cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የእረፍት ህይወት

የዚህ Channel አላማው እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰጠንን የእረፍት ህይወት ቅዱሳን እንዲለማመዱ መፅሐፍ ቅዱስን ዋቢ በማድረግ የሚያስተምር ቻናል ነው። !"...ካልታዘዙትም በቀር ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እናማን ነበሩ ? ባለማመናቸው ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን። @yeerefthiwot

Show more
Advertising posts
496Subscribers
No data24 hours
-47 days
-1230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

(መዝሙረ ዳዊት 65 ) ------------ 11፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። 12፤ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። 13፤ ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም። መልካም አዲስ አመት ለሁላችን ! አዲሱ አመት የቅድስና ; የስኬት ; የሰላም ; የጤና እንዲሁም ካለን ነገር ለሌሎች የምናካፍልበት አመት ይሁንልን ።
Show all...
ወንጌልና ተሰሎንቄ ( ክፍል 2 ) ሐዋሪያው ጳውሎስ እና አብረውት ያሉት አገልጋዮች በብዙ ትጋት ና መሰጠት ተሰሎንቄን አገልግለዋል ። በአይሁድ ምክንያት ብዙ መከራን ስለ ወንጌል  ተቀብለዋል ። ሞግዚት ልጅን እንደምትንከባከብ በብዙ ፍቅር ተመላልሰዋል ። ምንም እንኳን መብት ቢኖራቸውም በገዛ እጃቸው ሌሊት ና ቀን እየሰሩ ወንጌልን መስክረዋል ። ወንጌልን ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸውን ሳይቀር  እንኳን ለማከፍል ፈቃደኞች ነበሩ ። ነቀፋ የሌለበትን የፅድቅ ኑሮ በመኖር ታላቅ ምሳሌዎች መሆናቸውን አስመስክረዋል ። ይህ የሐዋሪያቱ የህይወት ምልልስ ለተሰሎንቄዎች ታላቅ ምሳሌ ሆኖላቸዋል ። የክርስቶስን ወንጌል ለመቀበላቸው  አንዱ ምክንያትም   ይኸዉ የህይወት  ጥራት ነው ፤ ስለዚህ የሐዋሪያቱን ህይወት አይተው ወንጌልን ተቀበሉ ።ወንጌልን ሲቀበሉ ግን  የተቀበሉት ወንጌሉን ብቻ ሳይሆን የሐዋሪያቱን ህይወትም ጭምር ነበር ። ከሀዋሪያቱ ከወሰዱት ምሳሌ አንዱ ወንጌልን መመስከር ነው  ። እነዚህ ሰዎች እነሡ የተካፈሉትን ህይወት አፍነው የሚይዙ ሳይሆኑ ሌሎችም መዳንን ያገኙ ዘንድ የምስራቹን ይናገሩ ነበር ። ለወንጌል የነበራቸው ልብ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነበር ።  ወንጌልን በድፍረት በመናገር እነሡም እንደ ሐዋሪያቱ  በዙሪያቸው ላሉ   ምዕመናን ምሳሌ መሆን ችለዋል  ። በመከራ ውስጥ ወንጌልን የመስበክ አርበኞች ናቸው ። የሚያስደንቅ ህይወት  - የሚያስደንቅ ምሳሌ ። ይቀጥላል
Show all...
