cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ETHIO-MEREJA®

Addisababa, Ethiopia🇪🇹 News & Media Company® . USA : Washington . . . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

Show more
Advertising posts
132 272Subscribers
-2024 hours
-2017 days
-36830 days
Posts Archive
ዜና፡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የፕሪቶሪያው ስምምነት "እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር" ጠየቁ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር “በአካባቢው ማህበረሰቦች መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት በጥልቀት እየተከታተሉ” መሆኑን ገልጸው፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት “እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር” ጥሪ አቀረቡ። የህብረቱ ሊቀመንበር በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ፤  ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት “በጣም አዋጭ አካሄድ”  የሆነው “የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ ያቀረቡ” ሲሆን በህወሃት እና ፌደራል መንግስቱ መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ  የተደረሰው የሰላም ስምምነት “እንዲከበር እና ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር ጠይቀዋል።
Show all...
👍 34😁 15👎 5 2
🌺Manual Press Fruit Juicer 👉Safe & Quick 👉Super Easy to Clean and 👉Effective Juicing 💰 ዋጋ፦ ✅  1200 ብር / free delivery       ☎️ 0901882392       ☎️ 0931448106
Show all...
👍 9
🌺Adjustable Laptop & Tablet Stand 💯High Quality(ብረት የሆነ) የቀሩት ጥቂት ናቸው! ✔️ላፕቶፕ ጭን ላይ አስቀምጠው መጠቀም ለከፋ ጉዳት እንደሚያጋልጥ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፤ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ተጣጣፊ የላፕቶፕ ፣ ታብሌት Holder በተመጣጣኝ ዋጋ ገዝተዉ ጤንነቶን ይጠብቁ። 💦 ዋጋ፦ ✅ 1200 ብር! Free delivery ሱቅ ሲመጡ ና ብዛት ለምፈልጉም ቅናሽ አለን።  ☎️ 0901882392   ☎️ 0931448106
Show all...
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር። የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።
Show all...
👍 20 2
አየር መንገዱ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡ የአፍሪካ አቪዬሽን የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ተቋማት ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ትላንት በአዲስ_አበባ ተከፍቷል፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን አገልግሎት ያስጀምራል፡፡ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን አካል ክፍሎች ጥገና ኮምፕሌክስና መለዋወጫዎች ማዕከል እየገነባች ነው ያሉት አቶ መስፍን፤ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ወደ አገልግሎት ለማስገባት እየተሠራ ነው ብለዋል። የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገናው አየር መንገዱን ጨምሮ በአፍሪካ በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ አየር መንገዶች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የአየር ፍሬም፣ ሞተርና አካል ጥገናን ጨምሮ የምሕንድስና የቁሳቁስ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ማስረዳታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
Show all...
👍 32🥰 4👎 2 1
ዜና፡ አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡ አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል። ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።ፍርድ ቤቱም በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጾ፤ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Show all...
😁 58👍 54👎 26 7🥰 3🤔 1😱 1
በኢትዮጵያ በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የ35 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች ተጠየቀ የ #ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር “በፀጥታ ችግር” ምክንያት በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገዶች ፕሮጀክቶች ላይ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች መጠየቁን አስታወቀ። አስተዳደሩ እስከ 2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ድረስ “በፀጥታ ችግር” ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ውላቸው የተቋረጠ” 31 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል 19ኙ የሚገኙት የፋኖ ታጣቂዎች እና የፌደራል መንግሥቱ ግጭት ውስጥ በገቡበት የአማራ ክልል ነው። ለሁለት ዓመታት ያህል ጦርነት በተካሄደበት የትግራይ ክልል ደግሞ 11 የመንገድ ፕሮጀክቶች ውላቸው ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሚንቀሳቀስበት የኦሮሚያ ክልል ደግሞ 19 የመንገድ ፕሮጀክቶች በጊዜያዊነት ቆመዋል ብሏል። በፀጥታ ችግር በተቋረጡ እና በቆሙ ፕሮጀክቶች ላይ የአገር ውስጥ፣ የውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች በድምሩ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ ጠይቀዋል።ከዚህ ውስጥ 87 በመቶ ወይም 30.5 ቢሊዮን ብር ካሳ የጠየቁት የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች ናቸው።
Show all...
