EECSF
Open in Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Show more508
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
508
# 2. የሚከተለውን የሕብረቱ አገልግሎት ዘርፍ መሪዎች(ዋና መሪን ጨምሮ) ሥም ዝርዝር በየአገልግሎት ዘርፉ በትክክል መድቡ፡፡
1 ቦኒ....................A Literature
2 ሄለን...................B Graphics
3 ዘሩባቤል.............C Love sharing
4 ቃልኪዳን..............D Prayer
5 አበባየሁ...............E Main leader
6 ልዑል...................F Worship
7 ዲቦራ...................G Evangelism
በትክክል ለመለሰ ብቻ 100 MB😋😋
508
እሺ ጥያቄውን መመለስ የቻለው "ችዋ" ነው
1:59 ሰዓት ላይ መልሶታል ስለዚህ የ 25 MB ተሸላሚ ይሆናል፡፡
መልስ፡ የወርቅነህ አላሮ መዝሙር ሲሆን ሀና
ተክሌ አጅባዋለች
508
ስለነበረን የቃል ጊዜ ክብር ለጌታ ይሁን!!
በተማርንበት እንድፀናም ጌታ ይርዳን፡፡
አሁን ሽልማት ወደሚያስገኙ ጨዋታዎች እናልፋለን አብራችሁን ቆዩ፡፡
508
Continued...
📖 1 ጢሞቴዎስ 6:3-10
Part 2
🔐 "ያለኝ ይበቃኛል"
👉 መገለጫው:
🔖 እግዚአብሔርን መምሰል በራሱ ማትረፊያ የሆነላቸው
🔖 ክርስቶስ ኢየሱስን የህይወት እስትንፍሳቸው ያደረጉ
📌 ዻውሎስ ክርስቶስን በደማስቆ ሲያገኘው የነበረውን ወዝ አይተን
ከዛም መጨረሻ ላይ በሮም እስር ቤት እየማቀቀ እና ወዝ አልባ ሆኑ ስናየው የከሰረ ሊመስለን ይችላል:: ግን ከሆነው በላይ የሆነለትን እሱ ብቻ ነው የሚያስተውለው::
📌 ድሮ እግዚአብሔርን የሚመስል አንዳች መልክ አልነበረኝም አሁን ግን ያን መልክ መያዜ በራሱ ከትርፍ በላይ ነው
📌 ከ አብ ጋር ያለን ህብረት ብቻውን ከትርፍ ይልቃል
📌 ህይወት ለሌለው ሰው ይህ ሁሉ ያንተ ነው ብትሉት ምን ይጠቅመዋል
📌 መልካምነታችን ከሰው የምንቀበለው ምላሽ ላይ ከተመሰረተ መንፈሳዊ ህይወታችን መፅናት አይችልም
📌 ከመንፈሳዊ ህይወታችን ጀርባ "እኩል ይሆናል" ብለን ያስቀመጥናቸው ትርፍቸው ሞት ነው
📌 ቅድስናችን ከ ሰው ለምናገኘው ክብር አይሁን
📌 አገልግሎታችን ለ ዝና እና ጭብጨባ አይሁን
👉 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ በማያሳፍር ህይወት እንገኝ
👉 እራሳችንን በስቃይ አየወጋን ከእውነት አንራቅ
👉 የጌታ መሆናችን በራሱ ከትርፍ በላይ ነው!!!
ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!!!
508
📖 የእግዚአብሔር ቃል
📝 ርዕሰ: "አትርፎ መኖር "
(ከ ወንድም ፊሊዾስ ሰለሞን ጋር)
📖 1 ጢሞቴዎስ 6:3-10
" እነዚህን አስተምርና ምከር :: ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል......"
Part 1
🔐 "ልዩ ትምህርት"
👉 መገለጫው:
🔖 ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚስማማ ቃል የለውም
🔖 ትምህርቱ ምንም ያህል ኢየሱስ ቢል እንኳ "እግዚአብሔርን ወደ መምሰል የማያደርስ ነው::"
📌 ከትላንት ይልቅ ጌታን ወደ መምሰል የማያደርሰን ትምህርት ሁሉ "ልዩ ወንጌል" ይባላል
📌 የሚገርመው ነገር ደግሞ ልዩ ወንጌል የሚሰብኩ ሁሉ በትዕቢት የተሞሉ ናቸው
📌 ጠጋ ብለን ስንቀርባቸው ከሚያውቁት ይልቅ የማያውቁት ይበልጣል:: እነዚህ ሰዎች በድሮ ልምዳቸው የሚንቀሳቀሱ ናቸው
📌በ መንፈስ የጀመሩ ግን በስጋ የጨረሱ
📌 በመንፈስ አለም ጀምረው በአለም አለም የጨረሱ
📌 ትርፍ ካላመጣላቸው እግዚአብሔርን መምሰል ለእነርሱ ኪሳራ ነው
📌 ትሁት ከሆኑ ትሁት ለመሆን አይደለም
📌 ፍቅር ካሳዩ ፍቅር ስላላቸው አይደለም
📌 ከትህትናቸው እና ፍቅራቸው ጀርባ የሆነ ትርፍ(profit) ይፈልጋሉ
📌 ይህ ትርፍ የቆመ ዕለት ፍቅራቸው ይቀራል
📌 ከእነዚህ ሰዎች ራቁ!!!
👇👇👇👇
Next.........
508
ናዝራዊ በዝማሬ ስላገለገልከን ጌታ ይባርክህ!!
ማስታወቂያ
ጊዜው በአካል ተገናኝተን ነገሮችን የምናካሂድበት ጊዜ እንዳልሆነ ይታወቃል ነገር ግን በተለያየ መንገዶች ከብዙ ሰዎች ጋር መገናኘት እንችላለን ለምሳሌ በማህበራዊ ድረ ገፆች፤ እንግዲህ እነዚህን መንገዶች በመጠቀም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በጎነት፣ አዳኝነት ፣ ታዳጊነት እና ጌትነት እንድመሰክር ለሁላችንም ጥሪ አለብንና እርሱን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ተባረኩ!!
አሁን የእግዚአብሔርን ቃል ከ ፊሊጶስ ሰለሞን ጋር አብረን እንካፈላለን፡፡
508
አሜን!!
ስለነበረን የፀሎት ጊዜ ጌታ ይመስገን፡፡
አሁን አምላካችንን በዝማሬ የምናመልክበት ጊዜ ይሆናል በዝማሬ የሚያገለግለን ወንድማችን ናዝራዊ ነው፤ ተባረኩበት፡፡
