በእጅጉ ትጎዳዋለህ፡፡ እንዲህ በማድረግህ አንተም እርሱንም ሌሎችንም ብዙ ሺህ ጊዜ ትጎዳቸዋለህ፡፡ በሐሜትህ አንተን የሚሰማህ ባልንጀራህ የሐሜት ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርገዋለህ፡፡ እርሱም በእርሱ ላይ ከነገሠበት ኃጢአት የተነሣ ለሌላ ለወዳጁ ምን መርጦ ማውራት እንዳለበት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ጻድቅ ልንለው እንችላለንን? እንዲህ ዓይነት ሰው በመጦሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል፡፡ ሰዎችን ወደ ኃጢአት እየመራ ትልቅ ሥራን እንደሠራ ሰው ራሱን በከንቱ ያስኮፍሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ሊታይ የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር ስለቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል የእንዲህ ዓይነቱን ሰው ንግግር ከመስማት መከልከል እንደሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም የዚህ ሐሜተኛ ወሬ እርሱን ብቻ ኃጢአተኛ የሚያሰኝ ጉዳይ ሳይሆን ቤተክርስቲያንንም ጭምር የሚያሰድብ ነውና፡፡ ስለዚህ በጦም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን አይሁን ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡- እነርሱም.... ✟ ክፉ ከመናገር መከልከልን፣ ✟ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና ✟ እንደልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ እመክራቸኋለሁ፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Show all...
በግቢ ጉባኤው ቴሌግራም ገጽ ላይ ለጥፉት
Show all...
ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ? ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡ ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡ + ጸሎት + ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ! አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡ ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡ ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!" ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የካቲት 27 2013 ዓ.ም #share
Show all...
ማስታወቂያ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለግቢ ጉባኤያችን አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ ክረምት አብነት ለመክረም መመዝገባችሁ ይታወቃል ነገር ግን በፊት በነበረዉ መረጃ መሰረት ግቢ እስከ ሀምሌ15 እንደምትቆዩ ነበር ነገር ግን ግቢዉ ድንገተኛ የመርሀ ግብር ለዉጥ ስላደረገ የአብነት ትምህረት መረሀ ግብሩም በዚህኛዉ መርሀ ግብር የማይኖር መሆኑን እናሳዉቃለን ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን ግሽ ዓባይ ግቢ ጉባኤ
Show all...
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ አሐዱ አምላክ አሜን።✝ ውድ ተመሪዎቻችን እንዴት ቆያችሁ? አሜን ያቆየን የጠበቀን ቸሩ መደኃኒዓለም ስሙ የተመሰገነ ይሁን። #ዛሬ_ማለትም_ሰኞ_26/10/2015ዓ.ም ቅድስት አርሴማ አዲስ የሚሰራዉ ህንፃ ቤተክርስቲን የበረከት ስራ ስላለ ሁላችሁም 10:00 ሰዓት ጀምሮ እየመጣን የበረከቱ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በሰማዕቷ በቅድስት አርሴማ ስም ተጠርታችሗል ስለሆነም ሁላችንም አየተቀሳቀስን እንድንመጣ ይሁን። #ቦታ:-ቅ/አርሴማ አዲስ የሚሰራዉ ቤተ ክርስቲያን #ሰዓት:-10:00 #ረድኤተ_እግዚአብሔር_አይለየን!!! ✝✝#የግሽ_ዓባይ_ግቢ_ጉባኤ✝✝
Show all...