cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ግጥምና ታሪኮች

በዚ Channel ★የራሴን የግጥም ስራዎችና በሌሎች ገጣሚያን የተሠሩ አሪፍ አሪፍ የግጥም ስራዎች★ እንዲሁም ተከታታይ መሳጭ ታሪኮችየምታገኙ ይሆናል አብራቹኝ ሁኑ★ግራፋክስ ዲዛይን ማሰራት የምትፈልጉ @darkniha ላይ አውሩን ★ Anything አስተያየት እና ሀሳብ ካለዎት💛 for any comment @darkniha @dark_niha_bot @Hanan_Akmel

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
978
Subscribers
No data24 hours
-107 days
-1930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሠርግ ማታ ባል ለሚስቱ የሰጠው ምክር|| የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ በእኔ እና ባንቺ መሃል ከእንግዲህ ምንም አይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም። የኔ ውድ በፊት እኔ ትልቅ ልጅ ነበርኩ አሁን ግን በድጋሚ ህፃን እሆናለሁ፣ ትዝ ይለኛል ህፃን እያለሁ ምግብ ባልቼ እንደሆነ ወይንም እርቦኝ እንደሆነ የምታውቃኝ እናቴ ነበራች ጥዋት ከእንቅልፍ የምትቀሰቅሰኝ እናቴ ነበራች ከቤት ከመውጣቴ በፊት መስተካከል ያለበትን ነገሮች አስተከክለ የምትሸናኝ እናቴ ነበራች ከእንግዲህ ግን እናቴ አንቺ ነሽ ከእንግዲህ የኔን ደካማ ጎን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም ከእንግዲህ ጥማቴን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም አየሽ ፍቅር ልጅ እያለሁ የሆንኩትን ነገር ሁሉ ለእናቴ ነበረ መጥቼ የምናግራት እሷም ምስጢሬን ለማንም ነግራ አታውቅም አሁን ግን እናቴ አንቺ ነሽ ምስጢሬን የምነግርሽ ላንቺ ብቻ ነው ለማንም ምስጢሬን አሳልፈሽ አትስጪ ልጅ እያለሁ ብዙ ጥፋቶችን አጠፋ ነበረ እናቴም ለጊዜው በጣም ትቆጠኝ ነበረ ግን ቁጣዋ ብዙም አይቆይም ወዲያውኑ ተመልሳ መሳቅ ትጀምራለች የኔ ፍቅር ምናልባት አንቺንም ሊያስከፋሽ እችላለሁ እባክሽን ግን ቂም አትያዥብኝ ጥፍቴን ግን አይተሽ ዝም አትበይ ምክር ስጪኝ እቀበላለሁ የኔ ማር ወደ ጣፋጭ የአልጋ ጨዋታ ከመሄደችን በፊት ደግሜ የምነግርሽ ነገር ለሰዎች ወሬ በፍጹም ጆሮ አትስጪ ከእንግዲህ ወዲህ ላንቺ ከእኔ የሚቀርብ ማንም ሊኖር አይችልም መኖር የለበትም። የኔ ፍቅር የብዙ ሰዎች ትዳር መፍረስ ምክንያት ጎሮቤት አልያም የጓደኛ ብዛት ነው ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከልክ በላይ አታቅርቢ በፈጣሪ ፊት ቃል እገባለሁ እኔም ምርጡ አባትሽ ሁሌም ከጎንሽ መቆም የምችል ከማንም አስቀድሜ ለልጄ ለሚስቴ የሚል መልካም ባል እሆንልሻለሁ!! የባል ምክር የተመቻው ብቻ ሼር ያድርግ #ሼር_ሼር
Show all...
