en
Feedback
E tech

E tech

Open in Telegram

Some tech | Innovating tech solutions to elevate your business. @WISEgeneration

Show more
1 112
Subscribers
No data24 hours
-117 days
-2930 days
Posts Archive
E tech
1 112
"You are the sum total of the choices and decisions you make every day." - Dr Myles Munroe

E tech
1 112
"Just like a tree trapped in a seed, your destiny is not ahead of you but trapped within you." - Dr Myles Munroe

E tech
1 112
"How you see the world is determined by how you see yourself.It is more important to change yourself than to change others- change yourself" - Dr Myles Munroe

E tech
1 112
photo content
+3

E tech
1 112
Maturity is when you are at peace with your self
+9
Maturity is when you are at peace with your self

E tech
1 112
photo content

E tech
1 112
photo content

E tech
1 112
photo content

E tech
1 112
"Greatness is not a pursuit but a result of SERVING others. Serve your way to Greatness by making others greater than yourself." - Dr Myles Munroe Make ethiopia great again @megaygra

E tech
1 112
በአሰላ ከተማ ሰፊ የመኖረያ ቤት አድራ።ሻ : ቀበሌ 07 ስፋት : 400 ካሬ ዋጋዉ : 1.6M 0953384141 0923303057 የደወሉልን
+2
በአሰላ ከተማ ሰፊ የመኖረያ ቤት አድራ።ሻ : ቀበሌ 07 ስፋት : 400 ካሬ ዋጋዉ : 1.6M 0953384141 0923303057 የደወሉልን

E tech
1 112
ኔልሰን_ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ # የህግ_ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው። ስሙም ፒተር ይባላል። • አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ ማንዴላም "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ። • በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ • " ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ 'ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖር የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ሲጠይቀው • ማንዴላም"ገንዘቡን እወስደዋለሁ" …ብሎ መለሰለት። ፕሮፌሰሩም በድል አድራጊነት "አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ እወስድ ነበር" ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ "ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው። በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ • "ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ረስተኸዋል" ብሎት እርፍ ……… ምንጭ፦ Addis Admas newspaper @megaygra

