cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ: https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0 የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Show more
Advertising posts
724
Subscribers
+124 hours
+67 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሕማማተ መስቀል 👉 የፊጥኝ መታሰር /ተዓስሮ ድኅሬት/፡- ኢየሱስ ለህዝቡ ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጎመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርኩ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝምን ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈፀም ዘንድ ነው እንዳለ ጌታችን አይሁዶች በኋላ አስረው ወሰዱት፡፡ 👉 በገመድ ታስሮ መወሰድ/ተስህቦ በሀብል/፡- ጌታችን አስቀድሞ ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ እንደተናገረው ‹‹ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ስለ በደላችን ሲል እንደሚታረድ ጠቦት በገመድ ታስሮ እየተዳፋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ ከጲላጦስ ወደ ሃና ከሃና ወደ ሄሮድስ ተጎተተ ተንገላታ›› ኢሳ 53÷6 እንዳለው ስለእኛ ሲል መንገላታቱ በገመድ መጎተቱ ነው፡፡ 👉 በአፍጢም መዳፋት/ወዲቀ ውስተ ምድር/፡- አይሁድ ጌታን ኋላውን ከፊት ከግራ ከቀኝ አስረው እየጎተቱ ይጥሉት ነበር ቀኙ ሲጎተት ግራ ይለው ነበር እንዲህ መከራ እያበዙበት መሬት ሲወድቅ እየረገጡት በፈረስ በበቅሎ እየረገጡት ወዴት ሔደ ይሉ ነበር ሳዖል/ጳውሎስ/ ራሱ ይረግጠው ነበር ጌታችንም ‹‹አንተም መመለስህ ላይቀር ትረግጠኛለህ›› ብሎት ነበር፡፡ 👉 ተቀዝፎ ዘባን /ጀርባውን መገረፍ/፦ ከግንድ ጋር አስረው ኦሪት ከአርባ አትግረፍ ትላለችና እነሱ ግን ሠላሳ ዘጠኝ ይደርሱና ጠፋብኝ ዘነጋሁት እያሉ እየተመለሱ ይገርፉ ነበር ታድያ እንዲህ እያሉ 6666 /ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት/ ጊዜ ገረፉት ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር ድረስ አስቀድሞ ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ ‹‹ጀርባዬን ለገራፊዎች ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ›› ኢሳ 50÷6 ብሎ እንደተናገረ፡፡ 👉 ከምሰሶ (ከግንድ) ጋር መጋጨት ተገፍኦ ማዕከለ ዓምድ/፡- ሁለት ወፍራም ግንድ መኃሉን ፈልፍለው ፊትና ኋላ ግንዶቹን ተክለው ጌታን በሁለቱ ግንድ መሐል በማቆም ክንዱን በገመድ አስረው ግማሾቹ ከፊቱ ግማሾቹ ከኋላ ቆመው ተራ በተራ ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየሳቡ ከግንዱ ያጋጩት ነበር፡፡ 👉 በጥፊ መመታት /ተጸምዖ መልታህት/፡- በጥፊ እየመቱት ክርስቶስ ሆይ የመታህ ማነው? ትንቢት ተናገርልን እያሉ ይዘብቱበት ነበር አስቀድሞ ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ ‹‹ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ እንዳለ፡፡ 👉 ምራቅ መተፋት /ተወክፎ ምራቅ ርኩሳን/፡- አይሁዳውያን ይሳለቁበት ምራቅ ይተፉበት ነበር ጌታ ግን አስቀድሞ አዳምና ሔዋን በድለው ሳሉ ዲያቢሎስ በህገ ልቡናቸው ምራቅ እየተፋ ሲኦል አውርዷቸው ነበርና ለእነርሱ ካሳ ሊሆን በፊቱ ተተፋበት፡፡ 👉 ተኮርዖተ ርዕስ /በዘንግ በዱላ ራሱን መመታት/፡- አይሁድ ከመሳለቃቸው ምራቅ ከመትፋታቸው አልፎ በዘንግ/በዱላ/ ራሱን ይመቱት ነበር ጌታ ግን የአዳም ርዕሰ ሕገ ልቡናውን ዲያቢሎስ በዘንግ እየመታ አውርዶት ነበርና ካሳ ሊሆን በዘንግ ራሱን ተመታ፡፡ 👉 አክሊለ ሦክ/የእሾህ አክሊል ደፋ/፡- ለመላዕክት የእሱ ባለሟል ለሆኑ ብርሀናዊ የፀጋ አክሊል የሚያቀዳጀውን አምላክ አይሁድ ሺህ ጥቃቅን ሰባ ታላላቅ የብረት እሾህ ያለውን ዘውድ ጎንጉነው ምድራዊ ንጉስ ነህ ሲሉ በራሱ ላይ አቀዳጁት፡፡ ሊቃውንት አባቶቻችን እንደሚሉን የእሾህ አክሊሉ ሲያቀዳጁት ራሱን በስቶ ልቡ ጋር ይደርስ ነበር ይላሉ፡፡ 👉 ሰሪበ ሐሞት/ሐሞት መጠጣት/፡- አስቀድሞ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረው ‹‹ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ ለጥማቴ ሖምጣጤ አጠጡኝ›› መዝ 68÷21 ብሎ ልበ አምላክ ዳዊት የተናገረው ይፈፀም ዘንድ ለሰው ልጆች ዳግም የማያስጠማ የዘላለም መጠጥ ዳግም የማያስርብ ዘላለማዊ ምግብ የሚሰጥ አምላክ በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ ሲል ሆምጣጤና ሐሞት ነው የቀረበለት በዘመነ ስደቱ ለእናቱ ከአለት ላይ ውኃ አፍልቆ ያጠጣ አምላክ አስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ ከሰማይ መና አውርዶ ከአለት ላይ ውኃን አፍልቆ ያጠጣ አምላክ ዛሬ ተጠማሁ ሲል ግን የቀረበለት ሆምጣጤና ሐሞት ነበር፡፡ ✍ በአጠቃላይ ‹‹በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ›› ብሎ ኢሳይያስ እንደተናገረው ከትኩሳቱ ከሚያቃጥለው አብርዱልኝ ከስቃይ ከመከራው አስታግሱልኝ ሳይል በትዕግስት በትህትና መከራ መስቀልን ተቀብሏል አባ ህርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ ‹‹በመከራው ጊዜ በሚመቱት ጊዜ አፉን ያልከፈተ ምን ዓይነት ትዕግስት ነው›› ብሎ ቁ 1ላይ እንደገለፀው አንዲት እንኳ ቃል አልታናገረም ሲል ምንም አልተናገረም ማለት አይደለም ግን የትዕቢትና የፍርሀት ቃል አልተናገረም እንጂ ግን አሰረ ፍኖቱን ለሚከተሉ አብነት ሊሆን ከላይ በዝርዝር ያስቀመጥነውን ሰባቱን አፅርሐ መስቀል ተናግሯል፡፡ 👌 ለኛ ሲል ፈጣሬ ኩሉ ፍጥረታት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጥረት ሊቀበለው የማይችለውን መከራና ስቃይ ተቀበለ። ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን! ይቆየን!
Show all...
ዛሬ አንድነቱ በስራ ላይ ለነዳያን ☝️ሰላም ለእናንተ ይሁን! የተወደዳችሁ ውድ ወንድሞችና እህቶች የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመስቀል ስር የአደራ ልጆች እንደምን ከረማችሁ! እንደምን አላችሁ! አሜን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር እስከዚች ዕለት ስላደረሰን ስሙ ይክበር ይመስገን! በፍጥረታት አንደበት ሁሉ የተመሰገነ ይሁን! እንዲሁም አትለይምና እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብርና ምስጋና ይድረሳት አሜን:: 🤲✝️🕊 በየካ ክ/ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ስር የምትገኙ ሰንበት ት/ቤቶች በሙሉ፡ በ2016 ዓ.ም የየካ ክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች እንዲሁም የቤተ-ክርስቲያናችን ሚዲያ በተገኙበት በአደይ አበባ እየተገነባ ባለው አዲሱ ስቴዲየም አካባቢ ልዩ ቦታው አያት ሆስፒታል አጠገብ ወይም ከሞይንኮ ጀርባ በሚገኘው ቦታ ላይ ከ500 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን እና ነዳያንን ሚያዚያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ ለመመገብ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በእናንተ በኩልም የሚጠበቅባችሁን እንድታደርጉ በነድያን አምላክ ስም እንጠይቃለን። "ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።" [ ማቴ.፲፱፥፳፩ ] አስተባባሪ:- የየካ ክ/ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልማትና በጎ አድራጎት ክፍል የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! 👇 Telegram: https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Show all...
13ቱ ሕማማተ መስቀል!!! 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት) + + + + + + + ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት!!! 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46) 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34) 3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43) 4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27) 5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28) 6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46) 7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30) + + + + + + + ሰባቱ ተዐምራት !!! ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት፦ 1. ፀሐይ ጨልሟል 2. ጨረቃ ደም ሆነ 3. ከዋክብት ረገፉ 4. ዐለቶች ተሠነጠቁ 5. መቃብራት ተከፈቱ 6. ሙታን ተነሡ 7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ + + + + + ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች፦ 1. # ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት 2. # አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት 3. # ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት 4. # አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት 5. # ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት + + + + + # አምስቱ_የእመቤታችን ኃዘናት፦ 1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35 2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:41-48 3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1 4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡ ዮሐ 19:17-22 5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:38-42
Show all...
