cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Time is life

ጊዜ ህይወት እንጂ ወርቅ አደለም ጊዜን በምንም ነገር መግዛት አይቻልም ልክ ህይወት አንዴ ካጣነው መመለስ እንደማንችለው ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀምበት የባከነ ጊዜ ህይወት ላይ የለም

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
360
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለ_ፈ_ገ_ግ_ታ ፈገግታ ሱና ነው ! ስለሆነም እስኪ ለፈገግታ ይችን ፅሑፍ እንጋብዛችሁ ። 🌺🌺አስገራሚ ትህትና🌸🌸 በአንድ ወቅት አንድ ሰው ከአንድ ነጋዴ ጋር ይጓዛል። ይህ ሰው እስኪደክመው ድረስ በጉዞው ላይ የሚያስፈልጉ ስራዎችን በሙሉ ይከውናል። ምግብ 🍳በማዘጋጀት የጉዞ ጓደኛውን ይመግባል። ከጉዞ እየተመለሱ እያለ ምግባቸውን ለማብሰል አንድ ቦታ ላይ አረፉ። አንደኛው እግሩን ዘርግቶ ተኛ ። ሌላኛው ጭነቱን አወረደ ለጓደኛውም "እኔ ስጋ🍖🍗🍗🍗 እስክቆራርጥ ተነሳና እንጨት ሰብስብ" አለው "ወላሂ ረጅም መንገድ መጓዙ አድክሞኛል" በማለት መለሰለት። ራሱ እንጨት ሰበሰበና "እሺ እንጨት አቀጣጥል🔥🔥" አለው። "ወደ እሳት ስቀርብ ጭሱ ያፍነኛል" አለ። ራሱ አቀጣጠለና "ስጋውን በመቁረጥ አግዘኝ" ሲል አዘዘው።" እጄን ቢላዋ 🍴ሊቆርጠኝ ስለሚችል ይቅርብኝ" በማለት መለሰለት። ሰውዬው ራሱ ቆራረጠና "እሺ ስጋውን መጥበሻው ላይ አድርገህ አብስል🥘 ?" "ምግቡ እስኪበስል ድረስ ቁጭ ብሎ መጠበቅ እጅግ በጣም አድካሚ ነገር ነው ይለፈኝ" አለ ራሱ አበሰለና በጣም ደክሞት ስለነበር ጋደም አለና "ሡፍራውን አንጥፈህ ምግቡን በሳህን አድርገህ አቅርብ🍽" ሲል ጠየቀው "እኔ በጣም ደክሞኛል አሁን ይህን የምሰራበት ምንም አቅም የለኝም " አለው። ሠውዬው ተነሳና ምግቡን🍛 አቀረበ። "እሺ ተነስተህ መብላት ትችላለህ?"ብሎ ሲጠይቀው ምን ቢል ጥሩ ነው ?? "ወላሂ ሁሉንም ነገር እንቢ ማለት በጣም አሳፈረኝ።" እስኪ አሁን እንኳን እሺ ልበልህ አለና ተነስቶ መብላት ጀመረ👍ይባላል https://t.me/timecanchangeeverything
Show all...
Time is life

ጊዜ ህይወት እንጂ ወርቅ አደለም ጊዜን በምንም ነገር መግዛት አይቻልም ልክ ህይወት አንዴ ካጣነው መመለስ እንደማንችለው ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀምበት የባከነ ጊዜ ህይወት ላይ የለም

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻውም ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመጻደቅና በማስከፋት አታበላሹ፡፡ ምሳሌውም በላዩ ዐፈር እንዳለበት ለንጣ ድንጋይ ኃይለኛም ዝናብ እንዳገኘውና ምልጥ አድርጎ እንደተወው ብጤ ነው፡፡ ከሠሩት ነገር በምንም ላይ (ሊጠቀሙ) አይችሉም፡፡ አላህም ከሓዲያንን ሕዝቦች አይመራም፡፡ ሱረቱል አል በቀራህ: ምዕራፍ {264} 🎓🎓🎓🎓🎓🎓  🎓join us @timecanchangeeverything 🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
Show all...
የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፡፡ ሙስሊም ሆኘ ግደለኝ፡፡ በመልካሞቹም አስጠጋኝ» [ዩሡፍ፡101]
Show all...