😊🤦‍♂️ ማድቤት ናቸው። ግን፦ ቡና እያፈሉ ፤ የሻይ ቅጠል እየቀቀሉም አይደልም። ምግብ ለመስራት እየተጋገዙ ነው፤ እሱ ለመስራት ተዘጋጀ። ፍርፍር ነው። መጠበሻውን እሷ አጠበች ፤ እሱ ሊያለቀልቅ ተቀበላት። ሽንኩርት ላጠ ፤ ሲከትፍ አይኑ እንባ አቀረረ ፤ ሽንኩርት በላጠው እጁ አይኑን ነካ፦ እንባው; ; ዱ ; ብ ; ዱብ አለ!፤ ቃሪያ ቢሆንስ ?! ሚስኪን ፦ የሽንኩርቱን ልጣጭ ጆሮ ላይ ሲያደርግ።የእንባው ኔትወርክ ተቋረጠ። [ በሂጃቧ ጠረገችለት :) ] ቀጠለ..ቲማቲም አዘጋጀ። መጥበሻውን 'ስቶፍ ላይ አድርጎ ፤ ዘይት አድርጎ ሽንኩርቱ ጨመረ- አቁላላ ፤ ቲማቲም ፤ በርበሬ አደረገ። በደንብ ሲቁላላ። የፈላ ውሃ በአናቱ ከለሰ። ጨውም አልረሳም! ሲንተከተክ፤ በስሱ አንድ ማንኪያ የቡና ዱቄት ፦ ይቅርታ አንድ ማንኪያ ሽሮ ማለቴ ነው፤ እላዩ ላይ ነሰነሰ።[ ውሃው ትንሽ! ብቻ እንዲወፍር ነው።] ውሃው ላይ የተነሰነሰው ሽሮ በደንቡ ተንተክትኮ ሲፈላ ፤ አወረደ። እንጀራ ጠቅልሎ ቆራርጦ ጨመረ።ጨረሰ። እሷ ወደ ሳሎን ሄዳ ፤ የማዕድ እቃ አቀራርባ ፦አዘጋጅታ ምግቡ ቀረበ። ታጠቡ። " ቢስሚላህ " ብሎ! ጠቅልሎ በመጠኗ አጎረሳት። " ቢስሚላህ! ሲጥም! " ፤ አለች። ፈገግ አለ! ሊደግማት እጁን ዳግም ዘረጋ። " ሀቢቢ አንተ-ም ጉረሳ" አለችው " አይ አንድ ያጣላል ይሉ የለ ?! መጣላት ደግሞ ከኛ አያምርማ! ፤ አንድ ሰው ሲፆም 70,ዐዐዐ ሺህ ዓመት ከጀሃነም አንደሚርቀው ከኛ መሀል ፤ ከቤታችን ይራቅ! " ሁለተኛ ደገማት። ሁለት ያፋቅራላ፤ በሁለቱ መሀል ያለውን ፍቅር እና እዝነትን ጎልቶ ያሳያላ! ሶስተኛ ደግሞ ፦ ምን ብሎ ያጉርሳት ?! ፤ ስትበላ የጠገበች አይመስለውም ፤ የሁለቱን ትስስር ጠንከር አድርጎ ፤ ፍቅራቸውን አጎልብቶ ይበልጥ የሚያቀራርባቸውን ድርጊት አሰበ። " ታውቂያለሽ የኔ ውድ ? " እያለ..ጉርሻ ጠቀለለ " ወዬ! " " አንድ ሰው ሚስቱን ምግብ ሲያጎርስ፦ ሰደቃ ነው ፤ መፅዋት እያደረገ ነው። የሚል አስተምህሮት በኢስላም እንዳለ ታውቂ የለ ?! " አላት ፈገግ ብላ ፦ ጎረሰችለት። እሱም ለነገ ቤቱ፦ ለአኪራ-ትንሳኤ ስንቅን ሰነቀ! ። እሷም፦ በተረዋ አጎረሰችው ፤ በሉም ፤ አል ሐምዱ ሊላህ" ሲሉ ምስጋናን አደረሱ።1❤❤❤
Show all...
እናት ልጃቸውን ለመጎብኘት ከወራት በፊት ወደተከራየው ኮንዶሚኒየም ይሄዳሉ። ለወትሮው የሚያውቁት ዝርክርኩ ልጃቸው ቤቱ ጽድት ብሎ፣ እቃው በስርዓቱ ቦታ ቦታውን ይዞ በማግኘታቸው በጣም ተገርመዋል። ከእዚያ ባሻገር የላጤው ልጃቸው ቆንጅዬ ጎረቤት ቡና አፍልታ፣ ምሳ አዘጋጅታ ቤቷ ጠራቻቸው። የልጂትና የልጃቸው ተግባቦት ከጉርብትና በላይ እንደኾነ የጠረጠሩት እናት ወደ ልጃቸው ቤት ሲመለሱ <<ዮኒዬ ሁለት የቤት ኪራይ ለምን? ለምን ጠቅለኻት አብራችኹ አትኖሩም?! በእዚያ ላይ ቆንጆ ናት፣ ባለሙያም ጭምር!>> ሲሉ ቡራኬም ጥያቄም አከሉ። <<እማ አንቺ እንደምታስቢው አይደለም። በቃ ጥሩ ጎረቤቴ ናት። ግንኙነታችንም የእህትና የወንድም ነው።>> <<እህቶች ከቤት ሞልተውኻል አስብበት>> ብለውት ወደቤታቸው ሄዱ። በሳምንቱ ቆንጆዋ ጎረቤቱ <<ስማማ ማዘር እዚህ ቤት ከመጡ በኋላ ከእኔ አንተ በቀር እዚህ ቤት የገባ ሰው የለም። ይኹንና ቤቴ ውስጥ የነበረውን አይ- ፓድ ብፈልገው ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም። ማሚ ትወስደዋለች ብዬ አላስብም። ምን ጉድ ነው የሰለበው?>> <<እኔም ትወስደዋለች ብዬ አላስብም። ምናልባት የኔ መስሏት ለእህቶቼ ሰርቃው ከሆነ ሚሴጅ ልኬ በዘዴ እጠይቃታለሁ።