E tech
1 112
ፈጣሪ ኢትዩጲያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ

E tech
1 112
አትተኩስ። ቼ ጉቬራ ነኝ። ከመሞቴ በላይ ቆሜ እጠቅማችኋለሁ። ] . . . . . . ሰኔ 14፣1928(እ.ኤ.አ) በአርጀንቲና ተወለደ። ወላጆቹ ያወጡለት ስም ኸርኔስቶ ጉቬራ ነው። የወደዱት ኩባዎች ግን ስሙ መሃል <ቼ> ብለው ጨመሩለት። <ቼ> ማለት የእኛ ማለት ነው። ቼ ጉቬራ ለብዙዎች ጀግና ለሌሎች ደግሞ የክፉ ምሳሌ ነው። የብዙ ወጣቶች ጣኦት፣ የብዙ አብዮተኞች መንገድ - ቼ ጉቬራ! ቤተሰቦቹ በሃብት የናጠጡ ባይሆንም ያላቸው የሚባሉ አይነት ናቸው። ቼ ግና በማለዳው ጭቁን ማህበረሰብ፣ ተበዝባዢ ሰርቶ አደር ወደሚለው የግራ ዘመም ርዕዮተ ዓለም አጋደለ። በ1948(እ.ኤ.አ) ወደ ቦነስ አይረስ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በህክምና ት/ት ዶክትሯል። ከዳር እስከ ዳር ድህነትን እስኪበቃው አይቷል። እንዲህም አለ፦ <<እንዲህ ከዳር ዳር ለተንሰራፋው ጭቆና እና ድህነት መፍትሄው ሁለትና ሁለት ነው - የትጥቅ ትግልና ኮሚዩኒዝም!>> ዶክተር ቼ ጉቬራ ተብሏል። ቼ ግን ብዙም ሳይሰነብት የዱክትርና ስራውን ትቶ ፣ መርፌውን አስቀምጦ፣ ልቡ ላይ ያበበውን አብዮተኝነት አቅፎ ወደ ኩባ አቀና። ዶክተሩ አብዮተኛ ሆነ። ካስትሮ የባስቲታን መንግስት ሲታገል፣ ቼ እኔም አለሁበት ብሎ ገባ። ዓለም ሁሉ ዜጋዬ፣ ጭቁን ሁሉ ወገኔ ብሎ ከኩባዊያኑ ጋር ተሰልፏል። ጠዋት ሲተኩስ ውሎ ከሰዓት በህክምና ሞያው በጦርነቱ ለተጎዱት ደርሷል። በዚህም በ1956(እ.ኤ.አ) የባስቲታን መንግስት በቂጡ ቁጭ አደረጉት። ቼ በዓለም ላይ ያሉ ጭቁኖችን ያፈነፍን ነበር። ኮንጎም ደርሷል፣ ቦሊቪያም አቅንቷል፣ ለጭቁኖች ዘብ ቁሟል። ነፍጥን አንግቦ ለነፍጠኛም ወኔ ሆኗል። ቼ 1966(እ.ኤ.አ) ወደ ቦሊቪያ ሲያቀና በቦሊቪያ ያለው መንግስት ጨቋኝ መሆኑን ተረድቷል። ከስልጣን መውረድ አለበት፣ ሊያወርዱት የሚጥሩትም መታገዝ አለባቸው ብሎ የአብዮት ዘፈኑን ዘፈነ። በቦሊቪያም ከታጣቂዎቹ ጋር ታጠቀ። ጥያቄአችሁ ጥያቄዬ ነው አለ። ግን በቦሊቪያ አመትም ሳይቆይ በሲ.አይ.ኤ በሚታገዙ የቦሊቪያ ወታደሮች ተያዘ። በተያዘ በቀጣዩ ቀን ተገደለ። የሰው ፍቅር ያለው፣ የጭቁኖች እምባ አባሽ ፣ ቼ በ39 ዓመቱ ምድር ከዳችው። ነፃነት ሞተ። << ጠመንጃዬን ሌላ ሰው አንስቶ ትግሉን እስከቀጠለ ድረስ ለሞቴ ግድ የለኝ። >> እንዲህም አለ፦ <<አትተኩሱ። ቼ ጉቬራ ነኝ። ከመሞቴ በላይ ቆሜ እጠቅማችኋለሁ። ብሎም ነበር። እሱነቱ እንቅልፍ የነሳቸው የ ሲ.አይ.ኤ ሰዎች ለሞቱ ቸኮሉ። ተያዘ። ተገደለም። ሬሳውን ሚዲያዎች እንዲያዩትም፣ ፎቶ እንዲያነሱም ተደረገ። ቼ ሞተ። ስለ ቼ ጋሽ ስብሃት እንዲህ አለ፦ << የቼ ጉቬራ የህይወት ታሪክ እና አሟሟት ብዙ ሃሳቦችን ይቀሰቅሳሉ። ለምሳሌ የህንዱ ማህተመ ጋንዲ፣ የግብፁ ገማል አብዱል ናስር፣ የቻይናው ማኦ ዜ ቱንግ፣ የቬትናሙ ሆቺ ሚኒ፣ የሰሜን ኮርያው ኪም ኢል ሱንግ፣ የኬንያው ጆሞ ኬንያታ፣. . . እነዚህና ሌሎችም ጀግኖች ነፃ አውጭዎች ይህንን ክ/ዘመን አስውበውታል። ነገር ግን ሁሉም ተዋግተው ነፃ ያወጡት የገዛ ሃገራቸውን ሰው ነው። ጀግና ለእናት ሃገሩ ሲዋጋ ይሞታል። ቼ ግን ለሰው ሃገር ሲዋጋ ነው የሞተው። >> ቼ ከጀግንነትም በላይ ነበር። @sslisten "share"

