cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከፍቅር ደጅ 💕💞

@ke_feker_deje_©በዚ group: ~#የተለያዩ የህይወት ገጠመኝ እና ታሪኮች፤ ~#የፍቅር ግጥሞችና ደብዳቤዎች፤ ~#የታዋቂ ሰዎች ምርጥ ንግግርና ፍልስፍና፤ ~#የፍቅር ገጠመኞች ~ #ሀገርኛ ጉዳዮች፤ ~ #ስለ ጤና እና ቴክኖሎጂ መረጃ፤ ~#በ ሃገርኛ እና ኢንተርናሽናል ቋንቋዎች፤ ~Amharic,English, Afan Oromo,Tigregna

Show more
Advertising posts
609
Subscribers
-224 hours
-57 days
-1530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰባኪው አዲስ ተጋቢ ሙሽሮችን ወደመድረክ ጠርቶ የጋብቻ ስስነርዓታቸውን እያስፈፀመ እያለ "ይህንን ጋብቻ የሚቃወም ካለ ወደ መድረክ ይምጣ አለ!" በዚህ ጊዜ አንድ የ3 ዓመት ህፃን ልጅ ያቀፈች እርጉዝ ሴት ከአዳራሹ መጨረሻ ወንበር ተነስታ ወደፊት ማዝገም ጀመረች። ሙሽሪትም ያች ህፃን የያዘች እርጉዝ ሴት ወደፊት ስትመጣ ስታይ ሙሽራውን ወራዳ ልክስክስ በሚስትህ ላይ ነው ልታገባኝ የነበረው አለችና በጥፊ መታው በጎን ባለው በር ወጥታ ሮጠች። ታዳሚውም አብዛኛው በተፈጠረው ክስተት ተገርሞ እያጉረመረመ በሚቀርበው በር እየወጣ ሄደ። ያች ህፃን የያዘች ሴት ፊት ወንበር ላይ ስትደርስ ከአንዱ ወንበር ላይ ቁጭ አለች። ሰባኪውም ግራ ተጋብቶ "ምነው ችግር አለ እህቴ?" አላት። ያች ሴትዮም "ምንም ችግር የለም ጌታዬ! ጆሮዬ የመስማት ችግር ስላለበት በደንብ እንዲሰማኝ ከፊት ልቀመጥ ብዬ ነው!" አለችው። ♥️የመልዕክቱ አንኳር ጭብጥ፡- የነገሮችን ፍፃሜ ሳናይና ሳንሰማ ቸኩለን በግምት አንደምድም ማስተዋል አለመቻላችን እና ቸኩሎ መወሰን ብዙ ያሳጣናል ። መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!! @natani273
Show all...
🍃👁በ'ነሱ ቤት👁🍃 👁🌸ክፍል ዘጠኝ🌸👁 🌸🍃🌸🍃🌸🍃🌸 ቦሌ አካባቢ የምትገኝ አነስተኛ ናይት ክለብ ውስጥ እነ ሰመረ በሞቅታ ጮክ ብለው እኩል በሚባል ደረጃ ያወራሉ ። አልፎ አልፎ ባልተግባቡበትም በተግባቡበትም  ጉዳይ ላይ እኩል ጮክ ብለው ይስቃሉ ። በናይት ክለቡ ውስጥ ደጋግሞ በመምጣትና ገንዘባቸውንም ያለስስት ስለሚረጩት እዛቤት ያሉ ቆነጃጂት አስተናጋጆች በነሱ መምጣት ደስተኞች ናቸው ። ስለዚህም በሳቃቸው ይስቃሉ ምቾታቸውን ይጠብቃሉ ። ሰመረና ጓደኞቹ ደሞ ከሌሎች ደረጃቸውን ከጠበቁ ትላልቅ ክለቦች ይበልጥ ይህንን ቤት ይወዱታል ። ምክንያቱም እዛቤት ያሉት ሴቶች ውበታቸው ይለያል  በዚያላይ እነሰመረ ለሚጠይቁት ጥያቄ ሁሉ መልሱ አላቸው ።ሲፈልጉ የፈለጓትን ሴት ይዘው ይወጣሉ ገንዘባቸው ይጨነቅ  ይህንን ቤት ግን ይበልጥ የሚወደው ጌታነህ ነው  ። ሌላ ስም ያላቸው ናይት ክለቦች ለሱ ምቹ አይደሉም ምክንያቱም የታላቅ ወንድሙ መስፍን  መኖር ሊረብሸው ይችላል ።ወንድሙ መስፍን እድሜው ወደ ሠላሳ ስድስት ቢገመትም ትዳር አልያዘም በዛላይ ጭፈራና መዝናናት እንደ ታዳጊ ጎረምሳ ነው የሚወደው ። እሱም እንደ ጌታነህ ከአንድ ሴት ጋር የመርጋት ችግር አለበት ። ይህንን አመሉን ደሞ ቤተሰቦቹ ጥግ ድረስ ነው የሚያውቁት ።ከበፊት ጀምሮ የቤት ሰራተኞቻቸውን ጭምር ሲያስቸግር ያውቃሉ ። ቤተሰቦቹ አመሉን ችለው ነው የሚኖሩት ።የመስፍንን የስራ ብቃት ግን ማንም የቤተሰቡ አካል አይወዳደር ።አባቱ አቶ ጀንበር የሚወዱትም በዚ ምክንያት ነው ።ብዙ ሴቶችን በተመለከተ ስሞታ ቢደርሳቸውም ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ያልፉታል። ጌታነህ ወንድምየው ያለበት መገኘት በጭራሽ አይፈልግም ።ምክንያቱም ልክ እንደ ቆፍጣና ወንድም ልቆጣጠርህ የሚል ፀባይ አለው ።ጌታነህ ደሞ አይዋጥለትም ስለዚ ከዚ ሁሉ ድብቅ ቦታ መርጦ መዝናናትን ያዘወትራል ።እነ ሰመረም የጓደኛቸውን ስሜት ተረድተው በሱ መንገድ መዝናናትን መርጠዋል ።      ሰመረ ሞቅ እያለው ሲመጣ ወሬው ተቀየረ ።'