en
Feedback
Accounting and Computer science

Accounting and Computer science

Open in Telegram
1 020
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
🚧 roof 🏗ጣራ(roof) በስነ ህንፃ ንድፋ ውስጥ ዋና የሆነውን ቦታ(space) በመፋጠር ሂደት ውስጥ የሰው ልጅ በስፍራው ውስጥ ያለውን የእንቅስቃሴና ተግባራት በማገናዘብ አማካይ የሆነውን የቁመት ልኬትን እንዲሁም የአየር ሁኔታን በዋናነት በማጥናት ይሰራል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የምንገነባውን ግንባታ ቁመት የሚወስን ሲሆን በተለያየ ቅርፀና የግንባታ መሳሪዎች ይኖሩታል፤ ከነዚህም ውስጥ 1, አሞራ ክንፍ(gabled roof) የምንለው በሁለት በኩል ያጋደለ መዋቅር ያለው ሲሆን በላዩ ለሚከሰቱ እንደ ዝናብ እና የበረዶ ክምርን በቀላሉ ለማስወገድ ተመራጭ ነው። 2,sloped roof ሲሆን ከመጀመሪያው የሚለየው የሚያጋድለው ክፍሉ በአንድ በኩል በመሆኑ ነው ይህም የግንባታ ጊዜና እቃን የማቃለል አማራጭን ይወስዳል። 3,ሶስተኛውና ሌላኛው በተለይም በዘመናዊ የስነ ህንፃ ዘርፍ የሚታየው በአሰራሩም ከሌሎቹ የሚለየው flat roof የሚባለው የጣሪያ አይነት ሲሆን የሚሰራበት የግንባታ እቃም እንደ ሲሚንቶና ብረት ያሉ ጠንካራ እቃዎችን በመጠቀም ነው። ዝርግ(flat) የሚለውን ስያሜ የግኝ እንጂ በአይናችን የማናየው የማጋደል ድርሻ በሁለቱም ወይም በአንዱ በኩል ይኖረዋል። flat roof ተመራጭ የሆነባቸውን ምክንያቶችን ስናይ 👉በዝናብ ወቅት ድምፅን በመቀነሱ፣ 👉የሙቀት መከላከያ(insulation) በማቀናጀቱ፣ 👉ጠንካራና ረጅም እድሜ እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን በላዩ ማስቀመጥ በማስቻሉ ነው። ▶️ጣራዎች(roofs) ከሚሰጡን የመጀመያ ደረጃ አገልግሎት በተጨማሪ እንደ green roof ያሉ ተክሎችን በላያቸው ላይ በማብቀል እንዲሁም solar panels በመያዝ ታዳሽ ለሆነው የግንባታ ዘርፍ የራሳቸውን አስተዋጽኦ የበረክታሉ።

🚧HOW TO CHECK QUALITY OF CEMENT ON SITE-- (1)Colour Test-- ✓colour must be uniform [Grey greenish shade] (2)Float Test-- ✓Take a cement and throw it into water and if - °cement is sink in water then it has good quality °cement floats it has bad quality (3) Rubbing Test-- ✓Take a pich of cement & rubbs in fingers if it is smooth it is good (4)Date Of Packing-- ✓As cement's age increases it's strength decreases ∆After 3 months of packing its strength decreases by 20 to 30% ∆After 6 months - Decreases by 30-40% ∆After 12 months - decreases by 40-50%

