cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማህበረ ማርያም ዘቅዱስ ገብርኤል ወተክለ ሀይማኖት

ያላችሁን አስተያየት እና ጥያቄ በ @maheberee በዚኛው ግሩፓችን ላይ ማሳወቅ ትችላላቹ እናመሰግናለን

Show more
Advertising posts
224
Subscribers
-124 hours
-47 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

+ መርጦ መወለድ + ከእገሌ ልወለድ ብሎ መርጦ የተወለደ የለም:: ምረጡ ብንባል ምን ዓይነት ወላጅ እንመርጣለን? ቀድመን የመገምገም ዕድል ቢኖረን ምን ዓይነት ወላጆች እንመርጣለን። መቼም በወላጆቼ ደስተኛ ነኝ የሚል ሰው "እኔ ደግሜም ብወለድ ከአባዬ ከእማዬ ነው መወለድ የምፈልገው" ማለቱ አይቀርም። ግን ደግሞ ዕድሉን ቢያገኝ መቼም ትንሽም ቢሆን የሚያስተካክለው ነገር አይጠፋም። መርጦ መወለድ አይቻልም እንጂ ቢቻል የምንመርጠው ልዩ ምርጫ ይሆናል። መርጦ የተወለደ ክርስቶስ ብቻ ነው። በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ተመልክቶ መዓዛዋን መርጦ ፣ በቅድስናዋ ውበት ተማርኮ ከእርስዋ ሊወለድ የመረጣት የተመረጠች እናት ድንግል ማርያም ብቻ ናት። የፈጣሪ ምርጫ እንደ ሰው አይደለም። ሰው ፊትን ያያል እርሱ ግን እስከ ልብ ድረስ ዘልቆ ይመለከታል። እንዴት ብትነጻ ፣ እንዴት ብትቀደስ ነው? እስከ ውስጥዋ ዘልቆ አይቶ ከእርስዋ ሊወለድ የመረጣት? ንጉሥ ውበትዋን የወደደላት ፣ ለእናትነት የመረጣት ቅድስት እንዴት የከበረች ናት? አዎ መርጦ የተወለደ የለም ፣ ክርስቶስ ግን መርጦ ብቻ ሳይሆን ፈጥሮ የተወለደ ነው። መቅደሱን አንጾ የገባባት እርሱ ነው። መርጦ ለተወለደብሽ ለአንቺ በጸጒራችን ቁጥር ምስጋና እናቀርባለን። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 21 2012 ዓ ም የግሸንዋን ንግሥት በረከት በመናፈቅ ሜልበርን አውስትራሊያ
Show all...
+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? + ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት:: "ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39 ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ:: "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ:: ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20) እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም? ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3 ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር:: የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23) ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን? ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ:: "ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም:: ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13) ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ:: ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ:: አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር:: የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 21 2016 ዓ.ም. ለእመብዙኃን ዝክር የተጻፈ "ንዒ ማርያም ለዕውር ብርሃኑ ወንዒ ድንግል ለጽሙዕ አንቅዕተ ወይኑ ኦ ኦ ተኃድግኒኑ ኦ ኦ ትመንንኒኑ ኀዘነ ልብየ እነግር ለመኑ" ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም
Show all...