ልጅቷ ያቺ ልጅ በናታቹ በጣም ታሳዝናለች 'ማለት ጀመረ ። እንየው የዘወትር አስተናጋጃቸው እና ሁለት ጊዜ አብሯት ያደረውን ንግስት የተባለች እድሜዋ ከሃያ የማይዘላትን ወጣት ጠርቶ መነካካት ጀመረ ። ጌታነህ ሰመረ ሞቅ ሲለው እንደልቡ እንደሚያወራ ስለሚያውቅ እንደ ቀኑ አልተከራከረውም ። "ስማ በጠይም ፊቷላይ የሚነበበውን የተጠራቀመ አዘን እንደኔ ተጠግተህ ብታየው እኮ ! ታውቃለህ በዛላይ እንደዛ እንካን ሆና የልጅነት ውበቷ ለየት ይላል መቼም እድሜዋ ሲጨምር እና ራሷን ስትጠብቅ ታየኝ ምን እንደምትመስል "አለ ወደ ጌታነህ እያየ ።ጌታነህ አልተዋጠለትም በግዴለሽነት ጭንቅላቱን ነቀነቀለት ። የሰመረ ሁኔታ ምቾት አልሰጠውም 'ምንድነው ለአንዲት የደሃ ልጅ የምጨነቀው 'ብሎ ለራሱ ፈገግ አለ ። ልጅቷ ቆንጆ ታዳጊ ናት ነገርግን ደረጃቸው አይደለችም እንደሷ ያሉ ልጆችን በጊዜ አስተናግዶ መሸኘት ነው የሚፈልገው። "ስማ እሷን ተዋትና ቤት ደውል እና ዛሬን እነ እንየው ቤት እንደምናድር ንገር እንዳያስቡ ።እኔም ለዳድ እደውላለው "አለው "ለምን እንዴ ገናነው ሰአቱ  "አለ ሰመረ "ኧረ በናትህ የችኮቹ እቅፍ አልናፈቀህም  እኑ እያበሰለ ነው እኔም ወደ ቤቲ ልዘምት ነው  በቃ ዛሬ ያማረኝ ቤቲን እያስጮሁ ማንጋት ነው ኪኪኪኪ "ብሎ ሳቀ ።ሰመረ አብሮት ሲስቅ ቆይቶ ። "እሺ እኔ ግን ማደር ካለብኝ ማፊን መጥራት ይኖርብኛል "አለ በቅርቡ የተዋወቃትን  ቅንጦት ያንገላታትን ልጅ ። "አትለኝም ያችን ሞዛዛ እኔማ እሷ ነገርየው ላይ እያለህ እራሱ አንዴ ሜካፔን ልየው ሳትልህ አትቀርም ኪኪኪኪኪ "ብሎ አሽካካበት "እሱን ለኔ ተወው ሰው ያለ አመል መች ይፈጠራል በጊዜ ሂደት አስተካክላታለው "አለው አብሮት ስቆ "ምን አስጨነቀ ዘና የሚያደርግህን ሰው አትፈልግም  ተመልከታት እዛጋር አዲስ ልጅናት መሰለኘ  የዋላው ደሞ የሰጠ ነው እሱላይ ውረድበት ኪኪኪ የምን ማፊ ነው "አለው ወደ አንዲት አስተናጋጅ እየጠቆመው። ሰመረ የጌታነህን ጥቆማ ወደጎን በመተው ከራሱ ጋር መማከር ጀመረ አወጣ አወረደ እና በመጨረሻ ወሰነ እነሱን እዛው ባሉበት ትቶ ወደቤቱ ሄዶ የሰላም እንቅልፉን ለመተኛት ። አሳቡን ሲነግራየው ትንሽ ተከራከሩትና ደየማይረታ ሲሆንባቸው ። እንደፈለክ አሉት በቅሬታ ።ሰመረ ቀን ላይ ካያት ትንሽዬልጅ ጀምሮ ፀባዩ ተቀይሮባቸዋል ።አዲስ ሰመረ ሆኗል ለነሱ ። ሰመረ ደሞ ድንገት ከጓደኞቹ ጋር የሚያሳልፈው ምሽት ስሜት አልሰጥ ብሎታል ። ስለዚ ተነስቶ ተሰነባብቷቸው ከናይት ክለቡ ወጥቶ ወደ መኪናው አመራ,,,,,,,,,,, ይቀጥላል......      ፍቅር፡ሰላምና ጤና ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምን ጊዜም ከዘመንህ አይለይ!!!!!!! ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ☑️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩት፡ ☑️#Share 👇👇👇👇👇👇👇👇         @natani273
Show all...
🔴🌸በ'ነሱ ቤት🌸🔴   👁 ክፍል ስምንት👁 🍃🌸🍃🌸🍃🌸🍃 የቤቱ ድባብ የሚመች አይደለም በሰውኛ ቢሆን ቅዝዝ ብሏል ሊባል ይችላል ። አብላካት እናቷን ደጋግማ እየተጣራች ወደውስጥ ገባች በሩ ክፍት ነው   መብራቱ ግን አልበራም ።ግራ እየገባት ወደ ጓዳ ዘለቀች እናም አይኖቿን በቀጥታ ወደ አልጋው ወርወር አደረገች ። በአልጋው ላይ እናቷን ጥቅልል ብላ ተኝታ አገኘቻት አብላካት እናቷ ስላለች እፎይ ብትልም ዳግም እንዳመማት ስለገባት ጭንቅ አላት እና ተጠግታ ትንፋሿን አዳመጠች ቶሎ ቶሎ ትተነፍሳለች ። ፊቷን ከጉንጯ ጋር አገናኝታ አሻሸቻት ።እናቷ ግን ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብታለች ።ቀስብላ ተነሳችና ሄዳ የቤቱን በር በመዝጋት ተመልሳ መጣች ያደረገቻትን ሲልፐር ጫማ በማውለቅ ከእናቷ ጎን ተኛች ምን አልባትም በርዷት ሊሆን ይችላል ብላ በማሰብ አቀፈቻት ።  እናም ስለ እናቷ አሰበች 'አንድ ነገር ብትሆንብኝስ ምንድነው የምሆነው? ያለ እሷ ማን አለኝ ? ያለሷ ፍቅር እንዴት እኖራለው  ሲከፋኝ ስጨነቅ ሳዝን ማን አለው ብሎ ያፅናናኛል ኡኡፍፍፍ እናቴ ምንም አትሁኚብኝ ፈጣሪዬ አደራህን ' ብላ ይበልጥ በእናቷ ዙሪያ የጠመጠመችውን እጇን ይበልጥ አጠበቀች ።  በዚ ጊዜ እናቷ በረጅሙ ተንፍሳ አይኗን ቀስበቀስ ገልጣ አየቻት  እናም ፈገግ አለች ።አብ ላካት እንባ ባቀረሩ አይኖቿ እያየቻት "እናቴ የኔ ውድ እናት  ነቃሽልኝ "አለቻት "ምነው አቢ ?ፊትሽ ልክ አይደለም ?