>> ብሎ ስልኩን አውጥቶ ወደ እናቱ መልእክት ይጽፍ ጀመር። <<እማ አንቺ የጎረቤቴ ቤት ምሳ ከተጋበዝሽበት ቀን አንስቶ አይ-ፓዷ ከቤቷ መጥፋቱን ነግራኛለች። <ሌባ ነሽ አንቺ ነሽ የወሰድሽው> ብዬ እየከሰስኩሽ አይደለም። ብቻ እቃው ስለመጥፋቱ ልንገርሽ ብዬ ነው። እወድሻለሁ - ያንቺው ዮኒ>> እናት ከልጃቸው የተጻፈላቸውን መልእክት አንብበው ሲጨርሱ ስልካቸውን አንስተው መልእክት መጻፍ ጀመሩ። <<ውድ ዮኒ፣ ከጎረቤትህ ጋር ትተኛለህ ብዬ እየከሰስኩህ አይደለም። ከእርሷ ጋር አልተኛህም እያልኩህም አይደለም። ብቻ እርሷ ቤቷ ብታድር ኖሮ የጠፋውን አይ-ፓድ አልጋዋ ውስጥ፣ ብርድ ልብሱን ስትገልጽ ታገኘው ነበር። እወድሃለሁ! ያንተው እናት>>
Show all...
አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡ || ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን... * እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:- «አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል። ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል። : ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ። : እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል... ሃሃሃ! ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው... : ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ... (ያዝ እንግዲህ¡) በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው። ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት። ሃሃ! : ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት። ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ። ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል። ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው። እህእ! : ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ። ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ። ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ። : ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም። ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም። : አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ። እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ። ሃሃሃ! : ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ። በዚህ መልኩ ሁሉም ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...» ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ። : መቼም ይህንን አንብቦ ያልሳቀ ካለ እኔንጃ¡ ሳቃችሁን በኮመንት! ||😂😂😂😂
Show all...