👍 65🤔 5😁 4 3🥰 3🤯 3👏 1
“ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ጭምር እየሠራን ነው” - አቶ ጌታቸው ረዳ #የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ “ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከፌደራል መንግሥቱ እና ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ጭምር እየሠራን ነው” ሲሉ ገለጹ አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከ'ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ' ጋር በነበራቸው ቆይታ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በፕሪቶርያ ከስምምነት መደረሱን አስታውሰው “ምዕራብ ትግራይ፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ እና ደቡብ ትግራይ ያሉ ሕገ-ወጥ አስተዳደሮች ፈርስው” ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የደኅንነት ማረጋገጫ መስጠን ይጨምራል ብለዋል። ይህን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ረዥም ጊዜ ወስዷል የሚሉት አቶ ጌታቸው፤ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ረዥም ጊዜ መውሰድ ባይኖርበትም “ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አብረን እየሠራን ነው። ከአማራ ክልል ጋርም ቢሆን በተወሰነ ደረጃ አብረን እየሠራን ነው” ብለዋል። ባለፉት ሳምንታት በአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተው የሰላም መደፍረስ ያጋጠመው በሁለቱ ክልሎች ባሉ “የሚሊሻ አባላት” የነበረ እንጂ መደበኛ ኃይሎች የተሳተፉበት ግጭት አልተካሄደም ብለዋል። የተከሰተውን ሁኔታ ሲያስረዱም፤ “በአማራ ክልል የነበሩ ሚሊሻዎች የተለያዩ አስጊ እንቅስቃሴያዎችን ሲያደርጉ ነበር። በእኛ በኩል ያሉ የሚሊሻ አባላት ምላሽ ሰጥተዋል” ብለዋል። ይህን ተከትሎ የአማራ ክልል ያወጣው መግለጫ “መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ” ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፤ የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት የደረሱት የሰላም ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን እያደረገ ያለው ሕጋዊ ያልሆነ የአማራ አስተዳደር ነው ብለዋል።
Show all...
👎 103👍 81👏 4 3🥰 3🤯 3😁 2🔥 1
በአዲስ_አበባ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ በመዲናይቱ አዲስ አበባ፣ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12፣ ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለው ቦታ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ። የመንግስት መገናኛ ብዙሃ የወረዳውን ስራ አስፈፃሚ አይዳ አወልን ጠቅሶ እንደዘገበው አደጋው የተከሰተው የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ነው፡፡ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 5 ሰአት ላይ ነው። ዜናው ስለ ተጎጂዎች፣ ስለ አደጋው መንስኤ እና ሌሎች ጉዳቶች ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
Show all...
የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል። ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት ድረገፅ አስፍሯል።
Show all...
❇️ Lark Air Humidifier with LED Light        💯 High Quality 🌼 በኤሌክትሪክ የሚሰራ 🌼 ለቤት መልካም መዓዛን የሚሰጥ 🚩Water Tank Capacity: 330ml 🚩Operating power: 2.5W 🚩 Spray Volume 30-50ml/H 🚩Purify the air & Beautify the Environment 🔅Three-level ambient light 🔅Silent humidification 🔅Two levels of fog 🔅Adjustable speed   💦 ዋጋ፦ ✅ 1,600 ብር    ☎️ 0901882392    ☎️ 0931448106
Show all...
👍 15 1
ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ፤ ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን አይፈታም ሲሉ ገልጸው፤ “ታሪካዊ አጋጣሚ” በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ኮሚሽነሯ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨምሮ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች በሀገራዊ ምክክሩ ከመሳተፍ እራሳቸውን አግልለዋል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኪሚቴ አባል የሆኑት ሱልጣን ቃሲም በቅርቡ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፓርቲያቸው የኮሚሽኑ ምስራታ ሂደት እና እያከናወነው ያለው ስራ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው አስረድተዋል።
Show all...
