cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ህያው PERCEPTION

PSYCHOLOGY AND MOTIVATION

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
284
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Start small
Show all...
#ዋሽቻችሁኛል!! ምን የማይዋሽ አለ? ማን የማይዋሽ አለ? ከሰሙአቸው በጣም ብዙ ውሸቶች በህይወታችን በዙሪያችን፣ በቤተሰቦቻችን፣ በጓደኞቻቻን በቅርብ ሰዎች ሳይቀር ብዙ ውሸት አሉ። ባህል፣ ህግና ስርአት፣ ከዚህ በፊት ያልተሳካላቸው ተሞክሮ፤ ሰዎች ስለ ነገሮች ያሏቸው አመላካከት ሁሉ ብዙ ውሸት አለበት። አትችልም፣ አይሳካልህም፣ እነ እንትናም አልሆነላቸው የሚል ድምጽ፣ ልታገባ ስታስብ ጋብቻው የፈረሰበት በጋብቻ ስኬታማ እንደማትሆን ይሰብክሃል፣ ራዕይ ይዘህ አንድ ነገር ለመስራት ስትነሳ ራዕያቸው የወደቀባቸውን ሰዎች ምሳሌነት በመያዝ ይሰብኩሃል። ትችላለህ ከሚለው ይልቅ አትችልም የሚል ቃል በትልቁ ተጽፎ ይጠብቅሃል። ነገሮችም ካለመቻል ወደ መቻል ያመጡ ጀግና ሰዎች አሉ። በሁላችንም ህይወት እንደዚህ አይነት ሰዎች፣ ሁኔታዎችና አጋጣሚዎች አሉ። ይኖራሉም። በራስህ እንዳታድግ ከቀደመው መስመር እንዳታልፍ የውድቀትና ያለመቻል ውሸቶች በብዙ ይነገራሉ። ራስህን ባዘጋጀህበትና ባመንክበት ደረጃ ትችላለህ። ውጣውረድና ድካም መውደቅና መነሳት ያለመቻል ምልክት አይደለም፣ ማንኛውም አዲስ ነገር ስትሰራ እነዚህ ነገሮች ያጋጥማሉ፣ አሉም። ተስፋ ሳትቆርጥ መቀጠል ግን ውጤታማ ያደርግሃል። ብዙ የውሸት አመለካቶችም አልቀበልም ካላልክ በቀር ዝም ብለህ ከሰማኃቸው ውጠው ያስቀራሉ። #አትችልም_ያላችሁኝ_ዋሽታችሁኛል_እችላለሁ!! ዘሪሁን ግርማ
Show all...
ሕልማችሁ እውን እንዲሆን ከፈለጋችሁ በዙሪያችሁ ያለውን አለም አሁን ባለበት ሁኔታ ሳይሆን በውስጣችሁ ካለው ከህልማችሁ አንጻርና እንዲሆን ከምትፈልጉት አንጻር መመልከት ጀምሩ፡፡ በአይነ-ስጋችሁ የምታዩት የአሁኑና የወቅቱ ሁኔታ “እውነታ” ይባላል በአይነ-ህሊናችሁ የምታዩት የነገው ሁኔታ ደግሞ “ሕልም” ይባላል፡፡ ዛሬን ከእውነታው አንጻር የመኖራችሁ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገን ግን ከሕልማችሁ አንጻር በመመልከት ወደዚያ ጉዞን ጀምሩ! ጣፋጭ እንቅልፍ ይሁንላችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
🌊''………እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ……… 💦ቢእንግዲህ……… የበላውን ያንሸራሽራል ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች።ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል። ጊዜው ሲደርስም ይጎላል…… ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው………… 💧ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል…… ገላችን፣ አእምሮአችን ይታመማል…… እንረበሻለን፣ እንጨነቃለን። ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው………… 🌊ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል። ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ። መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው……… 💦የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ። ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ……… እንደሚለወጥ ስለማውቅ !" 🌊'የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ ' ሲሉ አዛውንት 'ዝናቡን ፍራው' ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው። ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው። አይመስልህም እንዴ?'' ✍…አዳም ረታ❤️ ፦ ይወስዳልመንገድ ያመጣል መንገድ…… @bravegenbyyil @yilo15
Show all...
አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ! ሆንግኮንግ/አሜሪካዊው ብሩስ ሊ (Bruce Lee) ታዋቂ አክተር፣ ብቁ የማርሻል አርት ባለሞያና አስተማሪ፣ እንዲሁም ስመ-ጥር ፈላስፋ ነበር፡፡ ይህ ሰው አንድ ጊዜ ስለስኬቱ ምስጢር እንዲህ ሲል ተደመጠ፣ “አስር ሺህ አይነት የተለያዩ የካራቴ ምቶችን በአንድ ቀን ከተለማመደ ሰው ይልቅ እኔ የምፈራው አንድን አይነት የካራቴ ምት አስር ሺህ ጊዜ ደጋግሞ የተለማመደን ሰው ነው”፡፡ አንድ ቀን ተነስተን የተለያዩ ነገሮችን ስለሞከርን ብቻ የትም እንደማንደርስ አመልካች የሆነ ሃሳብ ነው፡፡ አስር ሺ አይነት ነገሮችን ከመሞካከር፣ ዓላማችንንና ግባችንን ከለየን በኋላ ያንን አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ አድምተን ብንደጋግመውና ብንለማመደው ለምነገባበት ስኬት ወሰን አይኖረውም፡፡ የዚህ እውነታ ምስጢር ያለው በመነሳሳት (Motivation) እና በዲሲፕሊን (Discipline) መካከል ያለውን ልዩነት በማወቅ ነው፡፡ የተነሳሳን አንድ ቀን ከምናደርጋቸው አስር ሺህ የዘመቻ ስራዎች ይልቅ የያዝነውን አንድ ነገር በዲሲፐልን አስር ሺህ ጊዜ ብንደጋግመው የተሸለ ውጤትን እናገኛል፡፡ በመነሳሳት የጀመርነውን ነገር በዲሲፕሊን መቀጠልን እስከምንለምድ ድረስ ስኬት የህልም እንጀራ እንደሆነ ይቀራል!!! @Dreyob @ethiopicmotivation @ethiopicmotivation
Show all...
የልማድ ምስጢር! “ደጋግመን የምናደርገውን ነገር ነን፡፡ ስለሆነም፣ ልቀትና ምርጥነት የአንድ ጊዜ ተግባር ጉዳይ ሳይሆን የልማድ ጉዳይ ነው” - Aristotle “እኔ የአንተ የዘወትር አጋርህ ነኝ፡፡ ታላቅ የሆንኩ ረዳትህ ነኝ ወይም ደግሞ ከባድ የምባል ሸክምህ፡፡ ወደ ስኬት ልገፋህ እችላለሁ፣ ወይም ደግሞ ወደ ውድቀት ልጎትትህ ብቃት አለኝ፡፡ ሁል ጊዜ እንዳዘዝከኝ ለመሆን ዝግጁ ነኝ፡፡ በየእለቱ ከምታደርጋቸው ነገሮች ገሚሶቹን ለእኔ አሳልፈህ ብትሰጠኝ ባፋጣኝና በትክክለኛው መንገድ አከናውናቸዋለሁ፡፡ ጠንከርና ጨከን ካልክብኝ፣ በቀላሉ ልትገራኝና ልታስተዳደረኝ ትችላለሀ፡፡ አንድ ነገር በምን መልኩ መደረግ እንዳለበት አሳየኝና ትንሽ ካለማመድከኝ በኋላ በፈለከው ጊዜ ሁሉ በፍጥነት አከናውንልሃለሁ፡፡ ታላላቅ የተሰኙ ሰዎች አገልጋይ ነኝ፤ ሆኖም የውድቀትና ያለመሳካትም ምክንያት እኔው ነኝ፡፡ ታላላቅ የሆኑን ሰዎች ታላቅ ወደ መሆን ያመጣኋቸው፤ የወደቁና ያልተሳካላቸውንም ሰዎች ለዚያ ያበቃኋቸው እኔ ነኝ፡፡ ማሽን አይደለሁም፤ ነገር ግን ልክ እንደ ማሽን የተሰጠኝን ሁሉ ሳላዛባ፣ ልክ እንደሰው ደግሞ በብልህነት እሰራለሁ፡፡ ከፈለክ ለትርፍ ተጠቀምብኝ ካለዚያም ለክስረት ተጠቀምብኝ፣ በእኔ በኩል እንደሆነ ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ ውሰደኝ፣ የራስህ አድርገኝ፣ አሰልጥነኝ፣ ጠንከርና ጨከን በልብኝ እኔም በተራየ አለምን አስገዛልሃለሁ፡፡ ቀለል በልልኝና ችላ በለኝ፣ አጠፋሃለሁ፡፡ ማን ነኝ? እኔ ልማድ እባላለሁ!” – Anonymous ልማድ ማለት በአንድ ነገር አቅጣጫ ራሳችንን ከማስለመዳችን የተነሳ ያንን ነገር በቀላሉ ማድረግ ስንጀምርና እንደውም ማቆም ሲሳነን ማለት ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ ለጤናማውም ሆነ ለጤና ቢሱ ልማድ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ልማድ ማለት ካለምንም የውጭ ግፊትና ጉትጎታ ማድረግ የጀመርነውና “የማንነታችን” ክፍል ወደ መሆን የመጣ ጉዳይ ነው፡፡ ከመልካም ልማድ ውጪ ማንም ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ በሌላ አባባል ወደ ልማድ ባልመጣ መልካም ነገር ወደ ስኬት መምጣት አንችልም፡፡ ብቃትና ጥራት ማለት የተለመደን ነገር ባልተለመደ መልኩ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ መልካምን ልማድ ማዳበር የግድ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በአንድ ስፖርት ኦሎምፒክ ላይ የሚወዳደሩ ሰዎች በአማካኝ ካለማቋረጥ ለስድስት ዓመታት ሙሉ በአመት ለ310 ቀናት፣ በየቀኑ ለአራት ሰዓታት ልምምድ ያደርጋሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች ቀኑን ሙሉ የማይሰሩትን ስራ እነዚህ ስፖርተኞች ጠዋት አንድ ሰዓት ከመሆኑ በፊት ሰርተው ይጨርሳሉ፡፡ አሁን ምንም አይነት የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰን ሰው ተመልከትና ጀርባውን አጥና፤ ለረጅም ጊዜ ደጋግሞ ያደረገውንና የገነባውን አንድ ነገር ታገኛለህ፡፡ በሌላ አባባል፣ አሁን የደረሰበት የላቀ ደረጃ የደረሰው በአጋጣሚ ሳይሆን አንድን መልካም ልማድ አዳብሮና በዚያ ልማድ ዙሪያ ደጋግሞ በመስራትና በመሻሻል ነው፡፡ የንጽህና ልማድ ቤትን፣ አካባቢንና አገርን በንጽህና ልቀው እንዲገኙ ያደርጋቸዋል፡፡ የስራ ልማድ በብልጽግና ልቀን እንድንገኝ ያደርገናል፡፡ የጥናት ልማድ በእውቀት እንድንልቅ መንገዱን ይጠርጋል፡፡ ከማንኛውም ውብ ነገር ጀርባ መልካም ልማድ አለ፡፡ በእኔና በአንተም ኑሮ ስሌቱ ያው ነው፡፡ አንድ ቀን ከእንቅልፋችን ስንነሳ በአንድ ነገር ልቀን አንገኝም፡፡ ከአንድ ግብ አንጻር በየእለቱ የገነባናቸው ልማዶቻችን ናቸው የነገን ልቀታችንን የሚወስኑት፡፡ ልማድ የሕወታችንን አብዛኞዎቹን (ምናልባት ሁሉንም) ነገሮች አቅጣጫ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ጤንነታችንን፣ ኢኮኖሚያችንን፣ ወዳጅነታችንን የኑሮአችንን ጥራትና ሌሎችም ዋና ዋና ነገሮችን ስለሚወስን፤ ልማድ ሲጨመቅ ማንነት ይሆናል፡፡ @Dreyob @ethiopicmotivation @ethiopicmotivation
Show all...