cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Zetseat Gospel Ministry

ኢየሱስ በድንገት ይመጣል።

Show more
Advertising posts
423
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"የተሻለውን ፈልጉ""ክርስትና ወሰን ያለው ህይወት እንጂ ልቅ ህይወት አይደለም" በዓለም ያለው የህይወት ስርዓት ፍላጎትን በማንኛውም መንገድ ማሟላት የሚል ነው፡፡ የሃገር አስተዳዳሪዎች ፍላጎትን ባሻው መንገድ የማግኘት ምኞትን ሌላን ሰው በማይጎዳ መንገድ እንዲሆን ህግን ያወጣል፡፡ይሁን እንጂ የዓለማዊ አእምሮ በህግ ተጠያቂ ሳይሆን ማጭበርበርን ተክኖታል፡፡ ይህ እንዳሻኝ ልሁን የሚል የአእምሮ ቀመር ህግን ሳይቀር ይሰብራል፡፡በክርስትና ግን ህይወት፣ ኑሮና የአእምሮ አስተሳሰብ እንደቃሉ እንጂ እንደ አማኞች ፍላጎት አይደለም፡፡ ሉቃስ:15-11ላይ ያለው የጠፋው ልጅ ከአባቱ ቤት ይልቅ ውጪ የተሻለ ኑሮ ያለ መስሎት ወጣ፡፡ የሚገርመው ከተሻለ ቦታ የተሻለ የሚመስል ግን ያልሆነ ቦታ ሄደ፡፡ የሄደበት ቦታ ከአባቱ ቤት እንደማይሻል በኪሳራ ህይወት አረጋገጠ ፡፡ በእኛ እና በጠፋው ልጅ መካከል ያለው ልዩነት እኛ አለምን በደንብ ማወቃችን ነው ፣ ስለዚህ ስለ አለም ቆንጆ መሆን አንሰበክም፡፡ አለም ተራ ሆና ተራ አድርጋን እንደነበር እናውቃለን፡፡ የህይወትን ትርጉም ግን በእግዚአብሔር በአባታችን ቤት አግኝተናል፡፡ መንግስት በህገወጥ የሰዎች ዝውውር በዋናነት ተጠያቂ ያደረገው ደላሎችን ነው፡፡ ዛሬም አማኞችን እንደ ቤቱ ስርአትና እንደ አባታቸው ድምፅ እንዳይኖሩ፣ የአባታቸውን ቤት አይመችም እያሉ በሚያባብሉ ደላሎች ላይ የቃሉን ብርሃን አውጀን እንጥላቸዋለን፡፡ ደላሎች ሁልጊዜ ያላችሁን እያሳነሱ ትላልቅ ያልተጨበጠና፣ ሊጨበጥ የማይችል ጉም አይነት ወሬ ያወራሉ፡፡ ልብ በሉ ሰይጣን ሄዋንን መቼም ልትሆነው የማትችለውን መለኮት ትሆኛለሽ ብሎ ሰበካት ፡፡ ከፍታን አውርቷት የማትወጣው ገደል ከተታት፡፡እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆኑ ከንቱ ንግግሮች በማንም ይነገሩ ሰውን አባብሎ ከመጣል የበለጠ የበለጠ ፋይዳ የለውም፡፡ እውነቱ ይሄ ነው፡፡አርነታቹ በእውነቱ ውስጥ አለ፡፡ ከአባታችሁ ቤት ውጪ የተሻለ ህይወት አይገኝም፡፡ያ የጠፋ ልጅ ከልጅ እውቀት የባርነት እውቀት ይዞ ቢመጣም በአባቱ ልብ ግን አሁንም ልጅ ነው፡፡አባቱ ያጠፋውን ሊተሳሰበው የሂሳብ ማሽን ይዞ አልጠበቀ ይልቁንም የተሻለውን እረዱለት አለ፡ የተሻለው በአባታቹ በእግዚአብሔር ቤት ነው ያለው፡፡ ፓስተር ሚኪ
Show all...