+ የመስቀሉ ደም + መስቀል ደም አለው ወይ? ከእንጨት የተሠራ ነገር ቢወጉት ይፋፋቅ ይሆናል እንጂ አይደማም:: ስለ ክርስቶስ መስቀል ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ግን "በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ" አለ:: (ቆላ. 1:20) "ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ" የመስቀሉ ደም የሚለው ቃል መስቀሉ ደምቶአል ለማለት አይደለም:: ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ጠዋት ሦስት ሰዓት ሊቶስጥራ ላይ ጌታን ሲያሸክሙት የመስቀሉ ቀለም የእንጨት ብቻ ነበረ:: ክርስቶስ መስቀሉን ተሸክሞ ለሦስት ሰዓታት ከወጣና ለሦስት ሰዓት ተሰቅሎ ነፍሱን ከሠጠ በኋላ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀሉ ሲያወርዱት የመስቀሉ መልክ የእንጨት አልነበረም:: በጥሩ ባለሙያ ቀይ ቀለም የተቀባ እስኪመስል ድረስ መስቀሉ በክርስቶስ ደም ታጥቦ ነበር:: እሾህ ከደፋው ራሱ ፣ ከተቸነከሩት እጆቹ ፣ ከተገረፈው ጀርባው ፣ ሚስማር ከያዛቸው እግሮቹ እንደ ውኃ የፈሰሰው ደም በመስቀሉ ላይ ፈስሶ ነበር:: መፍሰስን ለመግለፅ በግእዝ ሁለት ቃላት አሉ "ክዒው" እና "ውኂዝ" የሚሉ:: ወደ አማርኛ ሲመለሱ ሁለቱም መፍሰስ ቢሆኑም ግን ልዩነት አላቸው:: አንድ ሰው በብርጭቆ ውኃ ቢያፈስስ ውኃው ፈሰሰ ይባላል:: የወንዝ ውኃ ሲፈስስም ፈሰሰ ይባላል:: ግእዙ ግን ከአንድ ብርጭቆ ለሚፈስሰው ውኃ "ተክዕወ" ሲል እንደ ወንዝ ላለው ብዙ ፈሳሽ ደግሞ "ውኅዘ" ብሎ ይለየዋል:: ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ብለው አንገታቸው ተሰይፎ እንደሞቱ ሲናገር "ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ መንግሥተ ሰማያት" "ስለ መንግሥተ ሰማያት ደማቸውን አፈሰሱ" ይላል:: ይኸው አባት ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ክርስቶስ ደም መፍሰስ ሲናገር ግን "በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሖሙ ለመሃይምናን" "በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ያመኑትን አነጻቸው" ብሎአል:: የጌታችንን ደም መፍሰስ ለወንዝ ፈሳሽ በሚነገርበት ቃል ውኂዝ የተባለው ከጌታችን የፈሰሰው ደም ከመላው ሰውነቱ ስለነበረ ነው:: መስቀሉን ለዓመታት መፈለግ ፣ ማክበር ግድ የሆነውም መስቀሉ ዓለም በተገዛበት በከበረ ደም ስለተቀደሰ ነው:: (እስመ ተቀደሰ በደመ ክርስቶስ መድኅን) ወዳጄ ሆይ በደም የታጠበ መስቀል ስታይ ምን ይሰማሃል? በደም የተቀደሰው የመስቀሉ ክብር አይታይህም? አዎ መስቀል ክቡር ነው:: የመስቀሉ ደም ሌላ የሚያሳየው ክብርም አለ:: እርሱም የእኔና የአንተን ክብር ነው:: ምክንያቱም ያ ሁሉ ደም የፈሰሰው ለእኔና ለአንተ ነው:: በሰዎች የመጠሪያ ስምህ ማን ነው? ማን ብለው ሲጠሩህ አቤት ትላለህ? ቅዱስ ጳውሎስ ግን ለእኔም ለአንተም ስም አውጥቶልናል:: ጳውሎስ አንተን ለሰዎች ሲያስተውቅህ እንዲህ ብሎ ነው :- "ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው" 1ቆሮ.8:11 ወዳጄ የአንተ ክብር እዚህ ድረስ ነው:: አንተ ክርስቶስ የሞተልህ ወንድም ነህ:: አንቺ ክርስቶስ የሞተልሽ እኅት ነሽ:: ቅዱስ ጴጥሮስ ጨምሮበታል :- "በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ" 1ኛ ጴጥ. 1:18-19 ቅዱስ ያሬድም "አኮ በወርቅ ኃላፊ ዘተሳየጠነ አላ በደሙ ክቡር ቤዘወነ" ብሎ ዘምሮታል:: የእኔና አንተ ዋጋ በወርቅ በብር የሚመዘን አይደለም:: ዋጋችን በመስቀል ላይ የፈሰሰው ክቡር ደም ነው:: ጌታ "መላእክቶቻቸው የአባቴን ፊት ያያሉና ማንንም እንዳትንቁ" ብሎ ነበር:: (ማቴ.18:10) ሰውን ስለ መልአኩ ብለን እንዳንንቅ ከተነገረን ስለፈሰሰለት ደምማ ምንኛ ልናከብረው ይገባን ይሆን? ውድ ክፍያ ተከፍሎ ልብስ የተገዛለት ልጅ ልብሱን ስለተከፈለበት ዋጋ ሲል ተጠንቅቆ ይለብሰዋል:: በውድ የተገዛ ዕቃ የተሠጠው ሰው በጥንቃቄ ይጠቀምበታል:: የእኛ ሰውነት ግን የተገዛው በአምላካዊ ደም ነው:: እንደተከፈለልን እየኖርን ይሆን? ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ብሔራዊ ቴአትር ጋር ያለውን ሐውልት እጅግ በውድ ዋጋ አሠርተው ነበር ይባላል:: ንጉሡ የአንበሳ ሐውልት ሊመርቁ ሲከፍቱ ግን ሐውልቱ አንበሳ አይመስልም:: የአንበሳና ቀጭኔ ዲቃላ መስሎ ጉብ ብሎአል:: ንጉሡ አንጀታቸው እያረረ ከመረቁ በኋላ ንግግር ሲያደርጉ "ይህ አንበሳ አንበሳ ባይመስልም የወጣበት ገንዘብ ግን አንበሳ ያደርገዋል" አሉ ይባላል:: የእኛም ሕይወት እንደዚያ ነው:: ስንታይ ምናችንም ክርስቶስን አይመስልም:: አንዳንዴም በክፋት ከሰውነት ተራ እንወርዳለን:: ሆኖም እንዲህ ብንበድልም "ክርስቶስ የሞተልን ነን" ምንም እንኳን ክርስቲያን ባንመስል የተከፈለልን ደም የክርስቶስ ያደርገናል:: ምንም እንኳን የከበረ ሕይወት ባይኖረንም የፈሰሰልን ክቡር ደም ክቡራን ያደርገናል:: "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" 1ኛ ቆሮ.6:19 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 17 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
Show all...
