cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዜጋ ሚድያ- Zega Media የኢትዮጵያውያን ትክክለኛና ታማኝ የመረጃ ምንጭ

The voice of voiceless in Ethiopia ስለእውነት ለኢትዮጵያውያን እንሰራለን ይህ የዜጋ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናል ነው!!! ትክክለኛ፣ እውነተኛና ወቅታዊ መረጃ ለሁሉም ዜጎች ከዜጋ ሚዲያ! News and analysis on current National issues

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
211
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለሐሙስ ነሐሴ 5/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ የሕዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ዛሬ ወይም ነገ ተጠናቆ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ይፈሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋዜማ ከግድቡ ከፍተኛ ሃላፊዎች ሰምታለች። ባለፈው ዓመት ግድቡ እንዲይዝ የታቀደው 13.4 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ቢሆንም፣ የያዘው ግን 1.8 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ብቻ እንደሆነ ዋዜማ ተረድታለች። ዘንድሮ ግን የግድቡ ከፍታ 600 ሜትር ደርሶ፣ ተጨማሪ 14 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ይይዛል ተብሏል። የሁለተኛ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ተከላና ሙከራም ተጠናቆ ኃይል ለማመንጨት ዝግጁ ሆኗል። 2፤ በደቡብ ክልል የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ጉባዔ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል። የጉባዔው አጀንዳ የክልልነትo አደረጃጀትና ጥያቄ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። በተያያዘ፣ ትናንት የዞኑ በርካታ ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ እንዳስተናገዱ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ነዋሪዎች የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉት፣ ዞኑ ከሌሎች አጎራባች ዞኖች ጋር ባንድ ክልል ስር እንዲዋቀር መንግሥት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በመቃወም ነው። 3፤ ከሰሜን ኢትዮጵያ የተነሱ ከ100 በላይ የሕዝብ ማመላለሻ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ደብረ ብርሃን ላይ እንደታገዱ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስነብቧል። የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ትናንት ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን መንገድ ዘግተው መመልከቱን ጋዜጣው ገልጧል። የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሹፌሮችም፣ የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ተሳፋሪዎችን በብሄር እየለዩ እንደሚመልሱ እና ተሽከርካሪዎችን ለማሳለፍ የገንዘብ ጉቦ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። 4፤ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሰኞ'ለት ወደ ጋምቤላ ክልል ገብተው ባንድ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ሁለት ስደተኞችን መግደላቸውን የክልሉ መንግሥት ለቪኦኤ ተናግሯል። ታጣቂዎቹ አንድ ስደተኛ ጭምር አቁስለው፣ ሁለት ሕጻናትን አፍነው መውሰዳቸውን የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ገልጧል። ታጣቂዎቹ በስደተኞች መጠለያ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ያሁኑ ሁለተኛቸው ነው። ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎችን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቆም ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል። 5፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት የክልሉን የብዝሃ ከተሞች አዋጅ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁን የአገር ውስጥ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ዛሬ የጸደቀው አዋጅ፣ ክልሉ አራት መቀመጫ ከተማዎች እንዲኖሩት የሚደነግግ ነው። በአዋጁ መሠረት፣ ቦንጋ ከተማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ፣ ሚዛን አማን የዳኝነት አካሉ መቀመጫ፣ ተርጫ የክልሉ ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ቴፒ የብሄረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫ ይሆናሉ። 6፤ የዓለም ምግብ ድርጅት ለትግራይ ክልል 700 ሺህ ሊትር ነዳጅ በጅቡቲ ወደብ በኩል ማስገባቱን ሪፖርተር ዘግቧል። ዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች ለትግራይ ለሰብዓዊ ዕርዳታ አገልግሎት የሚውል ነዳጅ ያለ ቀረጥ እንዲያስገቡ ፈቅዷል። ባሁኑ ወቅት 14 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች አፋር ክልል ሠመራ ከተማ እንደደረሱ ዘገባው አመልክቷል። ተመድ ለክልሉ ሰብዓዊ ዕርዳታ በወር ሁለት ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ያስፈልጋል ይላል።
Show all...
