የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች
Open in Telegram
ግጥም በድምጽ በጽሑፍ ምርጥ አንድ ገፅ በሰው የተነበቡ ግጥሞች የአሪፍ መጽሐፍ ጥቁምታ አጫጭር ታሪኮች የሀሳብ ንሸጣዎችን ከሁሉም እንቃርማለን፡፡ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን፡፡የኤልያስንም የሌሎችንም ከያነያንን ስራ እንታደማለን፡፡ ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡ ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
Show more8 437
Subscribers
No data24 hours
+987 days
+35130 days
Posts Archive
🎂
ከመቼው እንደዚህ እንዳረጀው አላውቅም።
ብዙ ተምሬ ብዙ አንብቤ የማስታውሰው ነገር ግን ማንበብ መማሬን ብቻ ነው።
በቀደም መስታዎት ፊት ቆሜ ፀጉሬ መሐል ጥጥ ነገር መስሎኝ ላነሳ ስል የኔ ጥጥ ነው።
ሽበት ጀምሮኛል😀
ብዙ ነገር አይቻለሁ ባይ ነኝ። ብዙ ነገር አይቶኛልም።
መኖር ቀሎኝ አያውቅም።
የከበደኝ ገላዬ ውሰጥ መኖር ይሆን ሰው መሐል መኖር እንጃ ።
ለጉድ ስቄያለሁ
ለጉድ አዝኛለሁ።
አላውቀውም ነገዬን።
ያኖረኛል ከፈለገ ይገድለኛል ከፈለገ።
ሀገር እና ሰዎች የሉኝም ካልኩ ረጅም ዘመን ሆኖኛል።
እንጃ ለሌሎች አለሁ መሰለኝ እልፍ ሰዎች መወደድና ክብር መሐል ያቆመኛል 🙏 መባረክ ነው።
ወይ እኔ ቆሜያለሁ ወይ ጊዜው ይሮጣል።
ብቻ ልደትህ ነው አሉ።
ማመን ነው መቼም።
እንጃ ምሽቴን እንጃ ያን ወጋገን
ሁሉ አይነገረም እግዚአብሔር ይመስገን!