ተኝቼ ስለጠበኩሽ ነው ? ይቅርታ የኔ ቆንጆ ልጅ አሁን ተነስቼ ቤቱን ሞቅ ሞቅ አደርገዋለው ። ቅድም እኮ ጉሊት ወጥቼ ብታይ ፀሐዩ አናት አናቴን ሲለኝ እራሴን አመመኝና  ከተወኝ ብዬ ወደቤት መጥቼ ጋደም አልኩ በሩን እንኳ አልዘጋውትም እኮ ቶሎ እነሳለው ብዬ ሆሆሆ "እያለች የአብላካትን ግንባር ሳም ሳም አደረገች ።አብላካት እናቷ ህመሟ ከዛም በላይ መሆኑን ታውቃለች ።ስለዚ እራሷ ከተኛችበት በመነሳት ። "እማ አንቺ ተኚ እረፍት አድርጊ እኔ ቆንጆ ቡና አፈላልሻለው "አለቻት "አይ አብዬ እኔ ነኝ እንጂ ልጄን መንከባከብ ያለብኝ ደሞ በዛላይ ለአራት ሰአት ያህል የት እንደነበርሽ ትነግሪኛለሽ እሺ "አለቻት ልጇን መጫን ባትወድም አንዳንዴ እሷ ስራስራ ስትል ከቁጥጥር ውጭ እንዳትሆንባት ትሰጋለች "ውይ እናቴ አሁንስ ይበቃል ስለኔ የምትጨነቂበት ጊዜ አልፏል ትልቅ ሆኛለው እኮ እንዴዴዴ ከዚ በዋላ ስራ ፈልጌ መግባት አለብኝ እራሴንም መቻል እንዲሁም ላንቺም መትረፍ አለብኝ እስከመቼ ነው የምታባብይኝ !"አለቻት አሳቧን እንዳትቃወማት እያስጠነቀቀችም ጭምር "ወይ ስራ ወይ ትልቅ ሰው አብዬ አንቺ መቼ ከስራ ተለይተሽ ታውቂና ነው ይኽው ከኔጋር ከእፃንነትሽ ጀምሮ ጉሊት ስትሰሪ አልነበር ።የኔ ውድ አንቺ እኮ ልህልት ነበርሽ ምን ዋጋ አለው ከኔ ተፈጥረሽ ተሰቃየሽ አሂሂሂሂ"ብላ በቁጭት እጇን ጨበጠች አብላካት እናቷ በዛመልኩ እንዳታስብ እያፅናናች ሳመቻት እናም ከቤት ምን አስባ እንደሄደች አንዳችም ነገር ሳደብቃት አወራቻት ።ስለ ሰመረ ስለ ጓደኞቹ  ስላደረገላት ነገር  ስለ ሰሚር  ሁሉንም ። የአብላካት እናት ፊቷ ላይ ምንም ነገር ባታሳይም በልጇ ገጠመኝ ተጨንቃለች ።በተለይ ሰመረ የሰጣት አምስት ሺ ብር ያለነገር አይደለም ብላ ፈርታለች ። የምትፈራው ነገር ሊደርስ እንደሆነ ተሰማት በተለይ የልጇ ውበት እያደገች በሄደች ቁጥር ሲጨምር አንድ ቀን በጨካኝና ደንታ በሌለው ወንድ እጅ ትወድቅብኛለች ብላ ትፈራ ነበር ።ያጊዜ የደረሰ መሰላት ።  አንድ ልጇን ልክ እንደሷ ሕይወቷን እንዲያበለሻሹት  አትፈልግም ።ልጇን ደሞ እንዲእያለች ፍርሃት መልቀቅ የባስ እንድትደናበር ማድረግ እንደሆን ተሰማት  ድንገት ያደገችውን ልጇን በስስት እያየች በረጅሙ ተነፈሰች ኡፍፍፍፍፍ,,,,,,,, ይቀጥላል......     @natani273
Show all...
👁🔴በ'ነሱ ቤት🔴👁     ⚫️ክፍል ሰባት⚫️ 🔴👁🔴👁🔴👁🔴 አብላካት ከራሷ ጋር ስለችግሯ መብዛት እያወራች ከአምላኳ ጋር እየተሟገተች ረጅም መንገድ በእግሯ እንደተጓዘች እንኳ ልብ አላለችም ። በቻ ከዋላዋ አንድ ወጣት መጥቶ "እናት ጫማሽን ላሰራልሽ "ሲላት ።እንደመባነን አለች  በቀጥታ ወደ እግሯ አየች መሬት ለመርገጥ የሚያሳዝኑት እግሮቿ ስቃይ የበዛባቸው መሶለው ታዩዋት  ለዎትሮው ምንም የተሻለ ጫማ ባይኖራትም በእግሯ ግን ተራምዳ አታውቅም እንዲሁም መሬት ሲነካት ትንንሽ ጠጠሮች እንኳ ሲነካት እግሯን የበሳት ያህል ነው የሚያማት ። አብላካት ከዳሃዋ እናት ተገኝታ እንጂ ሁሉ ነገሯ የሚሳሳለት ነበር ።  እናቷም ብትሆን ባላት አቅም ልጇ እንዳይከፋት ታግላ ነበር ።አሁን ላይ ግን ምን እንደሚያማት ባታውቅም እመም እየደቋቆሳት የለት ጉርሳቸውን ከሟሟላት የዘለለ ለማድረግ አቅቷታል ። አኪም ጋር ሄዶ ለመታየት እራሱ ልቧ ፈርቷል ።እክምናው በቀላሉ የሚታይ ባይሆንስ ገንዘብ አውጥቶ ለመታከምም የተቀመጠ ነገር ያስፈልጋል እናስ ከየት ሊመጣ ነው ። የአብላካት እናት ባይሆን የምታመሰግነው ።አንዲት በእድሜ የገፉ የነበሩ ሴት አስጠግተዋት ኖረው የቀበሌ ቤታቸውን ስላወረሷት ።የቤት ክራይ ጭንቀት ስለሌለባት ነው ። አንዳንዴ ተከራይ ብሆን ኖሮ እኔና ልጄ ጎዳና እንወጣ ነበር ።እማማን ነብሳቸውን በገነት ያኑርልኝ ትላለች።        አብላካት ያናገራትን ወጣት ቀና ብላ ስታየው ልቧ ደነገጠባት ።ቅድም ከመኪናው ጎትቶ ያወጣት ያስተናጋጅ ልብስ ለብሶ የነበረው ወጣት ።እሱ ደሞ ለምን ተከተለኝ በዛላይ ልብሱን ቀይሮ በኖርማል ልብስ ነው "አልሰማሽኝም ሰሚር ጅላሉ እባላለው " "እሺ ምን አልከኝ "አለች እየደበራት "ጫማሽን ላሰራልሽ እዛ የሊስትሮ እቃ የያዘ ልጃለ አየሽው "አላት "እንዴት እዚ ድረስ ተከተልከኝ "አለችው በጥርጣሬ እያየችው "እሱ አስፈላጊ ነው ?"