" ሶስተኛው የግድቡ ሙሌት በሂደት ላይ ይገኛል " - ኢ/ር ክፍሌ ሀሮ ዛሬ የ2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጫ ማብሰሪያ ስነስርዓት ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሀሮ ከተናገሩት ፦ " ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዚህ በያዝነው ዓመት በ2014 ለማከናወን ከተያዙ አብይ እቅዶች መካከል በሁለት ዩኒት ማለትም በሁለት ታርባይንና ጀነሬተሮች ኃይል ማመንጨት አንዱ ሲሆን ይህ እቅድ ተሳክቶ በ2ቱም ዩኒቶች ኃይል ማመንጨት ተችሏል። ከለውጡ በኃላ በፕሮጀክቱ ላይ የማስተካከያ እርምጃ ከተወሰደ በሶስት ዓመታት ውስጥ በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሃ ማስተላለፊያ የብረታብረት ስራዎችን በማጠናቀቅ የመካከለኛውን የግድብ ከፍታ ከሃያ አምስት ሜትር ወደ መቶ ሜትር ማድረስ ተችሏል። እንደዚሁም የግድቡን ግራና ቀኝ በትንሹ እስከ ስድስት አርባ አምስት የደረሰም አለ ወይም ከባህር ጠለል በላይ እስከ ስድስት አርባ አምስት ወይም መቶ አርባ አምስት ሜትር ከመሰረት ከፍ ያለ በተጨማሪ በትንሹ እስከ መቶ አስራ አንድ ሜትር ከፍ በማድረግ ሁለት ሙሊቶችን ማከናወን የተቻለ ሲሆን #ሶስተኛው_ሙሊት_በሂደት ላይ ይገኛል ። ከምንም ደረጃ ተነስቶ ሁለት ተርባይኖች እና ጄነሬተሮች በመትከል ኃይል ማመንጨት ተችሏል። "
Show all...
ሰበር ዜና የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው። የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው እውን መሆኑን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። እንኳን ደስ አላችሁ ! 🇪
Show all...
ለ ረቡዕ ነሐሴ 4/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ መንግሥት የአዲስ አበባ ከተማን እና አዋሳኝ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞኖችን አስተዳደራዊ ወሰን እንደገና ለማካለል ያጠናውን ጥናት ለመተግበር እንቅስቃሴ መጀመሩን ዋዜማ ሰምታለች። ጥናቱ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ እንዲሁም ከኦሮሚያ ወደ አዲስ አበባ የሚካለሉ አካባቢዎችን ለይቷል። ጥናቱ ተግባራዊ እንዲሆን ዝርዝሩ ለገዥው ፓርቲ፣ ለከተማዋ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ተላልፏል። አቃቂ- ገላን: ለገጣፎ፣ የካ አባዶ፣ ቦሌ ቡልቡላ እና ጆሞ ኮንዶሚኒየም- ሁለት የአከላለል ወሰን ለውጥ ተደርጎባቸዋል። 2፤ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ጉባዔ እንደሚቀመጥ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ሆኖም የአስቸኳይ ጉባዔው አጀንዳ ምን እንደሆነ እንዳልተነገራቸው የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል። አንዳንድ አባላት ግን አጀንዳው በዞኑ የክልልነት አደረጃጀት ጥያቄ ላይ ለመወያየት እንደሚሆን ግምታቸውን ሰጥተዋል። በቅርቡ በርካታ የደቡብ ክልል ዞኖች መንግሥት ባቀረበው የክልል አደረጃጀት ጥናት መሠረት በሁለት ክልሎች ለመደራጀት ሲወስኑ፣ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ግን እስካሁን በውሳኔ ሃሳቡ ላይ በይፋ ውሳኔ አላሳለፈም። 3፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በገጠመው ከፍተኛ የበጀት እጥረት ሳቢያ የአዲስ ሠራተኞች ቅጥር ማቆሙን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ መናገራቸውን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ለክልሉ ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፣ በአዲሱ ክልል በመንገዶች፣ ድልድዮች እና በመጠጥ ውሃ ግንባታዎች አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ውስንነት የታየው በበጀት እጥረት ሳቢያ መሆኑን ገልጸዋል። 