E tech
1 112
የትኩረትህና የስሜትህ ግንኙነት እስቲ ስለቅርብ ወዳጆችህ አስብ፣ አንዳንዶቹ ብዙም አይፈልጉህም፣ ሌሎቹ አይተውህ አይጠግቡም ፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ አይነት ሰዎች በማን ላይ ታተኩራህ፡፡ ይህ ትኩረትህ ስሜትህን ይወስናል፡፡ በአንድ ጎኑ ባለፉት አመታቶችህ ያስመዘገብካቸውን ስኬቶች ስታሰላስል ለወደፊቱ የመነሳሳትና የእችላለሁ ስሜት ያሳድርብሃል፡፡ በተቃራው ደግሞ ያልተሳኩልህን እየመረጥክ እነዚያ ላይ ስታተኩር ወደፊት ያለመቀጠል፣ የውድቀትና የሽንፈት ስሜት ይጫጫንሃል፡፡ እስቲ በሰውነትህ፣ ወይም በራስህ ላይ ጎዶሎ እንደሆነ የምታስበውን ነገር አሰላስል፣ መሸማቀቅ፣ ሃፍረትና የመሳሰሉት ስሜቶች ይወርሱሃል፡፡ በተቃራኒው ያህን ሙሉ ነገር ስታሰላስል ቀና ብሎ መሄድና ድፍረት ይሞላሃል፡፡ ልዩነቱ ያለው ትኩረትህ ላይ ነው፡፡ በማንኛውም ወቅት ላይ ያለህ ስሜት የወቅቱን የኑሮ ጉልበት ይወስናል፡፡ ይህንን ጉልበትህን የሚወስነውን ስሜትህን የሚቆጣጠረው ደግሞ ትኩረትህ ስለሆነ ትኩረትህን በመለወጥ ስሜትህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ስሜትህን በዚህ መልኩ መቆጣጠር ስትጀምር እንዲሁ ካለምክንያት የሚሰማህ የዝለት ስሜት የት እንደገባ ሳታውቀው ይተንናል፡፡ ትምህርቶቼን በ YouTube የመከታተል ምርጫ አላችሁ:: Subscribe፡- https://m.youtube.com/user/naeleyob623የትኩረትህና የስሜትህ ግንኙነት እስቲ ስለቅርብ ወዳጆችህ አስብ፣ አንዳንዶቹ ብዙም አይፈልጉህም፣ ሌሎቹ አይተውህ አይጠግቡም ፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ አይነት ሰዎች በማን ላይ ታተኩራህ፡፡ ይህ ትኩረትህ ስሜትህን ይወስናል፡፡ በአንድ ጎኑ ባለፉት አመታቶችህ ያስመዘገብካቸውን ስኬቶች ስታሰላስል ለወደፊቱ የመነሳሳትና የእችላለሁ ስሜት ያሳድርብሃል፡፡ በተቃራው ደግሞ ያልተሳኩልህን እየመረጥክ እነዚያ ላይ ስታተኩር ወደፊት ያለመቀጠል፣ የውድቀትና የሽንፈት ስሜት ይጫጫንሃል፡፡ እስቲ በሰውነትህ፣ ወይም በራስህ ላይ ጎዶሎ እንደሆነ የምታስበውን ነገር አሰላስል፣ መሸማቀቅ፣ ሃፍረትና የመሳሰሉት ስሜቶች ይወርሱሃል፡፡ በተቃራኒው ያህን ሙሉ ነገር ስታሰላስል ቀና ብሎ መሄድና ድፍረት ይሞላሃል፡፡ ልዩነቱ ያለው ትኩረትህ ላይ ነው፡፡ በማንኛውም ወቅት ላይ ያለህ ስሜት የወቅቱን የኑሮ ጉልበት ይወስናል፡፡ ይህንን ጉልበትህን የሚወስነውን ስሜትህን የሚቆጣጠረው ደግሞ ትኩረትህ ስለሆነ ትኩረትህን በመለወጥ ስሜትህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ስሜትህን በዚህ መልኩ መቆጣጠር ስትጀምር እንዲሁ ካለምክንያት የሚሰማህ የዝለት ስሜት የት እንደገባ ሳታውቀው ይተንናል፡፡ ትምህርቶቼን በ YouTube የመከታተል ምርጫ አላችሁ:: Make Ethiopia great again @megaygra