1፦ሰዎች ምክንያት እየፈለጉ ጥፋተኛ ካደረጉህ ሊርቁህ እንደፈለጉ እየነገሩህ ነው። 2፦በህይወት ውስጥ ፈተና ከበዛብህ አትዘን ታገስ...የጨረቃ ውበት የሚጨምረው ጨለማ በዙሪያዋ በጨመረ ቁጥር ነውና። 3፦ጨለማን ጨለማ አያጠፋውም ጨለማን ማጥፋት የሚችለው ብርሀን ብቻ ነው፣ጥላቻን ጥላቻ አያጠፋውም፣ጥላቻን ማጥፋት የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው። @timecanchangeeverything
Show all...
Time is life በየቀኑ ባነበውም በየቀኑ ይገርመኛል . ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዘንድ አንድ ከገጠርየመጣ ኑሮው ያልሰመረለት (ድሃ) ግለሰብ ሰሃን ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል፡፡ነቢዩም ሰ.ዐ.ወ ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት ጀመሩ..የመጀሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ..ሁለተኛውንም ጎርሰው ፈገግ አሉ..ግለሰቡም እጅጉን ተደሰተ..የነቢዩ ጓዶች (ሰሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ስጦታ ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ..የአላህ መልእክተኛ ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ.. ስጦታ አቅራቢው እጅግ በጣም ተደሰቶ..ስጦታውንም ስለወደዱለት አመስግኖ ሄደ..አንድ የነቢይ ሰ.ዐ.ወ ጓድ (ሰሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው ‹‹የአላህ መልእከተኛ ሆይ..ምነው ሳያካፍሉን?›› እሳቸውም ሰ.ዐ.ወ ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሱቱን አይታችኋል አይደል?!.. ወይኑን ስቀምሰው በጣም ይመር ነበር..ባካፍላችሁ አንዳችሁ ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር እንዳታሳዩት ብየ ስለሰጋሁ ነው ብለው መለሱላቸው;;;;; ሀቢቢ የኔ ነቢይ እናቴም አባቴም ህይወቴም ፊዳ ይሁንሎት። @timecanchangeeverything
Show all...
መልካም አስተሳሰብ ሲኖርህ ❤️ ሁሉንም ነገር ውብ አድርገህ ታያለህ 💖 የምትወዳት ነብስ ስትኖርህ በትንሹም ቢሆን ትብቃቃለህ፡፡ ያለህ ዛሬን ያልፋል ለነገም ይተርፋል፡፡ 💓 ማንም ቢሆን የተሟላ ህይወት ያለው እንዱሁም ልቡ ከድካም ንፁህ የሆነ ሰው የለም በመከራ ፤በሀዘን ፤ በእንቅፋቶች መሀል ያላለፈ ተስፋ ያልቆረጠ የለም እየተደሰተ ያልተከፋ እያለቀሰ ያልሳቀ ማንም የለም ሁሉም ግን በጊዜውና በሂደት ያልፍና ትዝታ ትውስታ ሆኖ ይቀራል ‼️    👇👇👇             @timecanchangeeverything
Show all...
ኡሚዬ:- እስቲ ለወንድምሽ ደውይለት ምነው ቆየ?🤔 እኔ:- *📱ልደውልለት ቁጥሩን ስልኬ ላይ እየጻፍኩ* ኡሚዬ:- ኸረ እሱን ስልክ ተይና ደውይለት! እኔ:- 😳 በምኔ? 🙄🧐🧐 #እኔናኡሚዬ!❤️ @timecanchangeeverything
Show all...
አንድ ሰው ከጠላቱ ጋር ለመዋጋት መንገዱን እየተጓዘ ⇨መከላከያ ልብሱ ከብዶት ቢጥለው ⇨ሰይፉም ከብዶት ቢጥለው ⇨ምግብና መጠጡም ከብዶት ቢጥለውና ከጠላቱ ቢገናኝ ያለ መከላከያ ሆኖ ያለ መሳሪያ ሆኖ እርቦት እንዴት ይዋጋዋል እንዴትስ ድልን ያገኛል ?? ↪ ልክ እንደዛውም ⇨ዚክር ከብዶት የተወ ⇨ግዴታዎችን በጊዜው መፈፀም ከብዶት ያዘገየ ⇨ሱና ነገሮች ከብዶት የተወ ⇨የሸሪዓ ጉዳዮች ከብዶት የተወ እና ሸይጣን የተጫወተበት ሰው እንዴት ጥሩ ህይወት ሊኖር ያስባል እንዴትስ ጀነትን ይከጅላል ?? join 👉 👉👉 @timecanchangeeverything
Show all...
