cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የጌታ ደቀ መዝሙር

ቆይቼ የእግዚአብሔር ደጅ ጠናሁ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩህቴንም ሰማኝ። ከጥፋትም ጉድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ እግሮቼንም በድንጋይ አቆማቸው አረማመዴንም አቀና...........። አሜን ✟r✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ 👉ለአስተያየት :- @kidujo @fedhu9 👇👇ግሩፕ ለመቀላቀል 👇👇 @Deke_mezmur 👈

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
258
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#አጋፔ= #የእግዚአብሔር_ፍቅር ============================ ✍️ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጽሐፍት በተጻፉበት በመጀመሪያው የግሪክ ቋንቋ ፍቅርን በ4 ይከፍለዋል፦ 1ኛ. አጋፔ ይባላል 2ኛ. ሄሮስ (ኢሮስ) ይባላል 3ኛ. ፍሊኦ(ፊሊያ) ይባላል 4ኛ. ስቶርጅ ይባላል 👉ሄሮስ የሚባለው ፍቅር የፆታ ፍቅር ሲሆን፤ 👉ፍሊኦ የሚባለው የፍቅር አይነት ደግሞ የጓደኝ ፍቅር ነው፤ ስቶርጅ ደግሞ የቤተሰብ የፍቅር አይነት ነው። ሄሮስ፣ፍሊኦ፣ስቶርጅ የሚባሉት የፍቅር አይነቶች በባህሪያቸው ሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሠረቱ ሲሆኑ አንዱ የሌላኛውን እጅ በመጠበቅ ጥቅምን መሠረት ያደረጉ የፍቅር አይነቶች ናቸው።እንደውም አንድ አባባል አለ ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው ይባላል።እንዚህ ሦስቱ የፍቅር አይነቶች ሰቶ በመቀበል ላይ የተመሰረቱ የፍቅር አይነቶች ናቸው። ☑️አጋፔ ግን ከእነዚህ ይለያል፤ ============== #አጋፔ ሰቶ በመቀበል ላይ የተመሠረተ አይደለም። #አጋፔ እግዚአብሔር ሰውን ፍፁም ለዘላለም የወደደበት የፍቅር አይነት ነው። #አጋፔ፦ ያለምንም ጥቅም ፣ያለምን ቅድመ ሁኔታ እንዲሁ ዝም ብሎ ሰውን መውደድ ነው። #አጋፔ ፦ የሚባለው የፍቅር አይነት ዘር፣ቀለም፣ብሔር፣ሃይማኖት፣ሀብታም፣ደሃ፣የተማረ፣ያልተማረ፣ያመነ፣ያላመነ፣ አውሮፓዊ፣ኢትዮጵያዊ እያለ ሰዎችን አይመርጥም ዝም ብሎ ከራሱ ፍፁም ጥልቅ ከሆነ ፍቅር በመነሳት ሰዎችን ይወዳል።ስለ ሰዎች ፍቅር ሲል ራሱን አሳልፎ ለሞት የሚሰጥ የፍቅር አይነት ነው። ☑️ፍቅርም እንደዚህ ነው ፣እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።1ኛ ዮሐ. 4፥10 ☑️ኃጢአተኞች ፣በደለኞች ምንም የማንጠቅም ጠላቶች በነበርንበት ጊዜ በፍፁም ፍቅሩ የወደደን ቅዱስ እግዚአብሔር ነው ሕይቱንም አሳልፎ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማን ነው ለጠላቱ ህይወቱን የሚሰጥ ???? ጠላቱንስ የሚወድ ማን ነው ???? መገረፍ፣መሰቃየት፣መሞት የሚገባን እኛ ሆነን ሳለ የማይገባው ኢየሱስ የእኛን ሞት ሞተ እኛን ለማዳን በእኛ ፈንታ ምራቅ ተተፋበት፣ተገረፈ፣ተሰቃየ፣በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞተ፤ኃጢአታችንን፣ እርግማናችንን፣ነውራችንን ሁሉ አስወገደልን። ኢየሱስ ክርስቶስ ንጽህ ደሙን አፍስሶ፣ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ ውድ ሕይወቱን ስለእኛ ፍቅር አሳልፎ በመስጠት መውደዱን፣ፍቅሩን በቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሲገልጥልን ጭራሽ በእግዚአብሔር እንደተቀሰፈ፣እንደተቸገር ፣እንደተመታ ተቆጠረ። እርሱ አብዝቶ ቀረበን ፤ምንም የሚወደድ ነገር ሳይኖረን እርሱ በቸርነቱ ወደደን።በሰማይ ያለውን የክብሩን ዙፋን ትቶ ስለእኛ ፍቅር ሲል እንደ ኃጢአተኛ፣እንደ ወንበዴ፣እንደ ምናምንቴ ተቆጠረ።በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የገለጠው ፍቅር ከአዕምሮ ያልፋል። ☑️1 ዮሐንስ 4 (1 John) 19፤ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። ☑️1 ዮሐንስ 4 (1 John) 10፤ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ☑️ኤፌሶን 2 (Ephesians) 4፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ 5፤ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ☑️ሮሜ 5 (Romans) 8፤ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ☑️ዮሐንስ 15 (John) 13፤ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ☑️ዮሐንስ 17 (John) 23፤... እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። ☑️ዮሐንስ 13 (John) 1... በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። ☑️ዮሐንስ 15 (John) 13፤ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ☑️ይሁዳ 1 (Jude)33q 1111 1፤ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤ 2፤ ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ። @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur
Show all...
