cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

Show more
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#Thomas_Edison Once young Thomas Edison returned home from school and handed his #mother a letter from his teacher. His #mother read the letter aloud to him, tears in her eyes: "Your son is a genius. This school is too small for him, and there are no teachers here capable of teaching him anything. Please educate him yourself." Many years after his #mother's death (by that time, Edison was already one of the greatest inventors of the century), he was revisiting old family archives and came across this letter. He opened it and read: "Your son is mentally deficient. We cannot continue to educate him in school along with everyone else. Therefore, we recommend that you teach him at home." Edison wept for several hours. Then he wrote in his diary: "Thomas Alva Edison was a mentally deficient child. Thanks to his #heroic_mother, he became one of the greatest geniuses of his century." ✍Psychology @ይሄ ነው ሐበሻ!👳‍♀👩‍🦳👩‍🦰👱‍♀🤰 https://t.me/yihenewhabesha
Show all...
ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

#ወንድሜ_ጸልይ #ስታገኝም ጸልይ ፣ ባለህ ነገር ትረካለህ። #ስታጣም ጸልይ ተስፋን ይዘህ ትነሣለህ። #ስትስቅ ጸልይ ፣ ሳቅህን እውነተኛ ያደርግልሃል። #ስታለቅስም ጸልይ ፣ ከኀዘን ሸለቆ ያወጣሃል። #ስትወድድ ጸልይ ፣ ያረፈደው ፍቅር ያመሽልሃል። #ስትቀየምም ጸልይ ፣ ልብህን ያጥብልሃል። #በአገርህ ስትሆን ጸልይ ፣ ከወገን ጠላት ይጋርድሃል ፤ #በሰው አገር ስትሆንም ጸልይ ፣ ባዕዱን ዘመድ ያደርግልሃል። #ስታሸንፍ ጸልይ ፣ ጋሻህ እግዚአብሔር ይሆናል። #ስትሸነፍም ጸልይ የእንደገና ዕድል ይሰጥሃል። #ስትደፍር ጸልይ ፣ መለኮት ድጋፍ ይሆንሃል። #ስትፈራ ጸልይ ፣ እምነትን ይሰጥሃል። #ሲሳካልህ ጸልይ ፣ የመኸር ደስታ ታገኛለህ። #ሳይሳካም ጸልይ ፣ ፈቃደ እግዚአብሔር ልብህን ያሳርፈዋል። #አስታመህ ሲድንልህ ጸልይ ፣ ፈውስ የእግዚአብሔር ገንዘብ ናትና። #አስታመህ ሲሞትብህም ጸልይ ፣ ሞት ዕረፍት ነውና። #ደግ ንጉሥ ሲነሣ ጸልይ ፣ ደግ ሰው ዘመኑ አጭር ነውና። #ክፉ ንጉሥ ሲነሣም ጸልይ ፣ ለቅጣት ይላካልና። #ስትቀደስ ጸልይ ፣ ከኃጢአት የሚያድን ኢየሱስ ነውና። #ስትቆሽሽም ጸልይ ፣ በደሙ ያጥብሃልና። #ደም በባሕርይው ያቆሽሻል። የእግዚእ ኢየሱስ ደም ግን አምላካዊ ደም ነውና ያነጻል። #ደም ሲያዩት ያስደነግጣል ፣ የአማኑኤል ደም ግን መሢሐዊ ደም ነውና የተዘጋውን  በር ይከፍታል ። #ተደርጎልህ እንደሆነ የምታመሰግነው በጸሎት ነው። #የሌሎች ጉዳት አስጨንቆህ ከሆነ የምትማልደው በጸሎት ነው። #ኃጢአትህ ከብዶህ ከሆነ ንስሐ የምትገባው