#family ባልና ሚስት ከተጋቡ አራት አመታት ተቆጥረዋል ግን ልጆችን መውለድ አልቻሉም ነበርና ወደ ሀኪም ቤት ችግሩን ለማወቅ ይሄዳሉ አስፈላጊውንምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሯቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፣ የምርመራውን ውጤት ለመስማት ባል ወደ ሃኪም ቤት ቀድሞ ያመራል ዶክተሩ ጋር ሲገባ የተነገረው ውጤት እጅጉን አሳዛኝ ነበር ባለቤቱ መውለድ አትችልም መሃን ናት ባል የሰማውን ዋጥ በማድረግ እግዜርን ያመሰግናል ፣ ለዶክተሩም እንዲህ ይለዋል (ባለቤቴን ይዜ እመጣለው ግን ስትመጣ መውለድ እንደማትችል አትንገራት ይልቁንስ እኔ መውለድ እንደማልችል አሳውቃት) በማለት ለምኖ ያሳምነዋል። ዶክተሩም ባል ያለውን እሺ ባማለት ለሚስት ባለቤትዋ መውለድ እንደማይችል እና ተስፋቹ አንድ እግዜርን ብቻ መማፀን ነው ሲል ከምክር ጋር ውጤቱን ያሳውቃታል ፡ ብዙም አልቆየ ይህ ወሬ በባልና ሚስት ቤተሰቦች ዘንድ ይሰራጫል፣ በዚህ መልኩ ለአምስት አመታት ያህል ከኖሩ በኋላ ሚስት ለባል ከዛሬ ጀምሮ ከሱ ጋር መኖር እንደማትችል እና ዘር ፍሬዋን ልጆችዋን ወልዳ ማየት እንደምትፈልግ ትነግረዋለች ፣ባል በጣም ሀዘን እየተሰማው ይህ የእግዜር ውሳኔ ነው እባክሽ በእግዜር ላይ ያለሽ ተስፋ የጠነከረ ይሁን በማለት ነገሩን ለማርገብ ይሞክራል እሷም ጥሩ ይህንን አመት እታገሳለው ከዛ በኌላ ግን ከኔ ጋር ትቆያለች ብለህ እንዳታስብ ትለዋለች። እሱም በእግዜር ተስፋውን አስጠግቶ ይስማማል በዛው አመት ሚስት በኩላሊት በሽታ ትጠቃለች ሀኪሞችም ግዴታ ኩላሊቷ መቀየር እንዳለበትና ካልሆነ ነገሮች ሊከብዱ እንደሚችሉ ይነግሯታል፡ ሚስትም ይህንን ስትሰማ ወቀሳዋን በባል ላይ አጠናክራ ቀጠለች ሰበቡ አንተው ነህ ፍታኝ ኑሮዬን ልኑርበት ስልህ እምቢ ብለህ ብዙ ወቀሰችው በዚህ ወቅት ባል ባለቤቱን አስፈቅዶ ኩላሊት በፍቃደኝነት ለባለቤቱ የሚሰጥ ሰው ለማፈላለግ ከሀገር ውጭ እንደሚሳፈር ይነግራት እና ተሰናብቶ ከሆስፒታል ይወጣል ብዙም አልቆየ ከሳምንት ቦኌላ ይደውላል ፣ ኩላሊት የሚሰጥ ሰው አግኝቻለው አብሽሪ በማለት ያበስራታል። አንድ የአረብ ሀገረ ተወላጅ ወጣትም ያለችበት ሆስፒታል ድረስ መጥቶ ኩላሊቱን ሊሰጣት ፍቃደኛ የሆነው እሱ መሆኑን ይነግራታል፡ ቤተሰብ ሁሉ ተደሰተ ምስጋነው ዘነበበት ለነገሩ ኩላሊቱን የሚሰጠው በእርግጥ ባል እንጂ ይህ ወጣት አልነበረም ሚስት እና ቤተሰብ እንዳያውቁ የተጠቀመው ዘዴ ነበር ፡ባልም አስፈላጊውን የቀዶ ጥገና ከተደረገለት በኌላ ኩላሊቱን ለሚስት ይሰጥና የኩላሊት ዝውውሩ በተሳካ መልኩ ይጠናቀቃል፡፡ ብዙም አልቆዪ ሚስት የመጀመርያ ልጅዋን መፀነስዋን ታውቃለች!!! በ ዘጠነኛው ወር የመጀመረያው ልጅ ተወለደ ቤተሰብ ሁሉ በደስታ ተዋጠ ፥ ይህንን ሁሉ በቀን ውሎው መዝገብ ላይ ግን ከማስፈር ባል አልተዘናጋም ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ አንድ ቀን በቤት ውስጥ ካለ ጠረጴዛ ላይ ይህንን መዘገቡን ረስቶ ጥሎት ከቤት ይወጣል ሚስትም አንስታ ማንበብ ትጀምራለች ያኔ ነበር እውነታው ሁሉ የተብራራላት በለቅሶ ተዋጠች ወዲያው ባል ጋር ደውላ ተንሰቅስቃ እውነታውን እንዳወቀች አስረዳችው እሱም እያለቀሰ ምን ያህል እንደሚወዳት ነገራት፡፡ ታሪኩን ፀሀፊው ባልም ሚስቱ ለሱ ካላት ክብር እና ከፍተኛ ወዴታ የተነሳ ከዛ ቀን ጀምሮ ቀና ብላ በሙሉ አይኗ ደፍራ እንዳላየችው በመግለፅ ለባለፉት አስር አመታት ብቻውን ያለቅስ እንደነበር እና እምባውን ይጠርግለት የነበረ ሰው እንዳልነበረ እና ዛሬ ባለቤቱ ስታለቅስ አይዞች በማለት እምባዋን እንደሚያብስላት ይናገራል። ለወዳጅዎ ሼር በማድረግ ያካፍሉ ተጨማሪ ቁም ነገር አዘል ጽፎችን ከፈለጉ ፔጃችንን ላይክ
Show all...
