የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Open in Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Show more2 760
Subscribers
+124 hours
+37 days
+4430 days
Posts Archive
"ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።" ማቴ 19 ÷6
በዛሬው እለት ጥር 25/2017 ዓ.ም ጋብቻችሁን በቅድስት ቤተክርስቲያን በሥርዓተ ተክሊል የፈጸማችሁት የደብራችን አገልጋይ ዲ/ን ዳዊት ገ/ሕይወት እና የሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋይ እህታችን ቤተልሔም በኃይሉ የአብርሃምን እና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ ጋብቻችሁን ይባርክላችሁ።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ከልሎ በፍቅርና በጤና ይጠብቃችሁ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!
እንኳን ደስ አላችሁ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በዛሬው እለት ጥር 24/2017 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በብፁዕ አቡነ አምባ ቢመን የሚመራውን የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ። ልዑካኑ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የተላከ የሰላምታ መልእክት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በማቅረብ በሁለቱ ተቋማት መካከል የነበረውን የጋራ ትብብር በማጠንከር ላይ ውይይት አድርጓል። እንደ ልዑካኑ ገለጻ ከዚህ በፊት በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሚገኙ የጋራ የመገልገያ ሥፍራዎችን በጋራ መጠቀም የሚያስችል አንድነት የነበረን በመሆኑ አሁንም የተለመደውን ሥራ ማለትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በምትገኝበት ቦታ ሁሉ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን እንድትገለገል የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ባለችበት ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መገልገል እንድትችል የሚያስችል ሁኔታን ማስቀጠል ነው ብለዋል ።
ልዑካኑን በጽሕፈት ቤታቸው ያነጋገሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ይዘውት የመጡት ሐሳብ የነበረና በመገልገያ ሥፍራ በማጣት የሚቸገሩ ምእመናን የሚታደግ ሐሳብ ነውና በአድናቆትና በደስታ ተቀብለነው እየተገበርነው ያለ ቢሆንም አሁንም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስም ይህንን የሰላም መልእክተኛ እና በሁለቱም ተቋማት ውስጥ የሚገለገሉ ምእመናን ችግርን የፈታ ሐሳብ በልዑካኑ በኩል የማጠናከሪያ ሐሳብ እንድንሰጥበት ስላደረጉ እናመሰግናለን ብለዋል።
በመቀጠልም ልዑካኑ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ የግብፅ ኮፕቲክ ፓትርያርክ የተላከውን ስጦታ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ያስረከቡ ሲሆን ቅዱስነታቸውም ስለ ስጦታው አመስግነዋል። በመጨረሻም ልዑካኑ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና ይሁንታ መደሰታቸውን ገልጸው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በኢትዮጵያውያን ምእመናን ትከሻ ተሠርቶ ማለቁ እጅግ ደስ እንዳሰኛቸው በመግለጽ የግብጽ ኮፕቲክ እንደተለመደው በካቴድራሉ መገልገል የሚችሉበት መንገድ ስለ ተመቻቸላቸው አመስገነው የውይይቱ ፍጻሜ ሆኗል።
©የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
+1
ጥር ሃያ አራት
በዚህች ዕለት ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ የተሰበረበትን (ስብረተ አፅማቸው) መታሰቢያ ይከበራል።
ከእንግዲህ አውሬ አዳኝ አትሁን፤ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ሰውን በትምህርት የምታድን ሁን እንጂ፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ጽኑዕ ሥልጣን ሰጥቶሃልና፤ ሙት ታስነሣለህ፤ ድውያንን ትፈውሳለህ፤ አጋንንትም አንተን በመፍራት ይሸሻሉ፡፡ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው››
የጻድቁ ተክለሃይማኖት ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ልዩ የባለትዳር አባላት ጉባኤ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
በየዓመቱ ከጥር እስከ ጥር ያገቡ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት መልስ የምንጠራበት መርሐግብር ለጥር 18/2017 ቀጠሮ ይዘን የነበረ ቢሆንም፣ በጥምቀት አገልግሎት መደራረብ ምክንያት ወደ የካቲት 02/2017ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር ለማሳወቅ እንወዳለን። ሁላችንም ባለትዳር አባላት መልስ የምንጠራቸውን ሙሽሮች በክብር ለመቀበል በእለቱ ሌላ መርሐግብር እንዳትይዙ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳን።
እሑድ የካቲት 02/2017 ዓ.ም
ከረፋዱ 5:30
እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ
የባለትዳር ጉባኤ

''ከእግዚአብሔር ጋር መኖር''
በመ/ር ኤልያስ ገ/ሥላሴ
የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር
የፊታችን ቅዳሜ ጥር 17/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ወርሐዊ የሰንበት ት/ቤት መዋጮ
ለሰ/ት/ቤታችን አገልግሎት መስፋፋት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርጉበት ቀን ደረሰ ወርሐዊ መዋጮ ከጥር 25/2017 እስከ የካቲት 03/2017 ዓ.ም ይክፈሉ። አገልግሎታችንን እናሳድግ መንፈሳዊ የአባልነት ግዴታችንን እንወጣ። በአካውንት የምታስገቡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000555650594 (ወርሐዊ አስተዋጽኦ) ብላችሁ በመጻፍ አስገቡ።
የፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት ልማት ክፍል
+1
በዓለ አስተርዕዮ
ወልድኪ ይጼውአኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር
ልጅሽ ይጠራሻል ወደ ሕይወትና ወደ ክብር መንግሥት
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በትምህርተ ሃይማኖት ኅብረት ካላቸው የአኃት አብያተ ክርስቲያን መካከል የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ስትሆን ቀደም ሲል ሁለቱ አብያተ ክርስቲያን የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በመቀራረብ ሲያከናውኗቸው የነበሩት ተግባራትና ስብሰባዎች በመላው ዓለም ተከስቶ በነበረው የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በተላለፉ ዓለም አቀፍ ክልከላዎች ተቋርጠው በመቆየታቸው የሁለትዮሽ ስብሰባዎቹን ለማስቀጠል እና በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ይቻል ዘንድ ከብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ኛ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የተላኩት፤ ሜትሮፖሊታን ማር ዩሊዮስ እና ፋዘር ዶ/ር ጆሲ ያዕቆብን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
የልዑኩ መሪ ሜትሮፖሊታን ማር ዩሊዮስ ከሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ የተላከውን መልእክትና ገጸ በረከት ለቅዱስነታቸው አቅርበው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰላም፣ የሰው ልጆች ነጻነት፣ ፍትሕ በዓለም እንዲሰፍን በየጊዜው የሚያከናውኑትን አባታዊ ጥረት አድንቀው በዚህም የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተባባሪ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስነታቸውም በልዑካኑ ጉብኝት መደሰታቸውን፤ እንዲሁም የአብያተ ክርስቲያናት አንድነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንዲጠናከር የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን ገልጸው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
በመጨረሻም ልዑካኑ በቅዱስነታቸው ለተደረገላቸው መንፈሳዊ አቀባበል አመስግነው፤ በቀጣይም የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ቅዱሳን ፓትርያርኮች በሀገራቱ ስለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፤ በቅዱስነታቸው ቃለ በረከትና ጸሎት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሚመለከታቸው የመንበረ ፓትርያርክ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ፦የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት