803
Subscribers
-224 hours
+37 days
+2530 days
Posts Archive
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 ዓ.ም ሊንክ ኦል አ.ማ መቀመጫውን በኢንግሊዝ ሃገር ካደረገው ድርጅት ጋር ዉጤታማ የስራ ትውውቅ እና ውይይት አድርጓል።
ሁለቱ ድርጅቶች በቀጣይነት በአውትሶርሲንግ እና የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ አብረው እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ድርጅታችን ሊንክ ኦል ቴክኖሎጂ አ.ማ በ 4ተኛዉ አገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ላደረግነዉ ተሳትፎ እና አስተዋፆ የምስጋና እና የእዉቅና ሰርተፊኬት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ እጅ ተቀብለናል ።
ሊንክ ኦል ቴክኖሎጂ አ.ማ መቀመጫውን አትላንታ፣ጂዮርጂያ ከሚገኘው ድርጅት ጋር በጋራ የሚያሰራቸውን የአውትሶርሲንግ (Outsourcing) ስራ ስምምነት ተፈራረሙ።
ሊንክ ኦል ቴክኖሎጂ አ.ማ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና (Capacity Building Training) ሰጠ።
የስልጠና ፕሮግራሙ የኢትዮጲያ የፊደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ መምሪያ አባላት የ ኤ ፒ አይ ኢንተግሬሽን (API Integration)፣ ማይክሮሰርቪስ (Microservices)፣ ጄ ኪውሪ ካላንደር ሎካላይዜሽን (jQuery Calendar Localization) እንዲሁም የዴት ፒከር ሎካላይዜሽን (Datepicker Localization) ኮርሶችን ሰጥቷል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ከነገ ጥቅምት 12 ጀምሮ በግዮን ሆቴል ለተከታታይ ለ4 ቀናት በሚያዘጋጀው 4ኛው የሳይበር ደህንነት ወር ላይ በልዩ ተጋባዥ ኤግዚብተርነት ሆነን በመጋበዛችን እርስዎም በስፍራው (በግዮን ሆቴል) መጥተው እንዲጎበኙን ጥሪ እናቀርባለን
የአኒሜሽን እና Visual Effects ስልጠና በመውሰድ ተፈላጊነትዎን አንድ ደረጃ ከፍ ያድርጉ ፤ ገቢዎትንም ያሳድጉ።
ታዲያ ባለንበት ዘመን እጅግ ተፈላጊ የሆነውን ይህን ስልጠና ከእኛ ይውሰዱ።
ምዝገባ ጀምረናል ፤ ፈጥነው ይመዝገቡ።
ለበለጠ መረጃ፡
ስልክ ቁጥር፡ +251 932105657 /+251 116157401
አድራሻ፡ ቦሌ ፍሬንድ ሺፕ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406
የ PDR ሆቴል ዲጂታል ሪከርድ ሲስተም አተገባበር እና ሂደት ላይ ሊንክ ኦል አ.ማ ከ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር የመጀመሪያ ዙር የፕሮጀክት አፈፃፀም ግምገማ አደረገ።
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 ዓ.ም ሊንክ ኦል አ.ማ ከቻይናዉ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት ሁዋዌ (HUAWEI) ጋር ዉጤታማ የቅድመ ትብብር የስራ ትውውቅ እና ውይይት አድርጓል።
በቅድመ ስራ ውይይቱም ከሁዋዌ ተወካይ እና የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሃላፊ ጂያን ሉንግ ጋር በቀጣይ የሁለትዮሽ ስራዎችን ክላውድ ኮምፒዩቲንግ እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ ለመስራት እንዲሁም ቀጣይ ሰፊ የትግበራ እቅዶችን መሬት ላይ ለማውረድ የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።
🌻🌻🌻 እንኳን ለ 2016 ዓ.ም ዘመን መለወጫ አደረሳችሁ። 🌻🌻🌻
አዲሱ አመት የሰላም ፣ የጤና እና የስኬት አመት እንዲሆንልዎ እንመኛለን።
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2015 ዓ.ም ሊንክ ኦል አ.ማ ከቻይናዉ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት ዋይዚም (Wayzim Technology Co. Ltd.) ጋር ዉጤታማ የቅድመ ትብብር የስራ ትውውቅ እና ውይይት አድርጓል።
በቅድመ ስራ ውይይቱም ከዋይዚም የአፍሪካ ተወካይ ጆን ሊዩ ጋር በቀጣይ የሁለትዮሽ ስራዎችን ለመስራት እና ቀጣይ ሰፊ የትግበራ እቅዶችን በጋራ ለመወያየት እና መሬት ላይ ለማውረድ ያሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።
ኢትዮ-ትዳር (M-net) አፕሊኬሽንን በመጠቀም ኢትዮጵያዊ ባህል እና ወግን በጠበቀ መልኩ እውነተኛ የትዳር አጋርዎን እንደሚያገኙ ያውቃሉ?
አፑን ለማውረድ ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.mnet.marriage_app
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2015 ዓ.ም
ሊንክ ኦል ቴክኖሎጂ አ.ማ ከስፓርክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ጋር በጋራ በመሆን ኢትዮ-ትዳር (M-net) የተሰኘ አፕሊኬሽን በይፋ አስመርቋል።
ኢትዮ-ትዳር (M-net) በኢትዮጵያዊ ባህል እና ስርዓት መሠረት እውነተኛ ትዳር ፈላጊዎችን አረጋግጠዉ የሚያገኙበት በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የትዳር አፕሊኬሽን ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ በ አለም ላይ በሚገኙ ከ 20 በላይ ሃገራት ላይ የሚሰራ እና በርካታ አለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ የክፍያ ስርዓቶችን የሚቀበል ሲሆን አፕሊኬሽኑን ለማበልፀግ በአጠቃላይ 2 አመታትን ፈጅቷል።
አፕሊኬሽኑ እውነተኛ ትዳር ፈላጊዎችን ከማገናኘት ባሻገር ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ችግሮችን እንዲቀርፍ ታስቦ የተሰራ በአይነቱ ልዩ የሆነ የመጀመሪያው አፕሊኬሽን ነው።
አፑን ከፕሌይ ስቶር ለማውረድ ሊንኩን ይጫኑ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.mnet.marriage_app
ኢትዮ ትዳር አፕሊኬሽን በኢትዮጵያዊ ባህል እና ስርዓት መሠረት እውነተኛ ትዳር ፈላጊዎችን አረጋግጠዉ የሚያገኙበት በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ አፕሊኬሽን።
አፑን ከፕሌይ ስቶር ለማዉረድ ሊንኩን ይጫኑ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.mnet.marriage_app
Link All Technology S.C have successfully graduated the first round of Graphic Design and Social Media Management Trainers in collaboration with MaxBridge Education and Development S.C.
2nd round registration is ON. You can register and get your spot by clicking here.
https://forms.gle/VLoqTyZoCFFg9wgG6
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 ዓ.ም
ሊንክ ኦል ቴክኖሎጂ አ.ማ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በሲስተም ዴቨሎፕመንት ፣ ኮንሰልተንሲ ፣ ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ እና ስልጠና ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የጋራ ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል፡፡
በተጨማሪም የስምምነቱ አንድ አካል የሆነውን "PDR (Police Digital Record information management system)" የተሰኘ የተለያዩ የፖሊስ የስራ ሂደቶችን የዲጂታል መረጃ አያያዝ ስርአት የሚያዘምን ቴክኖሎጂን የስራ ማስጀመሪያ የጋራ ስምምነት ፈፅመዋል።