🚧ስለ Professional ethics በ ኮንስትራክሽን ስራ ላይ ▶️Professional ethics በጣም ወሳኝ ነገር ነዉ። ስራዎችን በሀላፊነት ስሜት መስራት ማለት ነዉ። ራስን ላለማራከስ ና ለራስ ክብር ከመስጠት ይነሳል። ሰዉ ምን ይለኛል ብቻ ሳይሆን የተሸከምነዉ ህሊና ቅለትና ክብደትም ማሳያ ጭምር ነዉ። ▶️በርካታ መሀንድሶች Design ሲሰሩ ወተዉ ወርደዉ ሙያዉ እንደሚያዘዉ ትክክለኛ ዳታ በመሰብሰብ ከእንከኖች በተቻለ መጠን የፀዳ ሀገሪቷን ያላትን ዉስን ሀብት ከብክነት የሚጠብቅ ህ/ሰቡን ከመንገላታት የሚያድንና አሰሪ ተቋማትን ከህዝብ ወቀሳ የሚያተርፍ ራሱ ባለሙያዉን የሚያስመሰግን ብሎም ዘርፉን የሚያስከብር ስራ ይሰራሉ። ▶️በተቃራኒዉ ደግሞ ሳይሰሩ የደከማቸዉ አንዳንዴም ወደ ሳይት እንኳ ሳይሄዱ ቁጭ ብለዉ Data cook በማድረግ ሀገር የሚያወድሙ፣ የሙያ ብልግና የሚፈፅሙ የሙያዉ ጥላሸቶች አሉ። ▶️በመንግስት በኩል ከጥናትና ዲዛይን ጀምሮ እሰከ ተጠናቀቁ ግንባታዎች መልካም ያደረጉ ባለሙያዎችን ባግባቡ ለይቶ እዉቅና የመስጠት በዛዉ ልክ ደግሞ ያጠፉትን በይፋ መዉቀስና መቅጣት መጀመር መቻል አለበት። ▶️በት/ት ተቋማት ዉስጥም የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታዉን ማሻሻል የስፈልጋል። በስራ ላይ ስልጠና ክህሎትን ማሳደግ ያስፈልጋል። በየምህንድስና ዘርፉ የምርምርና የስልጠና ተቋም መክፈትና መስራት ያስፈልጋል። ✉️ከሁሉ በፊት ግን ዉድ መሀንድሶች ካለንበት ዝቅጠት ለመዉጣት፣ ሀገራችንና ህዝባችን ከኛ የሚጠብቁትን ለመወጣት ሙያችን በሚያስገድደዉ ልክ ለመስራት ቆርጠን እንነሳ።

🚧የሕንፃ ንድፍ ምንድነው? *የሕንፃ ንድፍ (ዲዛይን) ንድፍ በአንድ መዋቅር ክፍሎች ወይም አካላት ላይ የሚያተኩር ጽንሰ-ሀሳብ ነው፡፡ *በአጠቃላይ የሥነ ሕንፃ ንድፍ ኃላፊነቱን የሚወጣ አንድ መሐን
🚧የሕንፃ ንድፍ ምንድነው? *የሕንፃ ንድፍ (ዲዛይን) ንድፍ በአንድ መዋቅር ክፍሎች ወይም አካላት ላይ የሚያተኩር ጽንሰ-ሀሳብ ነው፡፡ *በአጠቃላይ የሥነ ሕንፃ ንድፍ ኃላፊነቱን የሚወጣ አንድ መሐንዲስ ነው። ተጓዳኝ እና ተግባራዊ መዋቅር ለመፍጠር ከቦታ እና አካላት ጋር ይሰራሉ። *በዲዛይን ሂደት ውስጥ ምን ይካተታል? ለህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ዲዛይን (ዲዛይን) ሂደት በርካታ ደረጃዎች አሉ፡፡ *እያንዳንዱ ደረጃ ለፕሮጀክቱ አጠቃላይ እይታ ፣ ስሜት እና ደህንነት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ *እርምጃዎቹ እንደሚከተለው ናቸው -የሶማዊ ንድፍ የንድፍ ደረጃው የመጀመሪያ ደረጃ መርሃግብራዊ ንድፍ ነው ፡፡ መርሃግብሩ (ዲዛይን) ንድፍ አውጪው በፍላጎት ፣ በአጻጻፍ ፣ እና በፕሮጀክቱ ፍላጎት ላይ መረጃ የሚሰበስብበት እና ከዚያ ለደንበኛው ለመከለስ ከ 2 እስከ ሶስት ዲዛይን አማራጮችን ይፈጥራል ፡፡ ደንበኛው በዲዛይን ላይ ማድረግ የፈለገው ማናቸውም ለውጦች በዚህ ደረጃ ላይ ከህንፃ ባለሙያው ጋር መገናኘት አለባቸው ፡፡

