cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የተስፋግጥም❤️

የተሰጠን ጸጋ ጥልቅ ነው።የሰጪው ስጦታ ብዙነው።የኛ ስብእና ርካሽ እስካልሆነ ድረስ ተቀባዮች እንሆናለን።የተስፋግጥም❤️

Show more
Advertising posts
351
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከተለቀቀ ቡኃላ በሁላችንም ዘንድ እጅግ የተወደደው አልበም ሊያልቅ አንድ ዘፈን ቀርቶታል። ሙዚቀኛው "የመጨረሻዋን ዘፈን ነፍሷን አላገኘሁትም" በሚል ጭንቀት ከተወጠረ ወራት ተቆጥረዋል። ድምፃዊው ጥበቃው ደክሞት ዘፈኖቹን ከስቱዲዮ አስዘርፎ ስለሚያወጣበት መንገድ እያሰበ ነው። "የቀረው ግጥሙ ብቻ ነው አይደል? እሱን ደግሞ በአምስት ደቂቃ መጨረስ እንደምትችል በተደጋጋሚ አይተናል። ችግሩ ምንድን ነው?" አለ እየተማረረ። (ድካም ተሰማው ሙዚቀኛው) "እውነቱን ልንገርህ? ... እኔ አንተ እንደምታስበው አይነት እውነተኛ አርቲስት አይደለሁም።" አለ በተሸነፈ ድምፅ። "እንዴ? እና ታዲያ ምን ልትባል ነው?" "....እኔ አርቲስት ሳልሆን ሙዚቃ በመስራት የሚያገግም በሽተኛ ነኝ።" "አልገባኝም!" "ማለቴማ...የሆነ ህመም ሲያንሳፍፈኝ እንጂ እንደ'ናንተ በፈለግኩት ሰዓት ተነስቼ መብረር የምችልበት ክንፍ አልታደልኩም። እኔን አርቲስት ማለት እፉዬ ገላን 'በራሪ ፍጡር ነች' እንደማለት ነው።" "እስኪ ተው በናትህ!...አንተ አርቲስት ካልተባልክማ እኛ ስቱዲዮ ድርሽ ማለት የለብንም።" "አያይ...እናንተማ ባሻችሁ ሰዓት ድምፃችሁን ማዘዝ ትችላላችሁ። አዬህ? ክንፉ ተሰጥቷችኋል። ትክክለኛ ስታሮች እናንተ ናችሁ።" "ትሰማኛለህ?!...እኛ ኮከብ ከተባልን አንተ ፀሀይ ነህ። ምክኒያቱም የምናፀባርቀው ያንተን ብርሀን ነው። ይሔንን መቼም እንዳትረሳ።" (ሁኔታው ስላስፈራው በራስ መተማመኑን ሊመልስለት ታገለ።) "ፀሀይ?!.." ፂም አልባ ፊቱን እየደባበሰ "...ታውቃለሀ እሷንም እኮ ከርቀት ስለምናያት ነው እንጂ የምታበራ የሚመስለን ጠጋ ብለን ስናያት እየነደደች ነው። The sun is actually burning. ...እንደምትለው 'ፀሀይ' ከሆንኩ እንኳን... ወይ ነድጄ አልቄያለሁ። ወይ ደግሞ የሚለኩሰኝ አጋጣሚ አጥቻለሁ።" "እንዲህ እንደዋዛ የምትነግረኝን ወሬዎች ቤት እንዲመቱ ብታደርጋቸው እኮ ጨርሰናል ወንድሜ።" "ግጥሙ በውስጡ አምቆ የሚይዘውን ታሪክ ሳናገኝ? በድኑን ብቻ ልናውጣው? ያለ ነፍሱ? ተው እንጂ!!..ስንቴ ነው የምነግርህ እንደዚህ እንደማይሆን?!" "ምናለበት አንዳንዴ እንኳን ቀለል ብትል አንተዬስ?! ሁሉንም ነገር ካላመናፈስክ ደስ አይልህም እንዴ?!..." ሊስቅ ብሎ ፊቱ መቀያዬሩን ሲያይ ደንግጦ ዝም አለ። (ሙዚቀኛው እንዳኮረፈ ስቱዲዮውን ጥሎለት ወጣ።) ዘፋኞቹ ሁላ ወሬ አስጀምረውት ጠለቅ እያለ ሲሔድባቸው ጨዋታውን ወደ ሹፈት የሚቀይሩበት ነገር ሊለመደው ያልቻለ የጋራ አመላቸው ነው። "..'