ከተረት ዓለም❤️ / ቆቋና ወርቃማው እንቁላል በድሮ ዘመን የሚኖር ገበሬ ገበያ ሄዶ አንድ ቆቅ ገዛና ወደ ቤቱ ይዟት ሄደ። በማግስቱ ቆቋ ሙሉ ወርቅ እንቁላል ጣለች። ገበሬው እጅግ ተደንቆ 'ይች በጣም ድንቅ ቆቅ ናት' አለ። የወርቅ እንቁላሉንም ጌጣ ጌጥ መሸጫ መደብር ወስዶ አሳየው። የመደብሩ ባለቤትም ንፁህ ወርቅ እንደሆነ ገልፆለት ብዙ ገንዘብ ለገበሬው ከፈለው። ከዚያም ጊዜ አንስቶ በየቀኑ ቆቋ አንድ የወርቅ እንቁላል መጣልዋን ቀጥላለች። ገበሬው ከደርዘን በላይ እንቁላሎችን አገኘ። 'በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀብታም እሆናለሁ፤ ነገር ግን ይህቺ ቆቅ በቀን ከአንድ በላይ እንቁላል እንድትጥልልኝ እፈልግ ነበር' አለ። ቆቋ በርካታ እንቁላሎችን ከጣለች በኋላ ገበሬው እንዲህ አለ:- 'ይህቺ ቆቅ በሆድዋ ብዙ እንቁላሎች ይዛለች። እኔ ደግሞ አንድ አንድ ቀን መጠበቅ አልፈልግም። ስለዚህ ቆቋን ገድዬ፣ ሆድዋን ከፍቼ፣ ሁሉንም እንቁላሎች በአንዴ እወስዳለሁ።' ከዚያም ገበሬው እንዳለው ቆቋን ገደላት ፤ ሆዷንም ከፈተው። ነገር ግን አንድም እንቁላል አልነበረም። ቁም-ነገር:- “ሁል ጊዜ ባለው የማይረካ ያለውን በሙሉ ያጣል።” ተረቴን መለሱ፣ አፌን በዳቦ አብሱ! #ሼር ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @timecanchangeeverything
Show all...
አስተማሪ ታሪክ❤️ / አሳ አጥማጁ አንድ ዓሳ አጥማጅ ነበር ይህ ሰው በስራውም ላይ ጠንካራ ሰው ነበር ።ይህ አጥማጅ በየቀኑ ውስጥ ዓሳ ያጠምድና አላህ አስከፈቀደለት ግዜ ይጠቀምበታል ልክ ሲያልቅ ወደ ባህር ዳርቻ በመሄድ ሌላ ያጠምዳል።     ከእለታት አንድ ቀን የዓሳ አጥማጁ ሚስት ባሏ ያመጣላትን ዓሳ በመቆራረጥ ላይ ሳለች አሰገራሚ ነገር ትመለከታለች!!!  ይህች ሰው የተመለከተችው ሉል ነው አዎ! በዓሳው ሆድ ውስጥ ሉል ተመለከተች በጣም ተገረመች “ሱብሐነላህ!!! በዓሳ ሆድ ውስጥ ሉል …? አያለች ባሌ… ባሌ… ባሌ… እያለች ባሏን መጥራት ጀመረች ከዚያም “ምን እንዳገኘሁ ተመልከት ሉል እኮ ነው!! ሉል … ከዓሳው ሆድ ውስጥ ” አለችው ። እሱም ” እንዴት አሰደሳች ሚስት ነሽ እስኪ አቅርቢው ለዛሬ ለቤት ቀለባችን መግዣ ትሆነናለች ….. ከዓሳ ሌላ ምግብ እንበላለን!!” አላት…..    ይህ ዓሳ አጥማጅ ሉሉን በመያዝ ወደ ሉል ገዢና ሻጭ በመሄድ ያሳየዋል። ገዢውም “እኔ ይህንን ሉል የመግዛት አቅሙ የለኝም፤ ዋጋው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ይህንን ሱቄንና መኖሪያ ቤቴን ብሸጠው እንኳ ን ልገዛህ አልችልም። ይልቁንስ እከሌ የሚባል ሀብታም ነጋዴ አለ እርሱ ሊገዛህ ይችላልና ወደርሱ ሂድ። አለው ።     