E tech
1 112

E tech
1 112
የምታከብረውን ነገር ታቆየዋለህ አጭርና ግልጽ አውነታ፡- የምታከብረውን ትስበዋለህ፣ የማታከብረውን ትገፋዋል! ያላከበርከውንና ዋጋ ያልሰጠኸውን ሰው በሙሉ ቀስ በቀስ ታጣዋለህ፡፡ ይህ ሰው ምንም ያህል የቅርብህ ቢሆንና የትም እንደማይሄድ ብታስብም ተገቢውን ክብር ካልሰጠኸው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ያንን ሰው ማጣትህ አይቀርም፡፡ ያላከበርከውንና ዋጋ ያልሰጠኸውን ንብረት በሙሉ ቀስ በቀስ ታጣዋለህ፡፡ በእጅህ ላለው ንብረት ተገቢውን አክብሮትና አያያዝ ካላዳበርክ ንብረቱ ቀስ በቀስ ከእጅ መውታቱ አይቀርም፡፡ ይህንኑ እውነት ከግልህ ጤንነት አንጻር ተግባራዊ ስታደርገው፣ ዋጋ ያልሰጠኸውንና በሚገባ ያልተንከባከብከውን አካላዊም ሆነ የአእምሮ ጤንነት ቀስ በቀስ ማጣትህ እንደማይቀር አትዘንጋ፡፡ ዛሬ ዋጋ ስለምትሰጣቸው ነገሮች በሙሉ በማሰብ ተገቢውን እንክብካቤና ትኩረት መስጠትህን እርግጠኛ ሁን፡፡ በእጅህ ስላሉና ሁል ጊዜ ስለምታገኛቸው ብቻ የትም እንማይሄዱ በማሰብ ችላ ከማለት ተጠበቅ፡፡ አለዚያ የምትባንነው ከእጅህ ከተወሰዱና ጊዜው ካለፈ በኋላ ነው፡፡

E tech
1 112
የጸጸት ተጽእኖ ጸጸትን ተገቢ ባልሆነ መልኩና ተገቢ ላልሆነ የጊዜ ርቀት ማሰላሰል በአእምሮና በአካል ላይ ይህ ነው የማይባል ተጽእኖ ያስከትላል፡፡ ራስን መውቀስና ወደ ሕይወት አቅጣጫ እንደገና በጉጉት ለመመለስ ያለመፈለግ ሰሜቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ጸጸትን ደግሞና ደጋግሞ ማብላላት ለድብርት (Depression) ከማጋለጡም በላይ የተለያዩ የአእምሮ ቀውሶች ያስከትላል፡፡ የጠለቀ ጸጸት በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ንጥረ-ነገሮች (Hormons) የማቃወስ ብቃት አለው፡፡ ጸጸት የሰውነትን የመከላከል ሂደትም (Immune system) የማዛባት አሉታዊ ተጽእኖ አለው፡፡ ጸጸትን ማስወገድ ያልቻሉ ሰዎች በሕይወታቸው አስቸጋሪ ገጠመኞችን የመያዝና የመቋቋም አቅማቸው ደካማ ስለሚሆን ለወራት፣ ለአመታትና አልፎም እስከ መጨረሻው የመጨናነቅን ዝንባሌ ይዘው ይከርማሉ፡፡ በሃርቫርድ የጽሁፍ ገጾች ላይ (Harvard Newsletter) ላይ የተጻፈ አንድ ታሪክ ለዚህ ምሳሌ ሊሆነን ችላል፡፡ አንድ በእንግሊዝ (Liverpool) ውስጥ ይኖር የነበረ ችግረኛ ሰው በየጊዜው ለረጅም አመታት አንድ አይነትን ቁጥር ሎተሪ በመቁረጥ ይታወቅ ነበር፡፡ ይህ ሰው አንዲት ቀን ብቻ ያንን ለአመታት ሲቆርጥ የነበረውን ቁጥር ከመቁረጥ ዘንግቶ ሌላ ቁጥር ያለው ሎተሪ ሲቆርጥ ያች ለረጅም አመታት የሞከራት ቁጥር የእለቱ በሚልየን ፓውንዶች የሚቆጠር ገንዘብን የምትሰጥ አሸናፊ ቁጥር ሆነች፡፡ ይህ ችግረኛ ሰው ራሱን በመውቀስና በጸጸት ከመመታቱ የተነሳ ራሱን እንዳጠፋ ይነገራል፡፡ በአእምሮው ለብልጽግና እጅግ ቀርቦ፣ ነገር ግን ከራሱ ቸልተኝነት የተነሳ እድሉ እንዳመለጠው ሲያሰላስለው ሊሸከመው የማይችለው ጸጸት ስለሆነበት የመኖር ተስፋውን ቀማው፡፡ ከጸጸት አጉል ተጽእኖ ለመዳ ከፈለክ በቁጥጥርህ ስርና ከቁጥጥርህ ውጪ የሆኑ ነገሮችን ለመለየት ሞክር፡፡ “የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡ Make Ethiopia great again @megaygra

