cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

The channel of mahibere kidusan

Show more
Advertising posts
29 523
Subscribers
No data24 hours
-287 days
-19530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
NEAR Wallet

Next-generation telegram wallet built over NEAR blockchain. Build in HOT mining

Show all...
Gemz

You’ve played clicker games before, but not one like this. Have fun while earning gemz coins and be among the first to prepare for the future of crypto.

Show all...
Dotcoin

Everything starts from a DOT

Show all...
Dotcoin

Everything starts from a DOT

Show all...
CEX.IO Power Tap

🤩 Farm CEXP tokens and earn rewards! CEX.IO App makes it simple and secure to buy, exchange, and store cryptocurrencies

Show all...
MemeFi Coin

Fight ghost enemies and collect MemeFi Coin rewards in the fastest-growing Telegram app! News:

https://t.me/memeficlub

ቅዱስ አባ አበስኪሮን ዳግመኛም በዚህች ቀን ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው አባ አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ። ➯ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዙ በደረሰች ጊዜ። ወዲያውኑ ይህ ቅዱስ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት። ➯መኰንኑም ወደ ሀገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስ፣ ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮን ጋራ ተስማሙ። ➯በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው። ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊልን ተቀበሉ። ➯የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ ይህንም ሁሉ አደረጉበት። ➯ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር። ➯ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት። እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። ➯ያም መሠርይ የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ። ➯ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለቤት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃያል አንተን ይቀጣሃል አለው። ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው። መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ። ➯በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ➯ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን አንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ከፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው። ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞቱ። ➯ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር። የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ አላቸው እነርሱም ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራችው። ➯እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ። ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላዕላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅድሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት። ➯የሀገር ሰዎች በጠዋት ነቅተው ወደ ውጪ በወጡ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ። ➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። #ስንክሳር ሰኔ 7
Show all...
👍 94 33🙏 18🕊 7
Show all...
$PRETON DROP

Preton community: @preton Preton community: @preton_cis Chat: @chat_preton Cooperation: @eleidans

Show all...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.