cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Meribah Times - መሪባ ታይምስ

በአገራችንና ቀጠናችን ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን በዚህ ቴሌግራም ገፅ እንጋራለን !!! This channel provides political, economical and social information, analysis on Ethiopia and the horn of Africa!!!

Show more
Advertising posts
975Subscribers
-124 hours
+37 days
+4230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አስመልክቶ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በአፍሪካ ቀንድ የኅብረቱ ተወካይ ኦሊሴጎ ኦባሳንጆ ኢትዮጵያና ሱማሊያ በንግግር ውጥረታቸውን እንዲያረግቡ የማገዝ ተልዕኮ እንዲሰጧቸው ጠይቋል። ምክር ቤቱ ይህን ጥሪ ያቀረበው፣ ትናንት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ ነው። ምክር ቤቱ ኹለቱ አገሮች ውጥረቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ፣ ውጥረቱን እንዲያረግቡና ለውጥረቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ትርጉም ያለው ንግግር እንዲያካሂዱ ጠይቋል። ውጥረቱ በቀጠናው ሰላም፣ ጸጥታና መረጋጋት ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ "በእጅጉ እንዳሳሰበው" ምክር ቤቱ ገልጧል። ዓረብ ሊግ፣ ሱማሊያ ኢትዮጵያን በዓለማቀፉ የተመድ ፍርድ ቤት ለመክሰስ የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታውቋል። የዓረብ ሊግ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ትናንት በካይሮ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ፣ የሱማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል። የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚ ሽኩሪ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ራስ ገዝ ጋር የባሕር በር ስምምነት በመፈረም "ያለመረጋጋት ምንጭ ኾናለች" በማለት ከሰዋል። ሽኩሪ፣ ኢትዮጵያ የምትከተላቸው “የተናጥል ፖሊሲዎች” መዘዝ ያስከትላሉ በማለት አስጠንቅቀዋል። የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ ኡጋንዳ በምታስተናግደው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ትናንት ማምሻውን ካምፓላ ገብተዋል። ጉባዔው፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ስምምነት መፈረሟን ተከትሎ በኢትዮጵያና ሱማሊያ መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ለማርገብ በሚችልበት ኹኔታ ዙሪያ ይመክራል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በጉባዔው ይሳተፉ አይሳተፉ፣ መንግሥት ኦፊሴላዊ ማረጋገጫ አልሰጠም። የሱዳኑ ጦርነትም ሌላኛው የጉባዔው አጀንዳ ሲኾን፣ ሱዳን ግን በጉባዔው እንደማትሳተፍ ቀደም ብላ አስታውቃለች። [ከዋዜማ]
Show all...
👍 1
"ከቤተክህነት የሚወጣ መኪና በሙሉ ይፈተሻል። ምንድነው የተፈለገው? ከቤተክርስቲያንስ ምንድነው የሚወጣው? መድፍ ነው? መሳርያ ነው? ቤተክርስቲያኒቱ አትታመንም?" "ልክ ፖለቲካው የፖለቲካው መስመር ሲደፈር ዝም እንደማይል ሁሉ እኔም ደግሞ የመጀመርያዋም፣ የመጨረሻዋም፣ ህይወቴም፣ ማንነቴም፣ ክብሬም ቤተክርስቲያኔ ስለሆነች እሷ ስትደፈር ዝም አልልም፣ እናገራለሁ። የመጣውን ለመቀበልም ዝግጁ ነኝ። ብፁዕ ኡቡነ አብርሀም ዛሬ ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ መሉ መልዕክቱን ለማየት: https://youtu.be/334HrNDLKnw?feature=shared @MeribahTimes
Show all...
