cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

🌹بسم الله الرحمان الرحیم🌹 🔺 طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ!! ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው!! 📖እስላማዊ ትምህርቶች 📖አስተማሪ ታሪኮች 📖 ጥያቄና መልሶች ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ያድርሱን @yeilmkazna_bot 📝በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ይገኛሉ።

Show more
Advertising posts
6 541
Subscribers
-424 hours
-387 days
-7530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መደመጥ ያለበት ግጥም‼️ ======================= ኢሳን አምላኪዎች ጥያቄዎች አሉን እንጠብቃለን ምላሽ እንድትሰጡን ======================= 📮 በሚል ርዕስ ለእየሱስ {ኢሳ} አምላኪዎች በግጥም መልኩ የቀረበ ግልፅ የሆነ ጥያቄ። [ከኢብኑል ቀይም ግጥም የተተረጎመ] 🎙 ኡስታዝ አቡ ሰልማን ዓብዱልመጂድ ቢን ወርቁ አላህ ይጠብቀው። 📆 በቀን 20.08.2012 E.C 📆 ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇 📎 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/16283 ♡ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲ ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ
Show all...
👍 4🏆 1
✍      ንጉሶቹ የሚወረወሩበት ጫካ!! ልብ ላለው ልብ የሚነካ ታሪክ   አንዲት ጉደኛ ሀገር አለች። በዚች ሀገር ውስጥ ከሚደረጉ አስገራሚ ነገሮች አንዱ፦ በሀገሪቷ ላይ የሚነግሰው የትኛውም ንጉስ መንገስና መምራት የሚችለው እስከ ተገደበለት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው። ልክ ያንን ጊዜ ሲጨርስ በሀገሪቷ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ወደ ለንጉሶች መጣያ የተዘጋጀ ጫካ ይወሰድና ይጣላል።    ጫካው የሚገኘው ከሀገሪቷ ራቅ ያለ ቦታ በመሆኑ የሀገሪቷ ህዝቦች ስለ ጫካው ብዙም ጠንቅቀው አያውቁም። ብቻ ግን የንጉሱ ጊዜ ሲያበቃ ለዚህ ተግባር የተመደቡ ሰዎች ወስደው ጥለዉት ይመለሳሉ።   ንጉሱ ከዝያ በኋላ ተመልሶ አይመጣም። በምን ሁኔታ እንደ ሚኖር? በምን ሁኔታ እንደ ሚሞት የሚታወቅ ነገር የለም።   ንጉሱም ምንም እንኳ በንግስናው ዘመን የፈለገውን ማድረግ የመቻል መብት ቢኖረውም ጫካውን የሚያየው ግን ተወስዶ በሚጣልበት ቀን ነው።   ነገሩ በዚህ መልኩ እየሄደ ሳለ በሀገሪቷ ላይ ተራው ይደርሰውና አንድ ንጉስ ይነግሳል።   ይህ ንጉስ በጣም አዋቂና በሳል ስለ ነበር በስልጣን ዘመኑ እንደ ፈለገ ተመቻችቶ በመጨረሻም በማያውቀው ጫካ መጣል አልፈለገም።      "ታድያ ምን አደረገ❓"    ከዕለታት አንድ ቀን አገልጋዮቹን በማስከተል ንጉሶች የሚጣሉበት ጫካ ምን ዐይነት እንደ ሆነ እንየው ብሏቸው ይሄዳሉ። [በንግስና ዘመኑ የፈለገውን ማድረግ ስለ ሚፈቀድለት] ወደ ጫካው ሄደው ሲያዩ; ጫካው፦   በአስፈሪ አራዊቶች የተሞላ፣    እሾሃማ እና የሚያቆስሉ ዛፎች የበዙበት፣ አየሩ በመጥፎ ጠረን የተበከለ እና   በአጠቃላይ በጣም የሚያስፈራ ጫካ ሆኖ አገኙት።    በዚህ ጊዜ ይህ አስተዋዩ ንጉስ ነገ ወደዚህ ጫካ ከመጣሉ በፊት የቤት ስራውን መስራት ጀመረ። በስልጣኑ ከሚያገኘው ገቢ አብዛኛውን ወደዚህ ጫካ ወጪ በማድረግ ጫካው እንዲመነጠር፣    አስፈሪ አውሬዎቹ እንዲታደኑ፣      እሾሃማ ዛፎች እንዲወገዱ፣        ማራኪና ጥሩ ማዕዛ ያላቸው ተክሎች እንዲተከሉ በማድረግ ያ አስፈሪ የነበረው ጫካ ወደ ውብ መናፈሻነት ቀየረው።   የማይደርስ የለምና የንግስና ማብቂያ ቀኑ ደርሶ ወደ ጫካው ሲጣልም እንደ ቀደምት ነገስታቶች ስቃይና እንግልት ሳይሆን ውብና ማራኪ የሆነ ህይወት መኖር ጀመረ። ♻️እዚህ ጋ ቆም በልና ታሪኩን በምናብህ ቃኘው!! ናልኝማ ወዳጄ👇 እስከ አሁን ታሪኳን የነገርኩህ ሀገር፦ 👉የምስራቅ አውሮፓዋ …… ሀገር አይደለችም። እስከ አሁን ታሪኩን የነገርኩህ ንጉስ፦ 👉ከላይ የተጠቀሰቿ ሀገር ንጉስም አይደለም። ሀገሪቷ………     ያለንባት ዱንያ ናት። ንጉሶቹ………     እኔና አንተ ነን። ንግስናው………    የዱንያ ሕይወት ነው። ንግስናችን (ሕይወታችን) ሲያልቅ የምንጣልበት ጫካ………     ቀብራችን ነው። ንጉሶቹ ወስደው የሚጥሉት………      ቀባሪዎቻችን ናቸው። ጫካው ውስጥ ያሉ አስፈሪዎች………   የቀብር ውስጥ ጠያቂዎች ናቸው። ንጉሱ ወደ ጫካው ግንባታ ወጪ ያደረገው………   መልካም ስራው ነው። ♻️ጥያቄው👇 በዱንያ ሕይወታችን (ንግስናችን)፦ 💫አስፈሪው ቀብራችን እየገነባንና እያስዋብን ነን?? ወይንስ………… 💫በአስፈሪው ቀብር ተወስደን እስከ ምንጣል ቸላ ብለነዋል?? https://t.me/AbuReyan_3030    https://t.me/AbuReyan_3030
Show all...
📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