በልተህ ላትበላ አታስፈትፍተኝ፤ ጠተህ ላትጠጣ ጋን አታስከፍተኝ' የሚለው እኮ ወዶ አይደለም አያ ሙሌ።" እያለ ብቻውን እያነበነበ ወጣ። ሰዎች እንዳይለዩት አፉን በስካርፍ...አናቱን ደግሞ በኮፍያ ከልሏል። በአይኖቹ አካሔዱን የሚኮርጀውን ጉብል፤ ፈገግታዋን የሚዋሳትን ሴት ያማትራል። "በህይወት ካሉ ሰዎች ላይ ብቻ ነው ታሪኬን የምወስደው እንጂ ፈጥሬ አልፅፍም!" የሚል ፍልስፍና አለው። ለዚህም ነው ደራሲ ሲሉት "ደራሲ አትበሉኝ...የአምላክ ጋዜጠኛ ነኝ!" እያለ የሚሟገተው። (ሀይማኖተኛ ነኝ ቢልም ፍልስፍናው ሳይበዛ አይቀርም።) ጎዳናው ላይ እየኳተነ መሸበት። ቢጨንቀው ከአመታት ቡኃላ ግሮሰሪ ገብቶ ተቀመጠ። ሲገባ በተስፋ መቁረጥ እንጂ "ፍለጋዬ የሚቋጭበት ቀን ይሆናል!" በሚል ጥርጣሬ አልነበረም። ከተቀመጠበት ጠረጴዛ ላይ ብዙም ሳይቆይ ሁለት ጠብደል ጎረምሶች ሳያስፈቅዱት ተቀመጡ። ውሀውን ጨበጥ እያደረገ በሰቀቀን አያቸው። አንደኛው ሁኔታውን አይቶ..."ከደበረህ መነሳት ትችላለህ!..ይሔ የኛ ቦታ ነው።" አለው። "ኧረ...ኧረ ችግር የለውም። እንዲያውም ልሔድ ስል ነው የመጣችሁት።" አለና ሒሳቡን ለመክፈል አስተናጋጁን በእጁ ጠራው። ወዲያው ሶስተኛ ሰው ወደነሱ ጠረጴዛ መጥቶ እየተቀላቀላቸው..."አንድ ጮማ ወሬ ብነግራችሁ ድራፍት ትጋብዙኛላችሁ?" አለ። "እንደ ወሬው ጮማነት ይወሰናል!" አሉት። "በሱ ምንም ጥርጥር አይግባችሁ።" "እሺ ቀጥል!" ሙዚቀኛው ለአስተናጋጁ ሂሳብ መክፈሉን ትቶ ለራሱም ቢራ እያዘዘ ጆሮውን ቀሰረ። "እሺ..." አለና ወንበር ስቦ ድራፍት ካዘዘ ቡኃላ ግማሽ አድርሶ እስኪያስቀምጠው ድረስ "ቆዩ" እያለ ትግስታቸውን ተፈታተነው። ሙሉ ትኩረታቸውን ማግኘቱን ሲያውቅ...."ትላንትና ማታ ሌላ ሰፈር ሂጄ እየተዝናናሁ ነበር።" ብሎ ወሬውን ጀመረ።..."ከዛ ማንን ባገኝ ጥሩ ነው?" "ማንን አገኘህ?" "የቢኒን ሚስት ማሒን!" "እንዴ? ምን እየሰራች?" (ሌላኛው) ዘና ብሎ ወደኋላ እየተደገፈ..."ቂጧን አስጥታ እ የ ሸ ረ ሞ ጠ ች ነዋ!" ባለማመን አዩት። ስልኩን አውጥቶ ፎቶ እያሳያቸው ሌላ ድራፍት አዘዘ። ሙዚቀኛው ሰረቅ አድርጎ ሊያይ ቢሞክርም አልመቸው አለ። ጠብደሎቹ ፎቶውን በግርምት እያዩ .. "ጭራሽ ተኝተሀታል?...የፈጣሪ ያለህ!" (ፎቶው ከጠረጴዛ ጠረጴዛ መዟዟር ጀመረ። ግሮሰሪዋ ባንድ እግሯ ቆመች።) ድንገት አንድ ሰው እየገነፈለ ወደ ውስጥ ከገባ ቡኃላ ወሬኛውን ልጅ ተንደርድሮ በቦክስ ነረተውና ወለሉ ላይ ዘረረው። ሁሉም ፀጥ ብሎ ሲያይ ሙዚቀኛው ሩጦ ገብቶ መገላገል ጀመረ። ሌሎቹም ከድንጋጤያቸው ነቅተው መሀላቸው ገቡ። የወደቀውን ልጅ አፋፍሰው ወደ ጓዳ ወሰዱት። የሚገለገለው ልጅ መንጭቆ ወደ ገላጋዩ ሲዞር...ያዬውን ሰው ማመን አቅቶት...."እንዴ ኤላ? እዚህ ምን ትሰራለህ?" አለ ግራ ተጋብቶ። ሲያገላግል ስካርፍ እና ኮፍያው መውደቁ ታውቆት ፀጉሩን እያከከ ዝም አለ ሙዚቀኛው። "የምትተዋወቁ ከሆነ አንተ እሱን ይዘህልን ውጣ ወንድሜ!" አለው አንደኛው ወደ'ሱ እየመጣ። ተያይዘው ወጡ። ወጣቱ ከግሮሰሪው ከወጡ ቡኃላም በግርምት ማዬቱን አላቆመም። ጠቁሮበታል። ተጎሳቁሎበታል። ግን ሊጠይቀውም አልፈለገም። እንዳይሰማው ብሎ ... "ያው ብዙዎቻችን ከካሜራ ጀርባ ያሉ አርቲስቶችን በመልክ ስለማናውቅ ነው እንጂ ስምህን ብነግራቸው ሁሉም ያውቁህ ነበር!" አለ። "ይገባኛል።" አለ ሙዚቀኛው እንዴት ወሬውን እንደሚያስጀምረው እያውጠነጠነ። ትንሽ ዝም ዝም ተባብለው ቆዩ። ልጁ አሁንም እጁን እያፍተለተለ "ባይዘዌ ሚስቴ ሴተኛ አዳሪ አይደለችም።" አለ። "ኧረ? አይ ጥሩ...ጥሩ ነው።" አለ በሀፍረት አቀርቅሮ። "የምሬን ነው!..መንታ እህቷ ነች ያን ስራ የምትሰራው። ውሀ እና ፀበል ናቸው። መልካቸው እንጂ ውስጣቸው አይገናኝም። ወይም ጨረቃ እና ፀሀይ በላቸው። ቅርፃቸው እንጂ ብርሀናቸው አይመሳሰልም።" እጁን በእልህ ጨበጥ ዘርጋ እያደረገ..! "እና ውሸት ከሆነ ምን ስሜታዊ አደረገህ? ማስረዳት አይቀልም ነበር?" "ልክ ነህ እሱማ ግን....ባልዋለችበት ስሟ ሲነሳ...ባልሰራችው ወንጀል እየተቀጣች ሳይ በጣም ከፋኝ። ትዕግሥት አጣሁ እውነት!! መጀመሪያ ላቅምሰው አልኩ።" ሳቀ! ሙዚቀኛው ከረጅም ጊዜ ቡኃላ እፉዬ ገላ ነፍሱ ከያዛት አጥር ተላቅቃ በህይወት ንፋስ ወደላይ ስትንሳፈፍ ተሰማው። እሱም ፈግግ አለ። የዛኑ ምሽት ስቱዲዮ ገብቶ የመጨረሻዋን ዘፈን በግጥም ሞልቷት አደረ። ድምፃዊው ሲያዬው "እንኳን ጠበቅኩህ!" እያለ በደስታ አቀነቀነው። እንዲህ እያለ... "ግልፅ እውነትሽ መች ጠፋኝ? ባላዩት እንጂ ባሙሽ የከፋኝ! "ሌትም ወ'ታለች አሉ አንቺን በማታ...ጨረቃ እያዩ!.. "ስትመጭ አይን ያያል...መውጣትሽን ጧት ሲነጋ..ሲመሽ መግባትሽን የሞቀው ወርቃማ ብርሀንሽን ጨፍኖስ ማን ያጣል ተፈጥሮሽን? (×2)..
Show all...
"አውቃለሁ አንቺ አይደለሽም! ... አንቺ ቀን ነሽ በቃ 'እሷው ነች አታርፍም' ቢሉም...ቢያሙሽም በጨረቃ እያዬው ሳይመሽ በጊዜ ... ቀን ተግተሽ ስትሰሪ ማታ ግን ተራሽ አይደለም...ምን በወጣሽ ልትበሪ?!.. "ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ..." ፧ (፨ የግርጌ ማስታወሻ:- ይሕ "እንዲህ ቢሆንስ?" በሚል ስራ ፈትነት የተፃፈ ልብወለድ ብቻ ነው👍) Mickel
Show all...
ደሞ መዝሙር ነው በሉ???
Show all...