አላት "አይ ግን ማወቅ ያለብኝ ነገር ካለ ብዬ ነው" "አትጨነቂ ቅድም ሳይሽ ፍፁም ከራስሽ ጋር አልነበርሽም በዛላይ እነዛ የሀብታም ልጆች ሲከተሉሽ ደስ አላለኝም ምክንያቱም እነሱን እኛ እሬስቶራንት ሲመጡ  አቃቸዋለውአንድም ቀን ስለሴት ልጅ መልካም የሆነ ነገር ሲያወሩ ሰምቼ አላውቅም  እና ከንቺን እንዳይተናኮሉሽ ፈርቼ ነበር ። ለዛ ብዬ ሰአቴም እየደረሰ ስለነበር ከስራ ወጣው እና እየተከታተልኩሽ ነበር ።ለምን ልጅ ስለሆንሽ ብር ሲሰጥሽ በቀላሉ እንዳትሸወጂለት ለመንገር እና ልረዳሽ የምችለው " ነገር ካለ ልጠይቅሽ ፈልጌም ነው "አላት ሰሚር "ይቅርታ ልጅ ስለሆንሽ እንዳትለኝ እና በቀላሉ በገንዘብ ትታለያለሽ ብለህ አታስብ እና አመሰግናለው ላደረክልኝ መልካምነት ጫማውን እንድናሰራው የጠየከኝን ግን ተቀብዬዋለው እሺ"አለች ለምን እንደው ባታውቅም ሰሚርን አምናዋለች "እሺ ነይ በቀላሉ ያስተካክሉታል አትጨነቂ እስከዛው ግን ከዛ ሱቅ ሲሊበር ጫማ እንገዛና ታደርጊያለሽ "አላት ሰሚር በአዘኔታ እያያት ።አብላካት ተስማማች ከሰሚር ጋር ጫማ ገዛች የጓደኛዋን ጫማ አሰራች አብረው እየሄዱ ብዙ አወሩ ስለራሷ ምንም ሳትደብቅ አወራችው ።ሰሚር የሰማውን ሁሉ ሰምቶ ዝም አላለም ስለራሱ አጫወታት  አመጣጡ ከደቡብ ኢትዮጲያ ገጠር አካባቢ መሆኑን እዛ የሚረዳቸው እናትና ታናሽ እህት እንዳለው  ።አባቱ መሞቱን የቤተሰብ አላፊነቱን እሱ መውሰዱን ። አብላካት የሱን ታሪክ ስትሰማ ትንሽ ቀለላት ። ሰሚር የሚያፅናናትን ቃላት ሁሉ እየነገረ አብሯት ሰፈሯ ድረስ ሄደ ። አብላካት ሰፈሯ ስትደርስ ያካባቢው ሰዎች ደሞ ከወንድ ጋር አየናት ብለው እንዳያወሩባት በማሰብ ። "በቃ ሰሚር ሌላ ጊዜ እንገናኛለን ቻው አመሰግናለው አለችው"ሰሚር ስለገባው "እሺ ብዙ አትጨነቂ እሺ ሁሉም ነገር በሰሃቱ ይስተካከላል ኢንሸሀላ እኔም ዝም አልልሽም እኛጋር መስተንግዶ እንድትሰሪ  አነጋግርልሻለው እሺ "አላት እንደታናሽ እህቱ በማባበል "እሺ እሱን ካመቻቸህልኝ ባለውታተዬ ነህ "አለችው ሲሰነባበቱ እንደታላቅ ወንድምና እንደ ታናሽ ወንድም በመተሳሰብ ነበር,,,,,,,,, ይቀጥላል......    ፍቅር፡ሰላምና ጤና ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምን ጊዜም ከዘመንህ አይለይ!!!!!!! ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ☑️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩት፡ ☑️#Share 👇👇👇👇👇👇👇👇         @natani273
Show all...
📍ደፋር መሆን ይኖርብናል ያልተሄደበትን መንገድ ለመሄድ መድፈር ትእቢትን እልህን ጥላቻን ይሉኝታን ለመተው መድፈር ራስን ለማዳመጥ መድፈር 💡አዎ ብዙ በደል ፈፅመሀል ተፈፅሞብሀል። ብዙ ሰው ጠልተሀል፣ ተጣልተሀል ፣  ተጠልትሀል ፣ ልብህ ተሰብሯል፣ ልቦችን ሰብርሀል ፣ግን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጋር ታርቀህና ራስህን አስታርቀህ ዳግም ለመውደድ ፣ ዳግም ለማዘን ፣ዳግም ለመርዳት፣ ዳግም እርዳታ ለመጠየቅና በቅንነትና በፍቅር ለመኖር ድፈር። 📍መጀመርያ ግን ከራስህ ጋር ለመታረቅ ድፈር። ራስህን ከነሙሉ ስህተቶቹ፣ ግድፈቶቹ ፣እንከኖቹ፣ውሸቶቹ፣ ቅጥፈቶቹ፣ አስመሳይነቶቹ ሁሉ ለመቀበል ለማዳመጥና ለመውደድ ድፈር የፍቅር የይቅርታ ዘመን ነው ሲባል ወደሰማይ አታንጋጥ፣ ወደጎረቤቶችህና ጠላቶቸ ብለህ ወደፈረጅካቸው ሁሉ አታፍጥጥ መጀመርያ ከራስህ ጋር ለመታረቅ ወደውስጥህ ተመልከት፣ ወደራስህ ተመለስ ፣ ውስጥህን ፣ልብህን ፣ ህሊናህን አፅዳ፣ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ 💡ራስን መመልከት ራስን ወደ መሆን የሚያደርስ ወሳኝ መንገድ ነው። ራስህን ስትመለከት የወንድምህን ጉድፍ ሳይሆን የአንተን ተራራ ታስተውላለህ፥ በዚህ ውስጥ ደግሞ ተራራህን እየነቀልክ ራስን ወደ መሆን ታድጋለህ። ራስህን ስትሆን ብዙ ነገሮችን ታሸንፋለህ፥ መሰናክሎችን በቀላሉ አልፈህ፥ የነከሰህን የመከራ ጥርስ ውሃ የማድረግን ጥበብ ትጎናጸፋለህ። 🔑ብቻ ምን አደከመህ ራስህን ስትሆን ብዙ የደረብካቸው አላስፈላጊ ኮተቶችን ከራስህ ላይ አውርደህ፥ ንጹህ አንተነትህን ብቻ ያነገበ ማንነት ስትገነባ ያን ጊዜ ሰው መሆን ትጀምራለህ።እናም ራስህን ለመውደድ ድፈር። ውብ አሁን❤️ @natani273
Show all...