'ድንግል ነሽ?' (ኑዕማን ኢድሪስ) (ተራኪዋ ሂክማ ናት) ከረፋዱ 4:25 እንደወትሮዬ ፌስቡክ ስገባ አራት መልዕክቶችን አገኘሁ። ሁለቱ የቅርብ ጓደኞቼ ሲሆኑ አንዱ በፌስቡክ የማዉቀዉ ኡስታዝ የጠየቅኩትን የፈታዋ ጥያቄ የሰጠኝ ምላሽ ነበር። ሌላኛዉ ደግሞ አልፎ አልፎ 'ሰላም' ይለኛል ነገር ግን እምብዛም ትኩረት ሳልሰጠዉ ለጻፈዉ ነገር ምላሽ እሰጠዋለሁ። እንደተለመደዉ ለሰላምታዉ ምላሽ ሰጥቼ ልወጣ ስል 'የሆነ ጥያቄ ልጠይቅሽ' አለኝ። ብዙ የሚያቆየኝ ስላልመሰለኝ እንዲጠይቀኝ ፈቃደኛ ሆኜ ከፌስቡክ መዉጣቴን ተዉኩት። 'ድንግል ነሽ?' ብሎ ጠየቀኝ። በእርግጥም የማይመለከተዉን ጥያቄ ጠይቆኛል ምን ብዬ ልመልስለት። ብዙ ነገር በሃሳቤ ዉስጥ ተመላለሰ። ለጠየቀኝ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ልስጠዉ ወይስ በስድብ ላቃለዉ። ትክክለኛዉ የቱ እንደሆነ ባላዉቅም እሱ ጋር ክርክር ከምገጥም ብዬ ትክክለኛዉን መልስ ነገሬዉ ንግግራችንን ለመቋጨት ወሰንኩ። 'አዎ ነኝ' ብዬ መልሼለት ከፌስቡክ መዉጣት ተሳነኝ። ቀጣይ የሚጽፈዉን ለማንበብ ስል ኦንላይን ቆየሁ። እንዲህ ይላል ... 'በጣም ደስ ይላል። በዚህ ዘመን ከአንድ ሺህ ሴቶች አንዷ ላይ ብቻ የሚገኝ ነገር ነዉ ያለሽ። እናም በጥብቅነትሽ ልትኮሪ ይገባሻል። ... አንድ በጣም ምትፈልጊዉን ልሰጥሽ እፈልጋለሁ። ይሄ ላንቺ ያለኝን ክብር ማሳያ ይሆንልኛል።' የሚል መልዕክት ላከልኝ። ስልኬን በእጄ እንደያዝኩ በሃሳብ ሰጠምኩ። 'ማን ነዉ?፤ የት ያዉቀኛል፤ የሚያስፈልገኝን ነገር በምን ሊያዉቅ ይችላል...።' እኔን ከማድነቁ በላይ የሚያስፈልገኝ ነገር ምን እንደሆነ ለኔም ስለጠፋብኝ ምን እንደሆነ ከሱ ለማወቅ ፈለግኩ። 'ምንድን ነዉ የሚያስፈልገኝ?' በማለት ጠየቅኩት። ጽሁፉን ቀድሞ ያዘጋጀዉ በሚመስል ሁኔታ የኔ መልዕክት እሱ ጋር ከመግባቱ ቅጽበት ነበር የመለሰለኝ። 'ከዚህ በፊት በፌስቡክ ገጽሽ The joy luck club የሚል መጽሀፍ በጣም እንደምትፈልጊ ጠይቀሽ ነበር?' 'አዎ በትክክል። መጽሀፉ አለህ?' በጉጉት ነበር የጠየቅኩት። መጽሀፉን ከዚህ በፊት ማንበብ ጀምሬ ታክሲ ዉስጥ ረስቼዉ ወርጄ ጠፋብኝ። ከዚያ በኃላ መጽሀፉን ማንም ጋር ላገኘዉ አልቻልኩም። በጣም ደስ አለኝ። '... በአላህ አዉሰኝ አንብቤ በቶሎ እመልስላሀለዉ' ብዬ በመማጸን መልኩ ጠየቅኩት። 'ላዉስሽ ሳይሆን ለጥብቅነትሽ ሽልማት ልሰጥሽ እፈልጋለሁ። አሁን መስቀል ፍላወር አከባቢ ነዉ ያለሁት መምጣት ከቻልሽ ሽልማትሽን አሁኑኑ መዉሰድ ትችያለሽ' አለኝ። በደስታ ልቤ ልትወጣ ደረሰች። የጀመርኩትን ታሪክ መጨረስ ስለምፈልግ ጊዜ መፍጀት አልፈለግኩም። 'ስምንት ሰአት ይመቻሃል?' ፈቃዱን ጠየቅኩ። 'ይመቸኛል። ስትመጪ በዚህ ቁጥር ደዉይልኝ 09...' ስልክ ቁጥሩን አስቀመጠልኝ። ከቀኑ 8:00 ሰአት ከአለም ባንክ ተነስቼ መስቀል ፍላወር ደርሻለሁ። በሰጠኝ ስልክ ቁጥር ደወልኩለት። 'ሄሎ' 'አሰላሙዓለይኩም ሂክማ ነኝ' 'ወዓለይኩም ሰላም .. እንዴት ነሽ ሂክማ' 'ደህና አልሐምዱሊላህ መስቀል ፍላወር ደርሻለሁ የቱ ጋር ነህ?' 'ሂጅራ ባንክ ዋናዉ ቅርንፍ ተሻግረሽ የቆመ ያሪስ መኪና አለ ወደዛ ነይ' አለኝ። ወደነገረኝ ቦታ ስሄድ እንዳለዉ አንዲት ያሪስ መኪና ቁማለች። ዉስጡ አንድ ሰዉ ተቀምጧል። መስታወቱን ዝቅ አድርጎት ስለነበር 'ያሲን አልኩት' ሞቅ ባለፈገግታ ስሜን ጠርቶ ተቀበለኝ። ወደ መኪናዉ እንድገባ ጋበዘኝ። 'ይቅርታ ያሲን በጣም እቸኩላለሁ' አልኩት። 'እንደሰረቀ ሰዉ ላጥ አድርገሽ ልትሄጂ ባልሆነ.. በይ ግቢና ሻይ ቡና ብለን መጽሀፍሽን ትወስጃለሽ' አለኝ። ቅር እያለኝም ቢሆን ወደ መኪናዉ ገባሁ። መኪናዉን ቀስ እያለ መንዳት ጀመረ። 'መጽሃፉን ለማግኘት ቸኩለሻል መሰል?' 'አዎ.. እዚህ ድረስ የመጣሁት ለሱ አይል' ፈገግታ ፊቱን ሞልቶታል። አነጋገሩ ደስ ይላል። 'በቃ ግብዣዉ ከሽልማቱ በኃላ ቢሆንስ...' ብሎ መጽሀፉን ዘረጋልኝ ከእጁ ላይ በመቅጽበት ላፍ አደረግኩት። በሽፋኑ ማመን ስላልፈለጉ መጽሀፉን ገልጬ ተመለከትኩት። አዎ እራሱ ነዉ። በጣም ደስ አለኝ። የምር የማገኘዉ አልመሰለኝም ነበር። ስለመጽሀፉ አንዳንድ ነገር እያወራኝ ሳለ የትና በምን ሁኔታ ዉስጥ እንዳለሁ መርሳት ጀመርኩ። የሚታየኝ ነገር ሁሉ ፍዝዝ፤ ድብዝዝ ይልብኛል። ምን ሆንኩ። በግድ አንገቴን ነቅንቄ ነቃ ለማለት ብሞክርም አልቻልኩም። በተቀመጥኩበት ተልፈስፍሼ እንቅልፍ ጣለብኝ። ወደቅኩ። ከሰአት 10:30 ከባድ ራስ ምታት ተጫጭኖኝ ከእንቅልፌ ነቃሁ። አይኔን ከፈት አድርጌ ስመለከት ያለሁት ፔንስዮን ዉስጥ ይመስለኛል። ደንግጬ ከተኛሁበት ብድግ ስል ሰዉነቴ ላይ ጣል ከተደረገዉ አንሶላ ዉጭ ራቁቴን ነኝ። ሂጃቤ፤ ቀሚሴ፤ ጡት ማስያዥዬ... ምንም ነገር ሰዉነቴ ላይ የለም። ጭኔ አከባቢ 'ርጥበት ተሰምቶኝ ተጣድፌ አንሶላዉን ወዲያ ጣልኩት አልጋዉ በደም ተነክሯል። አዕምሮዬ ዉስጥ የመጣዉ 'ድንግል ነሽ?' የሚለዉ ጥያቄዉ ነበር። ክፍሉን በጩኸት ሞላሁት 'ኡኡኡ....' አይኖቼ በእንባ ተሞሉ፤ የተንጨባረረዉን ጸጉሬን ይበልጥ አንጨባረርኩት። ድምጼን የሰሙ የሆቴሉ ጽዳት ሰራተኞች በሩን ከፍተዉ በሩጫና በድንጋጤ ወደ'ኔ መጡ። 'የት ነዉ ያለሁት?' አልኳቸዉ። ጥያቄዬ በልቅሶ ዉስጥ ስለነበር እርስ በእርሳቸዉ ተያዩ። 'ሶስት ወንዶች ናቸዉ። እህታችን ታማ ከክፍለ ሃገር መጥተን ነዉ ብለዉ አቅፈዉ ያስገቡሽ። እነሱ ቀጣዩ ክፍል ይዘዋል' አሉኝ። 'ሶስት ወንዶች?' ሁለቱንም እያፈራረቅኩ ከተመለከትኩ በኃላ እንደገና ጩኸቴንና ለቅሶዬን ለቀቅኩት። እብድ ሆንኩ። ራሴን ተመለከትኩ ራቁቴን ነኝ፤ ሰዉነቴን ጠላሁት ... ፊቴን እቧጭረዉ ጀመር። ሰዎች ተሰበሰቡ... ከ 4 ወር በኃላ አልሐምዱሊላህ በህይወት አለሁ። ያዉ አላህ በየትኛዉ ወንጀሌ እንደቀጣኝ አላዉቅም። ግን ደግሞ ሁሉም ነገር ቀድሞ የተጻፈ ነዉ። የHIV መድሃኒቴን እየወሰድኩ በህይወት አለሁ። ህይወት ይቀጥላል.... @achacher
Show all...