👍 4
መሆን የሌለበት እየሆነ ነው የህዝብን የጋራ ትውስታ (collective memory) ማጥፋት ከሰሞኑ እድሜ ጠገቡ እና የብዙ እኩያዎቻችን እና ታላላቆቻችን የጋራ ትውስታ ስፍራ የነበረው እንዲሁም በቅርስነት ተመዝግቦ የቆየው ሎምባርዲያ መፍረሱ መነጋገርያ ሆኗል። ታላቁ ነጋዴ፣ ዲፕሎማትና ኢትዮጵያን ወዳጅ የነበሩት ሼክ አሕመድ ሷሊህ ህንጻውን ያስገነቡት በ1926 ዓ.ም እንደነበር ታሪክ ይነግረናል። ሼክ አሕመድ ሷሊህ አልዛሕሪ በ1873 በየመን የተወለዱ በ1903 ኢትዮጵያ በመምጣት በንግድ ሥራና በሀገር ልማት ክብርና ሞገስ ያገኙ ሰው ነበሩ፡፡ ጣሊያን አገራችንን በወረረበት ዘመን ተቃውሟቸውን በማሰማት በተሌግራምና የተለያዩ ጽሑፎችን አባዝተው በመበተን ለኢትዮጵያ ታግለዋል፡፡ ለአርበኞች በድብቅ መሣሪያ በማቀበል የሕቡዕ አርበኛ ሆነውም ነበር፡፡ በሥራቸው የተበሳጨው ጣሊያን በወቅቱ ንብረታቸውን በሙሉ ወርሶባቸዋል፡፡ ንጉሡ ወደ ሀገር ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ ፒያሳ ፣እሪ በከንቱ፣ በአዋሽ ፣በአዳማ ፣በድሬዳዋ በአጠቃላይ ሁሉም ንብረቶቻቸው እንዲመለሱ አድርገውላቸዋል፡፡ ሆኖም በደርግ ዘመን 99 የሚደርሱ መጋዘንና ሕንፃዎቻቸው ብሎም ሌሎች ንብረቶቻቸው በሙሉ ተወርሰው ሸበሌ አካባቢ ያለው ቤታቸውና ሎምባርዲያ የሚገኝበት ሕንፃቸው እንዲመለስላቸው ተደርጎ ነበር፡፡ ከሰሞኑ አፍራሾቹ ከሕንጻው አጠገብ ወደ ሸበሌ የሚያልፈውን የእግረኛ መንገድ የሚያሰፉ መስለው ሲነሱ በህጋዊ ማህተም ነበር ከነንግድ እንቅስቃሴው ያሸጉት። ከዛ ከአንድ ወር በኋላ ባለፈው አርብ ማታ የፀሃይን መጥለቅ ተገን በማድረግ ተከራዮችን ሆን ብለው በድንገት በስልክ ''ኑ እቃ አውጡ፤ ቤቱ ሊፈርስ ነው'' አሏቸው። በቀን ከሆነ ግርግር ሊነሳ ስለሚችል ነው ተብሎ ሊታሰብ ይችላል፣ ባለሱቅ በሙሉ ከያለበት ተጠዳድፎ ከምሽቱ 1:00 አካባቢ መጥቶ ከፋፍቶ ሲገባ መብራት ቆረጡባቸው። በእጅ ባትሪ እንደምንም ያላቸውን ዋና ዋና እቃ ለማስወጣት ሲሞክሩ ደግሞ ህንጻውን በላያቸው ማፍረስ ጀመሩ። በዚህም 4 ሰዎች ከባድ አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን አንደኛው ሆስፒታል ሲደርስ ህይወቱ አልፏል። የሰዎቹ የአካል ጉዳትም ሆነ ሞት ግን ተደብቋል። ይህ ነው የሰሞኑ የአዲስ አበባ የመንገድ ዳር 'ልማት' ውጤት። ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ተብሎ በከተማዋ እንግዶች በሚያልፉበት አቅጣጫ ሁሉ የ ''ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ'' አይነት ስራ እየተሰራ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የብዙ ሰው እንጀራ እና ሕይወት ተመሰቃቅሏል። ሌላው እዛው ሸበሌ ፊትለፊት የሚገኘው የአ/አ ዩኒቨርስቲ የንግድ ሥራ ት/ቤት (ኮሜርስ) ከነዛ ውብ ሕንፃዎቹ ጋር ፈርሶ ለአንድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ መገንቢያ ሊሰጥ አሁን ዙሪያው በግንባታ ማስጀመሪያ አጥር መከለሉ ታውቋል። እንደ ኒውዮርክ፣ ለንደን፣ ቶክዮ ያሉ ከተሞች እንኳን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎቻቸው ስር ህዝባቸው collective memory ያለባቸውን ቅርሶች ጠብቀው አቆይተዋል፣ አሁን ድረስ የህዝቡን ታሪካዊ እሴት ለመጪው ትውልድ ያስተላልፋሉ፣ እናት እና አባቶቻቸው ያሳለፉባቸውን ግዜያት እያስታወሱ ይኖራሉ። "እና ልማት አይኑር ነው የምትለው?" አይነት ጉንጭ አልፊ ጥያቄ አይጠፋም። እርግጥ ነው ልማት ያስፈልጋል፣ በዚህ ወቅትም የሚፈርስ እና ቦታ የሚለቅ ይኖራል። ነገር ግን የህዝብ የጋራ ትውስታ ቦታውችን በማጥፋት የሚመጣ ልማት ምን ሊጠቅም? በቅርቡ እያቀረብኳቸው እንዳሉት አይነት መሬት በህገወጥ ወረራ መያዝ በተስፋፋበት ግዜ በቅርስነት የተመዘገበ ሀብትን ማፍረስ አይጋጭም? የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንስ ስራው ምን ይሆን? via  EliasMeseret @MeribahTimes
Show all...