ብሩክ 🎶title አጠብቁ ከላይ.mp39.02 MB
"ንስሀ ይሰጡሀል" ብለውኝ ነበር ያገኘኋቸው...የንስሀ ጓደኛዬ ሆነው አረፉት እንጂ። ኑዛዜ መቀበል አይፈልጉም። በተገናኘን ቁጥር አራት ኪሎን አራት ጊዜ እንዞራታለን። ሲደክመን ማሪያም ገብተን እናወራለን። ወይ በዝምታ እንቀመጣለን። በርግጥ ዝም ብለውም ዝም አይሉም። ላባቸው ጠብ እስኪል ድረስ ያስባሉ። ለምንድን ነው እንደዚህ የሚሆኑት? የሰውን ሀጢያት መስማት ደክሟቸው? የእግዜርን መሀሪነት ተጠራጥረው? በሽተኛ እንጂ ሀጢያተኛ አይደሉም ብለው? አላውቅም። ቅድስት ማሪያም ውስጥ አንድ ጥግ ላይ በዝምታ ተቀምጠን ነበር። በመሀል ያገናኘችን ጎረቤቴ ሂዊ ተሳልማ ስትሔድ ከርቀት አዬናት። ወደኔ እየዞሩ..."ወለተ ሀና ግን ትፈራሀለች ልበል?" አሉ። "እኔ'ጃ!...ትፈራኛለች?" አልኩ የውሸት እየተገረምኩ! "እንግዲህ እኔ ቀጥሬ ያረፈድኩባት ቀን የንስሀ አባቴ ነው ብላ ፈርታኝ አታውቅም። አንተ ግን ሶስት አራት ጊዜ ቀጥረህ እየጠፋህባት ምንም አትናገርህም።" "መርጣ ነው እንጂ እኔ ምን አደርጋታለሁ ብለው ነው?....እኔ እኮ ለማኝ የማይፈራኝ ሰው ነኝ!" "ታዲያ ለምን ነው እሷ ልትፈራህ የመረጠችው?" አሉ እየፈገጉ..! "እርግጠኛ አይደለሁም...እኔንም ይገርመኛል ...እኔ...እእእ..እኔ እናቴን ነበር እንደዛ አይነት ፍርሀት የምፈራት።" "ዱለኛ ናት እናትህ?" "አይ!..እንደዛ አትቀጣም እሷ...እንደ ትልቅ ሰው ነው አንድ ሁለት ሳምንት የምትዘጋኝ። ስለዚህ ሁሌም እጠነቀቃለሁ። ሂዊም ያን አይነት ፍርሀት የምትፈራኝ ይመስለኛል። ይመስለኛል ነው እንግዲህ። ጥሩ ነገር አይደለም በርግጥ።" "ታዲያ ይሔን ያህል ካወቅክባት...ለምን ነው የቀረበችህን ያህል ልትቀርባት ያልፈለግከው? ጥሩ ልጅ ነች'ኮ!" "ኧረ ከሷ ጋ የሚያገናኘው ነገር የለም።... ስለተውኩት ነው እሱኛውን ህይወት።" "ለምን? ማለቴ ለምን እየሔድክ አታዬውም መንገዱን? ስለነገ ማን ያውቃል?" አሉ የምለውን ያወቁብኝ ይመስል በመርማሪ አይን እያዩኝ። አይናቸውን ከሸሸሁ ቡኃላ አንድ እንጨት አንስቼ መሬቱን እየጫርኩ...."አካሔዴ ነዋ መም'ሬ!...እንዲያውም አንድ ጊዜ የሆነ ፊልም አይቼ ነበር የኔን ህይወት የሚመስል። ገፀባህርይው ሽማግሌ ሁኖ ተወልዶ ልጅ እየሆነ የሚሔድ ነው። አላውቅም ብቻ...እነሱ ወደሚሔዱበት ላልሔድ ጥልቀት ያለው ግኑኝነት መመስረት ጭካኔ ይመስለኛል።" "እንደኔ እንደኔ ማድረጉ እንጂ ማሰቡ ክፋት ያለው ነገር አይመስለኝም። ሁሉም ሰው ውስጡ ላይ አዲስ ማንነት ሊፈጠር ሲል...