cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ካቦድ ☁️

በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መኖር Living in the presence of God

Show more
Advertising posts
574
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-1730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

00:55
Video unavailableShow in Telegram
ፓስተር ጌቱ አያሌው(እግዚአብሔርን መፍራት)
Show all...
7.26 MB
Photo unavailableShow in Telegram
glory 5.mp35.16 MB
glory 4_1.mp33.18 MB
glory 3.mp33.31 MB
glory 2.mp31.25 MB
glory.mp35.24 MB
Photo unavailableShow in Telegram
መሲሁ ዛሬም ህያው ሆኖ ከጎንህ እንዳለ ቃሉ ሲነገር በልብህ የሚነድደው እሳት ምስክር ነው🔥 “እርስ በርሳቸውም፦ በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።” ሉቃስ 24፥32
Show all...
ንግሥተ ሳባ የኢትዮጵያ ወይንስ የየመን ንግሥት? ይህችን ሴት የሂብሩ ቃል (Malkaṯ Səḇāʾ) ማልካት ሳባ ብሎ ይጠራታል። ማልካት ለሚለው ቃል የአማርኛ አቻ ትርጉሙ ንግስት የሚለው ሲሆን ይህች ሴት በሳባውያን ላይ ትገዛ የነበረች ንግስት በመሆኗ ንግሥተ ሳባ ወይንም የሳባውያን ንግሥት የሚለውን ስያሜ አስገኝቶላታል። ሳባውያን ጥንት በደቡባዊ አረብ አከባቢ ሰፍረው ይኖሩ የነበሩ የመናውያን ሰዎች ሲሆኑ በዘመኑ የነበረውን የነገስታቶቻቸውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያሰፈሩበት ጥንታዊ ፅላት በቱርክ ኢስታንቡል በሚገኝ ኤንሸንት ኦሪየንት ሙዚየም (Ancient Orient Museum) ተመልክቶ ይገኛል። በሀገራችን በኢትዮጵያ በሚነገር አንድ ታሪክ ታዲያ ይህች ሴት የኢትዮጵያ ንግሥት እንደሆነችና ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንጉሥ ሰለሞን ሄዳ ከእርሱ ሚኒሊክ የሚባል ልጅ እንደወለደች፣ ይህም ልጅ ሰሎሞናዊውን መንግሥት በኢትዮጵያ እንዳስቀጠለ ይታመናል። መፅሐፍ ቅዱስ ይህች ሴት ወደ ሰለሞን መውረዷን ቢናገርም ከሰለሞን ግን ልጅ እንደወለደች ፈፅሞ አይነግረንም። በአዲስ ኪዳን ጌታ ኢየሱስ ይህች ሴት ንግሥተ አዜብ/የደቡብ ንግሥት (ከግእዝ ትርጓሜ አዜብ=ደቡብ) እንደሆነች ይጠቁማል(ማቴ 12፥24)። ከዚህ በተጨማሪ መፅሐፍ ቅዱስ ሳባውያን ወንዶች ነገስታቶች እንደነበሯቸው ይነግረናል (መዝ 72፥10)።
Show all...
የእግዚአብሔር ቃል ሲነበብ እንባዬ ይቀድመኛል። እምባዬ የሀዘን አይደለም የደስታ ነው፣ ልብን የሚሞላ ደስታ። የእግዚአብሔርና የበጉ ምስክሮች ያዩትንና የሰሙትን ሲተርኩ ነፍስም አይቀርልኝ። በሕይወቴ የትኛውም ደረጃ ብሆን የማይለዋወጥ የቃሉና የምስክሮቹ ፍቅር እኔነቴን ተቆጣጥሯል። በዚያ መፅሐፍ የማይታየው የክብር አምላክ ይተረካል፣ ለውበቱ መደምደሚያ የሌለው እርሱ በብርሃን ተከቦ ከፀሐይ ይልቅ ሰባት እጥፍ እያበራ ይኖራል ብለው ይመሰክሩለታል፣ ሰማያትን የዘረጋው እርሱ ጎንበስ ቀና እያሉ በሚያመልኩት በእልፍ አእላፋት መላእክት ተከቦ ይኖራል ይሉናል። የእግዚአብሔር ልጅ አለምን ለማዳን ወርዶ እንደሰው ሲመላለስ አብረነው ነበርን ይሉሃል፣ ከጎኑ ሆነን ተራምደናል ታምራቱንና ድንቁን በአይኖቻችን አይተናል ፣ በማንነቱ ተደንቀን በእውነት ይሄስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለን በፊቱ መስክረናል ይሉሀል። ስለሰው ልጆች መከራን ሲቀምስ፣ ለሰው ልጆች ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ በአሰቃቂ መንገድ ራሱን ሲሰጥ ያኔ ነበርን ይሉሃል። ደግሞም በሶስተኛው ቀን ከሙታን ለመነሳቱ ህያው ምስክሮች ነን ይሉሃል፣ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በደመናት በኃይል ከፍ ከፍ ሲል ወደ ሰማያት ወደ ውስጠኛው ሰንጥቆ ሲዘልቅ ቀና ብለን ተመልክተነዋል ይሉሃል...ይኸው ቃል እነዚሁ ምስክሮቹ ወደላይ ከፍ ያለው እርሱ ዳግም በክብር ከመላእክቱ ጋር ተመልሶ ይመጣል ይሉሃል። ዋሃሃህ! እንዴት ያለ ድንቅ ምስክርነት ነው! የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር እና የበጉ ምስክር❤
Show all...