+++ ሦስቱ ዛፎች +++ በአንድ ኮረብታ ጫፍ ላይ የተተከሉ ሦስት ዛፎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ዛፎች የወደፊት ተስፋቸውና ሕልማቸው ምን እንደሆነና ምን መሆን እንደሚፈልጉ መወያየት ጀመሩ፡፡ የመጀመሪያው ዛፍ ‹‹ታላቅ ንጉሥ የሚተኛበት አልጋ ለመሆን እመኛለሁ፡፡ ዙሪያዬን በልዩ ቅርጽ ተሠርቼ ሰው ሁሉ እንዲያከብረኝ ዝናዬ እንዲነገር እፈልጋለሁ›› አለ፡፡ ሁለተኛው ዛፍ ይኼን ሲሰማ የራሱን የተለየ ምኞት ተናገረ፡፡ ‹‹እኔ ደግሞ የምጓጓው ታላቅ መርከብ ሆኜ ለመሠራት ነው! በዓለም ላይ እጅግ ዝነኛ የሆኑ ነገሥታት በእኔ ላይ ተሣፍረው እንዲሔዱና ከጥንካሬዬ የተነሣ ሰዎች እኔ ላይ በመሳፈራቸው ያለ ሥጋት እንዲጓዙ ነው የምፈልገው!›› አለ - መርከብ ሆኖ በባሕር ላይ ሲንሳፈፍ በዓይነ ሕሊናው እየታየው፡፡ ሦስተኛው ዛፍ ግን ‹‹ዛፍነቴን ብተው ያንዘፍዝፈኝ›› አለ፡፡ ‹‹እኔ የምፈልገው ከዚሁ ሳልነቃነቅ ረዥም ዛፍ ሆኜ ወደ ላይ ማደግ ነው፡፡ እጅግ ከፍ ብዬ አድጌ የዛፎች ሁሉ ንጉሥ ሆኜ ፣ ለሰማይ እጅግ ቅርብ ሆኜ ሰዎች በእኔ መሰላልነት ወደ ገነት እንዲገቡና እኔን ባዩ ቁጥር ፈጣሪያቸውን እንዲያስታውሱ እፈልጋለሁ›› አለና ምኞቱን ተናገረ፡፡ ይህን ተነጋግረው እንደጨረሱ አናጢዎች ወደ እነዚህ ዛፎች መጡ አንደኛው አናጢ የንጉሥ አልጋ ለመሆን የሚመኘውን ዛፍ ቀረብ አለና ካየው በኋላ ‹‹ይኼ ዛፍ ጠንካራ ይመስላል ፤ ወስጄ ለቤት ዕቃ ሠሪዎች እሸጠዋለሁ›› አለ፡፡ ይህን የሰማው ዛፍ ‹የንጉሥ አልጋ› ሆኖ የመሠራት ሕልሙ ዕውን እንደሚሆን በመተማመን ፈነደቀ፡፡ አናጢው ወስዶ የሸጠላቸው እንጨት ሠሪዎች ግን የዛፉን ሕልም ሳይረዱ የንጉሥ አልጋ አድርገው በመሥራት ፈንታ የከብቶች የሣር ድርቆሽ ማስቀመጫ ሣጥን አድርገው ሠሩትና በአንድ በረት ውስጥ ተጣለ፡፡ ሁለተኛው አናጢ የንጉሥ መርከብ እሆናለሁ ብሎ የሚመኘውን ዛፍ ቀረብ ብሎ አየውና ‹‹ይኼ ዛፍ ጠንካራ ይመስላል ፤ መርከብ ወደሚሠሩ ሰዎች ወስጄ ባሳየው ጥሩ ዋጋ ያወጣልኛል›› አለ፡፡ ዛፉ ‹ስዕለቴ ሠመረ› ብሎ ተደሰተ፡፡ ሆኖም መርከብ ሠሪዎቹ ምኞቱን ሳያውቁ ቆራርጠው ቆራርጠው በርከት ያሉ የዓሣ ማጥመጃ ጀልባዎችን ሠሩበት፡፡ መርከብ እሆናለሁ ብሎ የተመኘው ይህ ዛፍ ዓሣ አጥማጆችን ጭኖ እየተንሳፈፈ የንጉሥ መርከብ ሲያልፍ ተመልካች ሆነ፡፡ ሦስተኛውን ዛፍም በመጥረቢያ ሲቆርጡት የዛፎች ንጉሥ ሆኖ ከፍ ብሎ የማደግ ሕልሙን አብረው ቆረጡት፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ አንዲት የጸነሰች ብላቴና ከአንድ አረጋዊ ጋር ቤተልሔም በሚባል የይሁዳ ከተማ መጣች፡፡ በወቅቱ የማደሪያ ሥፍራ ስላልነበር በከብቶች በረት ውስጥ ለማደር ገቡ ፤ ጸንሳ የነበረችውንም ልጇን በበረት ውስጥ ወለደችው፡፡ የመኝታ ሥፍራ ስላልነበር ሕጻኑን የከብቶቹ የሣር ድርቆሽ በሚቀመጥበት ሳጥን ውስጥ አስተኛችው፡፡ የዚያን