ራሱን ስለማጥፋት ያስባል።" አሉ መሬት መሬቱን እያዩ። "እኔ መች እንደዛ አልኩ?" አልኩ ደንግጬ ዙሬ እያዬኋቸው። "እ? ይቅርታ!" አሉ ቀጥ ብለው እያዩኝ። ወደራሳቸው ተመልሰው በመዳፋቸው ፊታቸውን ሲያሻሹ ከቆዩ ቡኃላ ... "...ምን ላድርግ ብለህ ነው የኔ ልጅ?...ሰሞኑን ብዙ ልጆቼ እንደዛ ሲለሚሉኝ ቀድሞ እሱ ነው የመጣልኝ።" አሉ። "ኧረ?...እሺ።" አልኩ የምለው ጠፍቶኝ። ዝም ዝም ተባብለን ቆዬን። ሲከነክነኝ ጠዬቅኳቸው። "ቆይ ሰው ራሱን ስለማጥፋት ሲያስብ ላዩ ላይ አዲስ ማንነት ሊወለድ ነው አሉ!...ታዲያ ህዝቡ እንዳለ ራሱን ስለማጥፋት ሲያስብስ ምንድን ነው የሚወለደው?" አልኩ በጥያቄ ስሜት እያዬኋቸው። "አብዮት!" አሉኝ በተዳከመ ድምፅ። የባሰ አሳዘኑኝ። እንዴት በትህትና እንደምመልስላቸው ሳስብ ከቆዬሁ ቡኃላ ... "አይ አባ!...ይሔን ትውልድ አያውቁትም ማለት ነው።.... ሁላችንም ለራሳችን ደስታ ብቻ መኖርን ከለመድን እኮ ቆዬን። ከ'ንግዲህ ማንም ለማንም አይሞትም።" "ተያይዞ መቆም ያልቻለ ህዝብ ለዬብቻ ይወድቃል..." "ይቀለናል እሱ! የምንነሳ ቢሆን እስካሁን ያለው ምክንያት አይበቃንም ነበር ብለው ነው?!" "ልክ ነህ እሱማ።" "እና ታዲያ?" "የወጣቱ ራስን ማጥፋት መፈለግ አብዮት እንዲነሳ ምክኒያት ይሆናል አልኩህ እንጂ...ማስነሳትና ማቀጣጠል የሚችሉትማ የራሳቸው የጨቋኞቹ ልጆች ናቸው።" "ምን አጣን ብለው ይነሳሉ እነሱ ደግሞ?" "እሱ ነው ከባዱ ጥያቄ።" "ያለነሱ መሆን አይችልም ብለው ነው የሚያምኑት እርሶ?" "የድሀ ልጅ የሚመራው አብዮት የት ይደርሳል ብለህ ነው? ጮማ ሲጋብዙት አርብ ሮብን የሚጥስ ረሀብተኛ...በየትኛው እምነቱ ነው ወንዝ ከፍሎ የሚያሻግርህ?" አሉና በራሳቸው አባባል ከት ብለው ከሳቁ ቡኃላ እንባቸውን እየጠረጉ "ምን ልልህ ፈልጌ መሰለህ?...የድሀ ልጅ ሹመት አልያም ሽልማት ሲሰጡት ለቤተሰቦቹ ደስታ ሲል እጅ ይሰጣል... "...እነሱ ምንም ሳይጎድልባቸው የሌላው ቁስል አሟቸው...ቤተሰባቸውን ተቃውመው የወጡ የባላባት ልጆችን ግን በምንም አትደልላቸውም።"... አሉና ግራ እጃቸው መንቀጥቀጥ ሲጀምር በቀኝ እጃቸው ይዘው እያስቆሙ "ጥ..ጥ...ጥላሁን ግዛው እኮ ምንም የጎደለበት ነገር የሌለው...የንጉሱ ቤተሰብ ነበር። ጠርተው ለምነውታል። 