👍 3🔥 1
ከቋሚ ሲኖዶስ ነተሰጠ መግለጫ ሙሉ ቃል | መንፈሰ ሰላም ማዕከለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወማዕከለ ቤተ ክርስቲያን… ውእቱ… የሰላም መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ነው:፡ (መጽሐፈ ምሥጢር) በዚህ የሕይወት ቃል አማካኝነት የሰላም መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል በየዘመናቱ ያለና የሚኖር መሆኑን እንመለከታለን፡፡ የዚህም መንፈሰ ኃይል በቤተ ክርስቲያን መኖር ሕማመ ነፍስ በሌለበት ምግባረ ሃይማኖት በፍቅር እንድንኖር ለምንሻው ሁሉ እግዚአብሔር በምልዓት በሚከብርበት ቤተ መቅደስ በኩል የሚሰማው የሰላም ጥሪ በማያቋርጠው የመንፈሳዊ ኑሮ ሂደት ለመንፈስ አንድነት፣ ለአካላዊ ሕብረት የሚጠቅም የሕይወት ምሰሶ ነው፡፡ በመሆኑም ‹‹ወብነ ክሂል ከመ ንቅትል ኅሊና ሰይጣናዌ …ሰላምን የሚያሳጣ ክፉ ሓሳብን በቤተ ክርስቲያናችን መካከል ባለው ሰላም ከእኛ የማራቅ ችሎታ አለን›› ተብሎ እንደተጻፈው ፍጥረተ ሰብእ ሕይወቱን ለበጎ በሚቀርጸው ሥርዓተ ሃይማኖት በመመራት፣ የሰላምን አስፈላጊነት በትምህርት በድርጊት በመግለጽ ባልተዛነፈ ሰብእና በተሟላ ሰላም መኖር የሚችልበት ክሂል ያለው ፍጡር መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ (ዜና አበው)  የሰላም መንፈስ በመካከሏ ሆኖ ከስሕተት የሚጠብቃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም አመለካከቱ ስሕተት ንግግሩ ሐሰት በሆነው ዓለም የጽድቅና የሰላም ባሕርይ መገለጫ ነው፡፡ ልጆቿ በሰላም በፍቅር በታነጸ ዕለታዊ ሕይወት እንዲኖሩ በማድረግ ሰላም የደግነት ሁሉ አክሊል የመንፈሳዊ ምግባራት ዘውድ መሆኑን ስታውጅ መኖሯን የታሪክ መዛግብት፣ ዕውነትን ለመግለጥ የሚተጉ ጸሐፍት ከመቅድም እስከ ህዳግ ይመሰክሩላታል።  መሪዋና አጽናኟ ከሆነው መንፈስ ቅዱስ በተገኘው የሰላም እሴት በእምነታቸው ጸንተው በምግባር በትሩፋት አጊጠው የሚኖሩት ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምእመናንም የረጅም ዘመናት የቅድስና ታሪክ ጉዞዋ ማሳያዎች ናቸው።  የእውነትና የሰላም አምድ እንደመሆኗም በሀገራችን እየተከሰቱ ያሉ አለመግባባቶችንና የእርስ በእርስ ደም መፋሰሶች እንዲቆሙ የሰላም ጥሪ ከማድረግ ጀምሮ ምህላ፣ ጾምና ጸሎት በማወጅ እግዚአብሔር ለሀገራችንና ለሕዝባችን ሰላምን እንዲሰጥ ስትማጸን ቆይታለች። የየዕለት አገልግሎቷም ይህንኑ መሠረት ያደረገ ነው።   በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላም መንፈስ በመካከሏ እንዲሆን አድርጎ ወኃቤ ሰላም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ስለሆነ  በዓለም ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ የክብር ስፍራውን ይዞ የሚቀጥል ቀዳሚና ዐቢይ ተልእኮዋ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን ።  በመጨረሻም ሰላም የሚጸናው ማንኛውም ማኅበረሰብ እርስ በእርሱ በመተሳሰብና በፍቅር በእውነተኛ መግባባትና በፍትሕ በርኅራሄና በመከባበር አብሮ መኖር ሲቻል ነው. መረጃ፦ 1. ድረገጽ:- https://eotceth.org 2. ፌስ ቡክ ገጽ:- የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation 3. ስልክ፦ +251111262652 | +251111262818 4. ኢሜል፦ [email protected] 5. ፖስታ፦ 1283 አዲስ አበባ @MeribahTimes
Show all...