"አንድ እግር የለለው እንዲህ ሳይሰለች ይሰግዳል🙏 "እኛስ እስኪ እራሳችንን እንጠይቅ ለምን ከበደን ለፈጣርያችን ስግደት እንዳንሰግድ አዚም ያደረገብን ምን ይሆን ❗️
Show all...
“#እንደ_ጲላጦስ_ግራ_የገባው_ዳኛ_አትሁኑ!” ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ገና በሕፃንነታቸው የጉባዔ ቤት ደቀመዝሙር ሆነው ሳለ አጼ ካሌብ ከአንድ ወጥ ድንጋይ በሚያስደንቅ ጥበብ ያነጸውን ጥንታዊውን ብልባላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሊሳለሙ ሲሄዱ ነበር እጅግ ከፍ ባለውና በከበረው ማዕረገ ክህነት ጵጵስናው ደረጃ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንደሚያገለግሉ የተገለጠላቸው። ብፁዕነታቸው ወደ ብልባላ የሄዱበት ተሳክቶም ያቺ የቤተመቅደሱ ጠባቂ የብልባላዋ ንብ ተነግሮ የማያልቀውን መለኮታዊ ተአምር ገልጣ ነድፋቸው፤ ከሕመማቸው ተፈውሠው፤ ስብሐተ እግዚአብሔርን እያደረሱ ነበር ወደ ቤተ ጉባዔ የተመለሱት። እንግዲህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከድቁና እስከ ጵጵስናው ማዕረገ ክህነት ደርሰውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ፍቅር በተሞላበት ትሕትና እያገለገሏት ያሉ ብፁዕ አባታችን ናቸው። ብፁዕነታቸው በሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት ከተመደቡበት ጊዜ እስከ ዕርግናቸው ድረስ ሃገረ ስብከቱን በግሩም አባታዊ ጥበብ የመሩ ሲሆን በእርጅና ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ለማገልገል ቢቸገሩ ግን ሊቁ አባታችን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ተመድበውላቸዋል። ብፁዕነታቸው በዓለ ትንሣኤን አስመልክቶ ያስተላለፉትን አባታዊ መልእክታቸውን የወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ዘግቦታል። ብፁዕ አባታችን መላው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻቸውን፦ “እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!” ብለዋል። በተጨማሪም፦ “በመሪነት ደረጃም ያላችሁ እንደ ጲላጦስ ግራ የገባው ዳኛ አትሁኑ! ጲላጦስ ጌታን፦ «ምንም ዓይነት ለግርፋት ለስቅላት ቀርቶ ለወቀሳ የሚሆን ወንጀል አላገኘሁበትም!» ካለ በኋላ «ስቀለው! ስቀለው!» እያሉ የሚጮሁት ስለበዙ ብቻ በትክክለኛ አቋሙ እንዳይፀና በጊዜያዊ ጥቅሙ ግራ ተጋብቶ ተገቢ ያልሆነ ፍርድ ሰጥቷል፡፡ ዛሬ ወቅቱ ተገቢ የሆኑና ያልሆኑ ድምፆች የተበራከቱበት መጥፎ ጊዜ ነው፤ መሪዎች እንደ ጲላጦስ ጥቅም ይቀርብኛል በሚል ሥጋት ግራ ሳትጋቡ እውነተኛ ድምጽን ሰምታችሁ ፍትህ ስጡ!” በማለት ብፁዕ አባታችን አሳስበዋል። ለቅዱስ ሲኖዶስ ሞገስ ከሆኑት አረጋዊያን ብፁዓን አበው መካከል አንዱ የሆኑት የብፁዕነታቸው የአቡነ ቄርሎስ ክብርት ቡራኬ ለሁላችን ትድረሰን! አምላከ ቅዱሳን ቅድስት ሃገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅልን!!! 👉 "ወከመዝ፡ ያድኅን፡ በፍፁም፡ ሰብአ፡ ሐመ፡ ወሞተ፡ ወተቀብረ፤ ወተንሥአ፡ እሙታን፡ አመ፡ ሣልስት፡ ዕለት። - ሰው ሆኖም ሰውን ፈጽሞ ያድን ዘንድ ታመመ፣ ሞተ፣ ተቀበረ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡" ሃይ.አ. ዘ፫ቱ ምዕት ፲፱፥ ፳፬ 👉 ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድም፦ “ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፡ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን፡ ብርሃኖሙ ለፍጹማን፡ መርዐዊሃ ለቤተ ክርስቲያን - የጻድቃን ሞገሳቸው፣ የፍጹማን ብርሃናቸው፣ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ክርስቶስ በገናና ኃይልና ሥልጣን ከሞት ተነሣ።” ብሎ ዘምሮለታል። 👉 ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ መጥቶ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” ያላቸው እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ቅድስት ዕለት ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን በያሉበትና ለሃገራችን ኢትዮጵያ የማይናወጽ ፍፁም ሰላሙን ያድለን። ዮሐ ፳፥ ፲፱ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ የቃልኪዳን ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች ሁላችሁ በያላችሁበት ከመላው ተወዳጅ ቤተሰቦቻችሁ ጋር መልካም በዓለ ትንሣኤ ይኹንላችሁ!!! 👇በቴሌግራም ቤተሰብ እንሁን👇 ⛪👉 @degusamraw ⛪👉 @degusamraw ⛪👉 @degusamraw
Show all...