ቀን ለተወለደው ሕጻን ከሩቅ የመጡ ነገሥታት ሳይቀር ሥጦታን አመጡለት፡፡ የንጉሥ አልጋ መሆን ይመኝ በነበረው ያ ዛፍ ሳጥን ሆኖ ቢሠራም የነገሥታት ንጉሥ መኝታ ሆነ፡፡ ይህ ከሆነ ከሠላሳ ዓመታት በኋላ የዓሣ ማጥመጃ ሆኖ በተሠራው ጀልባ ላይ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ዓሥራ ሦስት ሰዎች ተሳፈሩበት፡፡ የንጉሥ መርከብ ለመሆን የተመኘው ይህ ጀልባ በጀልባነቱ ዓሥራ ሦስት ተሳፋሪዎችን ተሸክሞ ሲማረር በጉዞ መካከል ድንገት ትልቅ ማዕበል ተነሥቶ መርከቧን ያናውጻት ጀመረ፡፡ ተሳፋሪዎቹ ጀልባዋን ለመቆጣጠር ታገሉ፡፡ ከመካከላቸው ግን አንዱ ተሳፋሪ ተኝቶ ነበር፡፡ ሞገዱ እየባሰ ሲመጣ የተኛውን ተሣፋሪ ‹‹ስንጠፋ አይገድህምን?›› ብለው ቀሰቀሱት፡፡ እሱም ተነሥቶ ማዕበሉን ገሠጸው፡፡ ጀልባው ድሮ እንደተመኘው የጫነው የነገሥታትን ንጉሥ እንደሆነ ተረዳ፡፡ ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ የዛፎች ንጉሥ ለመሆንና ወደ ሰማይ መውጫ መሰላል ለመሆን የተመኘውን ዛፍ አምጥተው ለአንድ ወንጀል ለሌለበት ንጹሕ አሸከሙት ፣ ከተራራ ጫፍ ሲደርሱም ባሸከሙት እንጨት ሰቀሉት፡፡ እንደተሰቀለ ምድር ለሦስት ሰዓታት ጨለመች ... ብዙ ተአምራት ተፈጸሙ፡፡ ይህ ዛፍ እንደተመኘው የዕጽዋት ሁሉ ንጉሥ ሆነ ፤ ሰዎች በእሱ መሰላልነት ወደ ገነት ገቡ ፤ እሱን ያዩ ሁሉ ፈጣሪያቸውን ያስታውሳሉ፡፡ በሁላችንም ሕሊና ውስጥ የእነዚህ ዛፎች ሕልም የተበላሸው ገና ያን ጊዜ ወዳላሰቡት ሥፍራ ሲጣሉ ነበር፡፡ ነገሩ አበቃ ብለን ስናስብ ግን የሦስቱም ምኞት ተሳካ፡፡ ይህ ጥንታዊ ታሪክ ምሳሌ እንጂ እውነተኛ ታሪክ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ግን አንድ እውነታ አለ፡፡ በሕይወታችን ውስጥ እኛ አበቃልን ስንል እግዚአብሔር ሥራውን ይጀምራል፡፡ ‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀ የተቈረጠ ነገርን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል።›› ኢሳ. 10፡23 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 2007 ዓ ም ኩዌት የተጻፈ [ከሞት ባሻገር በተሰኘው መጽሐፍ የታተመ] (ይህን በሥነ ጽሑፍ ዓለም የታወቀ ጥንታዊ ትረካ ያገኘሁት Archangel Michael Coptic Orthodox Church News letter (St. Mary Coptic Orthodox Church, East Brunswick, N.J./ volume 3 Feb. 2002) ዕትም ላይ ሲሆን ሃሳቡን ብቻ በመውሰድና አንዳንድ ለውጦች በማድረግ በዚህ መልኩ አስቀምጬዋለሁ፡፡ ይህ ታሪክ ምክር አዘል ምሳሌ ብቻ እንጂ ለተባሉት ዕቃዎችም ሆነ ለመስቀል ታሪካዊ አመጣጥ የሚጠቀስ ተአማኒ ታሪክ እንዳልሆነ አስታውሳለሁ፡፡)
Show all...