E tech
1 112
ያለህን ሳይሆን ማንነትህን መዝነው! ያለህንና የሌለህን ከመቁጠርህ በፊት ማንነትህን ለካው፡፡ የሕይወትህ ጥራት የሚመዘነው በማንነትህ ጥራት ስለሆነ ማለት ነው፡፡ የማንነት ጥራት ስኬትን ያመጣል እንጂ ስኬት የማንነትን ጥራት አያመጣም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህ እውነታ ይምታታባቸዋል፡፡ ስለዚህም፣ ተሳክቶላቸዋል ብለው የሚያስቧቸውን ሰዎች ጨዋ ማንነትና አመለካከት ይመለከቱና፣ “እኔም በእውቀት፣ በሃብትና በመሳሰሉት ሁኔታዎች እዚህ ደረጃ ብደርስ ኖሮ ጥራት ያለው ሕይወትና ማንነት ይኖረኝ ነበር” ብለው ያስባሉ፡፡ ይህ ጉዞ የምኞት ጉዞ ነው እንጂ የእውነታ ጉዞ አይደለም፡፡ እነዚያ ሰዎች የጀመሩት ከማንነት ለውጥ መሆኑንና ሁኔታቸውን ከመለወጣቸው በፊት ማንነታቸውን ለመለወጥ ጥረት ማድረጋቸውን አልተገነዘቡም፡፡ ምናልባትም ሰዎቹ ከማንነት ጥራት ሳይነሱ የተለያዩ ነገሮችን ማካበት ላይ ዘልለው ከገቡ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ነገሩ መፈራረሱ አይቀርም፡፡ ከማንነት ጥራት ቀድሞ የመጣ ነገር የኋላ ኋላ የመፈራረሱ ምስጢር ያለው የሚመጣውን የስኬት ሸክም መሸከም የሚችል የማንነት ብቃት ባለመኖሩ ነው፡፡ ስለዚህም፣ ጊዜአዊ ስኬት ከዚህና ከዚያ ሊለቃቀምና በእጅ ሊገባ ይችላል፡፡ ዘላቂና ጥራት ያለው ስኬት ግን መነሻው ጥራት ያለው አስተሳሰብና ማንነት ነው፡፡ ስኬትህን ከቁሳቁስ ብዛት አትጀምረው፤ ምክንያቱም እሱኛው ስኬት ስላልሆነ ማመለት ነው፡፡ በተቃራኒው ግን፣ ስኬትህን ከማንነት ጥራት ጀምረው፡፡ የማንነት ጥራት ማለት . . . • ሲሳካለት አጉል ትምክተኛነት የማይሰማው ማንነት . . . • ሳይሳካለት ሲቀር በዝቅተኝነት የማይመታ ማንነት . . . • ከዘር ምንነት፣ ከገንዘብ አቅምና ከእውቀት ደረጃ በዘለለ ሁኔታ ሁኑን ሰው እኩል የሚያይ ማንነት . . . • የበላይነት የማግኘትን እድል ሰዎችን ለመደቆስ ሳይሆን ለሰዎች ጥቅም የሚያውል ማንነት . . . • ሁለት መልክና ሁለት ምላስ የሌለው ማንነት . . . “የማንነትህ መለኪያ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ፡፡ Make ethiplopia great again @megaygra

E tech
1 112
Our Beloved PSYCHOLOGICAL THERAPIST & COUNSELOR #SHIMELIS_GEBEYEHU From #DKt_Ethiopia ዘወትር #ረቡዕ እና #ቅዳሜ ምሽት በ #መልህቃዊያን ቻናል Join Us ❍●◦─━⊱🌹⊰━─◦●❍ ●◦ @Anchorss ◦● ●◦ @Anchorss ◦● ❍●◦─━⊱🌹⊰━─◦●❍