cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ahmad Muhammad - አሕመድ ሙሐመድ

ኢሰላማዊ አስተማህሮት : የተለያዩ አሰተማሪ መልክቶች በፅሁፍና በድምፅ በመታገዝ ወደናንተ ያደርሳል ። ወቅታዊ መረጃዎችን ያደርሳል። እንዲሁም ከተለያዩ ግሩፕ የተላኩ ምርጥ ነገሮችን እዚህ ያገኛሉ። አርሂቡ ለበለጠ መረጃ ..... @Ibnukocha

Show more
Advertising posts
275
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሁለተኛ ሰለባ ኢማም ማሊክ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) ኢማም ማሊክ፣ ለሙጀሲማና ሙሸቢሃዎች አረዳድ ግልፅና የማያሻማ አፀፋ መስጠታቸው እሙን ነው። ኢማሙ እንዲህ ይላሉ፡- "الإستواء غير مجهول –أي ذكر في القرآن والكيف غير معقول أي بصفة يعلمها الخلق أو يدركونها" “ኢስቲዋእ- የማይታወቅ (ርዕሰ ጉዳይ) አይደለም፤ በቁርኣን የተጠቀሰ ነውና። እርሱም ከይፍ (እንዴት ባለ አኳኋን) አይባልም። በፍጥረት መገለጫ በሆነው ከይፍ (አኳኋን) ከመባልም ፍፁም ነው። በአንፃሩ፣ የወሃቢያህ ሰለፍ አዝማች የሆኑት ኢብኑ ተይሚያህ በልዩ ልዩ ድርሳኖቻቸው ዓርሽ ላይ ነው። አኳኋኑ (ከይፍያው) አይታወቅፈም የሚል ብልሹ ዐቂዳ አሰራጭተዋል። ይኸው ነው ሙጀሲማ እንዴት ማለትን ለአሏህ ያወሳሉ። ለምሳሌ፣ “ታዕሲስ” በተሰኘው ድርሳናቸው፣ አሏህን ሱብሃነሁ ወተዓላ “በአርሹ ላይ ተደላደለ” ሲሉ አስፍረዋል። አለፍ ሲልም፣ “እስተዋእ” ማለት፣ “صعد” “على” “إرتفع” ሲሉ አብራርተውታል። “ሰዒደ” (ሽቅብ ወጣ) የሚለው አተረጏጎም እጂግ ያሳቅቃል። ይህ ደግሞ አሏህ በፊት ከታች ነበር ከዚያ ከፍ ብሎ ወደ አርሹ ወጣ እንደማለት ያለ ነው አሏህ ይጠብቀን የሙጀሲማ ነገር፣ ሁልጊዜ ግራ ነው! ኢማም ማሊክ በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ሲያስተምሩ፣ "ولا يقال كيف والكيف عنه مرفوع" “እንዴት (በምን ያለ አኳኋን) አይባልም ይህ ለርሱም አይገባም (አይመጥንም)” ይህ ይፋ የሆነ ምላሽ ሳለ፣ የኢማም ማሊክን አባባል እያሉ እንዲሁ ይመላልሳሉ። "الاستواء معلم والكيف مجهول" “ኢስቲዋእ” የታወቀ ነው። አኳኋኑ ግን አይታወቅም ባይ ናቸው። ይህ የኢማም ማሊክ አባባል በዚህ መልኩ አለመቀመጡን ግን ልብ ይበሉ። ስለዚህ የኢማሙ ማሊክ ንግግር ነው፡- “ኢስቲዋኡ የታወቀ ነው። ሁኔታው ከይፍያው ግን አይታወቅም የሚለው ንግግር ፍፁም ስሑት ነው። ምንያቱም በከይፍያ በአኳኋን የሚገለፅ ፍጡር እንጂ አሏህ አይደለም።ትክክለኛ የኢማሙ ማሊክ ንግግር ከላይ የተጠቀሰው ነው። ይህው ነው የአህሉ ሱና ዓቂዳ። https://t.me/Islamic_Teaching_com
Show all...
የአራቱ መዝሃብ ዐቂዳ የጥንቶቹ ሃሽውያህ፣ የዛሬዎቹ የወሃቢያህ ሙጀሲማዎች፣ አፈንጋጭና ብልሹው አረዳዳቸውን እንደሚያጠናክርላቸው ያላመኑባቸውን ተሰሚ አካል ሁሉ ወደራሳቸው ከመጎተትና የክፉ አላማቸው መስዋዕት ከማድረግ ወደኋላ አይሉም። ታዲያ የአራቱ መዝሃብ አውራ ሊቃውንትም ቢሆኑ፣ ከንዲህ ያለው የወሃብያዎች ጥቃት አላመለጡም። የሚያራምዱትን አፈንጋጭ አረዳድ፣ ከመላው ሙስሊም ዘንድ ይሁንታ ያገኝላቸው ዘንድ፣ ከነኝህ የኢስላም አውራዎች (አኢማዎች) ጋር ለማቆራኘት ሲደክሙ ይታያሉ። እውነታው ግን እነኝህ ሊቃውንት፣ የወሃቢ ሙጀሲማዎች፣ ከአሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ አምላካዊ መገለጫ አንፃር የያዙትን አቋም ይፀየፉት ብቻ ሳይሆን መሰል አቋም የሚያራምድን አማኝ ሁሉ ያከፍሩ የነበረ መሆኑ ነው። የወሃቢያህ ባለቤቶች፣ የአራቱ መዝሃቦች ኢማሞችን ወደራሳቸው ለመቀላቀል ያደረባቸው ከንቱ ምኞች፣ በሊቃውንቱ ላይ ዐይን ያወጡ አሉባልታዎችን እስከመንዛት አድርሷቸዋል። መሰል አስነዋሪ ተግባራቶቻቸውን አንድ ሁለት እያልን እንመለከታለን። አንደኛ ሰለባ - ኢማም (አዕዞም) አቡ ሓኒፋ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) ኢማም አቡ ሃኒፋ፣ የወሃቢያህ ሙጀሲማ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ከሆኑ ሊቃውንት አንዱ ናቸው። የወሃቢያህ ባለቤቶች፣ በለመደ አፋቸው በአቡ ሃኒፍ ስም የሚከተለውን አሉባልታ ይነዛሉ። "من قال لا أعرف ربي أفي السماء أم في الأرض فقد كفر لأن الله يقول ﴿الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ﴾" “ጌታዬ ከሰማይ ይሁን በምድር አላውቅም የሚል ይከፍራል። ምክንያቱም አሏህ ራሱ፣ “አራህማን በዓርሹ ላይ ተደላደለ ብሏልና። ዙፋኑ (አርሹ) ከሰባት ሰማያት በላይ ነው።” ይህ እብለት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ተረት መሆኑን