👎 90👍 60😁 9 8
ከአበባ የተሰራው የመጀመሪያው አልማዝ!! ቻይና በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ከአበባ የተሰራ አልማዝ አበረከተች። አልማዝ በተፈጥሮ ከሚገኙ እጅግ ውድ ማዕድናት መካከል አንዱ ነው፡፡ በተፈጥሮ ከሚገኙ ነገሮችም እጅግ ጠንካራው ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቻይና ሳይንቲስቶች ፔኦኒ ከተሰኘ ቀይ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በላብራቶሪ ውሰጥ ይህን በተፈጥሮ የሚገኝ ውድ ማዕድን መስራት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህ አልማዝ ሎያንግ ታይም ፕሮሚስ የተሰኘ በቻይና ሎያንግ ከተማ ውሰጥ የሚገኝ ድርጅት የሰራው ሲሆን አልማዙን ከአበባው በሚገኝ የካርቦን ንጥረነገሮች በመጠቀም እንደተሰራ ገልጸዋል፡፡ አልማዙ ከከተማው የፔኦኒ አባባ ማእከል በተገኙ አበቦች የተሰራ ሲሆን ድርጅቱ የተሰራውን 3 ካራት አልማዝ መልሶ ለአበባ ማእከሉ አበርክቷል፡፡የአምራች ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አልማዙ 41 ሺሕ ዶላር የሚጠጋ ዋጋ እንዳለው ጠቅሰው አልማዙን ለማምረት ባዮ ጄኒክ ካርቦን ኤክስትራክሽን የተሰኘ ከፍተኛ ሙቀትና ግፊት የሚጠቀም ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል፡፡ ይህ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚሰራ አልማዝ በተፈጥሮ ከሚገኘው አልማዝ ጋር በአካልና በኬሚካል ስሪታቸው አንድ አይነት ሲሆኑ የሚለዩትም በዋጋቸውና ለመሰራት በሚፈጁበት ጊዜ ነው ተብሏል፡፡ ሰው ሰራሽ አልማዞቹ በወራት የሚፈጠሩ ሲሆን በተፈጥሮ የሚገኝ አልማዝ ግን ለመፈጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታትን ይፈጃሉ፡፡ በተጨማሪም በላብራቶሪ ውስጥ የሚሰሩት አልማዞች ዋጋቸው በተፈጥሮ ከሚገኙት አነስ ያለ ነው መባሉን ከብሪዚ ስክሮል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Show all...
👍 42 4🥰 2
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ውጥረት አሳስቦናል ሲሉ ገለጹ የካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል “አጨቃጫቂ ቦታዎች” ሲሉ በገለጿቸው የደቡብ ትግራይ አከባቢዎች የተፈጠረው ውጥረት አስግቶናል ሲሉ ገለጹ። ሁሉም አካላት ትጥቅ የማስፈታት፣ ተዋጊዎችን የመበተን እና መልሶ የማቋቋም እንዲሁም ተፈናቃዮችን በሰላማዊ መንገድ ወደ ቀያቸው የመመለስ ጥረት እንዲያፋጥኑ ጠይቀዋል። ሁኔታዎች እንዲረጋጉ እና ንጹሃንን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ የሚታየው ውስብስብ የፖለቲካ እና የጸጥታ ቀውስ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው እና ዘላቂ ሰላም የሚሰፍነው ሁሉን አቀፍ ንግግር በባለድርሻ አካላት መካከል ሲደረግ ብቻ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
Show all...
