የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Open in Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Show more2 757
Subscribers
+124 hours
+37 days
+4430 days
Posts Archive
የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 16/2017 ዓ.ም ከ11:30 ጀምሮ በደብራችን አውደ ምሕረት ላይ ጉባኤው ይከናወናል። እንዳይቀሩ እንዲገኙ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 16/2017 ዓ.ም ከ11:00 ጀምሮ በደብራችን አውደ ምሕረት ላይ ጉባኤው ይከናወናል። እንዳይቀሩ እንዲገኙ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።

የሐዘን መግለጫ
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው የእህታችን ምዕራፍ እንዳሉ አጎት አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ተፈጽሟል። ስለዚህ መኖሪያ ቤታቸው ጎላ ቤ/ክ በላይኛው በር ላይ ስለሆነ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። ነፍሳቸውን ይማርልን ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
+6
ዝክረ ቅዱስ ያሬድ የምስጋና እና የዝማሬ መርሐ ግብር በትላንትናው እለት ሊቁ ማኅሌታይ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ በተሰወረበት ቀን ግንቦት 11 ቀን ተከናወነ።
መርሐ ግብሩ ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ መርሐ ግብራት የተከናወነ ሲሆን በደብራችን ስብከተ ወንጌል ኃላፊ ሊቀ ጉባኤ ታረቀኝ የቅዱስ ያሬድ ሕይወትና አበርክቶውን በቃለ መጠይቅ በሰፊው አብራርተዋል። ዝክረ ቅዱስ ያሬድ በሰንበት ትምሕርት ቤታችን ከበርካታ ዓመታት በፊት ጀምሮ በተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ የሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሥራዎች በማንሳት መርሐግብሮች ሲከናወኑ ቆይተዋል። እንደ ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክ ፈቃድ ከዚህ በኋላ በሚኖሩት ጊዜያትም ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ዕለት የምስጋናና የዝማሬ ቀን ሆኖ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከናወነ የሚቀጥል ይሆናል።
የቅዱስ ያሬድ ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ሰላም ለአዕይንቲከ እለ ኀበ ልዑል ያንቃዐድዋ
ለውሉደ ሰብእ ሣህለ እንዘ ይሴፈዋ
ሚካኤል ቀዋሚ ለደቂቀ ጼዋ
ለምክረ ጸርየ በትንባሌከ ዕልዋ
ምዕቅብና ነፍስየ ወሥጋየ ወሀብኩከ ነዋ
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወርሐዊ በዓል አደረሳችሁ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ
ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅዱስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት።
ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ።
ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው።
ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ።
በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ።
ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ።
ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ።
ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።
የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም።
በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም።
ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው።
ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበርሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።
ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግም ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።
የቅዱስ ያሬድ በረከት በሁላችንም ላይ ይደር።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
" የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሔ በመስጠት ሐዋርያዊ አደራውን እንዲወጣ በልጅነት መንፈስ ዝቅ ብለን እንማፀናለን! " የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገ ስብሰባ የዘንድሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በርካታ ሥር ነቀል ለውጦችን ማምጣት የሚችል ፤ ለነገይቱ የቤተክርስቲያን ተረካቢ ወጣቶች መሰረት የጣለ እንዲሆን ያለመ ምክረ ሐሳብ ተወያይቶ ማቅረቡን አስታውቋል።
ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው መፍትሔ እንዲሰጥባቸው ከቀረቡት ውስጥ ፦ የቤተክርስቲያንን ሲኖዶሳዊ ልዕልና እና አንድነትን ማስጠበቅ ፣ የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ ችግሮችን በመለየት መፍታት ፣ የሥነ ምግባር ግድፈት እና የቀኖና ጥሰት መበራከት ፣ በሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ የሚኖሩ ተሳትፎዎች ዋና ዋና ጉዳዮች ስለመሆናቸው በመልእክቱ ተላልፏል።
ሐሰተኛ የሆኑ የኑፋቄ ትምህርቶች ፣ በሰላም እጦት የሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሚና ፣የሀብት ብክነት ፣ ዘመኑን የዋጀ የአሠራር መንገድ መዘርጋት ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ እና አፈንግጠው የወጡ ሥርዓቶች ፣ በከተማ ልማት መስፋፋት የምእመናን ከአምልኮ ሥፍራ መራቅ ፣ ሀገራዊ የችግር አፈታት መንገዶች ላይ ምልዓተ ጉባኤውም በስፋት እንዲወያይ አንድነቱ በዝርዝር ካስቀመጣቸው ሐሳቦች መሐል ይገኙበታል።
እነዚህን እና ሌሎች የውይይት ሐሳቦችን በዝርዝር በማቅረብ " የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መፍትሔ በመስጠት ሐዋርያዊ አደራውን እንዲወጣ በልጅነት መንፈስ ዝቅ ብለን እንማፀናለን! " በማለት አንድነቱ መልእክቱን አጋርቷል።