ለመረዳት አይነተኛው መንገድ የታሪክም ይሁን ታሪክን ያስተላለፈው፣ አቡ ሙጢዕ አልበኸዒ የተሰኘው ግለሰብ ከብዙሃን የኢስላም ሊቃውንት ዘንድ በዋሾነቱ የተመሠከረለት አባይ (ወዷዕ) ግለሰብ ነው። አልሓፊዝ ዘሃቢ፣ “ሚዛን” በተሰኘው ድርሳናቸው፣ ኢማም አህመድ ስለ ግለሰቡ እንዲህ ማለታቸውን ፅፈዋል። "لا ينبغي أن يروى عنه شيء" “አንዳችም መልእክት ከእርሱ ቀስሞ (እሱን አምኖ) ማሰራጨት አይገባም!” ሃፊዝ ኢብኑ ሃጀርም እንዲሁ፣ በሃገረ ህንድ በታተመውና “ሊሳኑል ሚዛን” በተሰኘው ድርሳናቸው፣ አቡ ሃቲም ራዚን ዋቢ በማድረግ ስለዚህ ግለሰብ ሲፅፉ እንዲህ የሚል ነው። قال أبو حاتم الرازي "كان مرجئا كذابا" “ሙርጂዕና እጅግ ዋሾ ነው።” ኢብኑ ሃጀር በዚህ ሰው ጉዳይ ያጠናቀሩትን መልእክት ለማስረግ የተጠቀሙት ሃሳብ እንዲህ የሚል ነው። "وقد جزم الذهبي بأنه قد وضع حديثا فينظر من ترجمة عثمان بن عبد الله الأمري" “እነሆ ይህ ግለሰብ፣ ሃዲስ የፈለሰፉ (ያልተባለን ፈጥሮ ያሰራጨ) መሆኑን ዘሃቢ አረጋግጠዋል።” (ለተጨማሪ፣ የዑስማን ኢብኑ አል ዑመዊይን ጥንቅር የይመልከቱ።) እንግዲህ የኛም መከራከሪያ በኢማም አህመድ መጠይቅ የሚጠናከር ነው። "لا ينبغي أن يروى عنه شيء كيف يعتمد ما رواه عن الإمام أبي حنيفة" “አንድ በዋሾነቱ የሚታወቅ ሰው የተናገረውን ተመርኩዞ፣ አቡሃኒፋ እንዲህ ብለዋል ብሎ በአደባባይ መለፈፍ እንዴት ያለ ተግባር ነው?! ومن كذب على رسول الله ﷺ كان أهون عليه أن يكذب على من دونه على أبي حنيفة أليس كذلك؟ ከፍ ብሎ እንደተመለከትነው፣ ግለሰቡ በነብዩ ﷺ ላይ ሳይቀር ለመወሽከት ያላቅማማ ወራዳ ሆኖ ሳለ፣ ስለ አቡ ሃኒፍ ሃቅ ይናገራል ብሎ ይታመናልን? አሳዛኙ ነገር፣ እርስ በርስ በሚቃረን አረዳዳቸው የሚታወቁት የወሃብያህ ሸይኽ የሆኑት አልባኒ “እንኳ በተቀረፁ የድምጽ መልዕክታቸው የግለሰቡን ታሪክ አቡ ሙጣዕ (ዘገባ) በ(ፊቅሁል አክበር) እንደማይቀበሉት ተናግረው ሳለ፣ በአንፃሩ አሏህ በሰማይ ነው በምድር የሚለውን ያወራውን ግን አፅድቀው ያደናግሩናል። በእርግጥም፣ አልባኒ፣ ግለሰቡን የሚቃወሙት “ፊቅሁል አክበር” ከተሰኘው ዐቂዳ ዕይታቸው የሚፃረር ሆኖ ስላገኙት ብቻ ነው።
Show all...
ለ. ተፍዊድ በውሃቢያ ዘንድ ወዲህም በአፅንኦ ልናስተውለው ግድ የሚለን ፍሬ ነገር አለ፡- እርሱም ከውሃብያህ ዘንድ “ተፍዊድ” እናደርጋለን በሚሉበት አግባብ ትክክል አለመሆኑን ነው። ምክንያቱም እነሱ “ተፍዊድ” የሚያደርጉት፣ ቃሉን ተርጉመው ስለ ከይፍያ (አኳኋኑን) ነው። ለምሳሌ፣ “እጅ አለው ብለው ካፀደቁ በኋላ፣ ባይሆን የኛን አይመስልም፤ ሁለት እጆች አሉት”፣ ሁለት አይኖች አሉት ዓርሽ ላይ ነው የመሳሰሉ ሌሎቹንም አሻሚ አንቀፆች ይተረጉሙና ለርሱ ብቻ በሚገባ የሚል የማግባቢያ ሀረግ ይቋጩታል። ይህ ሁሉ የተጀሲምና የተሸቢህ ዝንባሌና አድራጎት ነው። ይበልጥ ለመረዳት የአራቱ መዝሃብ ዓቂዳ በተሰኘው ርዕስ ስር ይህንን ፈሊጣቸውን ለማስረፅ የሚጠቀሙበትን የማሳቻ ስልት አስመልክቶ አብራርቻለሁና ይመልከቱ። ስለዚህ የሰለፎች (አህለል ሱና) ‘ተፍዊድ’፣ እነርሱ ከሚሉት ‘ተፍዊድ’ ፍፁም ዝምድና የለውም። የሰለፎች (የአህለ ሱና) የተፍዊድ ስልት ከላይ እንደጠቀስኩት ቃሉን እንደወረደ ከነሙሉ ይዘቱ ማሳለፍ ነው። ሌላው አስተውሎን የሚሻ ነጥብ ኢብኑ ተይሚያህ፣ “አል ሙዋፈቃህ” በተሰኘ ድርሳኑ፣ “ተዕዊል፣ የቢድዐ ሰዎች (አሻጥረኛ) አሳሳች ማደናገሪያ ነው” ሲል ይሞግታል። እነኛ ተፍዊድ እናደርጋለን የሚሉና መለስ ብለው ደሞ ሱናንና የሰለፎችን መንገድ እንከተላለን የሚሉ ወገኖች የእነርሱ ነገር የቢድዐ ሰዎች ማደናገርያ (ማሳሳቺያ) መሆኑ ተጋልጧል!” ይላል። አሏህ ፈር ከመልቀቅ ይጠብቀን! “ታእዊልም ሆነ ተፍዊድ”ን ከነኛ በነብዩ አንደበት ከተመሠከረላቸው የሁነኛው ትውልድ ሊቃውንት (አኢማዎች) እንደተቀሰመ በሚገባ አስረግጠናል። ሱነን ትርሚዚይ በመሳሰሉ የታላላቅ ሊቃውንትን መዝሃቦች፣ በእንዲህ ያለ አኳኋን መዝለፍ፣ በርሱ (ኢብኑ ተይሚያ) አስተሳሰብ ካፊርና ሙልሂድ ብሎ መፈረጅ እጅግ የሚያሳፍር ነው። ይልቁንም፣ እርሱ ራሱ በግብረገብ አረዳዱ የሚወገዘው የአልባ ተከታይ መሆኑ ያስደንቃል። ለ. ተፍዊድ በውሃቢያ ዘንድ ወዲህም በአፅንኦ ልናስተውለው ግድ የሚለን ፍሬ ነገር አለ፡- እርሱም ከውሃብያህ ዘንድ “ተፍዊድ” እናደርጋለን በሚሉበት አግባብ ትክክል አለመሆኑን ነው። ምክንያቱም እነሱ “ተፍዊድ” የሚያደርጉት፣ ቃሉን ተርጉመው ስለ ከይፍያ (አኳኋኑን) ነው። ለምሳሌ፣ “እጅ አለው ብለው ካፀደቁ በኋላ፣ ባይሆን የኛን አይመስልም፤ ሁለት እጆች አሉት”፣ ሁለት አይኖች አሉት ዓርሽ ላይ ነው የመሳሰሉ ሌሎቹንም አሻሚ አንቀፆች ይተረጉሙና ለርሱ ብቻ በሚገባ የሚል የማግባቢያ ሀረግ ይቋጩታል። ይህ ሁሉ የተጀሲምና የተሸቢህ ዝንባሌና አድራጎት ነው። ይበልጥ ለመረዳት የአራቱ መዝሃብ ዓቂዳ በተሰኘው ርዕስ ስር ይህንን ፈሊጣቸውን ለማስረፅ የሚጠቀሙበትን የማሳቻ ስልት አስመልክቶ አብራርቻለሁና ይመልከቱ። ስለዚህ የሰለፎች (አህለል ሱና) ‘ተፍዊድ’፣ እነርሱ ከሚሉት ‘ተፍዊድ’ ፍፁም ዝምድና የለውም። የሰለፎች (የአህለ ሱና) የተፍዊድ ስልት ከላይ እንደጠቀስኩት ቃሉን እንደወረደ ከነሙሉ ይዘቱ ማሳለፍ ነው። ሌላው አስተውሎን የሚሻ ነጥብ ኢብኑ ተይሚያህ፣ “አል ሙዋፈቃህ” በተሰኘ ድርሳኑ፣ “ተዕዊል፣ የቢድዐ ሰዎች (አሻጥረኛ) አሳሳች ማደናገሪያ ነው” ሲል ይሞግታል። እነኛ ተፍዊድ እናደርጋለን የሚሉና መለስ ብለው ደሞ ሱናንና የሰለፎችን መንገድ እንከተላለን የሚሉ ወገኖች የእነርሱ ነገር የቢድዐ ሰዎች ማደናገርያ (ማሳሳቺያ) መሆኑ ተጋልጧል!” ይላል። አሏህ ፈር ከመልቀቅ ይጠብቀን! “ታእዊልም ሆነ ተፍዊድ”ን ከነኛ በነብዩ አንደበት ከተመሠከረላቸው የሁነኛው ትውልድ ሊቃውንት (አኢማዎች) እንደተቀሰመ በሚገባ አስረግጠናል። ሱነን ትርሚዚይ በመሳሰሉ የታላላቅ ሊቃውንትን መዝሃቦች፣ በእንዲህ ያለ አኳኋን መዝለፍ፣ በርሱ (ኢብኑ ተይሚያ) አስተሳሰብ ካፊርና ሙልሂድ ብሎ መፈረጅ እጅግ የሚያሳፍር ነው። ይልቁንም፣ እርሱ ራሱ በግብረገብ አረዳዱ የሚወገዘው የአልባ ተከታይ መሆኑ ያስደንቃል። https://t.me/Islamic_Teaching_com
Show all...
.......... የቀጠለ የፍፁሙና ልዕለ ኃያሉ አምላካችን አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቁርዓናዊ መልዕክትም ጋር የሚጣጣም እንጂ የሚቃረን ሆኖ አናገኘውም። በአልዒምራን ቁ. 7 የሠፈረውን የቁርዓን አንቀፅ ልብ ይሏል። ﴿ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُ إِلَّا اللَّهُ ۗ وَالرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ يَقُولُونَ آمَنَّا بِهِ كُلٌّ مِّنْ عِندِ رَبِّنَا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ﴾ { (ትክክለኛ) ፍቺውን አሏህ ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁት «በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም::} ታላቁ ሊቅ፣ አልሃፊዝ ኢብኑ ሃጀር፣ “ፈትሁል ባሪ” በተሰኘው ድርሳናቸው እንዲህ ይላሉ።“ኢብኑ ሙነይ እንዳወሱት፣ የአሏህን መገለጫ ባህሪ በተመለከተ ሶስት አይነት አተያዮች አሉ።” ካሉ በኋላ ከሶስቱ አረዳዶች አንዱ ይኸው “እንደወረደ የመረዳት ዘይቤ” መሆኑን ይጠቅሳሉ። አያይዘውም፣ ጦበሪን ዋቢ በማድረግ፣ “ይህ ተፍዊደል ማዕና) ቀደምት ቀናዒ አባቶች (ሰለፎች) ያለ ተቃርኖ ይሰራበት የነበረ መንገድ ነው።” አሁንም ኢብኑ ሃጀር፣ “ፊትሁል ባሪ” በተሰኘው ድርሳናቸው ስለተፍዊድ ሲያብራሩ እንዲህ ይሉናል፡- “እውነታውን (እንዳወረደ) ወደ አሏህ በመተው፣ አሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በቁርዓኑና በነብዩ ﷺ አንደበት በደነገገብን ጉዳይ አምኖ መቀበል ብቻ ነው።” አልሃፊዝ ኢብኑ ሃጀር (ረዲየሏሁ ዓንሁ) ከፍ ብሎ ካሰፈርነው ሃሳብ በስተፊት፣ በ “ፊትሁል ባሪ”፣ ኢብኑ ደቂቅ አል ዒድ የተሰኙ ታላቅ ሊቅ፣ ታእዊልን እና ተፍዊድን አስመልክተው የሰጡትን ሃሳብ እንዲህ አካተው አቅርበውታል። قال ابن دقيق العيد في العقيدة :"نقول في الصفات المشكلة إنها حق وصدق على المعنى الذي أراده الله ومن تأولها نظرنا فإن كان تأويله قريبا على مقتضى لسان العرب لم ننكر عليه وإن كان بعيد توقفنا عنه ورجعنا إلى التصديق مع التنزيه"اه “(የአሏህን) ለኛ አሻሚ የሆኑትን የመገለጫ ባህርያቱን አስመልክቶ የተጠቀሱት ቃላት አሏህ በፈቀደበት ትርጓሜ ሃቅና እውነት ናቸው። ታእዊል አደርጋለሁ ያለ (ሲተረጉሙ) አተረጓጎማቸው ዐረብኛውን (ቃልና ገለፃ) በቅጡ በመረዳት ወደ ትክክላኛ አረዳድ (ግንዛቤ) ለመድረስ ከቻሉ አንቃወማቸውም። ግና እጅግ በተራራቀ (ፈር በለቀቀ) መልኩ ሲሆን መታቀብን እንመርጣለን። ፍጹማዊነቱን በማመን ወደ ልከኛው (አረዳድ) እንመለሳለን።” ለልዕለ ሃያሉ አሏህ ምስጋና ይግባውና፣ “ታእዊልም ሆነ ተፍዊድ” ከሰለፎች ዘንድ ዕውቅና ያለው የአረዳድ ዘይቤ ከመሆኑ ባሻገር፣ በቁርዓንና ልከኝነቱ በተረጋገጠ ሃዲስ መነሻና መሠረት እንዳለው እንገነዘባለን። ወዲህም፣ “ተፍዊድ የሰለፎች (የቀደምት ሊቃውንት) መዝሃብ ነው፣ ታእዊል ግን የኸለፎች (የመጤዎች) ነው የሚል (የዘ ልማዳዊ) አባባል ሥሁት መሆኑን ተረድቶ መታረም ግድ ይባላል። ለምን ቢባል፣ ሠለፎች አንዳስፈላጊነቱ ይተረጉማሉ እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ እንደወረደ ያሳልፉታል (ተፍዊድን ይጠቀማሉ)። https://t.me/Islamic_Teaching_com
Show all...