🚧What is Liquidated damage? ➡️ስራ ተቌራጩ ለወሰደው ውል በግዜ ላለመጨረሱ ለባለቤት ወይም ለውል ሰጪው አካል የሚከፍለው የካሳ ክፍያ ሲሆን∷ የጠቅላላ ኮንስትራክሽን ውል ይህ ሳይሆን ሲቀር ከዚህ በታች በተጠቀሰው ቅጣት መሰረት ስራ ተቌራጩ መቅጣት እነደሚቻል ይጠቅሳል። 1. ቅጣቱ 0.1 ፐርሰንት ወይም የጠቅላላ ፕሮጀክቱን አንድ አንድ ሺኛ (1/1000) ላልፈፀመው ስራ ቀናት በየቀኑ ሊቀጣ ይገባል። 2. ነገር ግን ስራ ተቌራጩ በጠቅላላው ሊቀጣ የሚችለው የፕሮጀክቱን አስር 10% (አስር ፐርሰንት). ሊበልጥ አይገባም። ↔️"Liquidated damages" means the compensation stated in the contract as being payable by Contractor to the Public Body for failure to perform the contract or part thereof within the periods under the contract, or as payable by Contractor to the Public Body for any specific breach identified in the contract; (a) A penalty of 0.1% or 1/1000 of the value of undelivered Service for each day of delay until actual delivery or performance, (b) The cumulative penalty to be paid by the Contractor shall not exceed 10% of the contract price. .

🚧በኮንስትራክሽን ውል ጉዳይ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate ምን ይላል? 👁‍🗨የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ በአሰሪው በሚመደብ አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና በተቋራጩ ተረጋግጦና ተማምነውበት የሚፈረም ሲሆን ለተቋራጩ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠንም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ *የክፍያ ምስክር ወረቀት ጋር ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪ አባሪ ተደርጐ ይያያዛል፡፡ *ቴክ ኦፍ ሽት የአሰሪው አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና የተቋራጩ መሀንዲስ በግንባታ ቦታ በአካል የሳይት ቪዚት በማካሄድ የተሰራውን ስራ መጠን እና አይነት ከለቀሙ በኋላ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ከተመለከተው የእያንዳንዱ ስራ አይተም ዩኒት ሬት/ነጠላ ዋጋ አንጻር በዝርዝር በተናጠል በዋጋ የሚያስቀምጡበት የተሰራውን ስራ መጠን እና የገንዘብ መጠን ገላጭ ዝርዝር ሰነድ ነው፡፡ *ግራንድ ሳመሪ ደግሞ በዋናነት የግንባታወችን ዝርዝር/ብሎክ በማስቀመጥ የውሉን ዋጋ፣አስቀድሞ የተከናወነ ስራ መጠን፣አሁን የተከናወነ ስራ መጠን እና አጠቃላይ በተቋራጩ የተሰራውን የግንባታ ስራ መጠን ይጠቅሳል፡፡ *የክፍያ ሰርተፍኬት በአብዛኛው በአንድ ገጽ ተጠቃሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በይዘት ደረጃ ግን ብዙ መረጃወችን አምቆ የያዘ ሰነድ ነው፡፡ *የክፍያ ሰርተፍኬት በተለይ ክፍያው የመጀመሪያ ዙር፣ሁለተኛ ዙር እያለ በሚታወቅበት መንገድ የሚዘጋጅ ሲሆን የመጨረሻ ዙር ክፍያ የሚባልም አለው፡፡ *የመጀመሪያ ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በአብዛኛው ከቅድሚያ ክፍያ በኋላ ሲሆን ክፍያውም ለተሰራ ስራ የሚፈጸም ነው፡፡ *የመጨረሻ ዙር ክፍያ ደግሞ ግንባታው ተጠናቆ ጊዜአዊ ርክክብ/provisional acceptance/ ከተከናወነ በኋላ በህግ ከተቀመጡ ተቀናሾች በስተቀር ቀሪውን የስራ ክፍያ ጠቅልሎ አካቶ ወዲያውኑ በግንባታ ውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡ *የክፍያ ሰርተፍኬት የፕሮጀክቱን ስም፣ቦታ፣አሰሪውን፣ተቋራጩን፣አማካሪውን ይጠቅሳል፡፡ ዋናውን የውል ገንዘብ መጠን፣ተቀጽላ ስራዎችን፣ቫሬሽንን እና የተከናወነውን የስራ መጠን ያመለክታል፡፡ውሉ የተደረገበትን ጊዜ እና ኮመንስመንት ዴት ይጠቁማል፡፡በተጨማሪም የቅድሚያ ክፍያ መጠን እና አድቫንስ ሪፔይ ያመለክታል፡፡በዚህም አስቀድሞ የነበሩ የክፍያ ቁጥሮችን ጭምር ይጠቁማል፡፡ እንደዚሁም የሪቴንሽን መጠን እና የቅጣት መረጃንም የሚሰጥ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ መረጃ በያዘ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ አሰሪው/ተቆጣጣሪው/አማካሪው እና ተቋራጩ የሚፈራረሙበት ይሆናል፡፡ *ስለዚህ የክፍያ ሰርተፍኬት ጸደቀ ማለት በሰርተፍኬቱ ላይ የተመለከተው ስራ ስለመሰራቱ እና ዋጋውንም ጭምር አሰሪውና ተቋራጩ አምነውበታል ማለት ነው፡፡ *እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የአሰሪው ዋና ግዴታ ለተቋራጩ በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ነው፡፡ *የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ክሎስ 28.5 ላይ ስለኮንስትራክሽን ስራዎች ክፍያ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ይዘረዝራል፡፡ *በዚህ ረገድ በተለይ ክሎስ 28.5(a) ላይ የተቀመጠው እንደሚያስገነዝበው በኮንስትራክሽን ስራዎች ጉዳይ ክፍያ የሚፈጸመው በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠና የጸደቀ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ እንዲቀርብ በማድረግ መሆኑን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡ *እንግዲህ የክፍያ ጥያቄ የሚያቀርብ በመጀመሪያ ተቋራጩ እንደመሆኑ አማካሪው/ተቆጣጣሪው መሀንዲስ የሳይት ቪዚት በማካሄድ የክፍያ ጥያቄውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ የክፍያ ሰርተፍኬቱን፣ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪውን ጨምሮ የሚያጸድቅና አረጋግጦ የሚፈርምበት እና በማህተምም የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡ *አማካሪው/ቶጣጣሪው በተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበለት በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማረጋገጡን ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባው በዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(d) ላይ በአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡ *እንደዚሁም አሰሪው ደግሞ በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያውን መፈጸም እንደሚገባው በአስገዳጅ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡ *እንግዲህ ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በእጁ ይዞ እያለ እና አሰሪውም ደርሶት እያለ ሳይከፍለው ያዘገየበት እንደሆነ በግንባታ ውሉ እና የውል አካል በሚያደርጉት ጀኔራል ኮንዲሽን በተመለከተው አግባብ ተቋራጩ ኪሳራ ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል ዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(g) በግልጽ እና በአስገዳጅ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡ *ፒፒኤ 2011 ክሎስ 59 እንደዚሁ የኮንስትራክሽን ጉዳይ የስራ ክፍያ የሚፈጸመው በክፍያ ሰርተፍኬት አማካይነት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡ *በአጠቃላይ ከላይ የተመለከተው የክፍያ ሰርተፍኬት ባህሪ እና የፒፒኤ ድንጋጌ የሚያስገነዝበው ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በአማካሪው/ተቆጣጣሪው እስከጸደቀለት ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ክፍያ ሊፈጸምለት እንደሚገባ ነው፡፡