ወደፊት!!! “ከጀርባችሁ ሆነው እማይጠቅማችሁን  ወሬ ስለሚያወሩ ሰዎች አትጨነቁ፡፡ ከጀርባችሁ የሆኑት እኮ በምክንያት ነው” ስለ እነሱ ማሰብና ለወሬያቸው ምላሽ መስጠት ማለት እነሱ ወዳሉበት ወደ ኋላ መመለስ ማለት ነው፡፡ ወደ ፊት! መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!! @natani273
Show all...
🔴👁በ'ነሱ ቤት👁🔴 👉🌸ክፍል ስድስት🌸👉 🌸🍀🌸🍀🌸🍀🌸 ሰመረ የጓደኞቹ በአብላካት ዙሪያ ሽርጉድ ማለት አልተመቸውም ።እነሱን የራሱን ያክል ያውቃቸዋል ምን አስበው እንደሚዞሯት ያውቃል ።ያንን ሲያስብ ደሞ ስቅጥጥ አለው ።ምክንያቱም አብላካት ለሱ ያልደረሰች ልጃገረድ ፡ገና ምኑንም የማታውቅ ታዳጊ ናት እና የነሱ አቀራረብ ምቾት አልሰጠውም ።    እነሱ ደሞ የሰመረ እሳን ለመርዳት እያደረገ ያለው ጥረት ትንሽ ከተለመደው ማንነቱ ውጪ ሆኖባቸው እየቀለዱበትም ጭምር ነው ።    አብላካት ሰመረ በኤትኤም አውጥቶ ስለሰጣት የብር ኖቶች እራሱ ለማጣራት ጊዜ እስከማታገኝ ድረስ ነው የጨነቃት ።የነ ጌታነህ አነጋገር አሳሳቅ አስተያየት ብልግና እንዳለበት ልቧ ነግሯታል እናም በፍጥነት ከነሱ መራቅ ፈልጋለች  ስለዚ ሰመረ የሰጣትን ብር ምንም አይነት አስተያየት ሳትሰጥ ያረጀች ቦርሳዋ ውስጥ በፍጥነት ከተተች እና ሰመረ ቶሎ እንዲሸኛት አይን አይኑን አየችው። ሰመረ ስሜቷን የተረዳ ይመስል ከእነሱ ሊያርቃት እጇን ይዞ ወደፊት ተራመደ ። ጌታነህ ተከተላቸው "ቆይ ቆይ ከዚች ልጅ ጋርማ በደንብ ነው መተዋወቅ ያለብን ።ስምሽ ማነው ግን "አላት "አ አብ ላካት መሳይ "አለችው ድምጿ እየተርገበገበ "ውይይ እንዴት ደስ የሚል ስም ነው ከነ አባትሽ ጭምር !"አለ በፌዝ እያጋነነ "በቃ ተመለሱ እኔ ሸኝቻት እመጣለው "አለ ሰመረ የጓደኛው ቀልድ ለመጀመሪያ ጊዜ እየደበረው "ኧረ አንተ ደሞ የኔንም ስም ልንገራት ።እኔ ጌታነህ እባላለው  ያኛው ጓደኛዬ ደሞ እንየው ይባላል"አላት ፈንጠር ብሎ ወደ ቆመው እንየው እያሳያት ።እንየው አብላካት ስታየው እጁን አውለበለበላት ። አብላካት አይኗን ወደ ሰመረ መለሰች ።እናም "እእ እኔ ብቻዬን እሄዳለው ላደረክልኝ ነገር በሙሉ አመሰግናለው ።"አለችው ።ሰመረ ጥቂትሲያያት ቆይቶ "በቃ እሺ ሂጂ እዛች ጋር ላዳዎች ታገኛለሽ ።በቀጥታ ግን ወደ ቤት ሂጂ  በፍፁም እዛ ሰው ጋር እንዳትሄጂ እሺ "አላት ።አብ ላካት አንገቷን ነቀነቀች እና እንደማትሄድ አረጋገጠችለት ።ሰመረ ጥሩ ብሎ እንድትሄድ ፈቀደላት ።አብ ላካት መንገድ ስትጀምር ።ጌታነህ በሰመረ ቀለደበትና እሱን አልፎ በመሄድ አብላካትን አስቆማት ።ሰመረ ጨነቀው ለመጀመሪያ ጊዜ በጓደኛው ተማረረበት ።ምንድነው አንዲት ትንሽ ሴት ልጅ ላይ የዚን ያክል ፍላጎት ማሳየት ። "ቆይ ቆይ አቢዬ በናትሽ ስልክሽን ስጪኝ ለሌላ ነገር አደለም ብቻ በሰላም መግባትሽን ለማወቅ ስለሚያስፈልገን ነው እሺ የኔ ውድ "አላት አብላካት አመነታች ።ጌታነህ ደጋግሞ ሰላሟን ለማረጋገጥ ስለፈለገ ብቻ መሆኑን ሲነግራት እሺ ብላ ሰጠችው ።ጌታነ ስልኳን አባብሎ ሲቀበላት ።ሰመረ ንዴቱ ጨመረ ነገር ግን እሷው ስለሰጠችው ምንም ነገር ከመናገር ተቆጠበ ። አብላካት ከጌታነህ ጋር ስልክ ከተለዋወጠች በዋላ ፈጠን ፈጠን እያለች ዞራ ሳትመለከት ሄደች ። ጌታነ በድል አድራጊነት ።ወደነሰመረ እየሳቀ ሲመጣ ።ሰመረ አንገቱን ነቀነቀበት ።ጌታነ ይበልጥ ስቆበት "ምንድነው ዛሬ ሰሙ ሃሃሃሃሃሃ  እቺን እንቡጥ በጣም አባበልሻት ሃሃሃሃሃሃ! ግን በስተመጨረሻ አላወቅሽበትም ያሁሉ ብር ሰጥተህ በነፃ ልትሸኛት እናስ እኔ ጌትሽ ከአፍሽ ላይ ሞጨለፍኩሽ ።'እሟ ቀሊጥ !' አለ ጋሼ ሃሃሃሃሃ ተበላ!"