በጸሎት ነው። #አጥተህ ከሆነ የምትለምነው በጸሎት ነው። #ጸሎት_ለንጉሥ_አቤት_ማለት_ነው! #ጸሎት  ለዳኛ ይግባኝ ማለት ነው። #ጸሎት ለሰጪው ጌታ እጅን መዘርጋት ነው። #ጸሎት ለወዳጅ የፍቅር መልእክት መላክ ነው። #ጸሎት ለተዋጊው ጀግና መንገድ መልቀቅ ነው። #ጸሎት ለቤትህ ራስ ጉድለትህን ነግረህ መተኛት ነው። #ጸሎት ምግበ ሥጋ ፣ ምግበ ነፍስን የምንጠይቅበት ነው። #ጸሎት ወደ ሰማይ መደወያ ቍጥር ነው። #ጸሎት የሃይማኖት መሣሪያ ነው ። #ጸሎት_ሀልወተ_እግዚአብሔርን የምንመሰክርበት ነው ። #ከሕይወት ሥነ ሥርዓት አንዱ መጸለይ ነው ። ስለዚህ አፍ ከልብ ሆነህ ፣ ስፍራና ጊዜ ለይተህ በማለዳና በምሽት ጸልይ። #ከበረታህ በሃያ አራት ሰዓት ሰባት ጊዜ ጸልይ ። #ከቤትህ ስትወጣ የመንገድ ጸሎት ፣ #ስትመገብ የማዕድ ጸሎት አትርሳ ። #ወደ ወዳጅህ ቤት ስትሄድ ፣ ደግሞም ስልክ ስትደውል ጸልይ። የእግርህ ኮቴ እንዲናፍቀው ያደርጋል ። #ወደ ሥራ ስትገባና ሥራህን ስትጀምር ጸልይ። ሐኪም ሆነህ እንደሆነ ሳትጸልይ በሽተኛ አትንካ። “አንተም በእምነትህ ጸልይ”።  #ሠራተኞችህ ሊጋጩህ ሲፈልጉ ዘወር ብለህ ጸልይ ፣ #ሚስትህ ለግጭት ስትፈልግህ በልብህ ጸልይ ። #በማለዳ አፍህን በጸሎት ሳታሟሽ ከሚስትህም ጋር ቢሆን አትነጋገር ። ላንተ ማንጋት አልረሳምና በማለዳ ተነሥተህ አመስግን። #ታርፍ ዘንድ ላንተ ማስመሸት አልረሳምና ሲመሽ ጸልይ። #በመንገድ ስትሄድ ፣ ብቻህን ስትሆን ፣ ወደ መታጠቢያ ሄት ስትገባ ፣ ገላህን ስትታጠብ ጸልይ። #ከጸሎት ሁሉ አውራው “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ - አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን” የሚለው ነው ። #ያለማቋረጥ ይህን ጸሎት ጸልይ። #ፈተናና ትግሉ ሲበዛ መዝሙር 22ን እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚለውን ደጋግመህ ጸልይ ። #ደግሞም ጸሎተ ማርያምን ታዐብዮ ነፍስዬን- ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች የሚለውን ደጋግመህ ጸልይ (ሉቃ. 1፡47-55)። #የልብህን ሙቀት ለጌታህ አፍስስለት ። #የግል ጸሎት ፣ #የቤተሰብ ጸሎት ፣ #የማኅበር ጸሎት እንዳለ አስታውስ ። #የአጋንንት ፍላጻ ሲበዛ መዝሙር 90ን ደጋግመህ ጸልይ ። “በልዑል መጠጊያ የሚኖር…” የሚለውን ማለቴ ነው ። #አባቶችህ ስታገኝ ጸሎት ተቀበል ። አንተም ትባረካለህ ፣ እነርሱንም ታተጋለህ። #በማለዳ ጸሎትህ ላይ ውኃ በብርጭቆ አድርገህ ጸልይ ። ራስህንና ቤተሰብህን በተባረከው ውኃ ቀድስ። #ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ስላገኘህም ጸልይ። የሚፈልጉትን የማያውቁና የሚፈልጉትን ያጡ በዓለም ላይ አሉ ። የሚያድናቸው ጸሎት ብቻ ነው ። #ወደ ወዳጅህ ቤት ስትገባ ሳትቀመጥ ጸሎት አድርሱ ። #ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትገባ ሳትቀመጥ ጸሎት አድርስ ። #ወደ ጉባዔ ስትሄድ በቃሉ እንዲናገርህ ጸሎት አድርስ ። #በታላቅ መከራ ውስጥ ስትሆን ዝም ብለህ ጸልይ ። ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ ጸልዮአልና ። ጸሎት ለሥጋዊ ጤና ፣ ለአእምሮ መታደስ ፣ ለመንፈስ እረፍት ወሳኝ ነውና ጸልይ። #ወንድሜ_እባክህ_ጸልይ! #ጸልይ_ጸልይ… ጸልይ! ✍ዲያቆን አሸናፊ መኰንን @ይሄ ነው ሐበሻ!🙏🙏🙏🙏🙏 https://t.me/yihenewhabesha
Show all...
ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

#እስቲ_ባሕርን_ሁን_ወዳጄ ባንድ ወቅት በሕይወቱ #ደስታን ያጣው ታዳጊ ወጣት አንድ የዕድሜ ባለጸጋን ሽማግሌ ሕይወት እንዳማረረችው ገልጾ መፍትሄ እንዲጠቁሙት ጠየቃቸው፡፡     ሽማግሌው የወጣቱን ሀሳብ በጥሞና ካደመጡ በኋላ በእፍኙ ሙሉ #ጥሬ_ጨው በብርጭቆ ውሃ ጨምሮ በጥብጦ እንዲጠጣው አዘዙትና “ጣምናው እንዴት ነው?” በማለት ጠየቁት፡፡ ፊቱን አኮሳትሮ “በጣም አስቀያሚ ነው!” ሲል መለሰላቸው፡፡    ሽማግሌው ፈገግታ እያሳዩት ወጣቱን ወደ #ባሕር ዳርቻ ወስደው  ሌላ ጭብጥ ሙሉ ጨው  #ባሕሩ ውስጥ እንዲጨምርበት አመላከቱት፡፡ በመቀጠልም  #ከባሕሩ ጨልፎ እንዲጠጣ ካደረጉ በኋላ “ጣዕሙ እንዴት ነው?” ሲሉ በድጋሜ ጥያቄ አቀረቡለት፡፡ “ጥሩ ነው” በማለት መለሰ ታዳጊው፡፡ አስከትለውም  “የጨው ኮምጣጣነትና ያ አስቀያሚው ስሜት ተለይቶሃል?” በማለት ጠየቁት፡፡ “በፍጹም” ሲል መለሰ ወጣቱ፡፡ ከዚህ ሁሉ የተግብር ትምህርት ቀጥሎ ሽማግሌው የወጣቱን እጅ ይዘው ከጎኑ ተቀመጡና ይሄንን መከሩት፡፡    በሕይወት ጎዳና የምታደርጋቸው ትግሎች እንደ ንጹህ #ጥሬ_ጨው ናቸው፡፡ **ነገር ግን የስቃዩ መጠን ተመሳሳይ ቢሆንም የምንሸከመው ስቃይ የሚወሰነው በምንይዝበት #ዕቃ_መጠን ይወሰናል፤ ችግሩን የምናስተናግድበት አግባብም የሚፈጥረውን ጫና በዛው ልክ ይለያየዋል፡፡   ችግሩ ሲጠናብህ ልታደርገው የሚገባው ዋናው ነገር ምልከታህን ማስፋት ብርጭቆውን ሳይሆን #ባሕሩን መሆን ነው ትልቁ የአኗኗር መላው፡፡     እናም ብርጭቆ መሆንህን አቁመህ #ባሕሩን ሁን በማለት አሰናበቱት፡፡ አንተ ለራስህ የትኛው ነህ? #ወዳጄ_ባሕር_ሁን_ግዴለህም! @ይሄ ነው ሐበሻ!🥛🍵☕️🌝🌝 https://t.me/yihenewhabesha
Show all...
ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

+  #በርባን_ይፈታልን + ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታልን! #ክርስቶስ ግን ይሰቀል!› ማለታቸውን ስንሰማ መቼም ሁላችንም ማዘናችንና ‹ምን ዓይነት #ክፉዎች ናቸው?!› ብለን መውቀሳችን አይቀርም፡፡ #ወዳጄ_ሆይ! እባክህን እስቲ አይሁድንና ጲላጦስ ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያው ትምህርት ቤት ዲን የነበረው ሊቅ ‹‹በሥጋው #ክፉ_ነገርን የሚሠራ ሁሉ #በርባንን ፈትቶ #ክርስቶስን አሰረው ፤ መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ #ክርስቶስን ፈትቶ #በርባንን አስሮታል›› ይላል፡፡ #ወዳጄ_ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? #በርባንን ነው ወይንስ #ጌታን ነው? #በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ #በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹ #በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች #አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና #እጅህን_መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ #ጌታህን_ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ #ሥጋን_ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬)   ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታ› ብለው ቢጮኹም ሁሉም ለበርባን ፍቅር አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ሊቃነ ካህናቱ ባያባብሏቸው ኖሮ በዚያች ዕለት ሊያስፈቱት የሚፈልጉት ሌላ እስረኛ ዘመድ ያላቸውም ሰዎች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱ ለጌታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሣ ሕዝቡን ተለማምጠው በርባን እንዲፈታ አስደረጉ፡፡ ዛሬ በርባንን አግኝተን ‹በርባን ሆይ ማን ነው ያስፈታህ?› ብለን ብንጠይቀው ምናልባትም ‹የሰው #መውደድ_ይሥጥ ማለት ነው! የሚወደኝ ሕዝብ ነዋ ጮኾ ያስፈታኝ!› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱና ተከታዮቻቸው ግን ‹በርባን ይፈታ› ብለው የጮኹት ለበርባን ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በነበራቸው ጥላቻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ በርባንን ከሞት ፍርድ አድኖ ያስፈታው ሕዝቡ ሳይሆን #ጌታችን ነበር፡፡ ጌታችን በዚያች ዕለት የበርባንን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለበርባን ሠጠው ፤ የበርባንን ሰንሰለት አስፈትቶ እርሱ ታሰረ ፤ ከበርባን ጓደኞች ጋር በርባን ሊሰቀል በነበረበት ቦታም ተሰቀለ፡፡ ወዳጄ ሆይ! ልብ ብለህ ከተረዳኸው በርባን እኮ አንተው ነህ! ለበርባን ከተደረገለት ለአንተ ያልተደረገ ነገር ካለ እስቲ ንገረኝ! እንደ በርባን ክርስቶስ ሞትህን ወስዶ ሕይወቱን ፣ እስራትህን ወስዶ ነጻነትን አልሠጠህምን? ይህንን ያደረገውም ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጅ ሁሉ ነው ፡- ‹‹የእስረኛው በርባን (ወልደ አባ) መፈታቱ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያስታውስ ነው፡፡ በኃጢአቱ ምክንያት በሲኦል ውስጥ ታሥሮ የነበረው አዳምን በአዳኙ መሰቀል ምክንያት መድኃኒት አግኝቶ ነጻ መውጣቱን ያስታውሳል›› / ‹‹እስመ ተፈትሕዎቱ ለወልደ አባ ሙቁሕ ያዜክር ምሥጢራተ አምላካዊ ያሌቡ ግዕዛነ አዳም ዘኮነ ሙቁሐ ውስተ ሲኦል በእንተ ኃጢአቱ ወረከበ መድኃኒተ በስቅለተ መድኅን›› እንዲል፡፡  በዚያች የዕለተ ዓርብ ረፋድ ላይ ያስፈታውን የማያውቀው ይህ ወንበዴ ሰንሰለቱ ተፈትቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ #ጌታችን ግን ለመከራና ለመስቀል ተሠጠ፡፡ እውነቱንስ ለመናገር እኛ ክርስቲያኖች በርባን በመፈታቱ ላይ ላዩን ብናዝንም ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሎናል! ‹‹…በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት የሞቱን መድኃኒት …›› ብለው መሪጌታ ፍቅሩ ሣህሉ በበገናቸው ጨርሰውታል፡፡ ✍✍✍በዲ. ሔኖክ ኃይሌ @ይሄ ነው ሐበሻ!🗣🗣🗣 https://t.me/yihenewhabesha
Show all...
ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

ውድ እናቴ በኤሌክትሪክ ንዝረት የሞት ፍርድ የተፈረደበት ግለሰብ የመጨረሻ ኑዛዜ ከመሞቱ በፊት የመጨረሻ ቃሉ እንዲህ የሚል ነበር ውድ እናቴ ፡- ውድ እናቴ ህጉ አይናማ ቢሆን ፍትሀዊ ቢሆን ፣ጤናማ ቢሆን ማየት ቢችል ለህግ መከበር በፅናት የቆመ ቢሆን በዛሬዋ ቀን ይህንን የሞት ፅዋ አብረን እንጠጣ ነበር ግን ህጉ እንደዛ እይደለም ማየት የተሳነው ነው፡፡ ለዛ ነው በጋራ ለሰራነው ወንጀል ብቻዬን ብ…… ቻ…… ዬ…..ን የሞትን ፅዋ እንድጎነጭ የተፈረደብኝ፡፡ እማ ታስታወሻለሽ እንዴት እንደተጀመረ; የጓድኛየን ጣፋጭ ብስኩት ከረሜላ ስቀማ ስሰርቅ ታስታውሻለሽ አልቀጣሽኝም ነበር ፡፡ ልጄ ልጅ ስለሆነ ነው ነበር ያልሽኝ፡፡ እማ ታስታውሻለሽ እሰኪ የአባዬን ገንዘብ እንኳ ስሰርቅ አትናገሪብኝም ነበር፤፤ አስታወሸ እማ በ15 ዓመቴ ነበር ከጎረቤት ሳይክል ሰርቄ ጋራዥ ውስጥ ስደብቅ አይተሸ ለማንም አልነገርሽብኝም ነበር፡፡ ቆይቼ ስሸጠው እናም አብረሽኝ ነበርሽ ለማንም አልተናገርሽም ነበር፡፡ ምንም አላደርግሽም ነበር፡፡ ምን ይሄ ብቻ በትምህርት ቤት ሳጨስ እንዲሁም እፅ ስጠቀም ተይዤ ስታገድ you did nothing ምንም አላደረግሽም ነበር፡፡ ታስታውሻለሽ ሊቀጡኝ ሲሉ ከልክለሻቸዋል አሰቁመሻቸዋል፡፡ ልጄ አያደርግም ብለሻቸዋል፡፡ ታስታውሻለሽ አባቢ ከነሱ ጋር አብሮ ነው በማለት ከመምህራን ጎን ሲቆም አንቺ ግን መምህራን እንደተሳሳቱ ነበር የተናገርሽው፡፡ ምን ይሄ ብቻ እኔና ጓድኛዬ የከድርን ሱቅ ሰብረን ስንዘርፍ እሰኪ ለፖሊስ ደውለሽ ነበር? ሪፖርት አድርገሽ ነበር? አላደርግሽም? ታስታውሻለሽ ቤት ነበር የተደበቅኩት ፡፡ እናቴ ፈፅሞ ቀናውን ጎዳና አላሳየሽኝም! ፈፅሞ መልካሙን መንገድ አላስተማርሽኝም! ፈፅሞ ልጅ ነበርኩ ! ያው ትንሽ ልጅ! ቢነግሩኝ የምሰማ ሲቆጡኝ የማለቅስ! ትንሽ ልጅ ነበርኩ ያንቺ ቅጥ ያጣ ፍቅርና እንክብካቤ ያንቺ ቁጥጥርና ክትትል የሚያስፈልገኝ ትንሽ ልጅ ነበርኩ ትንሽ ልጅ አንቺ ግን ድርጊቴን ከልጅነቴም አብልጠሸ ወደድሽው አሰቃቂ የሞት ፍርድ ያበቃኝ፡፡ እና እናቴ አስታወሽ ያንቺ ቅጥ ያጣ ፍቅር ነው ለዚህ አሰቃቂ የሞት ፍርድ ያበቃኝ፡፡ በጋራ ለፈፀምነው ጥፋት ብቻዬን መቀጣቴ ህጉ አይፈቅድናማም ፍትሀዊም ስላልሆነ ነው፡፡ ውድ ልጅሽ! @ይሄ ነው ሐበሻ! 😃 https://t.me/yihenewhabesha😳
Show all...