ዋነኛው የስብከቶቻችን ችግር ምንጭ የትኩረት መዛነፍ ይመስለኛል፤ የይዘት ጉዳይ ለማለት ነው። እዚህም፣ እዚያም ታዳሚዎችን ለማስደሰት ዐልመው የተነሡ ሰው ተኮር መልእክቶች የመለኮትን ማእከልነት ማግለላቸውን ቀጥለዋል። በቀላሉ ቤተ እግዚአብሔር ከትወና ቤትነት በመጠኑ ብቻ ለየት ይል ዘንድ የተገደደ ይመስል ሕዝብ አጫዋችነት በመደዴ እየተንሰራፋ መጥቷል። እናም ስብከት አድማጮችን ወደ ማሣቅና ማዝናናት አገልግሎት ተለውጧል። የአደባባዮ እንደምናዳምጠው ፥ የስብከቱ መርሓ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሰባክያን በሣቅ ታፍነው እየተንከተከቱና በሁካታ "ድብልቅልቃቸውን የሚያወጧቸው" ጉባኤያት በየከተማችን ሞተዋል። ወዘበሬታ በቃለ እግዚአብሔር ምትክ ለሕዝቡ እየቀረበልን ነው። . ስብከት እግዚአብሔር "ያኔ"፣ "እዚያ" ለነበሩ "እኒያ" ሰዎች የተናገረውን መልእክት "ዛሬ"፣ "እዚህ" ላለን "ለእኛ" ማምጣት ነው። የዚህ አገልግሎት ማእከሉ መለኮት ሲኾን ኅላፊነቱ ታላቅ ነው። መላዓለሙን ከመነገር በሚያልፍ ሉዓላዊ ምጋቤው የሚያስተዳድረውን ምጡቅና ኢውስን አምላክ ሐሳብ፣ እጅግ በብዙ ውሱንነቶቹ ለተሞላው የሰው ልጅ ማቅረብ ነው- የሰባኪ ኀላፊነት። ይህን ኀላፊነት እንዲወጣ በጸጋ የተመረጠው ያው ውሱን የኾነው የሰው ልጅ ነው- ሰባኪው። ይህ እውነት ምን ይጠልቅ፣ ይህስ እውነት ምን ይረቅ! . የስብከት ዘዴዎች አንደበተ ርቱዕ ሊያደርጉን ይችላሉ። ለእውነተኛ ሰባኪነት የሚያስፈገን ግን ነገረ መለኮት ነው (ትምህርት ቤት ገብቶ ነገረ መለኮት መማር ለማለት ተፈልጎ አይደለም)። የእግዚአብሔር ዐደራ በታማኝነት በመወጣት የምናስተላልፈው ጤናማ ነገረ መለኮታዊ መልእክት በሰዎች ሕይወት ውስጥ ለውጥ ያመጣል። የክርስቶስ ወንጌል እውነት ከጥፋት በማዳን ሕይወት ያጎናጽፋልና። የትሩፋን ናፍቆት፣ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን
Show all...
የተሰሎንቄ ቤተ -ክርስትያን በመከራ ውስጥ ያበበች ቤተ ክርስትያን ነበረች ። በመለወጣቸው ምክንያት በተበሳጩ   አይሁዶች  ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል ።  ። ነገር ግን ምንም ያህል መከራ ቢበዛባቸውም  ወደ ኃላ ሚሉ አልነበሩም ። ይልቁንም መከራውን ከመንፈስቅዱስ ደስታ ጋር ተቀበሉት ። ከነ ጳውሎስ ጋር የመከራዎቻቸው ተካፋይ በመሆን ተጋድለዋል ። በእምነታቸው ፅናት እና ተግባር ፡ በፍቅራቸው መስዋዕትነት ና ድካም እንዲሁም ደግሞ ፅኑ በሆነው ሰማያዊ ተስፉቸው ምክንያት የተመሰከረላቸው አማኞች ነበሩ ። በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ ስለ ህይወታቸው የሚመሰክሩላቸው በህያው እምነት የሚመላለሱ የተግባር ክርስቲያኖችም ናቸው ። በተሰሎንቄዎች ዘንድ እንዲ አይነቱን ፅናት እና መጋደል ያመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ላይ ያነጣጠረ ህይወት ስለ ነበራቸው ይመስለኛል  ። ከሚመጣው ቁጣ የሚያድናቸውን እና በክብር ህይወታቸውን የሚቀይረውን ጌታ ይናፍቁ ነበር ፤ ስለዚህም በእምነታቸው ለመፅናት ከዚህ ተስፉ ውስጥ ሀይልን አገኙ ። በክርስትና ህይወታችን ወደ ፊት ለመቀጠል ከእነዚህ ሰዎች ህይወት የምንማረው ቁም ነገር አለ ። የመከራ ንፋስ እንዳይነቀንቀን በተስፋ የመሻገር ምሳሌዎቻችን ናቸው ። በእምነት ፈተና ውስጥ የጌታን መምጣት ና መዳንን ተስፉ ማድረግ በፅናት ያቆማል ። በምድር አዙሪት ተለክፎ ላለመጠላለፍ ሰማይ ላይ ማንጋጠጥ ሁነኛ  መፍትኤው ነው ። ኢየሱስ ይመጣል በእምነት ፅኑ !! ይቀጥላል
Show all...