አለው ስልኩን ከፍ አድርጎ እያሳየው "ምን አስበህ ነው ? አታረገውም ገና ትንሽ ልጅ ናት እኮ በዛላይ ችግር ውስጥ ናት  አንተ ደሞ ታበዛዋለህ !ሴት አጥተህ ነው ?ያው ቅድም ስልክ ስትሰጥ አልነበረ እንዴ ለዛች ለኮስሞቲክሷ ልጅ !ምንድነው እንዲ የሚያደርግህ ?"አለው ከምሩ ተቆጥቶ "ሃሃሃሃ ምን ፈልጌ እንደሆነ ልንገርህ ምንም ያልተነካካች እንቡጥ " "ነው እንደዛ ከሆነ መቼም ቢሆን አትነካትም እሺ"አለው  ሰመረ በእልህ። እንየው የነገሩ መቀየር አስጨነቀው ከዚ በፊት በጓደኞቹ መሃል እንዲ አይነት ፀብ የሚመስል ነገር አይቶ አያውቅም ። "ይቅርታ ይህንን ነገር መተው አትችሉም ።ይልቅ አንድ ቦታ ሄደን ዘና እንበል ቅዳሜን በዚ መልኩ አታበላሿት "አለ "አይ አይ ይናገር ልጅቷን አትነካትም ነው አይደል ያልከው በቃ ታየኛለህ በቅርቡ ።ታውቀኛለ የፈለኩትን ለማግኘት ምን ያክል እርሸት እንደምሄድ "አለው እያመረረ ።ሰመረ የጌታነህ የለየለት ጭካኔ ደበረው ።ከሱጋር የእልህ ወሬ ከማውራት ቢቀርብኝ ይሻላል ። ልጅቷን ይበልጥ ችግር ውስጥ መክተት ነው ብሎ እራሱን አረጋጋ እና የጌታነህን ደስ የማይል ወሬ ችላ ብሎ ከእንየው ጋር ስለሚያመሹበት ቦታ ማውራት ጀመረ ..... ይቀጥላል......     ❣❣❣❣❣❣❣❣❣ ፍቅር፡ሰላምና ጤና ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምን ጊዜም ከዘመንህ አይለይ!!!!!!! ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ☑️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩት፡ ☑️#Share 👇👇👇👇👇👇👇👇         @natani273
Show all...
ትዕግስት ማለት ለጊዜያዊ ደስታ ብለህ ነገህን የሚጎዳ ውሳኔ አለመወሰን ነው። 🧤ስትታገስ ሀያሉ ጊዜ ካንተ ጋር ነው! ሁሉን አሳልፎ ጥሩውን ቀን ያመጣልሀል። 🧤ስትታገስ የፈጀውን ይፈጃል እንጂ ከናቁህና ዝቅ አድርገው ካዩህ ሰዎች በላይ ከፍ ትላለህ። 🧤ስትታገስ ግዙፍ መስሎ የታየህ ችግር ሁሉ ምን ያህል ቁጫጭ እንደነበረ ይታይሀል። 🧤የፈጣሪ ታናሽ ወንድም የሚባለውን ሀያሉን 'ጊዜ' ከጎንህ ማሰለፍ ከፈለክ ታገስ ወዳጄ። @natan273
Show all...
🔴👁በ'ነሱ ቤት👁🔴 👉👉ክፍል አምስት👉👉 👁🔴👁🔴👁🔴👁 አብላካት ገና በጠዋቱ ከሕይወት አስከፊ ጎን ጋር ተላትማ ፡ባልገባት የኑሮ ሁኔታ ተጠላልፋ ግራ እንደተጋባች እንድትጓዝ ማን እንደፈረደባ አሰበች ፡ማነው እንዲ እንዲሆን የሚያደርገው  ፈጣሪዬ እኔና እናቴ ምን ብናረግ ነው በችግር የምንጠበሰው ። ለምን ?ለምን ? አሁንስ ማልቀስ እራሱ ሰለቸኝ ኡፍፍፍ ...... "ሚጣ ሚጣ...."ሰመረ እሮጦ ደረሰባት "አብላካት ነው ስሜ !"አለች አብላካት።  ሰመረን ዞራ እንኳ ሳታየው "እሺ አብላካት "አላት ከፊቷ ቀደም ብሎ በመቆም "ምን?"አለችው በግዴለሽነት "ይሄውልሽ ቅድም ከሆነ ሰው ጋር በስልክ ስታወሪ ሰምቼሻለው እና ስለሱ ማወቅ ፈልጌ ነው "አላት "ለምን ማወቅ ፈለክ እሱ የኔ ጉዳይ ነው?!"አለች ለመሄድ እየሞከረች። ሰመረ ከፊለፊቷ ቆሞ አገዳት "እባክህ የታመመች እናት አለችኝ ቢያንስ ገብቼ ልያት "አለች ፍቃድ የምትጠይቅ መስላ "እሺ ትሄጃለሽ ችግር የለም እዛችጋር መኪና አቁሜያለው እኔ ይዤሽ እሄዳለው በርሽ ድረስ ከፈለግሽ ።ግን ያ በስልክ ያናገርሽው ሰው ማነው በማታ ለምን ቀጠረሽ"አላት "ማነወ በማታ የቀጠረኝ እንደሱ ማን አለ"አለች ደንገጥ ብላ "ሰምቼሻለው በማታ እናቴ አትፈቅድልኝም ስትዪ "አላት እጇን ይዞ እንድታወራ እየገፋፋት "እባክህ በቃ ተው ያበቃለት ጉዳይ ነው ፡ሁሉም ነገር ተበላሽቷል "አለች "ምንድነው የሚበላሸው ለምን አታወሪም "አላት ቆጣ ብሎ ፡ "እሺ ይህውልህ እሱን የማውቀው በፌስቡክ ነው አግኝቼው አላውቅም ስራ ሊያስገባኝ ነበረ ፡ዛሬ የተቀጣጠርነው ታውቃለህ ለኔ ጥሩ ስራ ነበረ እናቴን ላግዛት የምችልበት ብቸኛው መንገድ ፡ስራው ቀላል ነበረ ቡቲክ ቤት ደሞ እህቱ ነበረች የምትቀጥረኝ ።