🌹بسم الله الرحمان الرحیم🌹 🔺 طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ!! ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው!! 📖እስላማዊ ትምህርቶች 📖አስተማሪ ታሪኮች 📖 ጥያቄና መልሶች ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ያድርሱን @yeilmkazna_bot 📝በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ይገኛሉ።

👍 11
ኪታቡ ተውሂድ ነው
Show all...
▫️አንዲት እናት ወደ አንድ ሸይኽ ፈትዋ ለመጠየቅ ትመጣና 🗣ለሸይኹ " ሸይኽ ሆይ የልጆቼ እንቅልፍ በጣም ከባድ ነው ፣ ለፈጅር ሰላት እነሱን መቀስቀስ ደከመኝና ምንድነው መፍትሄው? " በማለት ጠየቀች ። 🗣ሸይኹም " ሙቀት መቆጣጠሪያው ተቃጥሎ እሳት ቢተፋ ኖሮ ምን ታደርጊ ነበር? " አላት 🗣እናት " እቀሰቅሳቹዋለሁ " አለች 🗣ሸይኹ " ግንኮ እንቅልፋቸው ከባድ ነው " አላት 🗣እናት " በአላህ ይሁንብኝ አንገታቸውን እየጎተትኩ ቢሆንም እቀሰቅሳቸዋለሁ " አለች 🗣ሸይኹ|| " ይህን የምታደርጊው ከዱንያ እሳት ልታድኚያቸው ነው ፣ ልክ እንደዛውም ከአኺራ እሳት ለማዳን ቀስቅሺያቸው " አላት። ( ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻗُﻮﺍ ﺃَﻧْﻔُﺴَﻜُﻢْ ﻭَﺃَﻫْﻠِﻴﻜُﻢْ ﻧَﺎﺭًﺍ ﻭَﻗُﻮﺩُﻫَﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻭَﺍﻟْﺤِﺠَﺎﺭَﺓُ ﻋَﻠَﻴْﻬَﺎ ﻣَﻠَﺎﺋِﻜَﺔٌ ﻏِﻠَﺎﻅٌ ﺷِﺪَﺍﺩٌ ﻟَﺎ ﻳَﻌْﺼُﻮﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻣَﺎ ﺃَﻣَﺮَﻫُﻢْ ﻭَﻳَﻔْﻌَﻠُﻮﻥَ ﻣَﺎ ﻳُﺆْﻣَﺮُﻭﻥَ ) "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነች እሳት ጠብቁ ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች ፣ ኀይለኞች የሆኑ መላእክት አልሉ ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም ፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡"    💙ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ💙 https://t.me/AbuReyan_3030 https://t.me/AbuReyan_3030
Show all...
📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

🌹بسم الله الرحمان الرحیم🌹 🔺 طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ!! ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው!! 📖እስላማዊ ትምህርቶች 📖አስተማሪ ታሪኮች 📖 ጥያቄና መልሶች ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ያድርሱን @yeilmkazna_bot 📝በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ይገኛሉ።

👍 11
✅ከጁመዓ ቀን ሱናዎች ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️ ‏سنن يوم الجمعة ➊ الغسل ➋ الطيب ➌ السواك ➍ لبس الجميل ➎ قراءة سورة الكهف ➏ التبكير لصلاة الجمعة ➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 🔹ገላን መታጠብ 🔹ሽቶ መቀባት 🔹ሲዋክ መጠቀም 🔹ጥሩ ልብስ መልበስ 🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት 🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ 🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 📌((قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين)) 👉የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል)) 📚 صحيح الجامع - رقم : (6470) 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 https://t.me/AbuReyan_3030 https://t.me/AbuReyan_3030
Show all...
📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

🌹بسم الله الرحمان الرحیم🌹 🔺 طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ!! ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው!! 📖እስላማዊ ትምህርቶች 📖አስተማሪ ታሪኮች 📖 ጥያቄና መልሶች ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ያድርሱን @yeilmkazna_bot 📝በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ይገኛሉ።

👍 2