ውድ እናቴ በኤሌክትሪክ ንዝረት የሞት ፍርድ የተፈረደበት ግለሰብ የመጨረሻ ኑዛዜ ከመሞቱ በፊት የመጨረሻ ቃሉ እንዲህ የሚል ነበር ውድ እናቴ ፡- ውድ እናቴ ህጉ አይናማ ቢሆን ፍትሀዊ ቢሆን ፣ጤናማ ቢሆን ማየት ቢችል ለህግ መከበር በፅናት የቆመ ቢሆን በዛሬዋ ቀን ይህንን የሞት ፅዋ አብረን እንጠጣ ነበር ግን ህጉ እንደዛ እይደለም ማየት የተሳነው ነው፡፡ ለዛ ነው በጋራ ለሰራነው ወንጀል ብቻዬን ብ…… ቻ…… ዬ…..ን የሞትን ፅዋ እንድጎነጭ የተፈረደብኝ፡፡ እማ ታስታወሻለሽ እንዴት እንደተጀመረ; የጓድኛየን ጣፋጭ ብስኩት ከረሜላ ስቀማ ስሰርቅ ታስታውሻለሽ አልቀጣሽኝም ነበር ፡፡ ልጄ ልጅ ስለሆነ ነው ነበር ያልሽኝ፡፡ እማ ታስታውሻለሽ እሰኪ የአባዬን ገንዘብ እንኳ ስሰርቅ አትናገሪብኝም ነበር፤፤ አስታወሸ እማ በ15 ዓመቴ ነበር ከጎረቤት ሳይክል ሰርቄ ጋራዥ ውስጥ ስደብቅ አይተሸ ለማንም አልነገርሽብኝም ነበር፡፡ ቆይቼ ስሸጠው እናም አብረሽኝ ነበርሽ ለማንም አልተናገርሽም ነበር፡፡ ምንም አላደርግሽም ነበር፡፡ ምን ይሄ ብቻ በትምህርት ቤት ሳጨስ እንዲሁም እፅ ስጠቀም ተይዤ ስታገድ you did nothing ምንም አላደረግሽም ነበር፡፡ ታስታውሻለሽ ሊቀጡኝ ሲሉ ከልክለሻቸዋል አሰቁመሻቸዋል፡፡ ልጄ አያደርግም ብለሻቸዋል፡፡ ታስታውሻለሽ አባቢ ከነሱ ጋር አብሮ ነው በማለት ከመምህራን ጎን ሲቆም አንቺ ግን መምህራን እንደተሳሳቱ ነበር የተናገርሽው፡፡ ምን ይሄ ብቻ እኔና ጓድኛዬ የከድርን ሱቅ ሰብረን ስንዘርፍ እሰኪ ለፖሊስ ደውለሽ ነበር? ሪፖርት አድርገሽ ነበር? አላደርግሽም? ታስታውሻለሽ ቤት ነበር የተደበቅኩት ፡፡ እናቴ ፈፅሞ ቀናውን ጎዳና አላሳየሽኝም! ፈፅሞ መልካሙን መንገድ አላስተማርሽኝም! ፈፅሞ ልጅ ነበርኩ ! ያው ትንሽ ልጅ! ቢነግሩኝ የምሰማ ሲቆጡኝ የማለቅስ! ትንሽ ልጅ ነበርኩ ያንቺ ቅጥ ያጣ ፍቅርና እንክብካቤ ያንቺ ቁጥጥርና ክትትል የሚያስፈልገኝ ትንሽ ልጅ ነበርኩ ትንሽ ልጅ አንቺ ግን ድርጊቴን ከልጅነቴም አብልጠሸ ወደድሽው አሰቃቂ የሞት ፍርድ ያበቃኝ፡፡ እና እናቴ አስታወሽ ያንቺ ቅጥ ያጣ ፍቅር ነው ለዚህ አሰቃቂ የሞት ፍርድ ያበቃኝ፡፡ በጋራ ለፈፀምነው ጥፋት ብቻዬን መቀጣቴ ህጉ አይፈቅድናማም ፍትሀዊም ስላልሆነ ነው፡፡ ውድ ልጅሽ!
Show all...