+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ + "በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ "ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ "ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ "እንደኛ ስላልሆንክ አብደሃል" የሚሉበት ዘመን ይመጣል" ቅዱስ እንጦንዮስ "መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም" ቅዱስ ባስልዮስ "ይህንን ካስታወስክ በሰው መፍረድ ታቆማለህ:: ይሁዳ ሐዋርያ ነበር:: ከጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ነፍሰ ገዳይ ነበር" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው "የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው" ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ "እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD) "ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ ‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ "ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡ የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 26 2011 ጅማ ፣ ኢትዮጵያ https://t.me/deaconhenokhaile
Show all...
+ ከአንተ ባላውቅም ...+ በገነተ አበው (The Paradise of Fathers) መጽሐፍ ላይ ይህ ታሪክ ተጽፎአል:: አንድ መነኩሴ በበአቱ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ አንድ ቃል ሊገባው አልቻለም:: ለመረዳት በጣም ሲያስቸግረው "ይኼን ቃልስ እንዲገልጽልኝ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አለብኝ" ብሎ ወሰነ:: ነቢያቱ ያደርጉት እንደነበረውም እግዚአብሔር የቃሉን ፍቺ እስኪገልጽለት ድረስ መጾምና መጸለይ ጀመረ:: ነገር ግን ለሰባ ሳምንታት ያህል እየጾመ ቢጠባበቅም ምንም ነገር ሊገለጽለት አልቻለም:: በየሳምንቱ መጨረሻ ቃሉን ደግሞ ሲያነበውም የበለጠ እየተወሳሰበበት ሔደ እንጂ ጨርሶ ሊገባው አልቻለም:: በመጨረሻም ተስፋ ቆረጠ:: ስለዚህ ሌላ መነኩሴ ጋር ሔዶ ስለዚህ ቃል ትርጉም ሊጠይቀው ወሰነ:: በአቱን ዘግቶ መንገድ ሊጀምር ሲዞር ግን የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ ታየው:: "አይዞህ አትፍራ የፈለግኸውን የቃሉን ትርጉም ልገልጽልህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬያለሁ" አለው:: መነኩሴው ግራ ገባው "የጌታ መልአክ ሆይ ሰባ ሳምንት ሙሉ እየጾምሁ እንዲገልጥልኝ ስለምን ቆይቼ ምንም መልስ አላገኘሁም:: አሁን ተስፋ ስቆርጥ እግዚአብሔር ስለምን መለሰልኝ?" አለ በፍርሃት ውስጥ ሆኖ "እግዚአብሔር ሰባ ሳምንታት ከጾምኸው ጾም ይልቅ ወንድምህን ለመጠየቅ በመሔድ ያሳየኸውን ትሕትና ተቀብሎታል" አለው:: አላዋቂ መስሎ መታየትን ያህል የምንፈራው ነገር የለም:: "አላውቀውም አንተ ንገረኝ" ከማለት ይልቅ ብዙ ሰው ሞት ይመርጣል:: ትንሽ ተምሬያለሁ የሚል ሰውማ ጥያቄ መጠየቅ ዲግሪውን ማቃጠል ይሆንበታል:: የብዙዎቻችን ትሕትና የሚፈቅድልን ሰዓት ለመጠየቅ ብቻ ነው:: "ከአንተ አላውቅም ..." ብለው የሚጀምሩ ዐረፍተ ነገሮች ራሱ ልብ ብለን ከሰማናቸው ይዘታቸው "ከእኔ አታውቅም" ነው:: የእውቀታችንን ውስንነት ለማመን የሚከብደን በሥጋችን ውስጥ ያለችው ለባዊት ነፍሳችን በሥጋዊ እውቀት ራስዋን መገደብ ስለምትቸገርም ነው:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "አሁን ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ" ብሎ የእውቀትን ውስንነት ማመን ግን ዕረፍት ይሠጣል:: 1ቆሮ. 13:12 በመንፈሳዊው ዓለም እንዲህ ሲሆን ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ እውነታ ነው:: "የቀለም ቀንድ" ፣ "የእውቀት ምንጭ" ፣ "መልስ በጉንጩ"፣ "ተጠያቂው" የሚለውን የክብር ሥፍራ ስንፈልግ በማናውቀው ጉዳይ ሌሎችን ከመጠየቅ ይከለክለናል:: አላውቀውም አላነበብኩትም አልሰማሁትም ከማለት ይልቅ ሁሉን አዋቂ ሆኖ ለመገኘት ስንል የምንበላቸው ዕፀ በለሶች ብዙ ናቸው:: "ብዙ የማውቀው ነበረ ሰዓት ገደበኝ እንጂ" ብሎ ውስን እውቀቱን ባሕር ለማድረግ የሚደክምና ሰዎች ከተናገረው ከጻፈው በላይ አድርገው እንዲያስቡት የሚገፋፋ ሰው የሚወለደው ካላዋቂነት ፍርሃት ውስጥ ነው:: በጥቂት ንባብ ውስጥ ራስን በጥልቅ ምሁር ዓይን ማየትና "እኔ የማውቀው ማወቄን ነው" ማለት የአላዋቂነት ፍርሃት የሚወልዳቸው ኢሶቅራጥሶች መርሕ ነው:: ከሌላው በታች አላዋቂ መስሎ መታየትን እንፈራለን:: ስለዚህ ሌላውን ከመጠየቅና እንደ ጃንደረባው "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" "ነቢዩ ይኼን ስለማን ተናግሮታል?" ብሎ ከመማር ይልቅ በራሳችን ለመረዳት ብንሟሟት እንመርጣለን:: ብዙ "የእምነት" denominations የተፈጠሩትም ሌላውን ከመጠየቅ ሞት በሚመርጡ ትዕቢተኞችና "እንደገባኝና እንደተረዳሁት" በሚል አስተሳሰባቸው እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል:: "ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር" ፊልጵ. 2:3 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 2016 ዓ.ም. ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
Show all...