ዓሳ አጥማጁ ሉሉን በመያዝ ወደ ተባለው ሀብታም ሰው በመሄድ ጉዳዩን ነገረው። ይህ ታላቅ ነጋዴም “እኔ አልችልም ይህ የያዝከው ሉል በገንዘብ የሚተመን አይደለምና እኔ መፍትሔ ብዬ የማስበው ወደ ከተማው አስተዳዳሪ ሄደህ ብታሳየው ነው  እንደዚህ አይነት ውድ ሉል ከርሱ ውጭ የመግዛት አቅም አለው ብዬ የማስበው ሰው የለም ” አለው።   ጉዞውን ወደ ተባለው አስተዳዳሪ በማድረግ ቤቱ እንደደረሰ ወደ ህንፃው ለመግባት ፈቃድ እስኪያገኝ ድረስ መጠበቅ ጀመረ። (እንደገባም) ለአስተዳዳሪው የያዘውን ሉል ሲያሳየው አጅግ ተገረመ። “እንደዚህ አይነት ሉል ስፈልገው የነበረ ነው… እንዴት ተመኑን እንደምከፍልህ አላውቅም… ነገር ግን ለየት ወዳለው ካዝናዬ እንድትገባ እፈቅድልሃለሁ። እዛ ውስጥም ለስድስት ሰዓታት በመቆየት የቻልከውንና የፈለከውን ንብረት ተሸክመህ መውጣት ትችላለህ። ይህ እንግዲህ የሉልህ ክፍያ ነው።” በማለት ወደ ካዝናው እንዲገባ ጋበዘው። ዓሳ አጥማጁም “አለቃዬ ሆይ! ስድስት ሰዓት…!! እንደኔ ላለ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው እንደው ሁለት ሰዓት ብታደርግልኝ ” ሲል ጠየቀው። አስተዳዳሪውም “በጭራሽ አይሆንም ስድስት ሰዓት ሙሉ ከካዝናዬ የፈለከውንና የምትችለውን ያህል ይዘህ መውጣት አለብህ ”  አለው።        ዓሳ አጥማጁ ወደ ካዝናው ሲገባ በጣም የሚያስደንቅ ሁኔታን ተመለከተ።  በሦስት የተከፈለ ሰፊ ክፍል ሲሆን..       #አንደኛው ክፍል በአልማዝ፣ በወርቅና በተለያዩ ጌጣጌጦች የተሞላ ክፍል ነው።          #ሁለተኛው ክፍል ለመተኛት ምቹ የሆኑ ለየት ያሉ ፍራሾች ያሉበት ክፍል ነው።    #ሦስተኛው ክፍል አጠቃላይ በሚፈለጉና ውድ በሆኑ የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች የተሞላ ነው።    ዓሳ አጥማጁ ነፍሱን ማናገር ጀመረ። “ስድስት ሰዓት!! እንደኔ ላለው ድሃ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው በዚህ ስድስት ሰዓት ምን ማድረግ አለብኝ? ጥሩ!   በሦስተኛው ክፍል ባሉት ምግብና መጠጥ መጀመር አለብኝ ምክንያቱም ብዙ ወርቅ ለመሸከም የሚያስችለኝን ኃይል አገኝበታለሁ።” በማለት ወደ ሦስተኛው ክፍል በመሄድ መብላት ጀመረ። ይበላል… ይበላል… ይጠጣል… ከስድስቱ ሰዓታት በመብላት ሁለቱን ሰዓት ተጠቀመ። ልክ ሲጨርስ ወርቁንና ጌጣጌጡን ለመሸከም ወደ አንደኛው ክፍል በመሄድ ላይ ሳለ በሁለተኛው ክፍል ያለውን ያማረ ምቹ ፍራሽ ተመለከተና እራሱን ማናገር ጀመረ። “አሁን በጣም ጠግቤያለሁ ለምን ትንሽ በመተኛት በደንብ ለመሸከም የሚያስችለኝን እረፍት አልወስድም? ይህንን እድል ደግሜ አላገኘውምና ለምን አበላሸዋለሁ?” በማለት ወደ ፍራሹ በመሄድ በጀርባው ተዘረጋ በጣም ጭልጥ ያለ እንቅልፍም ወሰደው።    