#የዛሬ_ምርጫ ደስታ #የምርጫ ጉዳይ ነው፡ ደስታ ከራስህ ጋር ተግባብተህ፡ ታርቀህ፡ተስማምተህ መኖር ነው፡ ደስታ የሚገኘው በትንሽ ነገሮች ውስጥ ነው፡ የ ደስታ ምንጪ የገዛ ህሊናክ ነው፡ ካኣንተ ደስታ #የምበልጥ ምንም ነገር የለም በዚህች ምድር፡ የ ደስታ ቁልፍ ያልው #በእጅህ ነው፡ ያቺ ቁልፍ ኮፒ ካደረካት፡ ከህሊና አረፍት፡ ጭንቀት፡ ከጥቅም፡ ጉዳት፡ ከ ስኬት፡ ውድቀት፡ ከብርሃን፡ጨለማ፡ ከማዳምጥ፡ መስማት፡ ማውራት፡( የሚታወራው ፡ የራስህ ነው፡ ነገር ግን ያሚትስማው፡ የለሌህ፡የማታውቀው፡ያንተ ያልሆነ) ነው። #መደሰት የምንጀሚረው በዙራያችን ያሉ ሰዎችን በልጠን ስንገኝ ነው፡ የሚል ኣመለካከት ያለ ሰው ለኣንድ ደቂቃ ሳይደሰት፡ የ ደስታ ባህሪ፡ ሕይወት፡እሴት ጣዕም፡ ምን እንደሆነ ሳያውቅ ይህችን ዓለም እንደሚሳናበታት ማወቀ ኣለበት፡ #ሁሉ_ግን_የምርጫ_ጉዳይ ነው። "ትንሽ ቀዳዳዎች ትልቅ መርከብ የማስመጥ ኣቅም ኣላቸው ይላሉ ኣዋቅዎች"       ትንንሽ ጭንቀቶች       ትንንሽ ኣለመረዳዳት/ኣለመግባባት       ትንንሽ የ ድህንነት ስጋቶች(  የ ህይወት፡  የውሳኔ....       ተደማምሮው ወደ ትልቅ የኣእምሮ ጤና ቀውስ ውስጥ ልከቱን ይችላሉ። ስለዚህ #የዛሬ_ምርጫህን_ወስን @ይሄ ነው ሐበሻ!😂😀😆😁😄😃 https://t.me/yihenewhabesha
Show all...
ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

“ #ለአፌ_ጠባቂ_አኖራለሁ! ” 🤙በዚህ ዘመን ከፍተኛ ገንዘብ የሚወጣው ለጥበቃ ነው ። አገሮች ፣ ቤቶች ፣ ግለሰቦች ይጠበቃሉ ። የሰለጠኑ ጠባቂዎች በመላው ዓለም እየፈሉ ነው ። በአገራችንም ሰዎችና ንብረቶች ጥበቃ ይደረግላቸዋል ። 👌ጥበቃው ከደኅንነት ካሜራዎች ፣ በሰለጠኑ ውሾች ጭምር ይከናወናል ። አንዳንድ ለጥበቃ የሚውሉ ውሾች በመቶ ሺህዎች ዶላር ወጪ ይደረግባቸዋል ። 🤗የተለያዩ የጥበቃ ኤጀንሲዎች በየጊዜው የሥራ አድማሳቸውን ያሰፋሉ ። እነዚህ ሁሉ ጠባቂዎች አራዊትን የሚከላከሉ አይደሉም ፣ ሰው ሰውን የሚከላከልበት መሆኑ ያሳዝናል ። ከክፉ ሰው የሚጠብቁን ሌሎች ሰዎች መሆናቸው ደግሞ ሁሉ ጠላት አለመሆኑን ያሳያል ። 🙊ይህ ብቻ አይደለም ማን መሆኑን ከማናውቀው ጠላት በየቀኑ እንዲጠብቁን እንከፍላለን ። ሰው ጠላቱን እንኳ ለማወቅ ይቸገራል ። እነዚህ ሁሉ ጠባቂዎች እውነተኛውን ጠላት ሰይጣንን የሚከላከሉ አይደሉም ። 🔴የማይታየውን ጠላት የመመለስ አቅም የላቸውም ። አሁንም ሌላ የሚያስደንቀው ነገር ይህ ሁሉ ጥበቃ እየተከናወነ ወንጀል ሊወገድ አለመቻሉ ነው ። ቅጣቶች ወይም የጥበቃ ጓዶች ሰውን መቀደስ አይችሉም ። 💋ስለዚህ ባላቸውን የሚጠብቁ ሚስቶች ፣ ሚስታቸው ላይ ሰላይ የሚልኩ ወንዶች አርፈው ቢቀመጡ መልካም ነው ። ሰው አገሩን ፣ ንብረቱን ፣ ራሱን ለመጠበቅ ጠባቂ ያኖራል ። ነቢዩ ዳዊት ግን “ #ለአፌ_ጠባቂ_አኖራለሁ ” ይላል ። እያለ ያለው ሁልጊዜ አልናገርም አይደለም። ኃጢአተኛ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ #ጠባቂ አኖራለሁ ይላል ። መንግሥታት ፣ ባለጠጎች ፣ ግለሰቦች ሊያቆሙት የሚገባው ጥበቃ ከንብረት ይልቅ አንደበታቸው ላይ ነው ። አንደበት የሚያፈርሰውን ያህል ጠላት ሊያፈርስ አይችልም ። ጠላት እንደውም የማስተሳሰር አቅም አለው ። የተለያዩ ሕዝቦች አንድ የሚሆኑት ጠላት ሲመጣ ነው ። ጠላት ባለውለታ የሚሆንበት ጊዜ አለ። 