cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Education Department of Gondar City

ይህ የጎንደር ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያ የቴሌ ግራም ቻናል ነው። የፌስቡክ ገጻችንንም ይከተሉ፦ https://www.facebook.com/gondarcityeducation ትምህርት ነክ መረጃዎችን ያገኙበታል።

Show more
Advertising posts
948Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሠላም! ዛሬ በ 25/11/2015 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ሁለቱንም ፈተናዎች በሠላም አጠናቀዋል። የሌሎች ወረዳ እና የእኛን ተማሪዎች በአካል አግኝተን አነጋግረናቸዋል። የሚገርም የመረጋጋት ስነ ልቦና ተማሪዎቻችን ላይ ይታይባቸው ነበር። ነገር ግን ጊዜ አጠረን፣ ማታ ማታ ዶርም ለማንበብ ስለማይመች አማራጭ የጥናት ቦታ ቢኖር፤ የሚል ጥያቄ አቅርበውልናል። እኛም ለግቢው አመራሮች ያደረስን ሲሆን ላይብራሪ መፈተኛ ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ የማይቻል ሲሆን፤ ስማርት ቦርድ ያለባቸው ክፍሎችም ኮምፒውተርና የመሳሰለት ማቴሪያሎች ያሉበት በመሆኑ ቁልፍ መሆኑን ተረድተናል። ይሁን እንጅ ከአቶ ዮሃንስ(+251 98 821 7215) ጋር በመነጋገር ለነገ የሚከፈቱ ከፍሎች ሊያመቻችልን ስለተነጋገርን መጠቀም የምንችል መሆኑን ገልጸውልናል። ዛሬ ትኩረት በመስጠት ተማሪዎቻቸውን ግቢ ውስጥ ገብተው ያበረታቱ ርዕሰ መምህራን:- 1=አቶ ሙሉ የአንገረብ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር፤ 2=አቶ ሞላ አበበ የዋላጅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር፤ 3=አቶ ተስፋሁን የደ/ሰ/ቅ/ማ/ካ/ 2ኛ ደ/ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር፤ 4=አቶ ሃብቱ የዕድገት ፈለግ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር፤  ሲሆኑ ከላይ የተገለጹትን ጥያቄዎች አደራጅተው ያቀረቡም እነርሱ ናቸው። 4ቱንም ርዕሰ መምህራን በተማሪዎች ስነምግባርና ውጤት ላይ ተደማሪ ነገር ለማስመዝገብ ለምታደርጉት ጥረት መምሪያው ማመስገን ይፈልጋል። ይህን ጉዳይ ቀላል አድርጎ ማየት ተገቢ አይደለም። ጠቀሜታው በብዙ መልኩ ከፍ ያለ ነውና ቀሪዎቻችሁ ካበረታታችሁ አይቀር ፈተናው ሲጠናቀቅ ሳይሆን ከወዲሁ በጊዜ ተገኝታችሁ እንድታበረታቷቸው መልዕክታችን ነው። እናመሰግናለን!!!
Show all...
ንቅናቄ.pdf
Show all...
ሰላም ቤተሰብ! ዛሬ ሁሉም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተማሪዎች በሰላም ወደ ታላቁና የሰላሙ ዩኒቨርሲቲ በሰላም ገብተዋል! ➢የከተማው አስተባባሪ ኮሚቴው፣ የግ/ሃይል ኮሚቴውና የመንግስት ኮሙኒኬሽን፤ ➣የትም/መምሪያ ማኔጅመንትና ለ ሙያተኞች ➢የ2ኛ ደ/ትም/ቤት ር/መምህራን ➣የታላቁ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ ሙያተኞችና ሾፌሮች፤ ➢የአገ/ጽ/ቤት አመራር፣ ሙያተኞችና ሾፌሮች፤ ➣የመም/ኮሌጅ አመራሮችና ሾፌር፤ ➢የፋሲል ከነማ ስራ አስኪያጅና ሾፌሮች፤ ➣የግል ትም/ቤት ባለቤቶች፣ አመራሮችና ሾፌሮች እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት፤ ➢ከሁሉም በላይ ደግሞ የፖሊስ መምሪያ አመራሮችና ትራፊኮች እንዲሁም የፌዴራል ፖሊሶች በ2ኛው ዙር የተማሪዎች አገባብ ላይ ለነበራችሁ አስተዋጽኦ በመምሪያው ስም ልናመሰግናችሁ እንወዳለን! በቀጣይ ቀናት:- ➛ር/መምህራን በ24/11/15 ዓ.