ለአምላክ ሰው መሆን በራሱ ውረደት ነው ። (በትንሹ የሰው ሕይወት ) 👉👉 'ሰው' ማለት በአንድ ግዜ በአንድ ስፍራ ብቻ የምገኝ መልኩም ጥቁር ወይም ቀይ በመባል የምታወቅ  ቁመቱም አጭር ወይም እረጅም ሰውነቱም ወፍራም ወይም ቀጭን ስሆን ከልተመገበ መኖር የማይችል በሕይወት ለመቆየት መብላትና መጠጣት ከዛም ለመተንፈስ oxygen የግድ የሚስፈልገው ከበላና ከጠጣ ደግሞ መፀዳዳት የግድ የሆነበት ቀንና ምሽት የሚፈራረቁበት ሀይልን ለመገኘት መተኛት ግድ የሆነበት ስጋውን በልብስ የመሸፈን ግዴታ ያለበት ሌላም ሌላም ብዙ ብዙ እለት ተእለት የሚፈፅሟቸው አሰልቺ ተግባራት ያሉት ነው። እና ምን ለማለት ነው ????????? ?????????? ፣ፊልጵስዩስ 2¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ ⁸ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። 👉ለአምላክ(ያህዌ) ሰው መሆን በራሱ ውርደት ነው። ✋ 👆ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ሰው የሆኑ  ሁሉ እነዚህን ተግባራት ይፈፀማሉ።። እንደምናውቀው  እየሱስ ክርሰቶስ ፍፁም ሰው ነበር ። 👉እናማ በአንድ ግዜ በሁሉ ስፍራ ይገኝ የነበረው አምላክ ድንገት በአንድት ከተማ የዮሴፍ ልጅ እየተባለ በቁመት ተወስኖ ደም ግባት የሌለውን መልክ ይዞ እድሜ እየቆጠረ መኖር ጀመር የዮሴፍ ልጅ አደጋ እየተባለ እድገቱ በሰው እይታ ውስጥ ሆና  👉 እርሱ እራሱ ምድርም ታብቅል ብሎ የፈጠረውን እንጨት ወንበር ጠረጴዛ አድራጎት ከአባቱ ገር ይሰራ ጀመር 👉የብርታት ሁሉ ባለቤት የነበረው እሱ ይደክሞው ጀመር 👉የጥጋብ ሁሉ ምንጭ የነበረ አምላክ ድንገት ተራበ ውሀን የፈጠራ ጥማትን የማያውቅ ድንገት ተጠማ 👉የብርሃነት ሁሉ አምላክ የነበረ ማንም ልያየው በማይችል በረሃን የምኖር ድንገት ግን ቀንና ምሽት በሚባሉ የሰአት ልዩነት ወስጥ ልያልፍ ፈቀደ 👉 የዘላለም ፈጠረ የነበረው እሱ አንድ ሁለት እያለ እድሜውን ይቆጠር ጀመር 🙆🙆 #እና ለአምላክ ሰው መሆን ውረደት አይደለም  ብርሃናት እንዴ ልበስ የሆኑለት ጌታ ወርዶ የጨረቃ ልብስ ሲለብስ እንደሰው ሲበላ እንደሰው ሲፀዳዳ ከዝህ በላይ ምን ውረደት አለህ?😱😱 #የእየሱስ ክርሰቶስ ውረደት በመስቀል መሞቱ ብቻ ስይሆን እንደሰው መመላለሱም ጭምር ነው ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ክብር እንደሰው ተመላለሱ ለደነን  ለጌታ ለእየሱስ ይሁን አሜን ።።።።።።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Show all...
