cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ህልም

ውውውውውዶዶዶዶዶችችችችች ለመዝናናት ብቻ 😘😘😘😘😍🏆🏊🏊🏊🏄🏃🏃🏃🏂🏀🐰🐰🐰🐰🐰🐰🐰🍻🍻🍺🍦🍩🍩🍒🍑🍐🍇🌵🌰🌷🌷🌷🌷🌷😈😈😁😁😁😁😁

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
186
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስለ ናስሩዲን ይህን ያህል ከገለፅኩ ስለሱ ከሚያወሱ ፅሁፎች መሀል የሚከተለውን እነሆ ብያለሁ .... ናስሩዲን ሁልጊዜ ወደ ገበያ ለልመና ቢወጣም ሰዎች ግን ምፅዋት ከመቸር ይልቅ አንዲት የሽወዳ ብልሃትን እየተጠቀሙ ይሳለቁበት ነበር። ሁለት ሳንቲሞች ያቀርቡለታል። የአንደኛው ሳንቲም ዋጋ ከሌላኛው በአስር እጥፍ ይበልጣል። እርሱ ግን ሁሌ ያነሰ ዋጋ ያለውን ሳንቲም መርጦ ይቀበላል። በከተማው በጠቅላላ ይህ ወሬ ተነዛ። በየቀኑ የተለያዩ ሰዎች ወሬውን ለማረጋገጥ ይመጡና ሁለት ሳንቲሞች ያሳዩታል። ትንሽ ዋጋ ያላትን ይመርጣል። አንድ ቀን ታዲያ ቸርነት ያልተለየው ሀብታም ሰው ናስሩዲን ላይ የሚዘንበው ስላቅ ስላታከተው ወደ ገበያው ዳርቻ ወሰደውና እንዲህ አለው፡- “ሰዎች ሁለት ሳንቲም ሲያቀርቡልህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለውን ልትመርጥ ይገባል። ያን ካደረግህ አንደኛ ነገር ቶሎ ሀብታም ትሆናለህ። ሁለተኛ ሰዎችም አያሾፉብህም።” “ጥሩ ምክር ይመስላል” መለሰ ናስሩዲን። “ነገር ግን ትልቅ ዋጋ ያለውን ሣንቲም መምረጥ ከጀመርኩ ሰዎች ወደኔ መምጣት ያቆማሉ። ገንዘቡን የሚቸሩኝ እኮ ከእነሱ በባሰ ደደብ እንደሆንኩ ወይንም ከእኔ የተሻለ እውቀት እንዳላቸው ስለሚያስቡ ነው። ይህንን ብልሃት በመጠቀም ምን ያህል ብር እንዳጠራቀምኩ ታውቃለህ? ወዳጄ ሆይ ቂል መስለህ መታየት ያን ያህልም የከፋ ነገር የለውም። እንዲያውም የበለጠ ጠቢብ እየሆንክ ነውና።” Join 👉 @yenahelme
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 የመጨረሻው ክፍል😌 🖍...