🚧ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በMix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :- . [1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ . አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን። . [2] - መኮማተር (Shrinkage ) . ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking) ያስከትላል ። መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ። . [3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ . Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል። . [4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ . ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል። . [5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing ) . ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት። ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ ሊጠጣት አለበት ። «ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች : . [6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን . በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል። . [7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።

👉የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/ 🚧️የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡ አንድ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡ *ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡ *ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡ *ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤትስ?(Announcing the successful bidder) *ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡፡ የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን(Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የውል ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡፡ .

ማስታወቂያ፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ማሰራት የሚፈልግ ካለ ከበቂ በላይ ልምድ ባላቸው እና ፕሮፌሽናል ባለሙያዎች በጥራት፣ በታማኝነት፣ በሰዓቱ አቀላጥፈን እንሰራለን በስልክ ቁጥር 0947347442 አስራት ብለው ቢደውሉ ያገኙናል ✔ Take off sheet,BOQ,payment certificate preparation ✔Setting out (ቅየሳ) ✔form work ( አናፂ )ስራ ✔rebar (የብረት ስራ ) ✔concrete pouring(አርማታ መሙላት) ✔Electric ✔የሳኒተሪ ✔Block work ,masnory work and finshing work ✔Waterproof ✔የልስን(plastring) ✔የቻክ (gypsum painting,board ) ✔የአልሙኒየም ✔የሴራሚክ ✔የ ስክሪድ ✔የብረታ ብረት በያጅ ✔የቀለም ስራዎች (የውጭ እና የውስጥ ግድግዳ ፣ ኮርኔስ ✔የበር እና መስታወት ስራ

Applying Design Criteria to Alignments
Design criteria can be applied at the onset of the alignment creation, or added later by using the Design Criteria tab of the Alignment Properties panel. When criteria and design checks are assigned at the onset, the designer can have
the advantage of real-time warnings when violations occur.