' የ መስቀሉ ፍዳ ' የኢየሱስ መስቀል ስቃይ የበዛበት ነበር ። ከግርፉቱ እስከ ስቅለቱ እጅግ ተሰቃይቷል ። ጫፍ ጫፉን በአጥንት በተሰገሰገ የሮም ጅራፍ ሰውነቱ ተገርፏል ። ጅራፉ ሰውነት ላይ ሲያርፍ ስጋን የመግፈፍ አቅም ነበረው ። ሮማዊያን እንደ አይሁድ አርባ ጊዜ ሳይሆን እስከፈለጉበት ጊዜ የመግረፍ ልማድ ነበራቸው ። ኢየሱስን እንዳሻቸው ገርፈውታል ። አይኑን በጨርቅ ሸፍነው ጭንቅላቱን በበትር እየመቱ ተሳልቀውበታል ። ንጉስ አክሊል ይደፉ ነበር ና ሊሳለቁበት ስለፈለጉ የ እሾህ አክሊል አርገውለታል ። የንቀታቸው ብዛት ምራቅ ተፍተውበታል ።ንጉሣዊ  ቀይ ልብስ በሹፈት ሄሮድስ አልብሶታል ። ተዋርዷል ። ገርፈው ሲያበቁ መስቀል አሸክመው በግፍ ወደ ጎልጎታ ወስደውታል ። ያሸከሙት መስቀል እንኳን በዛ ጅራፍ ለተገረፈ ምንም ላልሆነ ጤነኛ ሰውም የሚከብድ መስቀል ነበር ። ኢየሱስም ከግርፉቱ የተነሣ መስቀሉ ስለከበደው የ 'ቀሬናው ስምዖን' ' መስቀሉን በመሸከም ረድቶት ነበር ።  የለበሰው ልብስ አንድ ወጥ ስለነበር ሙሉ እርቃኑን አስቀርተው ልብሱን ዕጣ ተጣጥለውበታል (ተከፋፍሎ ለመውሰድ አንድ ወጥ በመሆኑ ስለማይመች ነበር ) ። መስቀል ላይ የእጆቹ አንጓዎች  በወፍራም የ ሮም የብረት ሚስማር ተቸንክረዋል ። እግሮቹም ( ቁርጭምጭሚቱ ላይ ) መስቀል ላይ ተንቸንክረዋል ። ' ሌሎችን አዳነ ፡ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም ' እያሉ ሰዎች የመጣበትን ዕቅድ እንዳይፈፅም ተፈታትነውታል ።  ሰዎች አይተውት ይወዱት ዘንድ ደምግባት እና ውበት አልነበረውም ። ይልቁንም ሰው ፊቱን የሚሰውርበት የባሪያን መልክ ያዘ ።   ' እኛ ሁላችን አላከበርነውም '  ነበር እንዲል መፅሐፋ ። የተናቀ ፡ የተጠላ  ሆነ ። 'እግዚአብሔርም በደዌ ያደቀው ዘንድ ፈቀደ ' ። አሟሟቱ አሰቃቂ ስለነበር ደሙ ከሰውነቱ ፈሶ አልቆ እንደሞተ ይገመታል ። ( by Severe Bleeding ) "  እኔው ነኝ ስቅለቱ " ጀርባው ላይ ሚታየው የጅራፍ ቁስለቱ እጁ ላይ ያረፈው የሚስማር ዉጋቱ በደም የጨቀየው የደም ሰውነቱ የእኔው ደዌ ነበር ይኼው ነው እውነቱ !! ተጣማሁኝ ያለው የጥማት ጩኸቱ የነፍሱ ማቃሳት የፍርሀት ጭንቀቱ የስድቡ ናዳ  የውርደት ንቀቱ የእኔው ስድብ ነበር ይኼው ነው እውነቱ ። የእግሮቹ ችንካር የመስቀል ሸክሙ የጎልጎታው ስቃይ ስብራት ህመሙ የቆረሰው ስጋው የፈሰሰው ደሙ የእኔው ፍዳ ነበር እኔው ነኝ ድካሙ ። መቅበዝበዝ ፡ መንገላታቱ ልብሱን ገፈውበት እርቃኑን መቅረቱ መስቀል ተሸክሞ በግፍ መነዳቱ  የእኔው መስቀል ነበር እኔው ነኝ ስቅለቱ!! ........ይቀጥላል .....
Show all...