ም ሁሉም የ2ኛ ደ/ትም/ቤቶች ር/መምህራን ከረፋዱ 3:00 ሰዓት ፋሲል ካምፓስ በመገኘት የየትም/ቤታችሁ ተማሪዎች የጋራ ኦሬንቴሺን ላይ እንዲገኙ በአካል ተገኝታችሁ እንድታስተባብሩ! ይህን በተገቢው ሁኔታ መወጣት ከቀጣይ 4 ቀናት አንፃር ትርፉ ብዙ ነውና ትኩረት እንስጠው! ➛ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት ባይፈቀድም ግቢ ውስጥ ገብተን ዋናው መስመር ላይ በመገኘት ከፈተና በፊትና በኋላ ተማሪዎቻችን አግኝተን እንድናበረታታ የተፈቀደ በመሆኑ ይህን ዕድል እንጠቀምበት! ምክንያቱም ር/መምህራንን በየቀኑ ተገኝተው ካበረታቱ ተማሪዎቻችን ላይ ምንም ዓይነት የዲሲፕሊን ግድፈት ሊያጋጥመን አይችልም! ➛የፈተና ጉዳይ ፈፃሚዋም የር/መምህራንን መግቢያ ደብዳቤ በመያዝ ግቢ በር ለሚያስተባብሩ የፀጥታ አካላት በመስጠትና በማስተባበር ሃላፊነታችን እንድንወጣ፤ ➛በተለያዬ ምክንያት በየዕለቱ ልጆቻችሁን ተገኝታችሁ ማበረታታት ባትችሉ እንኳ የግቢውን የተማሪዎች ዲን አቶ ሃብታሙን(+251918735430) ደውላችሁ በማግኘት መረጃ ውሰዱ! ➛ወይንም ከግቢው ደህንነቶች ቴዲ(+251921639553) ጋር ተገናኙ! 🙏በድጋሜ እናመሰግናችኋለን🙏
Show all...
Photo from Netsanet Mengstie
Show all...
Share 'የ2ኛው ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች፣ የሙያተኛና የተሽከርካሪ ምደባ.docx'
Show all...
Share 'የ1ኛ ዙር ፈተና አፈፃፀም የቢሮው ግብረ መልስ.docx'
Show all...
የ2015 ማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከወሰዷቸው ፈተናዎች መካከል
Show all...
Repost from N/a
የሶሻል ሳይንስ ፈተና ነው።ተለማመዱበት
Show all...
የጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ የ2015 ክረምት ወቅት ስራዎች ግቦች • ግብ አንድ፡- የ2015 ትምህርት ዘመን የማጠቃለያ ስራዎችን በውጤታማነት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ • ትምህርት ቤቶች መርጃ ቋት ሊኖር ይገባል፤ • ግብ ሁለት፡- ትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ለማሻሻል በተዘጋጀው እቅድ መሰረት ንቅናቄ ተፈጥሯል፡፡ • ግብ ሶስት፡- የ2016 በጀት ዓመት መሪ የትምህርት ዘርፍ ዕቅድና ዝርዝር የማስፈፀሚያ ዕቅዶች በጥራት መዘጋጀታቸው ተረጋግጧል፡፡ • ግብ አራት፡- ፈፃሚዎችን ማዘጋጀት • ግብ አምስት፡- ግብአቶችን ማሟላት • ግብ ስድስት፡- የት/ቤቶች መሠረት ልማት ስራዎች ማጠናቀቅና ለ2016 በጀት ዓመት ዝግጁ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ • ግብ ሰባት፡- የአረንጓዴ ልማቱን ለማጠናከር በያዝነው የክረምት ወቅት በሁሉም ት/ቤቶች ችግኝ መተከሉ ተረጋግጧል፣ • ግብ ስምንት፣ በትምህርት ተቋማት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ማጠናከር • ግብ ዘጠኝ፡- የተማሪዎችን ምዝገባ በውጤታማነት ለመፈፀም የሚያስችል የአሠራር ስልት ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል፡፡ • ግብ አስር፡- ልዩ ልዩ የአደረጃጀት ስራዎችን ማጠናቀቅና የትምህርት መክፈቻ እለትም ሆነ የአዲሱ ስርአተ ትምህርት ትውውቅ መድረክ በሁሉም ት/ቤቶች በካሌንደሩ መሠረት መጀመራቸው ተረጋግጧል፡፡
Show all...