4፤ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ስደተኞች የሚውል 75 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አዲስ ባወጣው መረጃ አስታውቋል። ኮሚሽኑ የገንዘብ ዕርዳታ ጥሪውን ለለጋሽ አገራት እና ድርጅቶች ያቀረበው፣ በአገሪቱ ለሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች ነው። ሁለቱ ኮሚሽኖች ይህንኑ የገንዘብ ድጋፍ የጠየቁት፣ ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ለስደተኞቹ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶችን ለማሟላት እንደሆነ ገልጸዋል። 5፤ ኬንያዊያን አምስተኛውን የሪፐብሊኳን ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ትናንት በሰላማዊ መንገድ ድምጽ ሰጥተዋል። የምርጫ ኮሚሽኑ እስከ ዛሬ ምሽት 12 ድረስ በአጠቃላይ ከተሰጠው 12 ሚሊዮን ድምጽ ውስጥ ግምሹን ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አድርጓል። በከፊል ይፋ በተደረገው ውጤት ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ በተቀራራቢ ውጤት በመፎካከር ላይ ይገኛሉ። በሕጉ መሠረት ምርጫ ኮሚሽኑ የተረጋገጠውን የመጨረሻ ውጤት ለማወጅ ሰባት ቀናት አሉት። 6፤ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በሱማሊያ ላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲያነሳ ጥሪ ማድረጋቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል። መሴቪኒ ሱማሊያ ጸጥታ ኃይሏን እና ሌሎች መንግሥታዊ ተቋማቷን እንድትገነባ፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ተከታታይና በቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግላትም ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ይህን ያሉት፣ ከሱማሊያው አቻቸው ሐሰን ሞሐመድ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ከኡጋንዳ ጋር የጸጥታ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ስምምነቶችን በመፈራረም የሦስት ቀናት የኡጋንዳ ጉብኝታቸውን ዛሬ አጠናቀዋል። 7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ2502 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ2952 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 60 ብር ከ4227 ሳንቲም፣ መሸጫው 61 ብር ከ6312 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ53 ብር ከ4624 ሳንቲም ሲገዛ እና በ54 ብር ከ5316 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል።
Show all...
ለረቡዕ ነሐሴ 4/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ ጸረ ሰላም ባላቸው 28 ታጣቂዎች ላይ የኃይል ርምጃ መውሰዱን የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ለዶይቸቨለ ተናግሯል። የክልሉ ጸጥታ ኃይል በወሰደው ርምጃ አምስት ታጣቂዎች እንደተማረኩ ቢሮው ገልጧል። ታጣቂዎቹ ርምጃ የተወሰደባቸው፣ አንድ የወርቅ ማውጫ ቦታ ለመቆጣጠር ሙከራ ባደረጉበት ወቅት እንደሆነ ተገልጧል። አካባቢው የቤንሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ የሚንቀሳቀስበት ሲሆን፣ ቡድኑ ግን ከታጣቂዎቹ ጋር ግንኙነት የለኝም ብሏል። 