የእግዚአብሔር ቁጣ ከፅድቁ እና ከቅድስናው ይመነጫል ። ሀጢአትን በመቅጣት ፍትህን እና እውነትን ያረጋግጣል ። ሀጢአተኛው ስለ እሡ ሀጢአት የሚሞት ካገኘ ግን ከ ሀጢአቱ የመትረፍን ዕድል ያገኛል ።  የእንስሳው ደም በውክልና መሞቱ የእግዚአብሔር ምህረት ማሳያ ነው ። ኢየሡሥ ንፁህ በመሆኑ የራሱን ሞት አልሞተም ። ነውር የሌለውን ደሙን በማፍሰስ የአለሙን ሁሉ ሞት በውክልና ሞተ ። አንዱ ስለ ሁሉ ሞቷልና ።  አመፀኛ ሳይሆን እንደ አመፀኛ ተቆጥሯል ። ሞቱ ከአመፀኞች ጋር እንደሚሆን የተነገረው የመፅሐፍ ቃል ይፈፀም ዘንድ ከወንበዴዎች ጋር ተሰቅሏል ። እኛ እንፀድቅ እና ነፃ እንወጣ ዘንድ እግዚአብሔር ሀጢአት ያላወቀውን ልጁ እንደ ሀጢአተኛ በመቁጠር ሀጢአትን በኢየሱስ ስጋ ላይ ኮንኖታል ። ኢሳያስም ይህንን አለማስተዋለቸውን አይቶ" ማን አስተዋለ ? " ብሎ አዝኖ ነበር ። የራሱን ሞት እንደ ሞተ በማሰብ " በእግዚአብሔር እንደ ተቀሠፈ ቆጠርን "ብሎም ነበር ።በጎልጎታ ተራራ ላይ  ' ብዙ በርባኖችን '  አስፈትቶ እሡ ግን እንደ በግ ታርዷል ። በስርየት ቀን የእንስሳው ስጋ ከሰፈር ወጥቶ ይቃጠል እንደ ነበር ፡ ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም በመውጣት ከሰፈር ውጪ መከራን ተቀብሏል ። ጎልጎታም መጋረጃ ያልጋረደው ይፉዊ ቤተ መቅደስ በመሆን የኢየሡሥ ደም ፈሶበታል ። እንደሌሎቹ ካህናት ሌላ ደም ይዞ ሳይሆን የራሱን ደም ይዞ በመግባት ህያው ሊቀ ካህናችን ሆኗል ።በገዛ ደሙ በመዋጀትም የዋጋችንን ልክ የደሙን ያህል ውድ አድርጎታል ። እነሆ እውነተኛውን ደም በእምነት  የተረጫችሁ ደስ ይበላችሁ ።  ግና ላልተቀበሉት እና ለናቁት የፍርድ ቀን ይመጣል ። ኢየሱስ እንደቀድሞ ሊሰቀል ሳይሆን በአለሙ ላይ ሊፈርድ በክብር ይመጣል ። ያን ጊዜም ያልወለደች መካን ብፅዕት ትባላላች ፡፡ ከዚያ መዐት ለመሰወር ያፌዙበት ሁሉ ወደ ተራሮች ይጣራሉ ። ኮረብቶችንም ውደቁብን ከዚ መዐት ሰውሩን እያሉ ይጣራሉ ፡ የምጥና የሲቃ ቀን ይሆንባቸዋል ። የወጉትም በክብር ያዩታል !! “ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፦ እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፥ ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፦ መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።”   “በዚያን ጊዜ ተራራዎችን፦ በላያችን ውደቁ፥ ኮረብቶችንም፦ ሰውሩን ይሉ ዘንድ ይጀምራሉ፤”   — ሉቃስ 23፥ 28-30 ......ይቀጥላል .....
Show all...