(ተፍዊድ) እንደወረደ “ከቀደምት ሊቃውንት (ሠለፍ) ዘንድና ውሃቢያ ዘንድ ተፍዊድን በተመለከተ የማብራራው (የአህሉ ሱናህ ወልጀመዓ) የሚሉትንና በስመ ሰለፍ ተከልሎ ተጅሲም ተሽቢህን የሚያስፋፋው የውሃቢያህ አረዳድን ጭምር ነው። እነርሱ ተፍዊድ በማለት የሚፈስሩት ቃሉን በመተርጎም አካኻኑን (ከይፊያውን) ነው ተፍዊድ የሚያደርጉት ይህ ደግሞ በንዲህ ያለ መልኩ የተረዳ ከሶሓባም፣ከታቢዒይ እንዲሁ ከ አትባዑ ታቢዒይ ማንም የለም። በርግጥ የነሱ ሰለፍ የሚሉት ኢብኑ ተይሚያህ ቢሆን እንጂ “ተፍዊድና” አስፈላጊነት፦ ሀ .አህለሱናህ ዘንድ፦ ተፍዊድ (እንደወረደ ማሳላፍ) ይኸውም ብዙሃኑ ቀደምት አባቶች(ሰለፎች)፣ አሻሚ (ሙተሸቢሀ) የሆኑ የቁርኣን አናቅፅ አኳያ ቃሉን እንደወረደ የማሳላፍ (ተፍዊድ)ን ስልት ይከተላሉ። ለዚህም ቂርኣቱ (መነበቡ) እንደመተርጎም (መረዳት) ነው የሚል አቋም ይወስዳሉ። أمرارها كما جاءت دون تأويل والإيمان بها دون تشبيه أو تجسيم أو تمثيل لقوله تعالى (لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ) “ያለ ትርጓሜ (እንዳለውም እንደወረደ ማፅደቅ) ያለ ተሸቢህ ያለ ተጀሲምና ያለ ተምሲል በርሷም (በገለፃይቱ) ማመን ነው።” በማለት ያስተምራሉ። “ተፍዊድ”፣ ከአንዳንድ ረቂቅና እጅጉን ጥንቃቄ ከሚሹ ቁርዓናዊ ቃላት አንፃር ግድፈትን ለማስቀረትና ፈር ከለቀቀ ብልሹ አረዳድ ለመጠበቅ የሚወሰድ የተዐቅቦ ውሳኔ ነው። ቃል በቃል ሲቀመጥ “እንደወረደ” ማለት ይሆናል። ይኸውም፣ መሠል ቁርዓናዊ ቃላትና ገለፃዎችን ያለትርጉምና ትርጓሜ ከነይዘታቸው (ባሉበት አግባብ) መቀበል ማለት ሲሆን በጥቅሉ “አይነኬ ወይም ከሱ” ለሆኑ ቃላት ሁሉ የሚውል ምሁራዊ ዘይቤ ነው። ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት፣ ከአሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ መለኮታዊ መገለጫዎች አንፃር የተፍዊድን ስልት መጠቀምን ይመርጡ ነበር። በሌላ አነጋገር፣ ከአምላካዊ” ባህሪውና ስያሜው ረቂቅነት አኳያ በሰው ልጅ ምጥን ግንዛቤ ምክንያት ከሚፈጠር የአተረጓጎም ግድፈት፣ ፈጣሪን ከፍጡር ሊያማቱ የሚችሉ ገለፃዎችን፣ እንዳሉ (ከነምስጢራዊ ይዘታቸው) እንዳለ ማለፍን ይመርጡ ነበር። እንደ አብነት ለመጥቀስ ያህል፣ ኢማም አህመድ (ረዲየሏሁ ዓንሁ)፣ ስለ አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ መገለጫዎች በተጠየቁ ግዜ እንዲህ የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተመዝግቧል። نؤمن بها ونصدق بها ولا كيف ولا معنى “ያለ እንደምንና ያለ ትርጉም፣ በርሷ እናምናለን እናፀድቃለንም!” (ኸላል፣ በተረጋገጠ ሰነድ የዘገቡት) ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት፣ እንዲህ የመሰሉ ገለፃዎች በሚገጥሟቸው ግዜ፣ أمروها كما جاءت مع عدم الخوض في بيان معناها “እንዳለች (እንደወረደች) አስተላለፉት።” ማለትን ያዘወትሩ ነበር። ኢማም ትርሚዚይ፣ በሱነን ድርሳናቸው፣ በዚህኛው መዝሃብ (ጎራ) የተሰለፉ ታላላቅ ሊቃውንትን በምሳሌነት ሲጠቅሱ፣ እንደሱፍያን አስሰውሪ፣ ማሊክ ኢብኑ አነስ፣ ኢብኑ ሙባረክ፣ ኢብኑ ዑየይናህ ወኪዕና የመሳሰሉትን አውስተዋል። አክለውም፣ እንዲህ ያለው ዘዬ፣ የሃዲስ ሊቃውንት የመረጡት ነው።” ይላሉ። ሰለዚህ ተፍዊድን በተመለከተ ሊቃውንት የሚጋሩት አቋም፣ እንደሚከተለው ነው፡- ይታመንባታል ويؤمن بها አትተረጎምም ولا تفسر አትመረመርም ولا تتوهم እንዴት ነች (አኳኋኗ)ም ተብሎ አይጠየቅም ولا يقال كيف ። ይታመንባታል ويؤمن بها፡- ሲባል ያለ አንዳች ማመንታት በክፍት ልቦና ይታመንባታል።” ለማለት ነው። አትተረጎምም ولا تفسر)) ፡- አንዳንድ ቀደምት ሊቃውንት እንደሚሉት መነበቧ በራሱ እንደመተረጎሟ ይወሰዳል እንጂ፣ ሌላ መፍቻ አይበጅለትም። አትመረመርም ولا تتوهم)) ፡- የመሰል ስያሜዎች ቀጥተኛ (ውጫዊ) ትርጓሜ የአሏህን መገለጫ ከፍጡራኑ ጋር የማማታት ግድፈት እንዳያስከትል ሲባል፣ ረቂቅ ፍችውን ለአሏህ መተው ማለት ነው። “እንዴትነትን ( (ولا يقال كيفአኳኋንን ከመጠየቅ መቆጠብ)፣ ይህም የፍፁማዊውን አምላክ ባህሪና አደራረግ መጠየቅ፣ ፈጣሪን በፍጥረቱ መመዘኛ እንደመስፈር የሚቆጠር አፈንጋጭ አዝማሚያ በመሆኑ፣ እንዲህ ያለው ግብታዊ የአረዳድ መንገድ መዳረሻው ኩፍር ነው። ከአህለል ሱና ወልጀመዓ አውራ ሊቃውንት አንዱ የሆኑት አል ኢማም ማሊክ፣ እንዲህ ማለታቸው ተወስቷል። "ولا يقال كيف والكيف أنه مرفوع" “እርሱ (አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ) እንዴት አድርጎ (በእንዴት አኳኋን) አይባልም። እርስ በአኳኋን (በአደራረግ) የሚገለፅ አይደለምና! ፍፁሙን አምላክ የሚመስለው አንድም ወደረኛ የለምና! በቁርዓንም ሆነ በሃዲስ፣ አሻሚ ቃላት በሚያጋጥሙ ግዜ፣ የሰሃቦቹንና የቀናውን ትውልድ ሊቃውንት ፈለግ በመከተል፣ መለኮታዊና ነብያዊ ቃሉን ለመረዳት መጣር ግድ ይሆናል። ታላቁ የጀውሃራ ተውሂድ ባለቤትና ከአሸዓሪው ወገን የሆኑት ዓሊም እንዲህ ይላሉ፦ وكلُّ نصٍ أوهم التشبيها أوِّله أو فوِّض ورُمْ تنزيها አልሃፊዝ አዝዘሃቢ፣ “ሲየር አዕላም አንኑበላእ” በተሰኘው ድርሳናቸው እንዳወሱት፣ ኢማም ማሊክ ስለ አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ መገለጫ (ሲፋህ) የተመዘገቡ ሃዲሶችን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡- “أمروها كما جاءت” “ያለ አንዳች ትርጉም እንደወረደ አሳልፉት!” አልሓፊዝ ዘሃቢ እንዳሳለፉልን እንዲሁ፣ የኛ ድርሻና ሃላፊነት፣ መሠል ገለፃዎችን እንደወረዱ ማሳለፍ (ተፍዊደል ማዕና) ይሆናል። ይህ ደግሞ፣ ከኢማም አህመድ አቋም ጋር ስምም የሆነ አካሄድ ነው። ኢማም አህመድ እንዲህ ብለዋልና፡- “እንደምን አይባልም (አኳኋን አደራረጉ እንዴት ተብሎ አይጠየቅም)፣ ቃሉም አይተረጎምም።” እንግዲህ እንደነኢማም አህመድ የመሳሰሉ የታላላቅ ቀደምት ዑለሞችና የአህለል ሃዲስ ሁፋዞች ፈለግ ይህ ነው። እንደወረደ የማሳለፍ ዘይቤ (ተፍዊደል ማዕና)፣ የነኛ በቅዱሱ ነብይ አንደበት የተመሠከረላቸው ትውልዶች የዐቂዳ (የአረዳድ) መሠረት ነው። https://t.me/Islamic_Teaching_com
Show all...