2፤ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ አገራቸው የሱማሊያውን ነውጠኛ አልሸባብ ለመዋጋት የድርሻዋን መወጣት እንደምትቀጥል በኡጋንዳ የሦስት ቀናት ጉብኝት ላይ ላደረጉት የሱማሊያው አቻቸው ሐሰን ሞሐመድ እንዳረጋገጡላቸው የሁለቱ አገራት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሁለቱ መሪዎች በሰጡት የጋራ መግለጫ፣ ሙሴቪኒ ሱማሊያዊያን አልሸባብን ለማሸነፍ ከጎሰኝነት ወጥተው ጠንካራ ብሄርተኝነት መገንባት አለባቸው በማለት መክረዋል። ሙሴቪኒ ሱማሊያ የምሥራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ አባል እንድትሆን ድጋፋቸውን እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። 3፤ ኬንያዊያን ትናንት አምስተኛውን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ድምጽ ሰጥተዋል። ለምርጫው ከተመዘገቡት 22 ሚሊዮን ድምጽ ሰጭዎች፣ ድምጽ የሰጡት 12 ሚሊዮን ያህሉ ወይም 56 በመቶዎቹ እንደሆኑ ምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል። የምርጫ ውጤቱ ነገ ዛሬ እንደሚገለጽ ይጠበቃል። እስከ እክል ሌሊት በተገለጸው ውጤት ግን ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ በተቀራራቢ ድምጽ በመምራት ላይ ናቸው። 4፤ አሜሪካ ለአፍሪካ ወታደራዊ ዕዟ (አፍሪኮም) ዋና አዛዥነት አዲስ የሾመቻቸው ጀኔራል ማይክል ላንግሌይ ሃላፊነታቸውን ትናንት በዕዙ ዋና መቀመጫ የጀርመኗ ስቱትጋርት መረከባቸውን አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሥልጣን ርክክቡ ወቅት፣ ተሰናባቹ የአፍሪኮም ዋና አዛዥ ጀኔራል ስቲፈን ታውንሴንድ አሜሪካ አፍሪካን ፈጽሞ ልትዘነጋት እንደማይገባ ተናግረዋል። አዲሱ የአፍሪኮም ዋና አዛዥ ጀኔራል ማይክል ላንግሌይ ወታደራዊ ዕዙን በመምራት ሁለተኛው ጥቁር አሜሪካዊ ናቸው። 5፤ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ለአፍሪካ የቀረጸችውን አዲሱን ስትራቴጂ ደቡብ አፍሪካ ላይ ይፋ ካደረጉ በኋላ ትናንት ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ገብተዋል። ብሊንከን በኮንጎ ቆይታቸው በቀጠናዊ ጸጥታ ማለትም በኮንጎ እና ሩዋንዳ መካከል ሰላም ስለማውረድ እና በምሥራቅ ኮንጎ ስላለው ግጭት ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቲክሸስዴ ጋር ይወያያሉ። የብሊንከን ጉብኝት ሩሲያ እና ቻይና የኮንጎን ስትራቴጂካዊ ማዕድናት እንዳይቆጣጠሩ ያለመ ጭምር እንደሆነ ተገምቷል።
Show all...
ለማክሰኞ ነሐሴ 3/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ የደመወዝ እርከን፣ የሥራ መደቦች ምዘና እና የደረጃዎች ምደባ ደንብ ሥራ ላይ ማዋሉን ዋዜማ ተረድታለች። በአዲሱ ደንብ መሠረት፣ የደረጃ አንድ ሠራተኞች የደመወዝ መነሻ 1 ሺህ 100 ብር ሲሆን፣ ጣሪያው ደሞ 2 ሺህ 079 ብር እንዲሆን ተደርጓል። ከፍተኛው የደመወዝ መነሻ ደሞ 20 ሺህ ብር እንዲሁም ጣሪያው 26 ሺህ ብር 959 ብር እንዲሆን ደንቡ ደንግጓል። 2፤ መንግሥት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ፣ ካፋ እና ኮንታ ዞኖች ጸጥታ ለማስፈን ሠራዊት ሊያሠማራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ መግለጣቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ሠራዊቱ በዞኖቹ የሚሠማራው፣ የከብት ዝርፊያና የሰው ግድያ ፈጳሚ ወንጀለኞች መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት የወንጀል ድርጊቶችን እንዲቆጣጠር ነው። ነጋሽ ይህን የተናገሩት፣ ከክልሉ ምስረታ ጀምሮ ያለውን የክልሉን መንግሥት የሰባት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክተው በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ላለው የክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ነው። 3፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያምን የብሄራዊ አደጋ ስጋት እና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው እንደሾሙ ሪፖርተር ከምንጮቼ ሰምቻለሁ በማለት ዘግቧል። አምባሳደር ሽፈራው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት፣ በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በታሰሩት ምትኩ ካሳ ምትክ ነው። አምባሳደር ሽፈራው በደቡብ አፍሪካ በአምባሳደርነት ከመሾማቸው በፊት፣ የፌደራል ጉዳዮች እና የትምህርት ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። 4፤ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ዛሬ ቤት ውስጥ የመቀመጥ እና የሥራ ማቆም አድማ እንደተደረገ አዲስ ማለዳ ዘግቧል። በከተማዋ የመንግሥት ተቋማት፣ የግል መደብሮችና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቆሞ የዋለው፣ ጉራጌ ዞን ከአጎራባች ዞኖች ጋር በአዲስ ክልል ስር እንዲደራጅ መንግሥት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በመቃወም እንደሆነ ታውቋል። ስልጤ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ሀዲያና ሀላባ ዞኖች ከየም ልዩ ወረዳ ጋር ባንድ ክልል ስር ለመደራጀት የወሰኑ ሲሆን፣ ጉራጌ ዞን ግን የራሱን ክልል ለመመስረት ለፌደሬሽን ምክር ቤት ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን ይገልጻል። 5፤ ኢትዮጵያ አልሸባብን ለመምታት ሁለት ሺህ ያህል ወታደሮቿን ወደ ሱማሊያዋ ጁባላንድ ራስ ገዝ ጌዶ አውራጃ ማሰማራቷን የአካባቢው ባለሥልጣናት ለቪኦኤ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይልም በዚሁ አካባቢ በአልሸባብ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የአውራጃዋ ባለሥልጣናት ገልጸዋል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ወደ ጌዶ አውራጃ ስለማስገባቷና የአየር ድብደባ ስለመፈጸሟ ሞቃዲሾ በይፋ የሰጠችው አስተያየት የለም። አሜሪካም በሒራን ግዛት በአልሸባብ ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሟ ተሰምቷል። 6፤ ኬንያዊያን አምስተኛውን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ዛሬ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። የመራጮች ቁጥር ግን ከተጠበቀው በታች ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ከአራቱ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች መካከል ምርጫውን ያሸንፋሉ ተብለው ትልቅ ግምት የተሰጣቸው፣ የአሁኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና አንጋፋው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ እና የቀድሞው ጥምር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ ናቸው። ሩቶ እና ኦዲንጋ፣ የምርጫውን ውጤት በጸጋ እንደሚቀበሉ ቃል ገብተዋል። 7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ2398 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ2846 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 60 ብር ከ3757 ሳንቲም፣ መሸጫው 61 ብር ከ5832 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ53 ብር ከ2689 ሳንቲም ሲገዛ እና በ54 ብር ከ3343 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል።
Show all...