'እምቢ' ሲል ጊዜ ... ሰላሳ ጥይት አርከፈከፉበት። የዚያኔ ነው ጃንሆይ የወደቁት። ታውቃለሀ? የዛን ቀን ነው ጃ የወደቁት። የዛን ቀን ነው ሁሉም የሚወድቁት። የዛን ቀን ነው ሁሉም የሚወድቁት...!" አፋቸውን ማስቆም ያቃተቸው ይመስል እጃቸውን ጭነው ያዙት። "ቆይ እርሶ 'ችግራችንን እግዚአብሔር በጊዜው ይፈታዋል' ብለው አያምኑም?" አልኩ እንዲረጋጉ! በረጅሙ ከተነፈሱ ቡኃላ "በእምነቱ ያሸነፈው ዳዊትም ቢሆን ወንጭፍ አንስቶ ዲንጋይ መወርወሩን አትዘንጋ።" አሉ። "የዳዊትን ያህል ፃድቅ ሲኖር ነዋ እሱም!" "የዳዊትን ያህል ያልፀደቅክ እንደሆነስ? ሀይማኖትህን ሲያጠፉት እያዬህ ዝም ትላለህ?" "እኔ?...እኔማ ራሴም ስጠፋ እያዬሁ ምንም አላልኩም። መጀመሪያ ራሴን ላግኘው። ከዛ ነው ስለነሱ ነገሮች የማስበው።" "ሀገር እና ሀይማኖትህን ከነጠቁህ ወዲያ ራስህን ምን ላይ ትፈልገዋለህ?" ምራቃቸው ፊቴን ረጨኝ። ስሜት እንዳሸነፋቸው ገባኝና..."ደህና እደሩ መም'ሬ!" ብዬ በተቀመጡበት ጥያቸው ወደ ቤቴ ገባሁ። የዛን ቀን ምሽት ነበር አባን ለመጨረሻ ጊዜ ያዬኋቸው። ከዛ ቡኃላ ጭንቀቱ በርትቶባቸው... ለሶስት ወር ሱባኤ ደብረ ሊባኖስ መክተማቸውን ሰማሁ። ከከባድ እንቅልፍ እየተነሳሁ ነበር። እየነጋ ይሁን እየመሸ አልለዬኝም። ህይወት ነጠላ ለብሳ ስትመጣ ጧት መሆኑ ገባኝ። "ገና እየነጋ ነው?" አልኩ አይኔን እያሻሸሁ "ሞት ነው እንቅልፍ ይዞህ የነበረው? መሽቷል እንጂ እንግዲህ!...ለቅሶ ቤት ውዬ እየመጣሁ እኮ ነው።" አለች አይን አይኔን እያዬች። "ማን ሞተ?" ብዬ እንድጠይቃት የፈለገች ይመስላል ሁኔታዋ ሁሉ። ይቅርብኝ ብዬ አይኖቿን ሸሸሁ። "ብታይ ምን የመሰለ ሸበላ መሰለህ ራሱን በገመድ ሲጥ አድርጎ የሞተው! አይ ከንቱነት!!" አለች ዙራ እያዬችኝ። "ተይ ህይወት..." አልኩ...እየተቀመጥኩ። "አይደለማ!...አንተን አያናድዱህም እንዲህ አይነት ሰዎች? ራስ ወዳድነታቸው አያበሽቅህም?" ተናዳለች። "ቢያበሽቀኝስ ምን ትርጉም አለው? ራሱን ከጠላው በላይ እኔ ልጠላው እችላለሁ?!" መለስ እያለች "እሱማ ቢጨንቀኝ እኮ ነው።...የዚህ ነገር መብዛትማ..." "ተይ ይቅርብን በቃ!...እኔ ይሔ ርዕስ ላይ የማውራት ፍላጎት የለኝም።" አልኩ እያቋረጥኳት። "እሽ አንተ ካልክ!" አለች አገጯን እንደያዘች። ሳያት አሳዘነችኝ። ደስም አለችኝ። በዚሁ ሁሉ መሀል ደስ መሰኘት አይገርምም?
Show all...
🥰 1
"ሂዊ!" "ወዬ" "የአንድ ሰዓቱን ቲያትር ለምን ዛሬ አናዬውም?" "ደስ ይለኛል። ራስህ'ኮ ነህ ነገ ነገ እያልክ ያጓተትከው" "በቃ ዛሬ እንዬው የነገን ማን ያውቃል?" ደስ ብሏት ፈገግ እያለች "የታገሰ ነዋ!" Mickel
Show all...