Additional design speeds can be added as required in the Design Criteria tab of the Alignment Properties panel.
The use of a Design Check Set is also toggled on in the Design Criteria tab of the Alignment Properties panel. Tangency between alignment entities can also be checked via Design Criteria settings.
For real-time warnings during the layout of the alignment, the Use criteria-based design and Use design check set options are selected at the onset of alignment creation.

The Super elevation Wizard
The Super elevation wizard helps you define super elevation using a four-step process with visual cues at each step in the process. As options are selected, the associated configuration image will react to display the method scheme.
The wizard specifies roadway type, number of lanes, shoulder control, and attainment method for calculating super elevation. The Super elevation wizard is used to: • Calculate the super elevation for all curves or a selected curve in an alignment • Store the design criteria in the super elevation curve manager for review or editing after data is calculated. The designer should have a well-defined concept of the design and desired superelevation behavior before starting the wizard. However, if design intent changes it is easy to reapply the Superelevation wizard to existing data, and there is a warning prompt to verify that all existing values will be overwritten.

Assemblies Assemblies represent the cross-sectional composition of the road design. Assemblies are collections of individual subassembly components representing items such as medians, lanes, curbs, sidewalks, and shoulders. The assembly object serves as the baseline to which the designer snaps together any number of premade subassembly pieces from the Civil 3D Tool Palette. Assemblies may contain functionality that is critical in the building of complex road systems, such as intersections, conditional daylighting, and superelevation.

Superelevation
Superelevation is the banking of a curve to help counterbalance the centrifugal forces that a vehicle experiences while traveling through a curve.

When superelevation parameters are applied to the alignment object, the resulting corridor model will rotate and warp the cross-sectional links and shapes to reflect the raising of one
edge of the travel way above the other.

 
The corridor relies on the behavior of subassemblies to adjust their final shape and position accordingly. Many out of-the-box Civil
3D subassemblies support superelevation.

Profiles
Profiles define the surface elevation along an alignment. Design grade profiles are defined using tangents and vertical crest and sag curves.

Profile geometry may be controlled using design criteria that specify three types of minimum K tables based on stopping sight distance, passing sight distance, and headlight sight distance (K-value represents the horizontal distance along which a one percent change in grade occurs on the vertical curve).

Additional criteria and design checks can include slopes and curves that are designed for safe or comfortable driving at a particular speed, or for sag curve drainage considerations.

Super elevation Attainment Methods
AutoCAD Civil 3D supports two methods of superelevation attainment:

• Standard: used on undivided, crowned roadways and divided roadways with crowned or planar sections. • Planar: used on undivided, planar-section roadways, such as ramps and service roads.
The attainment method uses a series of formulas to calculate the length of the transition regions that transform the road from normal crown to full superelevation. Using formulas to establish relationships between maximum superelevation rates, runoff and runout lengths, and other variables, each specific transition region can be calculated. These values are obtained from the assigned design criteria file.

Applying Design Criteria Files to Profiles
Design criteria is applied to profiles using methods similar to the ones used for alignments; criteria and design checks can be applied at the onset of design or afterwards.

If the profile’s parent alignment uses design criteria, that design criteria file is automatically applied to the profile by default.

Editing and Displaying Super elevation Data Super elevation values for individual curves are displayed and edited using the Super elevation Curve Manager. It is accessed by selecting the alignment either in the drawing or from the Prospector tab. A grid view of all super elevation values for the entire alignment may also be used for review and editing. The grid view is launched by selecting the View Tabular Editor in the alignment context commands.

Alignments
Alignments define the horizontal routes for features such as channel ways, utility trenches, roads, and bridges. Their geometry is represented by straight line tangents and a variety of curve and spiral types.
                                                   When individual geometry is connected to create an alignment, rule-based design constraints may be applied.
Alignment Creation and Editing Alignments may be created in a variety of ways. They may be created from existing line, arc, and polyline entities, or they may be created using the Alignment Layout tools. Alignments can be edited using grip edits or alignment editing commands. Editing may also be done in tables using the alignment grid view.

Design Checks
Design checks are another way to help track and control the road design in real time and can be used by themselves or in conjunction with design criteria files. Design checks use mathematical expressions to compare a geometric property of an alignment or profile with a predetermined value.

For example, roadway design may require that tangent road segments be longer than a specified length, or that curve radii exceed a minimal radius.
Design checks are managed through the Settings tab of the Toolspace and can be arranged into design check sets.

The Design Criteria Editor is used to create custom criteria .