<<ለዛሬ የቀጠርኩህ በሲጋራ ማጨስና ጉዳቱ ዙሪያ ለጤናችን ፕሮግራም ካንተ ጋር ቃለ መጠይቅ ለመስራት ስለፈለግኩ ነው›› የመጨረሻዎቹን ቃላት በውል አላዳመጥኳቸውም፡፡ የተቀመጥኩበት ወንበር ወደ ውስጥ ይዞኝ የገባ መስሎኝ ከንፈሬን በጥርሴ እንደነከስኩ አይኖቼን በሀይል ጨፈንኳቸውና በዝምታዬ ውስጥ ራሴን ገደልኩ፡፡ ከተቀበርኩበት ድንገተኛ ሰመመን ስነቃ ሮማን በእጇ የያዘችውን የድምጽ መቅጃ እያሻሸች በድንጋጤ እየተመለከተችኝ ነበር፡፡ ‹‹ ደህና ነህ? ›› አለችኝ፡፡ ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነቅኩላት፡፡ ከዚያም እጄን ወደኪሴ ሰድጄ የተጨማተረ ሲጋራ መዘዝኩና አቀጣጠልኩ፡፡ ወደ ውስጥ የሳብኩት ጭስ ከአፌ እየወጣ አየር ላይ ተበታትኖ ወዲያና ወዲህ ሲቅበዘበዝ ሳይ እምባዬ መጣ፡፡ 🚬🚬🚬🚬 መድረሻውን የማያውቀው ጭስ የኔ ህይወት ተምሳሌት መሰለኝ፡፡🚬🚬 እንዲያውም ይህ የሲጋራ ጭስ መነሻውን ያውቃል፡፡ እኔ ግን መነሻና መድረሻዬን የማላውቅ፣ ከየት መጥቼ ወዴት እየሄድኩ እንደሆነ ያልተረዳሁ ምስኪን ሠው ነኝ፡፡ ሲጋራውን ጠላሁት፡፡ ጭሱን ማየት ቀፈፈኝ፡፡ መሬት ላይ ጣልኩትና በጫማዬ ደፈጠጥኩት፡፡ ኪሴ ውስጥ የነበረውን ሁሉ እያወጣሁ ስብርብር አደረግኩት፡፡ ነፍሴ ስትረጋጋ ታወቀኝ፡፡ በዛፎቹ መካከል እየተሽሎከለከ እኛ ወዳለንበት ጎጆ ቤት የሚገባው ነፋስ አዲሱን የህይወቴን ገጽ መግለጥ ጀመረ፡፡ ከዚህ በፊት የማላውቀው አዲስ ስሜት ውስጤ ገብቶ ቦታ ሲፈልግ አገኘሁት፡፡ ልቤን ሰጠሁት፡፡ በደስታ ተሞላሁ፡፡ መጮህ አማረኝ፡፡ ሮማን በሁኔታየ ግራ ተጋብታለች፡፡ ከአፏ ቃል ሳታወጣ በጭንቀት እየተነፈሰች የማደርገውንና የምሆነውን ትከታተላለች፡፡ የውስጤን ስሜት ሳዳምጥ ቆይቼ ዝቅ ባለ ድምጽ‹‹ አመሰግናለሁ ›› አልኳት፡፡ ከፀጉሯ ጋር በጣቷ እየተጫወተች በዝምታ ተመለከተችኝ፡፡ ‹‹ ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛዬ ጋ አለያዬሽኝ ›› ደነገጠች፡፡ ‹‹ ምን; ›› እንደምንም ከአፏ የወጣ ቃል ነው፡፡ ‹‹ ለረዥም ጊዜ እንደ ፍቅረኛዬ ስንከባከበው ከነበረው ሱስ ጋር ዛሬ አለያየሽኝ›› ከተቀመጠችበት ድንገት ተነስታ ተጠመጠመችብኝ፡፡ ሽቶዋ ልቤን አጠፋው፡፡ ከልቤ ጋር ፍርሃቴም አብሮ ጠፋ፡፡ ለካ የፍርሃት ቤቱ ልብ ነው! እንደተቃቀፍን የመጣው ይምጣ ብዬ ከንፈሯን ፍለጋ ስኳትን ያ- ክልፍልፍ አስተናጋጅ ዘው ብሎ ገባ፡፡ ‹‹ ጠራችሁኝ እንዴ? ›› እያለ፡፡ 📓ተፈፀመ📓 ሳቀርብላችሁ የነበርኩት Abena jç ነኝ:: JOIN & SHARE @Yenahelme CONTACT US @Gtamimoti 💞ህልም❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