' ፋሲካችን 'የሆነው ክርስቶስ ታርዶልናል ። በዛች በጌቴሴማኒ ምሽት የፋሲካው በግ ለመታረድ አሳልፎ ተሰጥቷል ። በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ደሙ  ከሰውነቱ ላይ አንድም ሳይቀር ፈሶ አልቋል ። ለዘመናት እየፈሰሰ በነበረ የእንስሳት ደም ያልበረደ የእግዚአብር ቁጣ በኢየሡሥ ንፁህ ደም ለዘላለም በርዷል ። ማንም ሰው  ይህንን ንፁህ ደም በእምነት በልቡ ላይ ቢረጭ ከአስፈሪ ቁጣ ለዘላለም መዳን ይችላል ።  እኛ ሁላንችንም በእሡ የስቃይ ሞት ዘላለማችን ተቀይሯል ። ከዚህም የተነሣ እነሆ ' የዘላለም ፋሲካችን ' እንላለን ። ይህ ደም እንደሌሎቹ የእንስሳቶች ደም ሀጢአትን የሚሸፍን ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ አቅም ያለው ደም ነው ። በሌሎች ደስ ያልተሰኘው አብም በዚህኛው ግን ፍፁም ረክቷል ። በዚ ደም አማክኝነት ቅዱስ እግዚአብሔር ፊት ማንም በህያው ህሊና  መቅረብ ይችላል ። እግዚአብሔርን በነፃነት ለማምለክ ነፃነትን ይጎናፀፉል ። ደግሞም እንደሌሎቹ መስዋዕቶች በየጊዜው የሚቀርብ ሳይሆን አንድ ጊዜ በመቅረብ ለዘላለም የመሆን ቤዛነትን  (once for ever ) አግኝቷል ፤ ስለዚህም ሁል ጊዜ ሊቀርብ አያስፈልገውም። እንደ ሌሎቹ የፉሲካ በጎች ሰው ያዘጋጀው የሰው በግ አልነበረም ። ነገር ግን እግዚአብሔር ' ለአለሙ ሁሉ '  ሀጢአት ያዘጋጀው የ ' እግዚአብሔር በግ ' ነበር ። እግዚአብሔር የገዛ ውድ ና አንድ ልጁን ለመታረድ በመስጠት የልጁን ያህል እንደሚወደን አረጋግጦልናል ። የኢየሱስ ደም ንፁህ ነበር ። ሀጢአትን በፍፁም አያውቅም ነበር ። በነገር ሁሉ ተፈትኖ ምንም እንከን አልተገኘበትም ። ፅድቅን ሁሉ ጥንቅቅ አርጎ በመፈፀም የእግዚአብሔርን መስፈርት አሟልቷል ። እግዚአብሔርም ደስ የሚሰኝበት ልጁ እንደሆነ መስክሮለታል ። በአፉም አንዳች ተንኮል አልተገኘበትም ፡ አንዳች ሳይገኝበት የግፍን ሞት ሞቷል ። ጲላጦስም መርምሮ አንዳች ስላላገኘበት ሊፈታው ፈልጎም ነበር ። ለሞት ያበቃው ክስ  ራሱን  ' የአይሁድ ንጉስ ' ብሏል የሚል ነበር ። በአንዱ መተላለፍ ብዙዎች ሀጢአተኞች እንደ ሆኑ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ፃድቃን ተደርገዋል ። “በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።”   — ሮሜ 5፥19 ' እነሆ ፋሲካችን ኢየሱስ ' ይቀጥላል ።
Show all...