አስበህዋል ግን በዚ ጫማ የተነሳ ስራውን አጣውት ።እዛ ጉሊት ላይ በፀሐይ የምትንቃቃዋ እናቴ ዕድለኛ አይደለችም ።ለኔስትል አመድ እንደወረሳት እንድትኖር የሆነ አይል ፈርዶባታል ምስኪን እናቴ በዛላይ ታማለች አቤት ስቃይዋ ።እሷ እየተቃጠለች ለኔ ብርሃን ለመሆን ትጥራለች ኡፍፍፍፍ "ብላ ተነፈሰች ሰመረ ግራ ገባው እሱ ከአብላካት የሚሰማው የኑሮ ዓለም የተለየ ነው አይቶም ሰምቶም አያውቅም መቼስ ስለዚ ልብ የሚልበት ጊዜ ኖሮት ያውቃል በጭንቀት ሲመለከታት ቆይቶ "እሺ ያሰው በፌስቡክ የምታውቂው ሰው ።እንዴት ትክክለኛ ሰው ነው ብለሽ አሰብሽ ።አንቺ እንዳልሺው ጥሩ ሰው ባይሆንስ ።አንቺን ለማማለል ሲል ቢሆንስ አንቺ ስለ ወንዶች የምታውቂው ነገር የለም ስራ ላስቀጥርሽ ብለው ልጁ ነትሽን የሚጠቀሙ ስንት አብታም ሰወች አሉ መሰለሽ "አላት እንዴት ማውራት እንዳለበት ግራ እየገባው "አይ እሱ አይደለም ጥፋተኛ እኔ ነኝ በጫማው ምክንያት ነው" "አይ አይደለም መጀመሪያም ያሰው ስራ ሊያስቀጥርሽ ፈልጎ አይደለም ስለዚህ በጭራሽ ደግመሽ እንዳታናግሪው ። መልካም ሰው ቢሆን ማታ ካልመጣሽ አይልሽም እሺ"አላት እንዴት እንደሚያስረዳት እየጨነቀው።አብላካት ሰመረን ለመጀመሪያ ጊዜ አተኩራ ተመለከተችው  እናም ገረማት እንዴት ከቅድም ጀምሮ አሳቢ ሆኖ ሊረዳኝ ፈለገ በጣም የሚያምርና ሀብታም ወጣት ወይም የሀብታም ልጅ እንደሆነ ያስታውቃል ሁሉ ነገሩ ፅድት ያለ ነው አጥብቆ የያዛት እጁ እራሱ ጠንካራ ቢሆኑም ለስላሳ ናቸው ። ቀናችበት  ምንም አይነት አሳብ ያለበት አይመስልም ። "ሲጀመር እሱም አያናግረኝም ለማንኛውም ግን አመሰግናለው ።አሁን ወደ ቤት መመለስ አለብኝ "አለችው ሰመረ እጇን እንደያዘ "ቆይ እዛ ጋር ባንክ ይታየኛል በኤትዬም ገንዘብ አውጥቼ እሰጥሻለው ።የቅድሙ ጥሩ ጫማ ለመግዛት አይበቃም "አላት "አይ አይ ለኔ ብዙ ነው አንተ አትቸገረ አንድ ጫማ አይደለም አራት ጫማ የሚገዛ ገንዘብ ነው የሰጠኽኝ "አለች "ግድ የለሽም ሚጣ በዛላይ የታመመች እናት አለሽ"አላት "ስሜ አብላካት ነው ሚጣ መባል አልፈልግም ነገርግን ለመልካም አሳብህ ምስጋና አለኝ ።ከዚ በላይ ግን ብቀበልህ አይናውጣነት ነው "አለች አብላካት ። ሰመረ ክስተር ብሎ "አታስቸግሪኝ እባክሽ እኔ ንዴት አልችልም ካልኩ አልኩ ነው የወሰንኩበትን ነገር ከማድረግ የሚከለክለኝ ሰው ያበሳጨኛል እና ብሩን አውጥቼ እሰጥሻለው ይዘሽ ትሄጃለሽ ።እና ደሞ ከዛሰው ጋር ዳግም ላታወሪ ቃል ትገቢልኛለሽ አለቀ "አላት ።አብላካት ፊቱን ስታየው ከምሩን እንደሆነ ተሰማት ።እናም እጇን እንደያዛት ወደ ኤትኤም ማሽኑ ሲያቀና ።በዝምታ ተከተለችው ። ሁኔታውን ከርቀት ሲከታተሉ የነበሩት ጓደኞቹ ጉዱን እንየው ብለው ወደነሱ መጡ ። አብላካት በዙሪያዋ በሚገባ የለበሱና የሚያማምሩ ወጣቶች ድንገት መከበቧ ሰላም አሳጣት በተለይ የሁለቱ ወጣቶች አስተያየት አስጨነቃት ። ፍርሃት ወረራት አይኖቿን ወደ ሰመረ ተከለች ።ከነዚ የሚያስጨንቅ አስተያየት ካላቸው ጓደኞችህ አድነኝ የምትል ይመስላል ............. ይቀጥላል......     ❣❣❣❣❣❣❣❣❣ ፍቅር፡ሰላምና ጤና ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምን ጊዜም ከዘመንህ አይለይ!!!!!!! ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ☑️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩት፡ ☑️#Share 👇👇👇👇👇👇👇👇         @natani273
Show all...