------- (ከፐርሺያ ወርቃማ ዘመኖች በአንዱ እንዲህ ሆነ!) ከመስጂዱ ፊት ለፊት አህያ ይሞታል። ኢማሙ ለማዘጋጃው ኃላፊ 'መስጂዳችን አቅራቢያ አህያ ሞቷል' የሚል መልእክትን ሰደዱ... ሃላፊው: "ታዲያ ከኛ ምን ይጠበቃል?" ኢማሙ: "እኔ ሃላፊነቴን ለመወጣት ተናግሬአለሁ። እናንተ ደግሞ እንደሃላፊነታችሁ አህያውን አንሱልን!" ሃላፊው: የንቀት አይነት ሳቅ እንደመሳቅ ብሎ "...ድሮ መድረሳ ስንማር የሞተን ማንሳት፣ ማጠብና መቅበር የናንተ ሃላፊነት እንደሆነ ተምረን ነበር!" ኢማሙ: "እሱስ ልክ ነህ። ነገር ግን ጀናዛ ከመታጠቡና ከመቀበሩ በፊት ለቤተሰቦቹ ማሳወቅ ግዴታ እንደሆነም አስተምረናችሁ ነበር!"😂😂😂
Show all...
ዛሬ ኡስታዝ አቡኪ (በክሪ) በአንድ መድረክ ላይ የሚገርም ቂሷ ነገረን ስለ ወንድማማችነት! ልብ የሚነካ! ____________ ማነው የታደለ በዙሪያው ይህ አይነት ወንድም ያለው?? በአረቡ አለም ሁለት ጓደኛሞች ለንግድ ወጥተው የሄዱበት ከተማ ላይ አንድ ክፍል ውስጥ 2 አልጋ ይዘው ያድራሉ።በክፍሉ ውስጥ ለየብቻ ነው የተኙበት አለጋ።አንድኛው የያዘውን 100 ድናር ከኪሱ ያጣዋል።ይደነግጥና ጓደኛውን ይጠይቀዋል።100 ድናር ኪሴ ነበር አጣሁት ወስደሃል? ብሎ ሲጠይቀው ይህኛው ጓደኛውም "አወ እኔ ነኝ የወሰድኩት ለሆነ ሀጃ ፈልጌው ሰጥሃለሁ" ይለዋል።ከዛ ይህኛውም ይረጋጋና ወደ ቁርስ ይሀዳሉ። ጠዋት ከወጡ በሗላ ሩማቸውን የምታፀዳው የልዳት ሰራተኛ "ከአንሶላው ስር 100 ድናር ወድቆ አገኘሁ።የናንተ ይሆናል ብየ ነው" ብላ ይዛ መጣች። ብሩ የጠፋበት በመወዛገብ ጓደኛውን እያየ "ብሩን ወስጀዋለሁ አላልከኝም ነበር እንደ?" ብሎ ይጠይቀዋል።ይህኛውም "እዚህ ክፍል ውስጥ ሌላ ሰው አልገባም።ያለነው እኔና አንተ ነን።አንተ ደግሞ ብሩ ጠፍቶህ ተደናግጠሃል።አልወሰድኩም ብለህ እኔን አታምነኝም።አንተም ትበሳጫለህ።አለወሰድኩም ብልህ ልታምነኝ አትችልም።በሁለታችን መሀል ያለው ወንድማማችነትም ይበላሻል።ስለዚህ ወስጃለሁ ብየ ብሩን ከፍየህ የአንተን ስሜትና ወንድማማችነታችንን ብጠብቅ ይሻል ብየ ነው!" አለው። የሚገርም ነው።እኔ በጣም ነው የተገረምኩት በዚህ ወንድም።በሁላችንም ዙሪያ ብዙ መልካም ሰወች አሉ።ግን የኛ አህላቅ ከመበላሸቱ የተነሳ እንዲህ አይነት ሰወች ለመኖራቸው ለማየት የሚያስችል አቅል አጥተናል። እስኪ እንደዚህ አይነት ወንድም ያላችሁ ሜንሽን አድርጉትና አመስግኑት! የእኔንም አሳውቃችኋለሁ!!