☝️☝️ ____ ምን ያህል ድሆች ነን!?___ አንድ ባለጸጋ አባት ልጁ ድሆች ምን የመሰለ ኑሮ ይኖሩ እንደሁ ያውቅ ዘንድ ወደ ድሀው ገበሬ ሰፈር ወሰደው፡፡ በአንድ የድሃ ገበሬ ቤትም አንድ ቀንን አሳለፈው ወደቤታቸው ተመለሱ፡፡ ወደ ቤታቸው እየተመለሱ በመንገድ ላይ ሳሉም አባት ልጁን ምን ያህል ድሃ እንደሆኑና በድህነት እንደሚኖሩ አየህ አደል!? ምን ተማርክ? ሲል ጠየቀው፡፡ ልጅ ያየውንና የተማረውን እንዲ ሲል ገለጸው፡፡ “እኛ እንድ ውሻ አለን እነሱ ግን አራት ውሾች አሏቸው፤ እኛ የታጠረ የመዋኛ ገንዳ አለን እንሱ ግን ወንዞችና ሐይቆች አሏቸው፤ እኛ ማታ ማታ የምንጠቀምበት አምፖል አለን እነሱ ግን ሰማይ ሙሉ ከዋከብት አሏቸው፤ እኛ ምግብ ገዝተን እናገኛለን እንሱ ግን ከማሳቸው ያበቅላሉ፤ እኛ እራሳችንን ለመከላከል አጥር ሰርተናል እነሱ ግን አጥር ሳይሆን ወዳጆችና ጓደኞች አሏቸው፤እኛ ኢንሳይክሎፒዲያ አለን እነሱ ግን መጽሐፍ ቅዱስ አላቸው፡፡ እናም አባየ ከኛ በጣም የላቁ ባለጸጎች ናቸው፡፡ እኛ ምን ያህል ድሀዎች እንደሆንን ስላሳየኸኝ አመሰግናለሁ” አለው ይባላል፡፡ ባለጸጎች እንድንሆን የሚያደርገን የሰበሰብነው ቁሳቁስ አይደለም የሚለውን መልዕክት ይነግረናል፡፡ በመንፈስ ድሃ ሁኖ ቁስን ቢሰበስቡት ከሸክም ውጭ ምን ፋይዳ አለውና፡፡ ገንዘብ ብቻውን ባለጸጋ አያደርግንም፡፡ በገንዘቡ አማካኝነት የምንፈጥረው እሴት ጭምር እንጅ፡፡ ስለዚህ በቁሶች የተዋጥን ሰዎች ከሌሎች ጋር ስንኖር ምን አትርፎልናል!? እያለንስ ምን ያህል ድሆች ሁነናል!? እሚለውን እንድናስብ ያስታውሰናል፡፡ Source: from Interesting Facts "How we are Poor?" Join and invite your friends 👉@yenahelme
Show all...
ባክኖ እንደመመለስ፣ ቆሞ እንደመጠበቅ ከጣፋጭ ፍቅር ላይ፣ አፍሮ እንደመላቀቅ🙈 የደስታን ጫፍ ቀምሶ፣ እንደመላስ ሀዘን ሰው እንደመለመን አጥቶ እንደማላዘን ታበሳጭኛለሽ ።።።።።።።።።።።። የጅል ማስታወቂያ እንደመደጋገም ዓመታት ታክሞ እንደማላገገም ሰው እየቀጠሩ ፈልጎ እንደማርፈድ አብሮ አደጎች ሆኖ አብሮ እንደመሰደድ ታበሳጭኛለሽ ።።።።።።።።።።። እየሔዱ እንደመቆም፣ እያሰቡ እንደመርሳት እየፃፉ እያጠፉ፣ እያወቁ እንደመሳሳት ሲደወል አንዳለማንሳት ታበሳጭኛለሽ ።።።።።።።።።።።። ቃለአብ @yenahelme @yenahelme @yenahelme
Show all...