ክርስቶስ በሰሙነ ሕማማቱና በዕለተ ስቅለቱ የተቀበላቸው ፀዋትወመከራዎች እጅግ በጣም ብዙዎች እንደሆኑ ከቅዱሳት መጻሕፍት መረዳት የሚቻል ሲሆን በተለይ በግብረ ሕማማቱና ድርሳነ ማሕየዊ በተሰኙ መጻሕፍት በዝርዝር ተገልጠው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ 13ቱ ሕማማተ መስቀል የተሰኙት ጥቂቆቹ ናቸው እነሱም ተአስሮ ድኅሪት፤ ተስሕቦ በሐብል፤ ወዲቅ ውስተ ምድር፤ ተከይዶ በእግረ አይሁድ፤ ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ፤ ተጸፍኦ መልታሕት፤ ተቀስፎ ዘባን፤ ተኮርዖተ ርእስ፤ አክሊለ ሶክ፤ ፀዊረ መስቀል፤ ተቀንዎ በቅንዋት፤ ተሰቅሎ በዕፅና ሰሪበ ሐሞት ናቸው፡፡ መድኃኒታችን በዕፀ መስቀል ላይ እያለ ዐርብ ከ6 እስከ 9 ሰዓት ባለው ጊዜ 7 ተአምራት ተደርገዋል፡፡ 1.ፀሐይ ጨልሞአል፤ 2.ጨረቃ ደም ሆኖአል፤ 3.ከዋክት ረግፈዋል፤ 4.አለቶች (ድንጋዮች) ተፈረካክሰዋል፤ 5.መቃብራት ተከፍተዋል፤ 6.ሙታን ተነሥተዋል፤ 7.የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ማንም ሳይነካው ራሱ ተቀዷል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
Show all...
#ዓርብ #የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። #መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ ተላልፎ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ሌሊቱን በሙሉ ከአንዱ ገዥ ወደ ሌላው ገዥ፤ ከአንዱም ሊቀ ካህናት ወደ ሌላው ሊቀ ካህናት እያመላለሱት በሐሰት ሲከሱትና ሲያስመሰክሩበት፤ ሲኮንኑትና ሲወነጅሉት አድረው ዐርብ ጧት ወደ ገዥው ወደ ጲላጦስ ዘንድ ቀርቦ ሞት የማይገባው አምላክ በግርግር፣ በተድእኖና በጩኸት ብዛት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እንዲሞት የተወሰነበት በመሆኑ በዚሁ በዕለተ ዓርብ በቀትር ጊዜ ስድሰት ሰዓት ሲሆን በግራና በቀኝ ሁለት ወንጀለኞች፣ ምንም ወንጀልና በደል የሌለበት ንጹሐ ባሕርይ ክርስቶስ ያላንዳች ጥፋት እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ በወንበዴዎች መካከል በመስቀል ላይ ተሰቅሏል፡፡ ከ6 -9 ሰዓትም በመስቀል ላይ ሆኖ ብዙ ተአምራትን ሲፈጽምና ለሰው ሁሉ ትምህርት ሰጭ የሆኑ ቃላትን ሲናገር ከቆየ በኋላ በ9 ሰዓት ተጠማሁ ሲላቸው ያቀረቡለትን መራራ ሐሞትና ከርቤ ከቀመሰ በኋላ ተፈጸመ የሚለውን የመጨረሻ ቃል ተናግሮ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለይቶ በራሱ ፈቃድ የመጣበትን የማዳን ሥራ ፈጽሞአል፡፡
Show all...
ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድን ጨምሮ ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ታሠሩ ! በቅርቡ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ ለጥያቄ ይፈለጋሉ በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለሚዲያችን ገልጸዋል። በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል። ምንጭ: ተዋሕዶ ሚዲያ የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! 👇 Telegram: https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Show all...
#ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! 👇 Telegram: https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Show all...