👍 49👎 13 7🤔 2
🌺Waterproof Kitchen Sticker ⚡ለኪችንዎ ግርማሞገስ የሚያላብስ ⚡ኪችንዎትን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ ተመራጭ ⚡ሙቀትንእና እርጥበትን የሚቋቋም ⚡ለማፅዳት ምቹ የሆነ ⚡ለመሳቢያ ፣ ለካቢኔ ፣ ለኩሽና Size: 60cm×5m(ትልቁ) ዋጋ፦  800ብር         :60cm*3m(ትንሹ) ዋጋ:- 550ብር  ☎️ 0901882392  ☎️ 0931448106    🌞 https://t.me/AddisEka1 የዴሊቨሪ ጨምረው ያሉበት እናደርሳለን። 5በላይ እቃ ካዘዙ ነፃ ዴሊቨሪ እንሰጣለን።      
Show all...
👍 5 1
አዲስ አበባ እና አቅራቢያ ለምትገኙ በሙሉ!! የOnline እቃዎችን በብዛት ዋጋ ከኛ ያገኛሉ💯 Amazon,Alibaba,Aliexpress, በኢትዮጵያ Join us ከታች ይጫኑ፣👇አሁኑኑ ይቀላቀሉ! https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ! በቅናሽ ይሸምቱ! 💯High Quality  💯Big Discount #Ethiopia   👉ተአማኒነት እና ጥራት መገለጫችን ነው!
Show all...
👍 9 3
This is 100% REAL!   Ethiopians this service is for you 🔥 We offer you a unique opportunity to open VIP Offshore bank accounts in US Dollars and Euros in Panama. Enjoy the security of one of the best banking jurisdictions worldwide and get approved by one of the TOP 3 best banks in Panama City! 🍀 Receive your Visa/Mastercard in 2 weeks via FedEx or DHL in Ethiopia or anywhere in Africa. Book your free call with our experts Today! 📞 ✅ Join our Official Channel NOW! ⤵️⤵️⤵️ 👉 https://t.me/myafricanwealthofficial 👉 https://t.me/myafricanwealthofficial
Show all...
👍 15 2🤯 1😱 1
29 ሺሕ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን ተገለጸ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት፤ 29 ሺሕ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) አስታውቋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ትናንት ሚያዝያ 11/2016 ባወጣው ሪፖርት፤ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉት ዜጎች በቆቦ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰቆጣ ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጿል፡፡ ከተፈናቀሉት 29 ሺሕ ዜጎች ውስጥ 70 በመቶዎቹ ሕጻናት እና ሴቶች ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ አዛውንቶች እና ታዳጊዎች ናቸው ያለው ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች ውስጥ 23 ሺሕ የሚሆኑት ቆቦ ቀሪዎቹ 5 ሺሕ 980 የሚሆኑት ደግሞ ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጿል። በአካባቢው ያለው ሁኔታ አሁንም ያልተረጋጋ በመሆኑ ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ ይችላሉ ያለው ጽ/ቤቱ፤ አሁን ላይ ለተፈናቃሉ ዜጎች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ሕይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ነገር ግን ለተፈናቃዮቹ የሚቀርበው የምግብ እና ውሃ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን በመግለጽ፤ ተፈናቃዮቹ አፋጣኝ የነፍስ አድን እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አመላክቷል። በተጨማሪም ለጋሽ አገራትና አጋር ተቋማት የሚያደርጉት ድጋፍ ውስን በመሆኑ፤ አሁን ላይ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ ለተጎዱ ተፈናቃዮች የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል። ኦቻ ለተፈናቃዮቹ በተለይም መጠለያ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችና የሕክምና አገልግሎት በአፋጣኝ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ሰራተኞች ጉዳዩን ለመከታተል ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ወደ ስፍራው ማቅናታቸውንም ገልጿል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው የራያ አካባቢ ዳግም ግጭት መቀስቀሱ የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህም ግጭት የህወሃት ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መምጣታቸውን ተከትሎ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸው ተገልጿል፡፡ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎም፤ የአማራ ክልል መንግሥት "ህወሕት ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ፈጽሞብኛል" ሲል ወቅሷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፤ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ "ክሥተቱ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በህወሓት አልያም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የፌደራሉ መንግሥት በበኩሉ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሣባቸው በእነዚህ አካባቢዎች ባለው ወቅታዊ ሁኔታ፤ ሁሉም ወገኖች ለፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲገዙና ከተንኳሽ ተግባራት እንዲቆጠቡ የጠየቀ ሲሆን፤ ሁሉም ወገኖች ካለፈው ግጭት ትምህርት መውሰድ እንዳለባቸው አሳስቧል።
Show all...