Show all...
እስከዛሬ ያልተደረሰባቸው የአለማችን እንቆቅልሾች (ምስጢሮች) አለማችን እስከዛሬ በይፋ ያልደረሰችባቸው ጥቂት እንቆቅልሾች ወይም ምስጢሮች አሉ። እስኪ ለዛሬ የተወሰኑትን በክፍል አንድ እንመልከት። አለፍ አለፍ እያልን ደግሞ እንቀጥልበት ይሆናል፤ ማን ያውቃል! 1. የጉግል ፍለጋ (Search engine) አልጎሪዝም ጉግል የብዙዎች የእለት ተዕለት የህይወት አካል ይመስለኛል። ጉግል ለአንድ ጊዜ ፍለጋ የተጠቀሙትን ርዕስ በመጠቀም ከዚያ ጋር ተቀራራቢ የሆኑ ሀሳቦችን ወይም ጉዳዮችን እንደፍላጎትዎ መጠን በደረጃ እያስቀመጠ በራሱ በተከታታይነት ያቀርብላችኋል። ይህ ጉግል የሚጠቀምበት ውስጣዊ አሰራር ወይም አልጎሪዝም ነው። በእርግጥ ቲክቶክ ተጠቃሚዎችም የሚወዷቸውን አይነት ቪዲዮዎች እያከታተለ ያቀርባል። በሁለቱም ቢሆን ሰዎች ምርጫዬን እንዴት ተረዳ ብለው መገረማቸው አይቀርም። ነገር ግን ጉግልም ሆነ ቲክቶክ ይህንን አልጎሪዝም እጅግ ጥብቅ በሆነ ምስጢር ይጠብቁታል። የሚያውቁትም በቁጥር ጥቂት የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው። ምክንያቱ ደግሞ ቀላል ነው....የፉክክሩን አለም በበላይነት ይዘው የሚቆዩት በዚህ መሰል ምስጢራዊነት በመሆኑ ነው! 2. የማሌዥያ አውሮፕላን ደብዛ መጥፋት እ.ኤ.አ በ2014 የማሌዥያው MH370 ከኳላላምፑር ወደቤጂን የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 239 ሰዎችን ይዞ ጉዞ በጀመረ በ38 ደቂቃ ውስጥ በህንድ ውቅያኖስ አካባቢ ሲደርስ ደብዛው ጠፋ። እስከዛሬም ድረስ የአውሮፕላኑ ክፍልም ሆነ የተሳፋሪዎች አስከሬን ሳይገኝና ለምንና እንዴት እንደጠፋ በብሂላችን 'እምጥ ይግባ ስምጥ' ሳይታወቅ አለ፤ ከተለያዩ ሀሳባዊ ትንታኔዎች ውጪ። ነገሩ የማሌዥያ አልን እንጂ የኛውስ አውሮፕላን ከአመታት በፊት በሊባኖስ ሲፈነዳና ወገኖቻችን ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳይተርፉ ሲቀሩ የተረጋገጠ ምክንያቱ በዜና ሲነገር አልፎኝ ይሆን? ከሆነ አካፍሉን እስኪ! 3. የኮካኮላ ቅመማ ፎርሙላ ብዙዎች የሚጠቀሙት ለስላሳ መጠጥ...ኮካኮላ ለጣዕሙ መሰረት የሆነው ቅመማ እንዴት ይሆን ብሀው አስበው ያውቃሉ?! ኮካኮላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ የበቃው በሚያዝያ 1886 ዓ.ም ነው፤ እንደ ኤሮፓውያኑ አቆጣጠር። ይኸው ታዲያ ላለፉት 135 አመታት በላይ የቅመማ መንገዱ ጥብቅ ሚስጥር እንደሆነ ዘልቋል። የመጀመሪያው የቅመማ ፎርሙላው ፈጣሪ ጆን ፔምበርተን ህልፈት በኋላ ሚስጥሩ በአለም ላይ ከአራት ሰዎች በላይ በተመሳሳይ ጊዜ እንዳያውቁት ተደርጎ ዘልቋል። ባለንበት ጊዜ የቅመማ ፎርሙላው አትላንታ በሚገኝ ባንክ ውስጥ በጥብቅ የሚጠበቅ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ፍርሙላውን የሚያውቁ ሰዎችም በአለም ላይ 2 ብቻ ናቸው። እነርሱም በምንም ጉዞ አብረው መንቀሳቀስ አይፈቀድላቸውም። ምስጢር ጠባቂ ማለት እንደነሱ ነው አትሉም!
Show all...