⚫️🍄በ'ነሱ ቤት🍄⚫️ 🍄👁ክፍል አራት👁🍄 🍓🍄🍓🍄🍓🍄🍓 ሰመረ እንደዚ አይነት መጨናነቅ የለመደ ልጅ አይደለም እና ሁኔታዋን አይቶ'ምነው እቺን ልጅ ላናድድ ብዬ ከተቀመጥኩበት ባልተነሳው በገዛ እጄ አባባይ ልሁን እኔ ሲጀመር ምን አገባኝ !ማድረግ ያለብኝን አድርጌላታለው  በቃ የራሷ ጉዳይ 'ብሎ ትቷት ወደ ጓደኞቹ ተመለሰ ። ጓደኞቹ ገና ከመምጣቱ በተረብ አላስቀምጥ አሉት። "እኔ የምልህ ከዚች አመዳም ጋር የዚን ያክል ክርክሩ ምንድነው ?ደሞ አይደብርህም እንዴ ያንን አስቀያሚ ጫማዋን ከእጇ እየነጠክ ትወረውራለህ ሃሃሃ በል በል አሁን ሂድና እጅህን ታጠብ ሆሆሆ ሳም ሙት! አንዳንዴ ምንም አትገባኝም በላይህ ላይ ጀርም ትጋብዛለህ ሃሃሃሃ"ብሎ ጌታነህ ሳቀበት ።እንየው ቀበል አድርጎ "እኔ እኮ የገረመኝ ገንዘብ አውጥተህ መስጠትህ ምን ፈልገህ ነው ግን ኪኪኪ ለነገሩ አጥበህ አስቆንጅተህ በትበላው የሚያስከፋ አይደለም በደንብ ከተያዘች ቆንጆ ነገር ናት ግን ጓደኞቼ እየወረዳቹ ነው ዛሬ 😀ወይ ከዚ በረንዳ ወደውስጥ እንግባ 😀"አለ ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ። ሰመረ እነሱ የተናገሩት ነገር ምኑም ደስአላለውም ይብስ ተከፋ ሁለቱም ባሰቡት መንገድ እንዳላሰበ ደጋግሞ አስረዳ ። ከነሱ ጋር ክርክሩ አላዋጣ ሲለው አይኖቹን መልሶ ወደ መንገዱ ወርወር አደረገ አብላካት እየተወለጋገደች ሁለቱን ጫማወቿን አንጠልጥላ በተስፋመቁረጥ ስትራመድ አያት  ለምን እንደው ያላወቀው ስሜት ወረረው ልቡ አዘነ ይህቺ ልጅ ገና ታዳጊ ናት ለምንድነው የዚን ያክል መከፋት ያለባት ምን አይነት የተቸገረ ቤተሰብ ቢያሳድጋት ነው እንዲ የሆነችው አለ ለራሱ ፣ሰው በዚመጠን ደሃ ይሆናል ጫማ እስከመዋዋስ ለዛውም ጀየሚያስጠላ ጫማ ይገርማል ። በመንገዱላይ ብዙ ሰው አይታይም  አብላካት ያመንገድ አላልቅ ያላት ይመስላል በራሷ በጣም ተሸማቃለች ገና ከሳምንት ጀምሮ ስትዘጋጅበት የነበረ ቀጠሮ ነው የተበላሸባት ለሷ የመጀመሪያ ቀጠሮዋ ነው ለዛውም ከችግር የምትወጣበት ቀጠሮ ነገር ግን በገዛ እጇ አበላሸችው ምነው ታምራትን ከማስከፋው የራሴን ጫማ አድርጌ በመጣው ይሄኔ እኮ አግኝቼው የምሰራበትን ቦታ አሳይቶኝ ሁሉም ነገር ተስተካክሎ እመለስ ነበር የተረገመ ጫማ ።ደሞስ ምን አጣደፈኝ ቀስ ብዬ አልሻገርም ነበር ።በራሴው ስህተት ነው ስራውን ያጣውት ።ዕድ ለቢስ ነኝ ሲጀመር  ብላ ስንጥቅ የበዛባትን የሞባይል ስልኳን አየች በተስፋ ታምራት የተባለው የፌስቡክ ጓደኛዋ ይደውል ይሆናል በሚል ምኞት ።ይህችን የሞባይል ስልክ ከሰው ላይ የገዛችላት እናቷ ነች  ከዘጠኝ ወደ አስር በጥሩ ውጤት ስላለፈችላት ደስታዋንና በሷ መኩራቷን ለማሳየት ።እና አብላካት የዛንቀን ከጓደኞቿ እኩል ሞባይል በመያዟ ደስታዋ ወደር አልነበረውም። ከዛን ጊዜጀምሮ ፌስቡክ ከፍታ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ታወራለች ከአንገት በላይ ተነስታ የምትለቃቸው ፎቶዎቿ የሚስቡ በመሆናቸው ብዙ ወንዶች ኢንቦክስ እየገቡ ያወሯታል የፍቅርጥያቄ ያቀርቡላታል አብላካት ለሁሉም በየዋህነት ገና ለዛ እንዳልደረሰች ትፅፍላቸዋለች ።ብዙዎቹ ያለምጡባታል ።ከነዛ ውስጥ ግን የታምራት አቀራረብ ይመቻታል ልጅነቷን ስትነግረው መገመቱን እና እሱ እህት እንዳለው ልክ በሷ ዕድሜ መሆኗን እየነገረ አግባባት ከዛ በዋላ ስለቤተሰብ ስለትምህርት እየጠየቀ ችግሯን ሁሉ ሳትደብቅእንድትነግረው አደረገ  ከዛም ነገረችው ።እናቷ እሷን በልጅነቷ ሰውቤት ሰራተኛ ሆና  ከአሰሪዋ ልጅ እንዳረገዘቻትና አሰሪዎቿ ይሄንን ሲያውቁ እንዳባረሯት ከዛም እሷን ጎዳናላይ እንደወለደቻት ከዛ በዋላም እናቷ እጅ ሳትሰጥ ጉሊት እየሰራች ፍራፍሬ አትክልት እየሸጠች እንዳሳደገቻት አወራችው ።በጣም የሚያሳዝን ታሪክ እንዳላት እና እሷን ለመርዳት ሲል የአክስቱን ልጅ እንደሚያናግራት እና እሷ ፑቲክ ውስጥ እንደሚያስቀጥራት ነገራት ።ይሄንን ያላት ቀን በደስታ ነበር የሰከረችው ። በተለይ እናቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲ እግሬን እየወጋኝ ነው እያለች ከምትሰራበት ጉሊት መመለሷ እየተለመደ መጥቷል እመም ይሰማታል ይሄን ስለምታውቅ ።እሱ ስለስራ ሲያወራት ቀጥታ የታያት እናቷን ማገዟ ነው ።አብላካት ስላረፈድሽ የማልቀርበት ጉዳይ ስላለኝ ሄጃለው ባይሆን ማታ ተገናኝተን ተጫውተሽ ትመለሻለ ሲላት አይመቸኝም ስትለው ድንገት ቅይር ብሎ ካልሆነ ይቅርብሻ ነበር ያላት በጣም ተናዳለች በፌስቡክ እንዳወራት አልሆነላትም  ።ሰው በአንድጊዜ ጥፋት እንዲ ይለወጣል ያሳዝናል ።'ወይኔ እናቴ መቼ ልደርስልሽ ነው 'እያለች በአዘን ተቆራምታ በባዶእግሯ ትጓዛለች ። ሰመረ የሰጣትን ብር ጨምቃ ይዛታለች ። *ሰመረ ተነስቶ ቆመ ጓደኞቹ እኩል ወዴት ነው አሉት መጣው ብሎ በረንዳውን በፍጥነት መውረድ ጀመረ ጓደኞቹ ግራ በመጋባት ተያዩ ሰመረወደ አብላካት አቅጣጫ ፈጠነ,,,,,,, ይቀጥላል......     ❣❣❣❣❣❣❣❣❣ ፍቅር፡ሰላምና ጤና ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምን ጊዜም ከዘመንህ አይለይ!!!!!!! ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ☑️ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩት፡ ☑️#Share 👇👇👇👇👇👇👇👇         @natani273
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.