"ብዙ አጥፍቻለው" ዘማሪ ዘላለም ሉቃስ Share ,, share ,, share 👇Join ,, Join 👇 @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur
Show all...
YouTube ላይ ዝማሬዎችን ለማግኘት
“ ክበር ” ዘማሪ ይትባረክ አለሙ Share,, share ,, share 👇Join ,, Join 👇 @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur
Show all...
⏩መዝሙር 145 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው። ¹⁴ እግዚአብሔር በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ የወደቁትንም ያነሣቸዋል። ¹⁵ የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። ¹⁶ አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ። ¹⁷ እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው። ¹⁸ እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። ¹⁹ ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም። ²⁰ እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ ኃጢአተኞችንም ሁሉ ያጠፋል። ²¹ አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤ ሥጋም ሁሉ ለዘላለም ዓለም የተቀደሰውን ስሙን ይባርክ።
Show all...
የማልደርስበት_ላይ MESKEREM GETU Share ,, share ,, share 👇 Join ,, Join 👇 @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur
Show all...
“የመጨረሻ” ዘማሪት ቃልኪዳን ንጉሴ Share ,, share ,, share 👇 Join ,, Join 👇 @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur @yegeta_Dekemezmur
Show all...
#መልካም_ዜና #አብራችሁን_ስለቆማችሁ_እናመሰግናለን በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ የፈረንሳይ ማህበረ ምዕመናን ላይ የደረሰውን የፍትህ መዛባት ተከትሎ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የደረሰበትን ውጤት አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ። ሐምሌ /2013ዓ.ም ካውንስሉ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ የደረሰውን ፍትህ መጓደል አስመልክቶ ሰኔ 30/2013ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። በመግለጫው በፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የሃገሪቱን 1/3ኛ የህዝብ ቁጥር የሚወክለውን የወንጌል አማኞችን ምዕመናን በእጅጉ ያስከፋ እና ሊታረም የሚገባ መሆኑን ተጠቅሶ ነበር። በተጨማሪም የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የተጠየቀ ሲሆን የካውንስሉ መስራች ቤተ እምነቶች እና ሚኒስትሪዎች እንዲሁም ሚዲያዎች መልዕክቱን እንዲያስተላልፉ ጥሪ መደረጉ ይታወሳል። የዛሬውን መግለጫ የሰጡት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በመልዕክታቸው የቤተክርስቲያን መሪዎች፤ የሚዲያ አካላት፤ ተቋማት እና ሌሎች አካላት መልዕክቱን ተቀብለው ለቤተክርስቲያኒቷ ድምጽ በማሰማት አብረውን ሰለቆሙ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ቄስ ደረጀ አክለው ካውንስሉ ከሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ እንደመከሩ እና በአጭር ጊዜ አወንታዊ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። ኢትዮጵያ የህኡላችንም ሀገር ነች፤ ሁላችንም ተደጋግፈን ተመካክረን የምንገነባት የጋራ ቤታችን እና ሃገራችን ነች ያሉት ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የጋራ እንደመሆኗ መጠን ነገሮችን ይበልጥ በረጋ እና በሰከነ መልክ እያየን ሁላችንንም እኩል የምታስተናግድ ሀገር እንድትሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ከዚህ ውጪ ለአንዱ ተፈቅዶ ለሌላው የሚከለከለውን ግን በአጽንዕት የምቃወም ጉዳይ ስለሆነ እንኳን ሊደረግ ሊታሰብም አይገባም። ወንጌላዊያን በሀገር ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ስራ እንደሚሰሩ እና እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል በተለያየ የሃላፊነት ቦታ የሚገኙ የመንግስት ሃላፊዎች ሁሉንም ዜጋ በእኩልነት ሊያስተናግዱ ይገባል ሲሉም ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ተናግረዋል። ካውንስሉ ለአባላቱ ብቻ ሳይሆን ድምጽ ለሌላቸው እና ፍትህ ለተጎደለባቸው ሁሉ ድምጽ ማሰማታችንንም እንቀጥላለን እስካሁንን አብራችሁን ለሆናችሁ እና ድምጻችሁን ስታሰሙ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው። አሁንም ለሃገር እድገት እና ሰላም በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጪ የምንገኝ ወገኖች በአንድነት ልንቆም ይገባል። ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ።
Show all...
ፍትህ ለፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን ! መላው ክርስቲያኖች በሃገር ውስጥና በውጪ ዓለም የምትገኙ ሁላችሁ በፈረንሳይ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ላይ በተወሰነው የተዛባ የፍትህ ውሳኔ መግለጫዎች በመስጠት ድምጻችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃን፡፡ የሚዲያ አካላት ሁላችሁም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና መጠበቅ የበኩላችሁን እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ @yegeta_Dekemezmur @yEGETA_Dekemezmur
Show all...