+ ድንገት የተበጠሰ ገመድ + የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል:: የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ) በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት:: ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል:: በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም::  የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ:: ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም! ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም
Show all...
+++ የኢየሱስን ልብስ ከላዩ ላይ ገፈፉት ±++ በወንጌል የምናውቃቸው ጌታችን የለበሳቸው ልብሶች አራት ሲሆኑ ሦስቱ ከዕለተ ዓርብ በኋላ የለበሳቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ከመያዙ በፊት ለብሶት የነበረው የራሱ ልብስ ነው ፣ ሁለተኛው ሄሮድስ ለመዘበት ያለበሰው የጌጥ ልብስ ነው ፤ ሦስተኛው ወታደሮቹ ያለበሱት ቀይ ልብስ (ከለሜዳ) ነው ፤ አራተኛው ከትንሣኤው በኋላ ሲገለጥ ለብሶ የታየውና ከየት እንደመጣ የሚያጠያይቀው ነጭ ልብስ ነው፡፡ ጌታችንን መስቀል አሸክመው ከጎልጎታ ኮረብታ ካደረሱት በኋላ ለብሷት የኖራትን ልብሱን ገፈፉት፡፡ ‹‹ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል በአራት አከፋፈሉት ፤ እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር እንጂ የተሠፋ አልነበረም፡፡ ስለዚህ እርስ በእርሳቸው ፡- ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ፡፡ ይህም ፡- ልብሴን እርስ በእርሳቸው ተከፋፈሉ ፤ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው›› (ዮሐ. ፲፱፥፳፫‐፳፬ መዝ.፳፩፥፲፰) የጌታችንን ልብስ የገፈፉት ዕርቃኑን ለመስቀል ሲሆን ልብሱን የተከፋፈሉት ደግሞ ሌላ የሚወደው ሰው መጥቶ ልብሱን እንዳይወስደው ነበር፡፡ አብረውት የተሰቀሉትን ወንበዴዎች ልብሶች እንዲህ እንዳደረጉ አልተጻፈም ፤ ይህም ትንቢት የተነገረለት እርሱ ስለሆነና የሚረዳው የሌለ ያማረ ልብስ የማይለብስ ደሃ ነው ብለው በእርሱ ለመሳለቅ እንዲመቻቸው ነበር፡፡ የጌታችን ልብስ ግን እነርሱ እንዳዩት ተራ ልብስ አልነበረም፡፡ ወታደሮቹ አላወቁም እንጂ ከላዩ ገፍፈው በእጃቸው የያዙት ልብስ በታቦር ተራራ እንደ ብርሃን ነጭ የሆነውን ልብሱን ነበር፡፡ (ማቴ. ፲፯፥፪) ይህ ልብስ ከዓሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረችውና ገንዘብዋን ከስራ ልትድን ያልቻለችው ሴት ‹‹የዳሰስሁት እንደሆነ እድናለሁ›› ያለችው ልብስ ነው፡፡ ይህ ልብስ የዚህችን ሴት የደምዋን ምንጭ ያደረቀላት ልብስ ነው፡፡ ጌታችን ሴቲቱን ከፈወሳት በኋላ ‹‹አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ አውቃለሁ›› ብሎ የተናገረበት ስለዚህ ልብስ ነበር፡፡ (ሉቃ. ፰፥፵፫‐፵፮) ስለዚህ ልብስ ‹‹በገባበት ስፍራ ሁሉ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር ፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳን ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር ፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማር. ፮፥፶፮) ይህንን ተአምረኛ ልብስ የሮም ወታደሮች ተከፋፍለው በእጃቸው ቢይዙትም ደም ይፈስሳት እንደነበረችው ሴት በእምነት ሆነው አልዳሰሱትምና አንዳች ተአምር አላዩም ፤ ‹‹ምንም ተአምር ከልብሱ አላገኙም ፤ ክርስቶስ የማይነገረውን ኃይሉን ገድቦ ነበርና›› ይላል አፈወርቅ፡፡ ሮማውያን ወታደሮች ጌታችን ልብሱን ገፍፈው በአደባባይ ዕርቃኑን አቆሙት ፤ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣትን አምላክ ፤ ሰሎሞን እንኳን በክብሩ ለብሶት የማያውቀውን ልብስ ለሜዳ አበቦች የሚያለብሳቸውን አምላክ ልብሱን ገፍፈው ዕርቃኑን አቆሙት፡፡ ‹‹እንደ ሸላቾች ልብሱን ከላዩ ላይ ሁለት ጊዜ ገፈፉት ፤ እርሱም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ዝም አለ፡፡ ዕርቃናቸውን ከገነት የወጡትን አዳምና ሔዋንን ለማልበስ ልብሱን ተገፈፈ፡፡ እርሱ በመዋረድ ውስጥ ሆኖ በልብሶቹ ዕርቃናቸውን አለበሰ፡፡ የእርሱ ልብሶች ለተዋረዱት አዳምና ሔዋን እንደሚበቁ ያውቅ ነበርና›› ይላል ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፡፡ በዚህ ሊቅ ምክንያት እስቲ ለአፍታ አዳምና ሔዋን ከገነት ወደ ወጡባት ቅጽበት እንመለስ፡፡ አዳምና ሔዋን ዕርቃናቸውን ለመሸፈን ቅጠል ባገለደሙ ጊዜ ከገነት ሲወጡ ‹‹እግዚአብሔርም ለአዳምና ሔዋን የቁርበት ልብስን አደረገላቸው አለበሳቸውም›› ይላል፡፡ (ዘፍ. ፫፥፳፩) እግዚአብሔር ከሌላ ዓይነት ልብስ ይልቅ ስለምን የቆዳ ልብስን ሊያደርግላቸው ወደደ? ብለን ስንጠይቅ ወደ ዕለተ ዓርብ ይመራናል፡፡ እንደሚታወቀው ቁርበት የሚገኘው ከእንስሳ ነው፡፡ አንድ ቁርበት ልብስ እንዲሆን በመጀመሪያ እንስሳው ይታረዳል ፣ ደሙ ይፈስሳል ፤ ቆዳው ይገፈፋል ፣ እንዲደርቅ በእንጨት ላይ ተወጥሮ ይሰጣል ፣ በላዩ ላይ ያለው ነገር እስከሚነጻ ድረስ ይለፋል፡፡ ከዚህ ሁሉ ሒደት በኋላ ልብስ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን ልብስ በገነት ያለበሳቸው አምላክም የእንስሳ ደሙ እንደሚፈስስ ደሙን አፍስሶ ፣ቆዳው እንደሚገፈፍ ቆዳው አልቆ አጥንቱ እስከሚታይ ተገርፎ ፣ ቆዳ እንደሚወጠር በመስቀል ላይ እንደ ቆዳ ተወጥሮ በዕርቃኑ ዕርቃናችንን ሸፈነልን ፤ እርሱም ለእኛ ልብሳችን ሆነልን፡፡ ‹‹የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋል›› እንዳለ ሐዋርያው (ገላ. ፫፥፳፯) ወታደሮቹ የጌታችንን ልብስ ለአራት ክፍል ተከፋፈሉ፡፡ ቀሚሱ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበርና አንቅደደው ተባብለው ዕጣ ተጣጣሉበት፡፡ እነዚህ ወታደሮች ለቀሚሱ ሳስተው ባለመቅደዳቸው ሳያውቁት ትልቅ ምስክርነት መሰከሩ፡፡ ጌታችን ብዙ መንገላታት ሲደርስበት ባደረው በጨለማው ፍርድ ቤት በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ከሕግ ውጪ ልብሱን ቀድዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም ሥራው ሊቀ ካህናት ልብሱ ሊቀደድ እንደማይገባውና ልብሱን መቅደዱም ሊቀ ካህናትነቱ ማለፍዋን የሚያመለክት እንደሆነ በሥፍራው ተመልክተን ነበር፡፡ እነዚህ ወታደሮች የጌታችንን ቀሚስ ባለመቅደዳቸው የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ መሆኑንና ልብሱም ፈጽሞ ሊቀደድ እንደማይገባው የሚያሳይ ታላቅ ምሥጢር ተፈጸመ፡፡ ያልተቀደደችውን የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ቀሚስና ለአራት የተከፋፈለውን ልብሱን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ብዙ አስተምረውበታል፡፡ ‹ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ› የሚለው ቃል ክርስቶስ ‹ሰው ብቻ ሳይሆን ከላይ የመጣ መለኮት መሆኑን ያመለክታል› ብሎ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አብራርቶታል፡፡ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምም ቀሚስ የተባለ መለኮቱ ሊቀደድ (ከሥጋው ተለይቶ ሊከፈል) አይችልም ፤ ለአራት የተከፈለው ልብሱ ግን አራት ሆና የተጻፈችውና በአራቱም ማዕዘን የምትዳረሰው ወንጌል ምሳሌ ናት ሲል ተርጉሞታል፡፡ ይህ የሊቃውንቱ ትርጓሜ ከእግዚአብሔር መንፈስ የተገኘ መሆኑም በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ተረጋግጧል፡፡ ዐሥራ ሰባተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስ የተባለውን በኩረ መናፍቃን ካወገዘው በኋላ የተፈጸመው ነገር