تأويل الإمام أبي الحسن الأشعري የኢማም አቡል ሃሰን አል አሸዕሪይ ታእዊል (ትርጓሜ) ኢማም አልአሽዕሪይ (ረዲየሏሁ ዓንሁ)፣ “ኢባና ፊ ኡሱሊዲያናህ ሪሳላ አህሉ ሰገር” በተሰኘውና በዳሩል አንሷር ታህቂቅ ዱክቱራህ ፈውቂያ” ስር በታተመው ድርሳናቸው፣ ሙጀሲማና ፈላስፋዎችን የሞገቱበትን የታእዊል (ትርጓሜ) ፋና እናገኛለን። ኢማም አልአሸዐሪ በዚሁ ድርሳናቸው፣ “ልዕለ ሃያሉ አሏህ፣ ኢስተዋ ዓለል ዐርሽ፣ በሚለው የገለፃ አግባብ፣ ከመደላደል ሆነ ከመቀመጥ፣ ከላይም ሆነ ከታች፣ በአቅጣጫና ሥፍራ ከመፈራረቅ ሁነት (የማይመሳከር) ፍፁም ነው። ((وأن الله تعالى استوى على العرش على وجه الذي قاله وبالمعنى الذي أراده استواء منزها عن المماسة والإستقرار والتمكن والحلول والإنتقال لا يحمله العرش بل العرش وحملته محمولون بلطف قدرته ومقهورون في قبضته وهو فوق العرش وفوق كل شيئ إلى تخوم الثرى فوقية لا تزيده قربا إلى العرش والسماء بل هو رفيع الدرجات عن العرش كما أنه رفيع الدرجات عن الثرى وهو مع ذلك قريب من كل موجود وهو أقرب من العبد من حبل الوريد وهو على كل شيء شهيد.اه ዐርሽ ከቶ አይሸከመውም። ይልቁንም ዐርሽንና የዐርሽን ተሸካሚ መላዕክት ሁሉ በመለኮታዊ ልዕልናው ቁጥጥር ውስጥ ናቸው። እርሱ ከዐርሽም ሆነ ከመሰል ፍጥረታቱ ከሰማያት ሆነ ከምድር ሁሉ የላቀ አምሳያና ወደር የለሽ ጌታ ነው። የልዕልናው ምጥቀት፣ በዐርሽም ሆነ በሌሎች ክፍለ ሰማያት አይሰፈርም። በገዛ መሻቱ ላስገኘው ዓለም (ሰማያትና ምድር) ጥገኛ ሊሆን ዘንድ አይገባም። አሳዛኙ ነገር፣ ይህ “ኢባና” የተሰኘ የአቡል ሀሰን አሸዕሪ ኪታብ፣ በወሃቢ ርዕዮት በተጠመቁ አሳታሚዎች አማካኝነት (ተድሊስ) እየተቀሸበና ሆን ተብሎ ከዐውዱ ውጭ በሚጣረስ መልኩ እየተፐወዘ መሠራጨቱ ነው። ነገሬ ብሎ በጥሞና ለሚመረምር አንባቢ፣ በኪታቡ ደራሲ ከተዘጋጀው ኦርጅናል ድርሳን ጋር እጅጉ የሚፃረር አያሌ ሃሳቦችን አጭቆ መያዙ እሙን ነው። ስለሆነም፣ ይህ በየመፅሃፍ መደብሩና በብዙሃኑ አንባቢ እጅ የሚገኙት መፅሃፍት የኢማሙል አሸዐሪ የብዕር ውጤቶች አለመሆናቸውን መገንዘብ ያሻል። እግረ መንገዴን፣ በኢማሙ እጅ የተዘጋጀው እውነተኛ ኪታብ፣ ከፍ ብሎ በጠቀስሁት ማተሚያ ቤት የተሠናዳ መሆኑን ለመጠቆም እወዳለሁ። አቡ ሃሰን አልአሸዐሪ (ረዲየሏሁ ዓንሁ)፣ “ሪሳላህ አህሉ ሰገር” በተሰኘው የማሳረጊያ ድርሳናቸው፣ (በገፅ -73) እንዲህ ይላሉ፡- (وأجمعوا على أنه عز وجل يرضى عن الطائعين له وأن رضاه عنهم إرادته لنعيمهم وأنه يحب التوابيبن ويسخط على الكافرين ويغضب عليهم وأن غضبه إرادته لعذابهم) “እነሆ ልዕለ ሃያሉ አምላክ፣ ለትዕዛዛቱ የሚያድሩትን (ምዕናን) ይወዳል” ማለት፣ ለፀጋው ይፈቅዳቸዋል ማለት መሆኑ በዑለሞች የወል ስምምነት የፀደቀ ነው። (አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ፣ ፀፀተኞችን ይወዳቸዋል።) በከሃዲያንም ላይ ቅጣትን ያወርዳል፣ “ቁጣው” ማለት፣ መቅሰፍቱን” በሚል ተተርጉሟል። تأويل الحافظ ابن جوزي የአልሃፊዝ ብን አልጀውዚ ትርጓሜ (ታእዊል) አልሃፊዝ ኢብኑ አልጀውዚ፣ “ደፍዑ ሺበህ አትተሸቢህ” በተሰኘው ድርሳናቸው፣ የታእዊልን (ሥነ-ትርጓሜን) ስልት ተጠቅመዋል። ይህን የታእዊልን ዘዬ በዑለሞች ዘንድ በሠፊው አገልግሎት ላይ መዋሉን ለማሳየት ከሃያ ያላነሱ ምሳሌዎችን ጠቃቅሻለሁ። ታድያ ከነኝህ የኢስላም ሊቃውንት መካከል፣ ዐስር ያህሉ፣ የሶሃቦችንና የተመረጡት ትውልዶች” በሚል በነብዩ ﷺ አንደበት የተመሰከረላቸው የዘመን አውራዎች መሆናቸውን ልብ ይላል። https://t.me/Islamic_Teaching_com
Show all...