👍 95👎 26 15😱 11🤯 8🥰 3
Who's here?  We've asked for a free link to a paid channel, for our subs. x2-x3 Signals here 👉 CLICK HERE TO JOIN 👈 👉 CLICK HERE TO JOIN 👈 👉 CLICK HERE TO JOIN 👈 ❗️JOIN FAST! FIRST 1000 SUBS WILL BE ACCEPTED
Show all...
👍 14😁 2 1
ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ናቸው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ሩጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡      በውድድሩ ወቅት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም  መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልለው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ  ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ያስታወሰው ፖሊስ በመጪው እሁድ  በከተማችን የሚካሔደው የሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡  የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ መነሻውን ከመስቀል አደባባይ በማድረግ   በለገሃር ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ጥላሁን አደባባይ አድርጎ  መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ውድድር  ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ •  ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ •  ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል •  ⁠ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ •  ⁠ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ •  ⁠ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ • ⁠ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ •  ⁠ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ •  ⁠ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት •  ⁠ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ •  ⁠ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ •  ⁠ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት •  ⁠ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት •  ⁠ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ •  ⁠ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ •  ⁠ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት •  ⁠ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ •  ⁠ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ •  ⁠ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት •  ⁠ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር •  ⁠ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት •  ⁠ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት •  ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ •  ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ  እንደሚሆኑ እና ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ ጎፋ ማዞሪያ ድልድይ ፣ በቅሎ ቤት ድልድይ እና ጥላሁን አደባባይ ድልድይ አካባቢ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጽም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡  በየአካባቢው ለተመደቡ የትራፊክ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ተባባሪ በመሆን የሚሰጡትን ትዕዛዝ አሽከርካሪዎች  በማክበር የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡
Show all...
👍 56👎 15 10
🌺KEMEI Rechargable Hair Clipper 3 in 1 multifunctional shaver ለራስ ፀጉር፣ ለአፍንጫና ለፂም የሚቀያየሩ ያሉት ፀጉር መስተካከያ መሳርያዎችን የያዘ ነው። 🔹በ1ጊዜ ቻርጅ ለ60 ደቂቃ የሚሰራ 👉 Hair Clipper 👉 Nose Trimmer 👉 Dual Blade USB Charging Shaving            ዋጋ⚡️1,500 ብር   ☎️ 0901882392     ☎️ 0931448106
Show all...
👍 8 3
⭐️ProGemei Professional Hair Straightener& Comb 👉ማበጠሪያ እና መተኮሻ በአንድ ላይ 👉በደቂቃ የሚሞቅና የሚያለሰልስ! 👉Quality የፀጉር መስሪያና ምንም ፀጉር አይጎዳም። 👉Power ያለው እና በትክክልም የሚሰራ ነው። 👉ለሀበሻ ፀጉር የሚሆን እና በደንብ የሚሰራ!     ዋጋ:- 2200 ብር ብቻ!!✅     📲 0901882392     📲 0931448106 አድራሻ፣ ከ4ኪሎ መገናኛ መንገድ ላይ ቤሊየር መብራቱ ጋር ከአቤኔዘር ህንፃ ፊትለፊት አዲሱ፣ አል-ዘይን ህንፃ 207ቁ 💬  በTelegram ለማዘዝ ⤵️ ይጠቀሙ        👉  @Antenehg1 ለተጨማሪ ማብራሪያ የቴሌግራም ገፃችን⤵️    🌞 https://t.me/AddisEka1    🌞 https://t.me/AddisEka1 የዴሊቨሪ ጨምረው ያሉበት እናደርሳለን። 5በላይ እቃ ካዘዙ ነፃ ዴሊቨሪ እንሰጣለን።  
Show all...