ይህን ግልጥ አድርጎ ያሳያል፡፡ አርዮስ ከውግዘቱ በኋላ በፓትርያርኩ ላይና በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ከንጉሥ መክስምያኖስ ጋር ሴራን ተብትቦ ቅዱስ ጴጥሮስን አሳስሮት ነበር፡፡ ከዚያም አርዮስ ፓትርያርኩ ጴጥሮስ ሊገደል እንደሚችል ሲረዳ እንዳወገዘው እንዳይሞት የዋሃን ካህናትን አማላጅ አድርጎ ምሕረት ሊያስለምነው ሞከረ፡፡ ፓትርያርኩም ለአርዮስ አማላጆች ሆነው ለመጡት ካህናት አርዮስን ከውግዘቱ መፍታት እንዳይችል ያደረገውን ራእይ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡-
Show all...
‹‹መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሌሊት የተቀደደ ቀሚስ ለብሶ ታየኝ ፤ እኔም ‹ጌታዬ ሆይ ልብስህን ማን ቀደደው?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ‹አርዮስ ልብሴን ቀደደው ፤ ከባሕርይ አባቴ (ከአብ) ለይቶኛልና ፤ እንዳትቀበለው ተጠንቀቅ› አለኝ›› አላቸው፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በእኔ ደም መፍሰስ የክርስቲያኖች ደም እንደጎርፍ መፍሰሱ ይቁም ብሎ ተስሎ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ጌታችን ‹ልብሴን ቀደደው› ብሎ ለዚህ ፓትርያርክ እንደነገረው የጌታችን የባሕርይ አምላክነት ላይ የክህደት ቃልን የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ ሮማውያን ወታደሮች ያልቀደዱትን የክርስቶስን ቀሚስ እንደቀደዱ ይቆጠራል፡፡ ሊቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ደግሞ የጌታችንን ልብስ አለመቀደድ ቤተ ክርስቲያንን ለሚከፋፍሉ ሰዎች ማስተማሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እንደ ሊቁ ትምህርት ያልተቀደደችውና ከላይ ጀምሮ ወጥ የሆነችው ቀሚስ ከዚህ ዓለም ያልሆነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ለአራት የተከፈለው ደግሞ የምታስተምረው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ሊከፋፈልና ለዓለም ሁሉ ሊዳረስ ይችላል፡፡ ወንጌል በዘር በቋንቋ በሀገር አይገደብምና የክርስቶስ ወታደሮች የሆኑ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ተከፋፍለው ለዓለም ማከፋፈል አለባቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያናት በየሀገራቱ ቢቋቋሙ ፣ አህጉረ ስብከቶች ቢስፋፉ ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሊቃውንት ፣ ሰባክያን በቁጥር በዝተው ፣ በቦታም ተከፋፍለው ቢያገለግሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሁሉ ጎዳና … ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል›› እንዳለ የመምህራን መብዛት የወንጌል መስፋፋት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ (ፊል. ፩፥፲፰) ቀሚሱ የተባለችን ቤተ ክርስቲያንን ከተቃደዷት ግን አደጋ አለው ፤ ‹የሐዋርያት በሆነች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን› ብለን የምንናገርላት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቀሚሱ ናት፡፡ በሰው እጅ ያልተሰፋች ፣ ማንምም ሊሠፋት የማይችል ቀሚስ ናት ፤ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆና በመሠራቷም አትከፋፈልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍሏት የሚፈልጉ ሰዎችን ሊቁ አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ሮማውያን እንኳን ያልቀደዱትን የክርስቶስን ልብስ እናንተ ስለምን ትቀድዱታላችሁ?›› ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ [email protected]
Show all...