👂ጠላት “በተቃወመኝ ጊዜ” ይላል ። “ጊዜ” የሚለው ዘላለማዊ ጠላት ፣ ቋሚ ተቃውሞ እንደማይኖር ያሳያል ። ትላንት የሚቃወሙን ዛሬ የዓላማችን ተባባሪ ሆነዋል ። የሁልጊዜ ጠላት ፣ የሁልጊዜም ወዳጅ የለም ። ⏰ቀኖች የሚለዋወጡት ብቻቸውን አይደለም ፣ ሰውን ይዘው ነው ። መንፈሳዊ ሰው ግን በቀኑ ላይ ይኖራል እንጂ ቀኑ አይኖርበትም ። ራስን መግዛት ማለት ራስን መቆጠጠር ማለት ነው ። ራስን መግዛት በትልቁ የሚለካው አንደበት ላይ የበላይ በመሆን ነው ። አስቦ መናገር ካልተቻለ ፣ ተናግሮ ማሰብ ይመጣል ። ያ ደግሞ ጭንቀትን ይወልዳል ። ዛሬ ሰዎች ያላቸው ግጭት ቦምብ ተወራውረው ፣ ጥይት ተተኳኩሰው አይደለም ። #በክፉ ንግግር ተጎዳድተው ነው ። አንደበት ትንሽ የምትመስል ግን ትልቅ ጥፋት የምትሠራ ናት ። የኒውክለር ቁልፍ ትንሽ ናት ፣ ግን ዓለምን ልታጠፋ ትችላለች ። #አንደበት በማነስዋ አትናቅም ። አንድ ስፖርተኛ እጁ ላይ ቆልመም ያለ ነገር ነበረው ። ግን ጎበዝ ተጫዋች ነው ። አሰልጣኙ “እኛ የአካል ጉዳተኛ ጣቢያ አይደለንም” የሚል ምጸትና ሞራል ነኪ ንግግር ተናገረው ። ያ ጎበዝ ወጣት በዚያው ደቂቃ ገብቶ ራሱን አጠፋ ። #አንደበት ስንቱን እንደ ቀጨና ከሕይወት እንዳፈናቀለ የፈጠረው ጌታ ይቍጠረው ። “ #ለአፌ_ጠባቂ_አኖራለሁ ” @ይሄ ነው ሐበሻ!🙏🙊🙊🙊🙊🙊🙏 https://t.me/yihenewhabesha
Show all...
ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

#Dear_Men… Truth about being a man 1. You can be a great man even if you grew up without a father or a #good_relationship with your father 2. Your worth as a man is not determined by the money you have but #your_character 3. There is always a younger man watching you  and how you carry yourself. #Be_a_good example 4. Wisdom doesn't come with age, but by you #fearing_God and seeking wisdom 5. Ego is the man's greatest enemy. Once a #man has self-control over his ego he is ready for greatness 6. Men have emotions too.  Be responsible with your #emotions and you will be responsible with the emotions of others 7. The earlier a man finds his #vision_and_purpose in life the better for him 8. A man who #seeks to grow marries a woman who challenges him and grows with him 9. A #grown_man not only expects respect, he also respects others Be a real man today, God bless ✍𝐌𝐲𝐅𝐞𝐞𝐥𝐢𝐧𝐠𝐬  @ይሄ ነው ሐበሻ!🦻👺👿👨👩‍🦱 https://t.me/yihenewhabesha
Show all...
ይሄ ነው ሐበሻ!

@ይሄ ነው ሐበሻ!

01:15
Video unavailableShow in Telegram
@ይሄ ነው ሐበሻ!
Show all...