Ahmad Muhammad - አሕመድ ሙሐመድ

ኢሰላማዊ አስተማህሮት : የተለያዩ አሰተማሪ መልክቶች በፅሁፍና በድምፅ በመታገዝ ወደናንተ ያደርሳል ። ወቅታዊ መረጃዎችን ያደርሳል። እንዲሁም ከተለያዩ ግሩፕ የተላኩ ምርጥ ነገሮችን እዚህ ያገኛሉ። አርሂቡ ለበለጠ መረጃ ..... @Ibnukocha

تأويل الإمام مالك የኢማም ማሊክ ትርጓሜ (ታእዊል) አልሃፊዝ ኢብኑ ዓብዲል በር፣ “ተምሂድ” በተሰኘው ድርሳናቸው እንዳወሱት ኢማም አዝዘሃቢም በ “ሲየር አዕላሙ ኑበላዕ” እንዳሰፈሩት፡- روى الحافظ عبد البر في التمهيد 7/143 وذكر الحافظ الذهبي في سير أعلام النبلاء 8/105 أن الإمام مالكا رحمه الله تعالى أول النزول الوارد في الحديث بنزول أمره سبحانه وهذا نص الكلام من السير ቃል በቃል ሲተረጎም፦ የተላቀው ጌታችን ይወርዳል” የሚለውን ሃዲስን አስመልክቶ ኢማም ማሊክ፣ “ጌታችን ይወርዳል” የሚለውን ገለፃ፣ “የጌታችን ትዕዛዝ (መመርያ) ይሰፍናል” ብለው ተርጉመውታል። " وقال ابن عدي" حدثنا محمد بن هارون بن حسان حدثنا صالح بن أيوب حدثنا حبيب بن أبي حبيب حدثني مالك قال :" ينزل ربنا تبارك وتعالى أمره فأما هو فدائم لا يزول" ኢብኑ ዓድይ “ከሙሃመድ ኢብኑ ሃሩን ብኒ ሐሳን፣ ኢብኑ ሃሰን ከሷሊህ ኢብኑ አዩብ፣ ኢብኑ አዩብ ከሃቢብ ኢብኑ ሃቢብ፣ ኢብኑ ሃቢብም ከማሊክ የቀሰሙት በማለት እንዳወሱት፣ ኢማም ማሊክ፣ “ፍፁምና የላቀው ጌታችን መመሪያው ይወርድ እንጂ እርሱ አሏህ ግን በነባራዊ ህላዌው የፀና ነው!” ብለዋል። قال صالح فذكرت ذلك ليحي بن بكير فقال "حسن والله" ሷሊህ እንዳወሱት፣ (ይህንኑ የኢማም ማሊክ ትርጓሜ) ለያህያ ኢብኑ በኪር ባወጋኻቸው ግዜ፣ “ወላሂ ድንቅ (አረዳድ) ነው፣ እርግጥ ከማሊክ (አንደበት) አልሰማሁትም?” አሉ። تأويل الحافظ الترمذي አልሃፊዝ ቲርሚዚይ ትርጓሜ (ታእዊል) በ “ሱነን” እንዳሰፈሩትና፣ “ሩእያ” በሚል ርዕስ አንቀፅ ስር እንዳወሱት፣ الحديث (ራሱን ያሳውቃቸዋል) የሚለውን ዘለግ ያለ ሃዲስ ክፍለ መልዕክት፣ “ራሱን ይገልጥላቸዋል” በሚል ትርጓሜ (ታእዊል) ፈስረውት እናገኛለን። تأويل الإمام سفيان الثوري የኢማም ሱፍያን አስሰውሪ ትርጓሜ (ታእዊል) ኢማም አዝዘሃቢ፣ “ሲየር አዕላሙ ኑበላእ” በተሰኘው ድርሳናቸው፣ ታላቁን ሊቅ፣ ኢማም አስሰውሪን ”﴿وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ﴾ "እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው።" የሚለውን የቁርአናዊ አንቀፅ ያብራሩላቸው ዘንድ በጠየቋቸው ግዜ፣ (አብሯችሁ ነው) የሚለውን ገለፃ፣ “በዕውቀቱ ያካልላችኋል”بعلمه)) እንደማለት መሆኑን ጠቁመዋል። እንግዲህ የታእዊል (ሥነ-ትርጓሜ) ፋይዳ የአንድን መለኮታዊና ነቢያዊ ገለፃ ረቂቅና ዕምቅ መልዕክት መርምሮና አገናዝቦ እንዲህ የመሰለ ሰምም ፍቺ የመስጠት ጥበብ ነው። እንዳየነው፣ ቁርዓኑ “የትም ብትሆኑ እርሱ አብሯችሁ ነው።” ሲሰኝ ስለፍፁሙ አምላካችን “ሐቂቃዊ ኑባሬ” (ዛት) እያወሳ ሳይሆን፣ ከርሱ ዕይታና ዕውቅና የሚሰወር አንዳችም ምስጢር ሊኖረን እንደማይችል የሚጠቁም፣ ይልቁንም የአሏህን ሱብሓነሁ ወተዓላ የሁሉ ዓዋቂነት እያፀናልን ነው። ስለሆነም፣ “አብሯችሁ ነው” የሚለው አገላለፅ፣ በሥነ ፅሁፍ ልሂቃን አጠራር “እማርያዊ ወይም ምስጢራዊ”፣ በቁርዓን ጥናት ሊቃውንት ዘንድ ደግሞ “መጃዝ” በመባል ይታወቃል። ታድያ መሰል ገለፃዎችን ከዚህ በተለየ መንገድ (ቃል በቃል) ለመረዳት መምከር ፈር መልቀቅ ይሆናል። https://t.me/Islamic_Teaching_com
Show all...