'  የፋሲካው በግ ' ሰሞኑን የፋሲካ ድባብ እየሸተተኝ ነው ። ሰሙነ ህማማት ፡ ስቅለት ፡ ትንሣኤ  ሁልጊዜም ደስ የሚሉ ድባቦች ናቸው ። ስቅለቱን ፡ ህማሙን ፡ ትንሣኤውን አለማውራት ፡ አለመዘመር ፡ አለመተረክ አይቻልም ህይወታችንም፡ እምነታችንም ድነታችንም  ክርስትናችንም ሁሉ ነገራችን ከእነዚህ ህያው ከሆኑ ኩነቶች ይቀዳሉና !!። ፋሲካ ሢነሣ የፋሲካውን በግ አብሮ ማንሳት የግድ ነው ።ፋሲካን ለእስራኤል ልጆች ፋሲካ ያደረገው በጉ ነውና ። የሞት መላዕክት የግብፁን በኩር በሞት እያጨደ ሲያተራምስ ለእነሡ ግን የፋሲካው በግ ሞትን ማለፊያ ሆነላቸው ። የእነሡን ደጅ ሞት ያላንኳኳ የተሻሉ ሰዎች ስለሆኑ ሳይሆን እግዚአብሔር የሚቀበለው ንፁህ የበግ ደም ስለፈሰሰ ና በራቸው ላይ ስለተቀባ ነው ። በጉ ተሰብስበው በደስታ እንዲያሳልፋ እና ሀዘን ከቤታቸው ጥላ ስር ፈፅሞ እንዳይሰማ ያደረገ የደስታቸው ምክንያት ነበር  ። እዚ በግ ላይ ሁለንተናቸውን አስጠልለው ሞታቸውን ሸኝተዋል ። ይህ የፋሲካ በግ  በእግዚአብሔር በተሰጠ መስፈርተ የሚዘጋጅ ነበር ። በጉ ምንም አይነት ስንኩል ነገር ሊገኝበት አይገባም ነበር ። አይኑ የታወረ ፡ አካለ ስንኩል የሆነ ፡ ግንዱሽ ፡ ሰባራ ወይንም በሽታ ፡ ቁስል ወይንም ነውር ያለበት በግ በፍፁም ተቀባይነት የለውም ነበር ። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚቀበለው  ፍፁም  ህያው እና ንፁህ የሆነ መስዋዕት ስለሆነ  !! ። ይህ በግ በሰው ተጠብቆ ለፋሲካ ቀን የሚዘጋጅ ' የሰው በግ ' ነበር ። እያንዳንዱ ሰው በግለሰብ ደረጃ ለራሱ የሚሆንን በግ ያዘጋጅም ነበር ። የበጉ ደም ንፁህ ስለሆነ ስለሌላው ሀጢአት  መቅረብ ይችል ነበር ። እያንዳንዱ ሰው እጁን እየጫነ ሀጢአቱን ከራሱ ወደ በጉ እንዲተላለፍ በማድረግ ከቅጣት ይድናል ። በጉም ' እንደ ሀጢአተኛ ' በመቆጠር የሀጢአትን ፅዋ ይቀበላል ። የሀጢሀት ደሞዝ ሞት ነውና ። የእንስሳው ደም መፍሰስ ይኖርበታል ህይወቱ የሚገኘው በደሙ ውስጥ ነውና ። በጉ ግን የራሱን ሞት አደለም የሚሞተው የሌላውን እንጂ ስለዚህ ሞቱ የውክልና ነው ማለት ነው ። T@M ይቀጥላል  ።
Show all...
🙏ለእግዚአብሔር ከምንሰጣቸው እና ከእኛ ሊቀበለው ከሚወዳቸው ነገሮች አንዱ #ምስጋና ነው። ምስጋና ከምንሰዋባቸው ምክንያቶች መካከል #አንደኛው:- እግዚአብሔር አምላክ ስለሆነ እና ስለሚገባው ነው። መልአክቶቹ ፍጥረት ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋናን ይሰዋል ያመሠግንዋል። “አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።”   — ራእይ 4፥8 “ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።”   — ራእይ 4፥10-11 #ሁለተኛው:- ለእግዚአብሔር ምስጋና የምንሰዋው ውለታው ስላለብን ማለትም ስላደረገልን ስላገዘን ነው። “ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ።”   — ዘፍጥረት 35፥3 “አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፥ በቅዱሳንህም ዘንድ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ።”   — መዝሙር 52፥9 #ሶስተኛው:- ለእግዚአብሔር ምስጋና የምንሰዋበት ምክንያት የእግዚአብሔርን ማዳን የምናይበት መንገድ ነው። “ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።”   — መዝሙር 50፥23 2ኛ ዜና 20:21-26 ንጉስ ኢዮሳፍጥ እና ጌጠኛ ልብስ የለበሱት መዘምረን "ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውና" ብለው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ እግዚአብሔር ድብቅ ጦር አስነስቶ ጠላቶቻቸውን መታ። በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ይሁንልን። ስናመሰግን አንድ ስለሚገባው ሁለት ስላደረገልን ሶስት ማዳኑን ስለምናይ ነው። ስታመሰግን እነዚህን ሶስት ነገሮች እያደረግክ ነው።
Show all...