"በቃ" ኢዮ 42:1-2 2ኛ ተሰ 2:6 በነዚህ ሁለት ምዕራፎች ውስጥ የተከለከለና የማይከለከል አሰራርና ሃሳቦች እናገኛለን። በኢዮብ መፅሐፍ ምዕራፍ 42:2"ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ" ብሎ አሳብህም ይከለከል ዘንድ በማለት ይቀጥልና። አሳብህም ሲል ድርጊት ከሃሳብ እንደሚጀምር ያመለክታል። የሰው ልጅ የፈለገውን የማሰብ መብት አለው ወደ ድርጊት የመቀየሩ ነገር ግን አጠያያቂ ነው። እግዚአብሔር ካሰበ ግን አሳብን ለመተግበር የሚከለክለው ምንም ሃይል የለም። እግዚአብሔር ሳራን አሰባት ካለ በቃ ሳራ ልጅ መውለዷ እርግጥ ነው ማለት ነው። ዛሬ ይሄን ተናገርኩ በናንተ ህይወት ላይ እግዚአብሔር ያሰበው ያለ ማንም ከልካይ በህይወታችሁ ይፈፀማል። በ2ኛ ተሰ 2:6 ላይ ደግሞ የአመፅ ሚስጥርን የሚያስብ ካለ ይሄን አሳብ ተገልጦ ተፈፃሚ እንዳይሆን አሳብ ተከልክሏል። እግዚአብሔር በሚስጥር የሚታሰብብንን የአመፅ አሳብ ከልክሎ የእርሱን መልካም አሳብ ያለከልካይ በማድረጉ ዛሬ በህይወት መኖር ሆኖልናል። እግዚአብሔር አምላክ ካወቅነው ፣ካላወቅነው፣ከገባን፣ካልገባን፣ከተሰወረብን፣ከተገለጠው ነገር የጠላትን እቅድና አሳብ እየከለከለ የራሱን በጐ ፍቃድ ያለመከልከል እያደረገ ያኖረን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ለዚህ ነው መዝ 91:1 ላይ "በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል" ካደረ የጨለማው ሃይል ምንም ስም ቢኖረው እግዚአብሔር እየከለከለ ያኖርሃል። እግዚአብሔር ትልቁና ብቸኛውን ሃይል የያዘ አምላክ ነው። በዘፍጥረት 11 ያሰበውን ከማድረግ ወደኋላ የማይል አንድ ህዝብና አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦችን ከክፉ አሳባቸው የሚያቆማቸው፣የሚከለክላቸው ቢጠፋ ሃይልን ሁሉ ጠቅልሎ የያዘ እግዚአብሔር በክፉ አሳባቸው ላይ ወረደ። ይሄ ለናንተ ነው! ወደ ቀኝና ወደ ግራ አይታችሁ ያለከልካይ ያስጨነቃችሁ ቢኖር ከሰማይ የሃይል ባለቤት የሆነው አምላክ ከሰማይ ይወርዳል። የእግዚአብሔር "በቃ" ሁለት ፊደል አይደለም ታላቅ መከራንና ጥፋትን ፀጥ የሚያደርግበት ሃይል እንጂ። ፓስተር ሚኪ
Show all...
“የእግዚአብሔርም መልአክ ለእርሱ ተገልጦ፦ አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው።” መሳፍንት 6፥12 አብሮነቱ ከእኛ ጋር ይሁን!!!!
Show all...
ስንፍና ደሀ ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ፈጽሞ ከሕይወታችን ያስወግደው!!!
Show all...
እግዚአብሔር ያለመጠን ካደከመህ/ሽ ብርታቱን ልያሳይህ/ሽ ነው፤ ያለመጠን ዝቅ የሚያደርግህ/ሽ ከሆነ አቅሙን ልገልጥብህ/ሽ ነው፤ እግዚአብሔር እየገደለህ/ሽ ከሆነ ሕይወቱ በአንተ/በአንቺ ልሰራ ነው፤ ከጨከነብህ/ሽ፣ እየተከታተለ ካፈረሰህ/ሽ እናም አልለቅ ካለህ/ሽ ደስ ይበልህ/ሽ ረጅም ዘመን ልሰራብህ/ሽ ነው።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የእግዚአብሔር አብሮነት ከእኛ ጋር ሲኖር በእጦት ውስጥ አቅርቦት፣በበሽታ መሃል ፈውስ እንዲሁም በፈተና ውስጥ መፍትሄ ያገኘናል:: ይህ ሳምንት  በእግዚአብሔር አብሮነት የተባረከ ይሁን!!!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰኔ የብርሃን እና ልዩ ምሪት ከእግዚአብሔር ዘንድ የምንቀበልበት ወር ይሁንልን!!!
Show all...
አብዝተን ጮሄን ለዘገየብን ሁሉ የምንጎበኝበት እናም የምንታሰብበት መለኮታዊ ተራ ይድረሰን!!!
Show all...