እኔ "ሞትህ ናፍቆህ አያቅም።እውነቱን እኮ ነው ጠቢቡ "ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም" ያለው።" ጆቢራው "መልካም"😒😒😒 እኔ 😳😳😳 ጆቢራው ወደኔ ዞሮ ሲጋራውምን እየተነፈሰበኝ"ታዲያ ለምን ሞተህ አትሞክረውም" እኔ "ድፍረቱ ቢኖረኝ የዛሬን ቀን ነገ ደግሜ መኖር አልፈልግም ነበር" ጆቢራው "መኖርም መሞትም ሁለቱም ከተስፋ ነው የሚመነጨው።በመሞት ውስጥ እረፍ እንዳለ በማሰብ ከሂወት ስንሸሽ።የሞት ጨለማነት አስፈርቶን አዲሱን መግለጥ ከብዶን ደሞ እንኖራለን" እኔ በውስጤ "እራሴው ቆስቁሼ ልለበለብ ነው" ጆቢራው ከሲጋራዋ ትንሽ ሳብ አድርጎ "በሁለቱም ምርጫዎች ተሸናፊዎች ነን።በመኖር ውስጥም ተስፋ ብቻ።በሞት ውስጥም ተስፋን ሰንቀን።" ፈገግ እያለ ወደኔ ተመልክቶ"የሰው ልጅ ተስፋ ቆርጦ አያውቅም። even እንዳንተ አይነቱ ፈሪ እራሱ ራሱን ቢያጠፋ በሞት ጉያ ተደብቆ ከህይወት ለመሸሽ ተስፋ አድርጎ ነው" እኔ ዛሬም እየተገረምኩ ተመለከትኩት።"መቼ ይሆን ከሀሳቡ ልቄ እኔ የምናገረው" በውስጤ ተናገርኩ ጆቢራው ሲጋራውን መረት ጥሎ በባዶ እግሩ እየረገጠ "ስቃይን ለማቆም ተጋፍጠህ ቁስልህን ማድማት አልያም ለምደህ እስኪሽር መጠበቅ ነው።ነገር ግን መሻሩ የጊዜ እንጂ ያንተ ፍቃድ አይደለም" እኔ "ጊዜን ታግዬ ላልጥለው ፈቃዱን ላላገኝ እስከመቼ ልጠበቅ ነው???" ከአይምሮዬ የጥያቄ ቋት አንዷን መዞዤ ሰነዘርኩ ጆቢራው ለመሄድ ከመቀመጫው እየተነሳ"ጊዜን ታግሎ የረታው የኖረም የሞተም አይደለም።ጊዜ ፈጣሪ ነው።የፈጠረውንም ያስረጃል።ስለዚህ በጊዜ የተፈጠረው ህመም አርጅቶ እስከሚሞት መጠበቅ ይኖርብሀል" ዝቅ ብሎ እየተመለከተኝ "ጅል መሆንህን ካቆምክ ደሞ ከህመምህ ጋር መግባባት ትጀምራለህ"ፈገግ እያለ ጉንጬን በመዳፋ በቀስታ እያጣፋ"ባይሽርም አያምህም ለምፓ" በጨፈገገው ፊቱ።በሚሞቀው ንግግሩ ውስጥ አይኖቹ ብዙ ይናገራሉ።"""እሱ ግን ባይስቅም ይስቃል"""
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዛሬ ሁለት አመት የመጀመሪያ መፅሀፌ የወጣ ግዜ በፅሁፌ የወደዱኝ የመሰሉኝ ሁሉ እንዳልወደዱኝ አየሁ። Everything I saw, people who I genuinely believed enjoyed reading my writing were against my book, so it was all a fake. It was a heart break. Unconsciously ስለመፅሀፌ መስማትም ማየትም እስክጠላ ድረስ ሆኜ ነበር። በችሎታዬ ጥርጥር ውስጥ እስክገባ ድረስ እንደሆንኩ ያወቅኩት የገዛ መፅሀፌ ቤት ውስጥ እንደሌለኝ realize ሳደርግ ነው። በቅርብ ነው በጣም በቅርብ ከአባቴ ወስጄ መፅሀፌን በድጋሚ ያነበብኳት። አብዛኛው እውነት አለበትና ልጠላው አልቻልኩም። እንዲያውም ጉብዝናዬን መስክሬበታለሁ። የዛን ግዜ ብዙ ያሉኝ ሰዎች እኔን personally ምንም የማያውቁኝ መፅሀፌን በደንብ ያላነበቡ ናቸው። ያነበቡ ሁሉ ወደውታል እያልኩ አይደለም። አንብበው ያልወደዱትም እኔ ጋ ሳያገናኙ በአግባቡ ያስቀመጡ ነበሩ። እኔ ብቻ የፃፍኩ እስኪመስለኝ የማያውቁኝ ሁሉ በመፅሀፍ አሳብበው ሊተቹኝ ይሞክራሉ። በየሄድኩበት ለጏደኞቼ እንኳ በድፍረት አልወዳትም ብለው የሚነግሩ ያም እንደ ደህና መልእክት የሚደርሰኝ ነኝ። ጠንካራ እና opinionated ነኝ ማለት ሰው አይደለሁም አይሰማኝም ማለት አይደለም። Opinionatedም ብሆን እንኳን አንድ “እሱ እኮ ፊትለፊት ነው የሚናገረው” ከሚባልለት ወንድ facebooker፣ አንድ የሙሉ ግዜ fuckery post የምታደርግ የሆነች ሴት ያሉትን ሲሶ ያህል በFacebook ታሪኬ አላልኩም። I know my works are good ምክንያቱም ያላየሁትን አልፃፍኩም። ያወቅኩትን፣ ያየሁትን፣ ልምድ ያገኘሁበትን የሆንኩትን ያህል ነው የምፅፈው። አለመስማማት፣ አፃፃፉን አለመውደድ ፣አስተያየት መስጠት ያባት ነው። ሰድብን ዘለፋን ነገሩን ፐርሰናል ማድረግ፣ መፅሀፍን በሆነ ግዜ Facebook post መተቸት ልክ ነው? ውስጣችሁ ደህና ነው? በድጋሚ ችሎታዬንም doubt አላደርግም፣ ከራሴም ጋ አልጣላም። ግን አንዳንዴ ህይወታችንንም ባታስተዳድሩልን ምንም ያላደረጋችሁን ሰው በመጥመድ የምታቀረሹትን ጥላቻ ለመቆጣጠር ሞክሩ። የሰውን መንፈስ ረብሻችሁ የምታገኙት እርካታ ይቅርባችሁ። ፅፈን መፅሀፍ አሳትመን የምንለወጥ መስሏችሁም ከሆነ ተሳስታችሁዋል። ገበያው እንዴት ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ ባወቃችሁ። ይመቻችሁ። 💚
Show all...