👍 9
ኢትዮጵያ ለአይኤምኤፍ ከጠየቀችው አዲስ ብድር ጋር በተያያዘ አሁንም ልዩነቶች መኖራቸው ተጠቆመ ኢትዮጵያ አይኤምኤፍ እንዲሰጣት በጠየቀችው ብድር እና በኢኮኖሚ ማሻሻያ ፓኬጅ ዙሪያ አሁንም ከአይኤምኤፍ ጋር ልዩነቶች መኖራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል የተቋሙ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደነገሩት አስታወቀ። ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ድጋፍ ማግኘት ከፈለገች መገበያያ ገንዘቧ ብር ከዶላር ጋር ያለው ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ እንድታዳክም መጠየቋን የጠቆመው ሮይተርስ በሀገሪቱ መደበኛ ምንዛሬ አንድ ዶላር ከሚመነዘርበት በ50 በመቶ ተዳክሞ በጥቁር ገበያ እንደሚመነዘር አመላክቷል። ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ የመገበያያ ገንዘቧን ማዳከም እንደሚጠበቅባት በባንኩ በኩል እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጥ አለመቀመጡን ማረጋገጥ አለመቻሉን የዜና አውታሩ ገልጿል፤ ተቋሙ ተለዋዋጭ የሆነ በገበያ ሁኔታ የሚወሰን የውጭ ምንዛሬ ተመን መኖር አለበት ብሎ እንደሚያምን ጠቁሟል። “ልዩነቶች ቢኖሩም አሁንም ድርድሩ እንደቀጠለ ነው” ሲሉ የአይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ልዑክ አልቫሮ ፒሪስ ድርድሩ በሚካሄድበት በዋሽንግተን ለጋዜጠኞች መናገራቸውነ ያስታወቀው ሮይተርስ “አስቸጋሪ ቢሆንም ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስፋ አለ” ማለታቸውን ጠቁሟል። በኢትዮጵያ መንግስት እና በአይኤምኤፍ በኩል ስላሉ ልዩነቶች ዝርዝር ጉዳዮች ከመጥቀስ መቆጠባቸውን አመላክቷል።
Show all...
👍 38
ቻይናዊውን ሆን ብለው እንዲያሸንፍ ያደረጉ የ ኬንያና ኢትዮጵያ አትሌቶች ሜዳሊያቸውን ተነጠቁ በቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ከስፖርታዊ ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ ቻይናዊውን አትሌት ሆን ብለው እንዲያሸንፍ አድርገዋል የተባሉ የኬንያ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙት ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ተነጠቀ። ባልተገባ መንገድ ውድድሩን እንዲያሸንፍ የተደረገው ቻይናዊ አትሌትም ሽልማቱን ተነጥቋል። ኬንያውያኑ አትሌቶች ዊሊ ምናንጋት እና ሮበርት ኬተር እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ሃይሉ ቢቂላ ማሸነፊያው መስመር ላይ ሆን ብለው ቻይናዊው እንዲያሸንፍ ፍጥነታቸውን ሲገቱ እንደነበር መታየታቸው ተገልጿል፡፡ ባለፈው እሁድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ላይ የተፈፀመውን ያልተገባ ድርጊት የተመለከተው የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ጉዳዩን እየመረመረ መቆየቱን ገልጿል፡፡ ኬንያዊው ምናንጋት መጀመሪያ ላይ የእስያ ጨዋታዎች ሻምፒዮናን እንዲያሸንፍ ያደረገው ጓደኛው በመሆኑ ነው ቢልም፤ ነገር ግን በኋላ ላይ ለማሯሯጥ እንደተቀጠረ ተናግሯል።ይህንንም ተከትሎ የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድር አዘጋጁ የአሸናፊውን ሂ ጄ እና የሦስቱን አትሌቶች ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት መንጠቁን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡
Show all...