تأويل الإمام هشام بن عبيد الله የኢማም ሂሻም ኢብኑ ዑበይዳህ ትርጓሜ (ታእዊል) አልሃፊዝ ዘሃቢ፣ “ሲየር አዕላም አንኑበላእ” በተሰኘው ድርሳናቸው (ቅፅ 10፣ ገፅ 446)፣ “በ221 አመተ ሂጅራ (ከዚህ ዓለም የተለየው) ራዚ፣ ከቀደምት የሱና ኢማሞች (ልሂቃን) አንዱና የፊቅህ ጠቢብ ነበር።” ካሉ በኋላ፣ ሙሀመድ ኢብኑ ኸለፍ አልኸራዝ፣ ከሸበ ቢን ዓብዲላህ አልራዚ የቀሰምሁት” ያለው ነው ያሉትን ፍሬ ሃሳብ እንደሚከተለው ያሠፍራሉ። قال محمد بن حلف الخراز سمعت هشام بن عبيد الله الرازي يقول: القرآن كلام الله غير مخلوق فقال له رجل : أليس الله يقول: ﴿مَا يَأْتِيهِم مِّن ذِكْرٍ مِّن رَّبِّهِم مُّحْدَثٍ﴾ فقال : محدث إلينا وليس عند الله بمحدث. “ቁርዓን የአሏህ ቃል እንጂ ፍጡር (መኽሉቅ) አይደለም” አለ። አንድ ሰው “አሏህም እንዲህ ብሎ የለም እንዴ? ﴿مَا يَأْتِيهِم مِّن ذِكْرٍ مِّن رَّبِّهِم مُّحْدَثٍ﴾ (ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸውም።) ያለው ብሎ ሞገተው። (ለዚም) “مُّحْدَثٍ (አዲስ) እኛ (ፍጡራን) ዘንድ እንጂ አሏህ ዘንድ አይደለም!” ብሎ መለሰለት።” (አዎን) እነሆ ይህ ከወደ አሏህ የሆነ ዕውቀት ነው። የአሏህ ዕውቀት ደግም በንግግር (በተናጋሪ) አይገለፅም! እላለሁ።” ይሉናል አልሃፊዝ በይሃቂይ። تأويل سفيان بن عيينة የሱፍያን ኢብኑ ኡየይናህ ትርጓሜ (ታእዊል) (ረህመቱሏሂ ዓለይሂ) አልሃፊዝ ኢብኑ አልጀውዚ፣ “ደፍኡ ሸብሂ ተሽቢህ” በተሰኘው ድርሳናቸው "أخر وطأة وطئها الرحمن بوج" أي أخر غزاة غزاها رسول الله ﷺ بالطائف. فانظره هناك አህለ ሱና ዘንድ የአሏህ መልእክተኛ ﷺ በጧዒፍ ያደረጉት ዘመቻ በሚል ይተረጉሙታል ታዲያ የውሃቢያ ትርጓሜ ምን ይሆን? تأويل ابن حبان የኢብኑ ሒባን ትርጓሜ (ታእዊል) (ረህመቱሏሂ ዓለይሂ) ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ሂባን (በ354ኛ ሂጅራ ያለፉ ዓሊም)፣ “ሶሂህ ኢብኑ ሂባን” በተሰኘው ዕውቅ የሃዲስ ስብስብ ድርሳናቸው፣ ከዚህ በታች የተመለከተው ሃዲስ፣ እንዲህ የመሠለ ትርጓሜ (ታእዊል) ሰጥተውታል። أول الحافظ ابن حبان في صحيحه (1/502) حديث "حتى يضع الرب قدمه فيها –أي جهنم" فقال: “ጌታ (በጀሃነም ላይ) ‘ቀደሙን’ እስቲያሳርፍባት” (ቅፅ 1፣ 502) ከሚለው ሃዲስ አንፃር፣ (ቀደም) የሚለው ቃል፣ ከዐረብ ማህበረሰብ ዘንድ የሚዘወተር ምሳሌያዊ አገላለፅ ነው። ይኸውም (ቀደም) የሚለው ቃል እንደአየአገባቡ የተለያየ ትርጉም ይይዛልና ነው። (هذا الخبر من الأخبار التي أطلقت بتمثيل المجاورة وذلك أن يوم القيامة يلقى في النار من الأمم والأماكنة التي يعصى الله عليها فلا تزال تستزيد حتى يضع الرب جل وعلا موضعا من الكفار والأماكنة في النار فتملئ فتقول "قط قط" تريد "حسبي حسبي" لأن العرب تطلق في لغتهم اسم القدم على الموضع. ለምሳሌ፡- አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ፣ በዕለተ ፍርዱ ህግጋቱን የተቃረኑ አመፀኞችን ወደ ጀሃነም እንዲጓዙ በሚያደርግበት ግዜ፣ ሃጥያት የተፈፀመባቸውን ክፍለ ምድር ከከሃዲያኑ ጋር ወደ ጀሀነም እንድትጠቃለል ይፈርዳል። በዚህን ግዜ ጀሃነም፣ “ቀጢንቀጥ (በቃ በቃ)” ትሰኛለች። እናም ከዐረቦች ዘንድ፣ “ቀደም” የሚለውን ቃል “ሥፍራ” የሚለውንም ይወክላል። እንደተጨማሪ ማሳያ ይሆን ዘንድ ለጥቆ የተመለከተውን የቁርዓን አንቀፅ እንጠቅሳለን። ﴿أَنَّ لَهُمْ قَدَمَ صِدْقٍ عِندَ رَبِّهِمْ ﴾ «ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን አብስር» እንግዲህ፣ አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቀደሙን ከጀሃነም ላይ ሲያሳርፍ የሚለውን ገለፃ፣ ከዚህ ምሳሌ ጋር በማመሳከር መረዳት አያዳግትም። ስለሆነም የቃሉ ትርጉም ብዙሃኑ ሙሸቢሃዎች ዘንድ እንደሚታመነው በጥሬው የሚረዱት እንዳይደለና አድራጊ ፈጣሪ የሆነውን ሁሉን ቻይ አምላክ የገዛ ስሪቶቹ ከሆኑት ፍጡራኑ ጋር ማመሳከር ከእስልምና የሚያስወጣ አድራጎት መሆኑን መገንዘብ ያሻል። https://t.me/Islamic_Teaching_com
Show all...
تأويل الإمام البخاري صاحب الصحيح የኢማም አልቡኻሪ ታእዊል (ትርጓሜ) አልሃፊዝ በይሃቂ፣ “አስማኡ ወሲፋት” በተሰኘው ድርሳናቸው ኢማም ቡኻሪ (معنى الضحك:- الرحمة) “ (ዶሒክ) የሚለውን ቸርነት (ራህማ) በሚለው ትርጎሜ (ታእዊል እንዳደረጉት) አስፍረዋል። روى الفربري عن محمد بن إسماعيل البخاري أنه قال:(معنى الضحك فيه :أي الحديث الرحمة) አልሃፊዝ በይሃቂ (በገፅ 298)እንዳሰፈሩት “አል ፊረብሪ፣ ከሙሀመድ ኢብኑ እስማዒል አልቡኻሪ (ረሂመሁሏህ) በቀሰሙት መሠረት፣ “በሃዲሱ ውስጥ የተጠቀሰው (ዳሒክ) የሚለው ሐዲስ (ራህማ)” ነው ብለው ተርጉመዋል።” ኢብኑ ሃጀርም እንዲሁ በ “በፈትሁል ባሪ” ላይ ይህንኑ አስመልክቶ በሰፊው አትተዋል። تأويل النضر بن شميل የነድር ኢብኑ ሹመይል ትርጓሜ (ታእዊል) አልኢማም አልሃፊዝ ነድር ኢብኑ ሹመይል፣ በ122ኛው ዘመነ ሂጅራ የተወለዱ ስመጥር የስነ-ቋንቋ ሊቅ ናቸው። አልሃፊዝ በይሃቂ፣ በ “አል አስማእ ወሲፋት” (ገፅ 352) ፣ አልሃፊዝ ኢብኑ አልጀውዚም በ “ደፍዑ ሹበሂ አተሸቢህ”፣ ነድር ብን ሹመይል “حتى يضع الجبار فيها قدمه” “ጀባርም እሳ ላይ ቀደሙን እስኪያኖርባት” የሚሰኘውን ሃዲስ እፊቱንም “የእሳት መሆኑ የታወቀ ማለት እንደሆነ ተርጉሞታል ብለዋል። ኢማም አቡ መንሱር አልአዝሃሪ ኢብኑ ጀውዚይ “ደፍዑ ሹባህ አተሸቢህ” የተሰኘን ድርሳን ዋቢ አድረገው እንደተረኩት፡- قال الحافظ ابن الجوزي (وقد حكى أبو عبيد الهروي – صاحب كتاب غريب القرآن والحديث- عن الحسن البصري أنه قال:" القدم هم الذين قدمهم الله تعالى من شرار خلقه وأثبتهم لها" “ገሪቡል ቁርዓን ወል ሐዲስ” ደራሲ የሆነው አቡል ዑበይድ አልሃረዊ፣ ሃሰን አልበሰሪን ዋቢ በማድረግ፣(ቀደም) ማለት እነኝያ አሏህ ዘላለማዊ እሳት የፈረደባቸው እርጉማን ማለት ነው!” በማለት ተርጉሞታል።
Show all...