ከተወሰነ ሰዓታት በኃላ “ተነስ ተነስ ቁም አንተ ጠባብ የሆንክ ዓሳ አጥማጅ ተነስ… ቁም…… ጊዜው አልቋል ” አለው። ዓሳ አጥማጁም ” እ  እ እንዴ ምምምንድነው…?” አለ። ሰውዬውም ” አዎ! ወደ ውጭ ውጣ ” አለው። አጥማጁም “ኧረ ምንም በቂ ዕድል አላገኘሁም ” አለ። ሰውዬውም “ስድስት ሰዓታት ሙሉ በዚህ ካዝና ውስጥ ሆነህ ጊዜህን ሳትጠቀም ቀርተህ አሁን ትባንናለህ? ከዚያም ሰዓት  እንዲጨመርልህ ትጠይቃለህ? እነዚህን አልማዝና ወርቆች በፍጥነት ሰብስበህ በመውጣት የፈለከውን ምግብና መጠጥ እንዲሁም ያሰኘህን አይነት የመኝታ ፍራሽ መግዛት ትችል ነበር። ነገር ግን አንተ ዝንጉና ጠባብ በመሆንህ በዙሪያህ ያለውን እንጂ ሩቅ ያለውን ነገር አታስብም።” በማለት “ወደ ውጭ አስወጡት! ” አለ። አጥማጁም “ኧረ ባካችሁ!! ኧረ!…   እባካችሁ አንድ እድል ይሠጠኝ ” ቢልም ሊሆንለት አልቻለም።       ታሪካችን አለቀ በውስጡ ያለው ትምህርት ግን አላለቀም……          ልብ በሉ -ሉሉ ምንድነው ካላችሁ ሩሃችን ነው ነፍሳችን! በገንዘብ የማትተመን ውድ ንብረት!! ነገር ግን ስንቶቻችን ይህንን እናውቃለን ??? -ካዝናውስ ካላችሁኝ   እርሷ ዱንያ ናት። ስንቱን ያዋለለች ፈታኝ ሃገር ! ስፋቷንና እንዴት ሽንጋይ እንደሆነች አስተዋላቹ? በምን መልኩ  እየተጠቀምንባት እንደሆነ እንመልከት !! -ካዝና ውስጥ ያሉት ጌጣጌጦች ደግሞ መልካም ስራዎች ናቸው። ሰውዬውእነርሱን በመያዝ ጊዜውን አልተጠቀመበትም። -ፍራሹ ደግሞ ዝንጉነትና ቸልተኝነት ነው። -ምግብና መጠጡ ደግሞ ዝንባሌዎችና ማታለያዎች ናቸው። አሁን ሁላችንም እራሳችንን እንደ ዓሳ አጥማጁ እንውሰድ። ከእንቅልፋችን የምንነቃበት ጊዜ አልደረሰምን? ጊዜያዊ የሆነውን ፍራሽና ምግብ  ትተን በዘላቂነት የምንጠቀምበትን አልማዝና ወርቁን መሰብሰብ አይሻለንምን?     ያ   ለዓሳ አጥማጁ በካዝና ውስጥ እንዲቆይ የተሰጠው ሰዓት አላህ ለሁላችንም የሰጠን በዱንያ ላይ የምንቆይባት ዕድሜ ናት።      -ሰዓቱ ከመቁጠር ወደኋላ አላለም ያ I ጊዜ ሳይደርስብንና ከዚህች ዱንያ ውጡ! ሳንባል ጊዜያችንን እንጠቀምበት!!         መልዕክቱ ለሁሉም መድረስ ስላለበት #ሼር ! ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @timecanchangeeverything
Show all...