😢በቃኝ😔 ትመጫለሽ ብየ አወ ጠብቄአለሁ እድሜየን በመላ ላንቺ ሰውቻለሁ አሁን ግን ሰለቸኝ ብቻየን መኖሩ ልቤም ሌላ አይቶ ተከፈተ በሩ እናም ሰላም ሁኚ ያንቺ ነገር በቃኝ ላትመለሽ ነገር መጠበቅ ሰለቸኝ share Share to your friends @yenahelme @gtamimoti
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 ክፍል6⃣ 🖍...አለባበሷ እንደነገሩ ነው፡፡ ‹‹ከስራ ቦታ በቀጥታ ነው እንዴ የመጣሽው?›› አልኳት ደግማ ስለመዘግየት እንዳታወራኝ አቅጣጫ ለማስቀየር፡፡ ቀስ በቀስ ፍርሃቴ እየጠፋ መጥቷል፡፡ ‹‹አዎን ከዚያው መምጣቴ ነው›› አለች አረማመዷን ከኔ ፍጥነት ጋር ለማስተካከል እየሞከረች፡፡ ዝናቡ ማንጠባጠብ ጀምሯል፡፡ መናፈሻ ውስጥ ካሉት ትንንሽ ጎጆ ቤቶች መካከል አንዱን መርጠን ገባን፡፡ ወዲያው የሆነ ክልፍልፍ አስተናጋጅ እየተንደረደረ መጥቶ የምንፈልገውን ጠየቀን፡፡ ፈጥኖ መምጣቱ አበሳጭቶኛል፡፡ ‹‹ቡና!›› አልኩት በቁጣ፡፡ የኔን ትዕዛዝ ተቀብሎ በመጣበት አኳኋን እየተክለፈለፈ ተመልሶ ሄደ፡፡ ሳቄ መጣ፡፡ ከጥድፊያው የተነሳ እሷን ሳይታዘዛት ነው የሄደው፡፡ እጄን ላጨበጭብ ስዘጋጅ ሮማን ድንገተኛ ወሬ ጀመረች፡፡ ‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ.....›› ከማለቷ አስተናጋጁ ተመልሶ መጣ፡፡ ‹‹ለእርስዎስ ምን ላምጣልዎት እመቤቴ?›› ሲል ጠየቃት እየተቅለሰለሰ፡፡ ‹እርስዎ› ስላላት ይሁን ወይም ንግግሯን ስላቋረጣት እንጃ ቆጣ ብላ ‹‹ለኔም ቡና!›› አለችው፡፡ እየሮጠ ወጣ፡፡ ሲሮጥ ድንጋይ አደናቅፎት ሊወድቅ ነበረ፡፡ እንደሰካራም ተንገዳግዶ ለጥቂት ተረፈ፡፡ እሱ እንደወጣ ሮማን ንግግሯን ቀጠለች፡፡ ‹‹ምን መሰለህ? ለዛሬ የቀጠርኩህ...እ...›› ጭኗ ላይ ያስቀመጠችውን ቦርሳ መደባበስ ያዘች፡፡ ልቤ በድንጋጤ መምታት ጀምሯል፡፡ አፈቅርሃለው የምትለዋን ቃል ለመስማት መቁነጥነጥ ያዝኩ፡፡ ግን ምንድነው የምመልስላት? እኔም አፈቅርሻለሁ ልበላት? ይሄ እንኳን አይሆንም፡፡ ገና በአንድ ቀን እንደዛ ብላት ትንቀኛለች፡፡ በቃ ላስብበት እላታለሁ፡፡ ወይኔ ጉዴ! ምንድነው የሚያቃዠኝ? እኔ በሃሳብ ስዳክር ሮማን ጉሮሮዋን አፅድታ የጀመረችውን ንግግር ጨረሰችው፡፡ ‹‹ያው ለዛሬ የቀጠርኩህ..... ይቀጥላል.... አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው፡፡የ👍 ምልክት በመጫን አበረታቱን። JOIN & SHARE @Yenahelme CONTACT US @Gtamimoti 💞ህልም❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