👍 1
የታገቱት ወጣቶች 12 ሚሊየን ብር ተጠየቀባቸው። ከቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በአል መልስ መንገድ ላይ የታገቱት ምዕመናን በእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር እንደተጠየቀባቸው ታውቋል። በአጋቾች እጅ የሚገኙት እና ለቤተሰቦቻቸው ተደውሎ ገንዘብ የተጠየቀባቸው የሚከተሉት ናቸው ። 1ኛ. ማስረሻ አበበ [ ኖሻ ] 2ኛ. ጌታሁን ሁንዴቻ [ የሞች አዲሱ ሁንዴቻ ወንድም ] 3ኛ. በኃይሉ ጀምበሬ 4ኛ. አበራ ቱሉ 5ኛ. ያሬድ ታሪኩ 6ኛ. ቢኒያም ከበደ [ ነብሶ] 7ኛ.ዘሪሁን ንጉሴ 8ኛ. ያሬድ ነጋሽ  [ አቢሊሉ ] 9ኛ. ቢኒያም ነጋሽ 10ኛ. ምሥጋናው 11ኛ . በኃይሉ ጆብሬ 12ኛ. አዲሱ ባይሳ የመተሃራ ከተማ ነዋሪ በበከላቸው እንደሚሉት ከቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ ደርሰው ሲመለሱ በተጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6 ደርሷል። እስካሁን ባለው መረጃ 12 ሰዎች ታግተዋል ሲሉ ሁኔታውን ገልፀዋል። @MeribahTimes
Show all...
የቤተክርስቲያናችን የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ  አባል  ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ  አያሌው ቢታኔ ታሠሩ ። (#EOTCTV ታህሣሥ 9 ቀን 2016 ዓ.ም) +++++++++++++++++++++++++++++++++++++ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የዕለት ችሎት ተከራርክሮ ከፍርድ ቤት ወጥቶ ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር  ሜክሲኮ በሚገኘው ነዳጅ ማደያ ለመኪናው ነዳጅ በመቅዳት ላይ ሳለ ሲከታተሉት በነበሩ በመንግስት የጸጥታ አካላት ተወስዶ የታሠረ መሆኑ ታወቀ። ጠበቃ አያሌው ቢታኔ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴን በመምራት ሙያዊ ግዴታቸውን በመወጣት ቤተክርስቲያንን ወክለው የሕግ አገልግሎት ሲያበረክቱ ቆይተዋል። በተለይም በቤተክርስቲያናችን ተከስቶ በነበረው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት  ተከትሎ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመፈጸማቸው በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራቸው ለተፈናቀሉ ምእመናን በነጻ የሕግ ማማከርና ጥብቅና አገልግሎት በመሥጠት ከፍተኛ አገልግሎት አበርክተዋል። በተጨማሪም በቅዱስ ሲኖዶስ በሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎችን በማርቀቅ ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል። @MeribahTimes
Show all...
ወ/ሮ መላት ወርቀሀይሉ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።
Show all...