ማክሰኞ ነሐሴ 3/2014 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎና ዋግኽምራ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለመግባት መቸገራቸውን መንገደኞች መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። መንግሥት በበኩሉ፣ የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች መንገደኞች ላይ ጥብቅ ፍተሻ የሚያደርጉት በጸጥታ ስጋት ሳቢያ መሆኑን ገልጧል። የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች በከተማዋ መዳረሻ ላይ የሚመልሷቸው የከተማዋ ነዋሪነት መታወቂያ አልያዛችሁም በማለት እንደሆነ ተናግረዋል። 2፤ ኦነግ የአፍሪካ ኅብረት ሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት የብሄር ግጭት አድርጎ አቅርቧል ሲል ተችቷል። ኦነግ መንግሥት ግጭቱን የብሄር ግጭት የሚያስመስለው ለአማጺያን ፖለቲካዊ ጥያቄ ምላሽ ላለመስጠት መሆኑ እየታወቀ፣ አፍሪካ ኅብረት የመንግሥትን አመለካከት ማንጸባረቁ ገለልተኛነቱ ላይ ጥያቄ ያስነሳል ብሏል። የመንግሥት ወታደሮች በክልሉ ስለገደሏቸው ንጹሃን ኦሮሞዎች ኅብረቱ አልጠቀሰም ያለው ኦነግ፣ ኅብረቱ አቋሙን እንዲያስተካክል ጠይቋል። 3፤ በ1983 ዓ፣ም ሥልጣኑን በኃይል የተነጠቀውን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲን እንደገና ለማቋቋም ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖች ከቦርዱ የምዝገባ ፍቃድ ምስክር ወረቀት እየተጠባበቁ መሆኑን መናገራቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የኢሠፓ ዳግም ምስረታ አደራጆች የፓርቲ ማቋቋሚያ ሰነዶቻቸውን ባለፈው ሰኔ ወር እንዳስገቡ ቦርዱ ለዜና ምንጩ አረጋግጧል። አንጋፋውን ፓርቲ ኢሠፓን መልሰው በማደራጀት ሕጋዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ካሉት መካከል፣ የቀድሞው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጭምር እንደሚገኙበት አደራጆቹ ተናግረዋል። 4፤ ኬንያዊያን ሁለት የሥልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ለመተካት ለሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዛሬ ድምጽ ይሰጣሉ። ለምርጫው ከ22 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል። በምርጫው ያሸንፋሉ ተብለው የሚጠበቁት ዕጩዎች፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶና አንጋፋው ተቃዋሚ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ ናቸው። የምርጫው ውጤት በሁለት ቀናት ውስጥ ይገለጣል ተብሎ ይጠበቃል። 5፤ ታንዛኒያ ዓመታዊውን የናይል ተፋሰስ አገራት ሚንስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በነሐሴ አጋማሽ እንደምታዘጋጅ የቀጠናው ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሚንስትሮቹ ስብሰባ በተፋሰሱ ላይ እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ይገመግማል።የተፋሰሱ አገራት ሚንስትሮች ምክር ቤት በናይል ወንዝ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን የሚነድፍ እና አፈጻጸማቸውን የሚከታተል ከፍተኛው ውሳኔ ሰጭ አካል ነው።
Show all...
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ምክር ቤት በጋዛ ጦርነት ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል፡፡ ስብሰባዉ በርካታ አባላት በእስራኤልና በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ከደረሱበት የተኩስ አቁም ስምምነት በኃላ እስራኤል ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በአካባቢው ላይ ስጋት መፍጠሩን ተከትሎ ነዉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የመካለኛዉ ምስራቅ ተወካይ ቶር ዌስላንድ የትኛዉም የእርስ በርስ ጦርነት ለእስራኤልም ሆነ ለፍልስጤም ከባድ መዘዝን እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል፡፡ የተኩስ አቁም ስምምነቱም ደካማ ነዉ ሲሉ ተችተዋል፡፡ የሩሲያ አማባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ ምክር ቤቱ ይህ ሁኔታ በጥልቅ ያሳሰበዉ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ተጀምሮ የነበረዉ ወታድራዊ ግጭት እንዲቀጥልና ቀደም ሲል በጋዛ የነበረዉ አስከፊ የሰብአዊ ሁኔታ እንዲባባስ ሊያደርግ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡ እስራኤል ባሳለፍነዉ አርብ በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረገችዉ ተከታታይ የቦምብ ድብደባ ቢያንስ 44 ፍልስጤማዉያን ንጹሀን ዜጎች መገደላቸዉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸዉን የፍልስጤም ጤና ሚንስተር ገልጸዋል፡፡ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን በምላሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ቢተኩስም አብዛሃኛዎቹ ኢላማቸውን ሳቱ ናቸው ተብሏል፡፡ @ethiofm
Show all...