ስለ ናስሩዲን ይህን ያህል ከገለፅኩ ስለሱ ከሚያወሱ ፅሁፎች መሀል የሚከተለውን እነሆ ብያለሁ .... ናስሩዲን ሁልጊዜ ወደ ገበያ ለልመና ቢወጣም ሰዎች ግን ምፅዋት ከመቸር ይልቅ አንዲት የሽወዳ ብልሃትን እየተጠቀሙ ይሳለቁበት ነበር። ሁለት ሳንቲሞች ያቀርቡለታል። የአንደኛው ሳንቲም ዋጋ ከሌላኛው በአስር እጥፍ ይበልጣል። እርሱ ግን ሁሌ ያነሰ ዋጋ ያለውን ሳንቲም መርጦ ይቀበላል። በከተማው በጠቅላላ ይህ ወሬ ተነዛ። በየቀኑ የተለያዩ ሰዎች ወሬውን ለማረጋገጥ ይመጡና ሁለት ሳንቲሞች ያሳዩታል። ትንሽ ዋጋ ያላትን ይመርጣል። አንድ ቀን ታዲያ ቸርነት ያልተለየው ሀብታም ሰው ናስሩዲን ላይ የሚዘንበው ስላቅ ስላታከተው ወደ ገበያው ዳርቻ ወሰደውና እንዲህ አለው፡- “ሰዎች ሁለት ሳንቲም ሲያቀርቡልህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለውን ልትመርጥ ይገባል። ያን ካደረግህ አንደኛ ነገር ቶሎ ሀብታም ትሆናለህ። ሁለተኛ ሰዎችም አያሾፉብህም።” “ጥሩ ምክር ይመስላል” መለሰ ናስሩዲን። “ነገር ግን ትልቅ ዋጋ ያለውን ሣንቲም መምረጥ ከጀመርኩ ሰዎች ወደኔ መምጣት ያቆማሉ። ገንዘቡን የሚቸሩኝ እኮ ከእነሱ በባሰ ደደብ እንደሆንኩ ወይንም ከእኔ የተሻለ እውቀት እንዳላቸው ስለሚያስቡ ነው። ይህንን ብልሃት በመጠቀም ምን ያህል ብር እንዳጠራቀምኩ ታውቃለህ? ወዳጄ ሆይ ቂል መስለህ መታየት ያን ያህልም የከፋ ነገር የለውም። እንዲያውም የበለጠ ጠቢብ እየሆንክ ነውና።” Join 👉 @yenahelme
Show all...
💗ሮ💗ማ💗ን💗 ክፍል5⃣ 🖍...ድንጋጤዬን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ‹‹ ነገ .. ነገ .. ነገ .. እ .. ነገ ስራ የለኝም! ›› አልኳት፡፡ ግን ውሸቴን ነበር፡፡ አያቴን ወደክሊኒክ ለመውሰድ ቀጠሮ ይዤ ነበር፡፡ ‹‹ እንግዲያማ መገናኘት እንችላለን ማለት ነው ›› አለች ሮማን፡፡ ‹‹ እ .. አዎ .. እንችላለን ››አልኩ ፈጠን ብዬ ሀሳቧን እንዳትቀይር የፈራሁ ይመስል፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ሮማን ከመቀመጫዋ ተነስታ እጄን ጨበጠችኝና የጠጣንበትን ሂሳብ ከፍላ የቀጠሮውን ቦታ ነግራኝ ተሰናብታኝ ሄደች፡፡ የካፌው ተሰተናጋጆች ሮማንን ከኋላዋ በአይኖቻቸው አጀቧት፡፡ እንደዚያ አፍጥጠው ሲያዩዋት ተበሳጨሁ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ጉሮሮአቸውን ፈጥርቄ ከግድግዳው ጋር ባጋጫቸው ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ቅናት ወረረኝ፡፡ ፍቅረኛዬ ላይ አይናቸውን ማፍጠጣቸው አንገበገበኝ፡፡ ሲጋራዬን እያወጣሁ አፌ ላይ መጣድ ጀመርኩ፡፡ ጭሱ በግንባሬ በኩል በቀስታ እየተመመ የካፌውን ጣሪያ ለመንካት ጉዞ ሲጀምር ቀና እያልኩ እመለከተዋለሁ እኔን ይመስለኛል፡፡ የማላውቀውን፣ መቼ እንደጠፋብኝ ያልተገነዘብኩትን ህልም እንደምፈልገው፡፡ በሃሳብ ውስጥ ስናውዝ ድንገት የሞባይል ስልኬ ጠራ፡፡ ደዋዩ ጓደኛዬ ዩሐንስ ነው፡፡ አለቃዬ ሲፈልገኝ እንደነበር ሊነግረኝ ነው የደወለው፡፡ ‹‹እሱን ተወው ባክህ! ይልቅ አንድ ወሬ ልንገርህ›› አልኩት፡፡ ‹‹ምንድነው የምትነግረኝ....ዝም ብለህ ለሰውየው ብትደውልለት ይሻላል›› ሲል መለሰልኝ፡፡ ‹‹በቃ እሺ እደውልለታለሁ... ዛሬ ምን እንደተፈጠረ ልንገርህ?›› ‹‹ምንድነው ምን ተፈጠረ?›› ‹‹ፍቅረኛዬን አገኘኋት!›› ‹‹አገኘኋት?›› ‹‹አዎ አገኘኋት.. ወይም አገኘችኝ! ቆይ አስተዋውቅሃለው... ብታያት በቃ ልዕልት ናት! Princess›› የካፌው ተስተናጋጆች ዘወር ዘወር እያሉ ተመለከቱኝ፡፡ ሳላውቀው በጣም እየጮህኩ ነበር ለካ፡፡ **** ‹‹ዘግይቻለሁ እንዴ ግን?›› ጠየቀችኝ ሮማን ጎን ለጎን ሆነን ወደመናፈሻው እየገባን ሳለን፡፡ ምን ነካት ልጅቷ ስንት ጊዜ ነው የምትጠይቀኝ? መዘግየት ብርቅ መሰላት እንዴ? ‹‹እንዲያውም ፈጥነሽ ነው የመጣሽው›› ስል መለስኩላት ለአፍታ በአይኖቼ እየቃኘኋት፡፡ አለባበሷ እንደነገሩ ነው፡፡ ይቀጥላል.......... አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው፡፡የ👍 ምልክት በመጫን አበረታቱን። JOIN & SHARE @Yenahelme CONTACT US @gtamimoti 💞ህልም❤ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
Show all...
ድሮ ህፃን እያለው ነው እና አንድ ጊዜ ፍሪ ፔሬድ ላይ ክላስ ተማሪዎች በ ወሬ ክፍሉን ብጥብጥ ስናደርግ አንድ ዘበኛ ሰማና ወደ ክላሳችን መጣ :- 💂ዘበኛው :- ክፍለ ጊዜያቹ ምንድነው? 👨‍🏫ተማሪ :- ፍሪ ነን 💂‍♀ዘበኛው :- በሉ የ ፕሪ ደብተራቹን አውጡና አኒቡ 👨‍🏫ተማሪ :- kakaka...😂😂 💂ዘበኛው :- ማነው የሳቄው? ተማሪ :- ክላሱ 💂ዘበኛው :- በል ክላሱ ደብተሪህን ዪዜ ዉጣ!! ተማሪ :- kakakakaka....😂.........😂....... ዝም ብሎ ማለፍ የለም 👍 🤣Share to your friends @yenahelme @gtamimoti
Show all...
ሰላም እንዴት ናቹ ሳምንቱ እንዴት አለፈ? *ዛሬ ቅዳሜ ገራሚ ገራሚ ዝግጅቶች አሉን ጠብቁን...Joni joni..ማለት እንዳይረሳ @yenahelme @gtamimoti
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.