cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

The Voice Of Gospel (በወ/ዊ ዮናስ)

©በዚህ ቻናል @Yonaskiy ፦ =>ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች => ዝማሬዎች => ጸሎት * creator ለማግኘት እንዲሁም ሀሳብ አስተያየት ካለዎት => @jonahts/0983030204/

Show more
Ethiopia12 039The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
157
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ደካሞች_ይቅርታን_አያውቋትም......... ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ እለት ከቅርብ ጠባቂዎቻቸው ጋር ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ። አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። እየተመገበ ሳለ እጁ ይንቀጠቀጣል ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነበርኮ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር" ይላቸዋል "አይደለም! ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናል።አሁን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር 'በመቻቻል እና #በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና- ሰላም ህልውናችን ነው ! Dr_Mehret Debebe 👇👇👇👇👇👇👇👇 @yonaskiy @yonaskiy @yonaskiy
Show all...
#የተፈተነ_እምነት (ክፍል 2) እምነትህ እንዲያድግ ትፈልጋለህ? የእግዚአብሔር እውቀት ጨምር፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ላይ ነፍስን አቆያት፣ ስላማንነቱ ተረዱት፣ ስሙት፣ አሰላስሉት፣ አባቶቻችንን የመራን ትናትና፣ ሁልጊዜ ወደ ቃሉ በተጠጋችሁ ቁጥር የቃሉን ባለቤት እየገባችሁ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ቃል ጀርባ ራሱ እግዚአብሔር አለ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ሁልጊዜ ወሳኝ ጉዳይ ነው። አማኝ ነው የሚለው ሰው እምነትን ካዛነፈው ከባድ ነው። ስለ እምነት እያስተማሩ ከእምነት ያጎድላችኋል።የአንዳንድ ሰዎች እምነት ጠጋ ብላችሁ ስታዳምጡት እብደት ይመስላል። አንዳንዶች ቃላቸውን ነው የሚያምኑት።የራሳቸውን ቃል ይፈሩታል ክፉ ቃል አልናገርም ይላል።ወድቀው ቆሜአለሁ ይላሉ።ደከመኝ ስትል ነው መነሳትህ የሚሆነው። ተኝተህ ቆሜአለሁ ቆሜአለሁ ብትል መቆም እቅድ አይሆንም።ለአንተ መተኛትም መቆም ስለሆነ ማለት ነው። እውነታው እኮ ከምላስ በሰማነው አይደለም። አንዳንዶች የፈረሰ ህይወት ይዘዋል ምላሳቸው ትልልቅ ያወራል እንደውም ይህን ስላሉ የበለጡ ይመስላቸዋል። እኛ ያልገባን አድርገው ያስባሉ። እኔ ሞኝ አይደሁለም ከህይወትህ ነው የማየው።የምትሆነውን ነው የማየው። እምነት እኮ ቆማችሁ የምትቀሩበት አይደለም፣ ተገፍትራችሁም፣ ብትገዳገዱም ወድቃችሁ የማትቀሩበት፣ ገና የመነሳት ተስፋችሁ ያለው እምነታችሁ ውስጥ ነው። ፃዲቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል በሰባተኛው ይነሳለወ ይላል። ወደቀ ብለህ እንዳትስቅበት ሳቅህን ሳትጨረስ ይነሳል ነው።የሚያነሳው ጌታ አለው፣ የተገደፈው ጌታ አለው። በትርህ እና ምርኩዝህ ያጽናኑኛል።