👍 56😁 20 6🤯 1
አዲስ አበባ እና አቅራቢያ ለምትገኙ በሙሉ!! የOnline እቃዎችን በብዛት ዋጋ ከኛ ያገኛሉ💯 Amazon,Alibaba,Aliexpress, በኢትዮጵያ Join us ከታች ይጫኑ፣👇አሁኑኑ ይቀላቀሉ! https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ! በቅናሽ ይሸምቱ! 💯High Quality  💯Big Discount #Ethiopia   👉ተአማኒነት እና ጥራት መገለጫችን ነው!
Show all...
👍 22 5🤯 1
እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች እስራኤል ከኢራን ለተቃጣባት የሚሳኤልና ድሮን ጥቃቶች የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ ተገለጸ። እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯ ነው የተጠቀሰው። ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች። ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች። የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል። በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል። ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው። ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።
Show all...
👍 106 16👎 6🥰 3👏 3🤔 3
የመንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው #የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ልዑክ ቡድን ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ። የልዑካን ቡድኑ ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጄቫ፣ ከአለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የምስራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ሃላፊ ቪክቶሪያ ክዋክዋ፣ ከዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የአይዳ ሃላፊ ከሆኑት አኪህኮ ኒሺዮ እና ከሌሎች የዓለም ባንክ እና የአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መገናኘቱ ተጠቁሟል። በተደረጉ ውይይቶችም ላይ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል፣ ስለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታና የወደፊት ተስፋ፣ የተረጋጋ አገራዊ ጥቅል ኢኮኖሚ ለማምጣት እየተሰራ ስላለው የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትና የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ምርታማነትን ማሳደግ እና የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚን ለማሳለጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መሆናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ሁለቱም ተቋማት ኢትዮጵያ እየወሰደቻቸው ያሉትን እርምጃዎች ማለትም ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ለመቅረፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁለተኛ ምዕራፍ ሀገር አቀፍ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አድንቀዋል ሲል ሚኒስቴሩ በመረጃው አካቷል።
Show all...
👍 27👎 19 2🤯 1
አዲስ አበባ እና አቅራቢያ ለምትገኙ በሙሉ!! የOnline እቃዎችን በብዛት ዋጋ ከኛ ያገኛሉ💯 Amazon,Alibaba,Aliexpress, በኢትዮጵያ Join us ከታች ይጫኑ፣👇አሁኑኑ ይቀላቀሉ! https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 https://telegram.me/AddisEka1 ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ! በቅናሽ ይሸምቱ! 💯High Quality  💯Big Discount #Ethiopia   👉ተአማኒነት እና ጥራት መገለጫችን ነው!
Show all...
👍 2
🌺Adjustable Laptop & Tablet Stand 💯High Quality(ብረት የሆነ) የቀሩት ጥቂት ናቸው! ✔️ላፕቶፕ ጭን ላይ አስቀምጠው መጠቀም ለከፋ ጉዳት እንደሚያጋልጥ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፤ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ተጣጣፊ የላፕቶፕ ፣ ታብሌት Holder በተመጣጣኝ ዋጋ ገዝተዉ ጤንነቶን ይጠብቁ። 💦 ዋጋ፦ ✅ 1200 ብር! Free delivery  ☎️ 0901882392   ☎️ 0931448106
Show all...
👍 9
🌺ቪዲዮ🎥12pcs Silcone Kitchen Set 👉 ከፍተኛ ሙቀት የሚቋቋሙ 👉 ከሲልከን የተሰሩ 👉የማይመነችኩ ✅ዋጋ ፣ 1700 ብር / ዴሊቨሪ 150ብር ☎️ 0901882392    ☎️ 0931448106 አድራሻ፣ ከ4ኪሎ መገናኛ መንገድ ላይ ቤሊየር መብራቱ ጋር ከአቤኔዘር ህንፃ ፊትለፊት፣ አል-ዘይን ህንፃ 207ቁ 💬  በTelegram ለማዘዝ ⤵️ ይጠቀሙ        👉  @Antenehg1
Show all...
3👎 1👍 15