የዛሬ ሁለት አመት የመጀመሪያ መፅሀፌ የወጣ ግዜ በፅሁፌ የወደዱኝ የመሰሉኝ ሁሉ እንዳልወደዱኝ አየሁ። Everything I saw, people who I genuinely believed enjoyed reading my writing were against my book, so it was all a fake. It was a heart break. Unconsciously ስለመፅሀፌ መስማትም ማየትም እስክጠላ ድረስ ሆኜ ነበር። በችሎታዬ ጥርጥር ውስጥ እስክገባ ድረስ እንደሆንኩ ያወቅኩት የገዛ መፅሀፌ ቤት ውስጥ እንደሌለኝ realize ሳደርግ ነው። በቅርብ ነው በጣም በቅርብ ከአባቴ ወስጄ መፅሀፌን በድጋሚ ያነበብኳት። አብዛኛው እውነት አለበትና ልጠላው አልቻልኩም። እንዲያውም ጉብዝናዬን መስክሬበታለሁ። የዛን ግዜ ብዙ ያሉኝ ሰዎች እኔን personally ምንም የማያውቁኝ መፅሀፌን በደንብ ያላነበቡ ናቸው። ያነበቡ ሁሉ ወደውታል እያልኩ አይደለም። አንብበው ያልወደዱትም እኔ ጋ ሳያገናኙ በአግባቡ ያስቀመጡ ነበሩ። እኔ ብቻ የፃፍኩ እስኪመስለኝ የማያውቁኝ ሁሉ በመፅሀፍ አሳብበው ሊተቹኝ ይሞክራሉ። በየሄድኩበት ለጏደኞቼ እንኳ በድፍረት አልወዳትም ብለው የሚነግሩ ያም እንደ ደህና መልእክት የሚደርሰኝ ነኝ። ጠንካራ እና opinionated ነኝ ማለት ሰው አይደለሁም አይሰማኝም ማለት አይደለም። Opinionatedም ብሆን እንኳን አንድ “እሱ እኮ ፊትለፊት ነው የሚናገረው” ከሚባልለት ወንድ facebooker፣ አንድ የሙሉ ግዜ fuckery post የምታደርግ የሆነች ሴት ያሉትን ሲሶ ያህል በFacebook ታሪኬ አላልኩም። I know my works are good ምክንያቱም ያላየሁትን አልፃፍኩም። ያወቅኩትን፣ ያየሁትን፣ ልምድ ያገኘሁበትን የሆንኩትን ያህል ነው የምፅፈው። አለመስማማት፣ አፃፃፉን አለመውደድ ፣አስተያየት መስጠት ያባት ነው። ሰድብን ዘለፋን ነገሩን ፐርሰናል ማድረግ፣ መፅሀፍን በሆነ ግዜ Facebook post መተቸት ልክ ነው? ውስጣችሁ ደህና ነው? በድጋሚ ችሎታዬንም doubt አላደርግም፣ ከራሴም ጋ አልጣላም። ግን አንዳንዴ ህይወታችንንም ባታስተዳድሩልን ምንም ያላደረጋችሁን ሰው በመጥመድ የምታቀረሹትን ጥላቻ ለመቆጣጠር ሞክሩ። የሰውን መንፈስ ረብሻችሁ የምታገኙት እርካታ ይቅርባችሁ። ፅፈን መፅሀፍ አሳትመን የምንለወጥ መስሏችሁም ከሆነ ተሳስታችሁዋል። ገበያው እንዴት ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ ባወቃችሁ። ይመቻችሁ። 💚
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.