አባቶቻችን በእምነት ጠላቶቻቸውን ድል ነሱ፣ ድል መንሳት በጦርነት ውስጥ አልፈው ፣ በእምነት ነው። እኔ አይነካኝም ፣ አይተኮስም ሳይሆብ ይተኮሳል ግን አልፈህ ትሄዳለህ ነው። እምነት እግዚአብሔር ያላችሁ የተስተካከለ እውቀት፣ ስለ ሀሳቡ ፣ እቅድ ያላችሁ የተስተካከለ እውቀት፣ ድፍረት ነው ። ሮሜ 10 ላይ ካልሰሙ እንዴት ያምናሉ ብሎ ይጠይቃል። እመን ባክህ ስላለክ ህዝብ አያምንም።እናንተ እንኳን ባታምኑ እኔ አምንሃለሁ የሚሉም አሉ።ሰዎች ወደ ኢየሱስ ሲመጡ እምነትህ አድኖሃል እያለ ወደ እምነታቸው ነው የሚመልሳቸው።ፈውሰኝ ሲል መፈውስ እንደምችል ታምናላችሁ ይላል አዎ ሲሉ እንደእምነታችሁ ይሁንላችሁ ይላቸዋል። እሱ ለመምጣት የተገፈተሩበት እወቅት ነው የሚያየው ከዛ ለዛ እውቀት ይለቃቸዋል።አንተ ነህ ማመን ያለብህ። ፑልፒት ላይ መጨቃጨቅ ሳይሆን ሰዎች ወደ እምነት የሚያደርስ እውቀት መስጠት ነው።ድሪቶ የሆነ ስብከት ሳይሆን ስርዓት ያለው፣ ምዕራፉን ያገናዘበ፣ አውዱን የጠበቀ፣ ዶግማውን ፣ቱፊቱን ፣ ቀኖናውን ያለቀቀ ጨዋ የሆነ ፑልፒት ከሌለን አማኞች ሳይሆን ስሜታዊያን ነው የምንፈጥረው፣ ከባባድ ቃል የሚናገሩ ነገር ግን ከተናገሩት የሚዘግኑት የሌላቸው እንደዚያ አይነት ሰዎች በየ ሶስት ወሩ አቋም ይቀይራሉ፣ በአንድ ጥቅሰ ስትይዛቸው ሌላ ማርከሻ ይፈልጋሉ እንጂ ሁለቱን ጥቅስ አጋብተን እውቀት ለመያዝ ትግዕስት የላቸውም። እንዲህ ተብሏል፣ ተብሏል እያሉ እርስ በእርሱ መጋጨት ነው የሚያስከትለው።ለትምህርታችን መጠንቀቅ አለብን።ጆራችሁን ጠብቁ። ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ተመለሱ። (ቄስ ፍቃዱ ቦረና) 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @yonaskiy @yonaskiy @yonaskiy
Show all...
#እግዚአብሔር_አለ አንዱ ነዉ ጸጉሩን ሊስተካከል ጸጉር ቤት ገብቶ በመስተካከል ላይ እያለ ፤ ጸጉር አስተካካዩ በመሀል ወሬ ይጀምራል። አሁን እንደዉ እግዚአብሔር አለ ? ብሎ በማማር የእግዚአብሔርን ያለመኖር ይናገራል ። በመሐል ጸጉር የሚቆረጠዉ ሰዉ አዎ እግዚአብሔርማ ሁሌም አለ ይለዋል። ቀጠለና ጸጉር ቆራጩ ጠየቀ እና ታዲያ እግዚአብሔር ካለ ለምን ሠዎች በፍርሀት ይኖራሉ ፣ ለምን ሰላም ይጠፋል ፣ ለምን ግፈኞች በሌሎች ላይ በደል ሲያደርሱ ዝም ይላል ፣ ለምን ፍትህ ይጓደላል .. ይሄ ሁሉ ሲሆን እግዚአብሔር ስላሌለ እንጂ ቢኖር ... ብሎ ሳይጨርስ በመሐል ጸጉሩን የሚቆረጠዉ ሰዉዬ አቋረጠዉና አንድ ነገር ተናገረ ፦ አሁን እዚህ ሐገር ጸጉር ቆራጭ አለ ነዉ የሚባለዉ ? ጸጉር ቆራጭማ የለም ብሎ ሲናገር ፥ ጸጉር ቆራጩ አዎ ጸጉር ቆራጭማ ሞልቷል ይሄዉ አንተ እራስህ አየተቆረጥክ ያለኸዉ ጸጉር ቆራጭ ስላለ አይደል እንዴ ብሎ ይመልሳል። በዚህ ወቅት ከጸጉር ቤቱ ዉጪ ማዶ መንገድ ዳር የተቀመጠዉንና ጸጉሩና ፂሙ እጅግ የረዘመዉን ሰዉ አሳየዉና ፥ ታዲያ ጸጉር ቆራጭ ካለ ለምን ያ ሠዉ እንዲ ሊሆን ቻለ ? ብሎ ጥያቄዉን ሲያስከትል ጸጉር ቆራጩም መልሶ ወደ ጸጉር ቤቱ ስላልመጣና ሊስተካከል ስላልፈለገ ነዉ ይለዋል ። ያን ጊዜ ጸጉሩን የሚቆረጠዉ ሰዉ አየህ ወዳጄ እግዚአብሔርም ሰዎች ስላልፈለጉት እና ወደ እርሱ ስላልመጡ ነዉ እንጂ አለ ለሚፈልጉት እና ወደ እርሱ ለቀረቡትም ሁሉ ይፈርድላቸዋል ፣ ሰላምን ይሰጣቸዋል ፣ ሲጠሩትም ይመልስላቸዋል እንጂ ዝም አላለም ። ዝም ያለ የመሰላቸዉም ሊሰሙት እና ሊፈልጉት ያልወደዱ ናቸዉ እንጂ እግዚአብሔር ህያዉ አምላክ ነዉ ደግሞም ሁሌም በስራ ላይ ነዉ ። እርሱ ለሚፈልጉትም ቅርብ ነዉ ። 👇👇👇👇👇👇👇 @yonaskiy @yonaskiy @yonaskiy
Show all...
#HAPPY_NEW_YEAR #Dr_Abiy 👇👇👇👇👇👇👇👇 ✅ @youarestillGod ✅ ✅ @youarestillGod ✅ ✅ @youarestillGod ✅ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Show all...