الإمام أحمد بن حنبل يؤول ኢማም አህመድና “ታእዊል” ታላቁ ሊቅ፣ አልሃፊዝ በይሃቂ - “መናቂብ ኢማም አህመድ” በተሰኘው። ኢብኑ ከሢርም “አልቢዳያህ ወኒሃያህ” ላይ ባሰፈሯቸው ፅሁፎች ኢማም አህመድ ከታእዊል (ሥነ-ትርጓሜን) ጥበብ አንፃር ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በግልፅ አስቀምጠዋል። ﴿وَجَاءَ رَبُّكَ﴾ የሚለውን وَجَاءَ أمر ربك “ የጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ!” ማለት እንጂ ጌታህ መጣ ማለት አይደለም ይላሉ። በይሃቂ ተረክ እንደተመለከተው አልሃኪም ከአቢ ዓምር ብን ሰማክ፣ ኢብኑ ሰመክም ከኢብኑ ሃንበል በቀሰሙት መሠረት፣ ኢብኑ ሃንበል (ኢማም አህመድ) ለጥቆ ከሠፈረው የቁርዓን ጥቅስ አንፃር የታእዊልን (ሥነ-ትርጓሜን) ስልት ተጠቅመዋል። ﴿وَجَاءَ رَبُّكَ﴾ “ የጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ!” ﴿وَجَاءَ رَبُّكَ﴾ የሚለውን ቃል፣ ሰዋቡህ (ምንዳው) ሲሉ በይነውታል። ኢማም በይሃቂ፣ ይህን ተረክ አስመልክቶ የተጠናቀረውን ሰነድ እንከን የለሽ መሆኑን በአፅኖት ገልፀዋል። በተመሳሳይ ኢብኑ ከሢር፣ ኢማም አህመድ የተጠቀሱትን የቁርዓን አንቀፅ ከፍ ብሎ በተገለፀው መልኩ የተረጎሙት መሆኑን አስፍረዋል። በሌላ በኩል እንዲሁ፣ ኢብኑ ከሢር “አልቢዳያ ወኒሃያህ” በተሠኘው ድርሳናቸው፣ ከዚህ በታች የተመለከተውን የቁርዓን አንቀፅ ጃህሚያዎች እንደ ማስረጃነት ሲጠቀሙት ለመረዳት ኢማም አህመድም የታእዊልን (ሥነ-ትርጓሜ) ስልት በመከተል መልስ መስጠታቸውን፣ አቢል ሃሰን አልመይሙኒን ዋቢ በማድረግ አሥፍረዋል። ﴿مَا يَأْتِيهِم مِّن ذِكْرٍ مِّن رَّبِّهِم مُّحْدَثٍ إِلَّا اسْتَمَعُوهُ وَهُمْ يَلْعَبُونَ﴾ (ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸውም። እነሱ የሚያላግጡ ሆነው የሚያደምጡት ቢሆኑ እንጂ)። ሱ. አል አንቢያእ ቁ. 2 ይህ ግልፅ አሻሚነት የሌለው ታዐዊል ነው። قال الحافظ الذهبي في سير أعلام النبلاء "قال أبو الحسن عبد الملك الميموني: قال رجل لأبي عبد الله - أحمد بن حنبل :- ذهبت إلى خلف البزار أعظه بلغني أنه حدث بحديث عن الأحوص عن عبد الله بن مسعود قال: (ما خلق الله شيئا أعظم من آية الكرسي....) وذكر الحديث فقال أبو عبد الله – أحمد بن حنبل:- ما كان ينبغي أن يحدث بهذا في هذه الأيام - يريد زمن المحنة- والفتن: ماخلق الله من سماء ولا أرض أعظم من آية الكرسي" وقد قال أحمد لما أوردوا عليه هذا يوم المحنة: إن الخلق واقع هاهنا على السماء والأرض وهذه الأشياء لا على القرآن. የኢማም አህመዲን የታእዊል (ሥነ-ትርጓሜ) ተሞክሮ አስመልክቶ፣ አልሃፊዝ አዘሃቢይም “ሲየር አዕላሙ ኑበላዕ” በተሰኘው ድርሳናቸው የአቡልሃሰንን ተረክ ዋቢ በማድረግ እንዲህ አሥፍረውልናል። “አንድ ሰው ለአቢ ዓብዲላህ (አህመድ ብን ሃንበል) እነሆ ኸለፍ ቢን በዝዛርን ለመገሰፅ በሄድኩ ግዜ (አህወስ ቢን መስዑድን ዋቢ አድርጎ ያስተላለፈውን) “አሏህ ከኣያተል ኩርሲይ የሚልቅ አንድም ነገር አልፈጠረም”። የሚለውን ሐዲስ አወሳ። በዚህ ግዜ አህመድ ኢብኑ ሃንበል፣ወቅቱ (የፊትና እንደመሆኑ የተጠቀሰው ሐዲስ) የሚነገርበት አለመሆኑን በመግለፅ፣ ጥቅል መልእክቱን (መትኑን) እንዲህ ባለ መልኩ አረሙት። روى الخلال بسند عن حنبل عن عمه الإمام أحمد بن حنبل أنه سمعه يقول:- (احتجوا علي يوم المناظرة فقالوا: تجيء يوم القيامة سورة البقرة ... الحديث قال قلت لهم: إنما هو الثواب) አሁንም ከሥነ-ትርጓሜ (ታእዊል) ጋር በተያያዘ፣ አልኸላል ባጠናቀሩትና ሃንበል ከአጎታቸው ኢማም አህመድ ኢብኑ ሃንበል እንደቀሰሙት ጠቅሰው እንደተረኩት፡-“በመወያየት ላይ ሳለን፣ “በዕለተ ፍርዱ የበቀራ ምዕራፍ ትመጣለች!” የሚለውን ሐዲስ እንደ ማሰረጃነት ሲጠቀሙ “አሰዋብ (ምንዳ) ማለት ነው” የሚል ምላሽ (ትርጓሜ) ሰጠኋቸው።” ብለዋል። ታእዊል (ሥነ-ትርጓሜ) ማለትስ ይኸው አይደል?!
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.